Telegram Web Link
እስራኤል ደቡባዊ ሊባኖስን በአየር ደበደበች

ጥቃቱ የጃራምክ-መህሙዲያ አካባቢን ኢላማ ያደረገ እንደነበር የስፑትኒክ ባልደረባ ዘግቧል፡፡

ከማሕበራዊ ሚዲያ የተገኙ ምሥሎች

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
👏83🔥2
በትግራይ ክልል የሕክምና አገልግሎት በግዜያዊ ስፍራዎች እንዲሰጥ ተወሰነ

በሰሜኑ ጦርነት የወደሙ የጤና ተቋማት ወደ አገልግሎት ባለመመለሳቸው የህክምና አሰጣጥን የአርሶ አደር ቤቶችን በመከራየት ለማስቀጠል መወሰኑን የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ አስታውቋል፡፡

የህክምና ተቋማቱን ወደ ነበሩበት ለመመለስ በቢሊዮን ዶላር የሚገመት ገንዘብ እንደሚያስፈልግ የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አማኑኤል ኃይለ (ዶ/ር) ለሀገር ውስጥ ሚዲያ ገልፀዋል፡፡

የክልሉ ጤና ቢሮ እና የዓለም ጤና ድርጅት ጥናት፦

◻️ በክልሉ የሚገኙ 89 በመቶ የሚሆኑት የጤና ተቋማት ጉዳት እንደደረሰባቸው፤ 3 በመቶ ሙሉ በሙሉ መውደማቸውን፣

◻️ 99 በመቶ የህክምና ዕቃዎች ላይ ጉዳት እንደደረሰ፣ 72 በመቶ ከፍተኛ ጉዳት እንደሆነ እና 27 በመቶ የሚሆኑት መውደማቸውን አመላክቷል፡፡

👉 ከ46ሺህ በላይ የኤችአይቪ ኤድስ ክትትል የሚያደርጉ ታካሚዎች ውስጥ 37ሺህ የሚሆኑት ተገኝተው ህክምናቸውን ሲቀጥሉ ቀሪዎቹ ያሉበት አይታወቅም ተብሏል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👎21😁1
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
በፑቲን እና ትራምፕ መካከል በአላስካ የተደረገው ስብሰባ ለወደፊት ግንኙነቶች መሠረት እንደጣለ ማሳየት በሞስኮ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው - የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
❗️የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ እና የአሜሪካ አቻቸው ማርኮ ሩቢዮ በስልክ መወያየታቸውን የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ

በፑቲን እና ትራምፕ ድርድር የተደረሱ ስምምነቶችን ለመተግበር በሚያስችሉ ተጨባጭ እርምጃዎች ዙሪያ መወያየታቸውን ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ አስታውቋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
3
🇷🇺☪️ የሩሲያ እስልምና እምነት ተከታዮች መንፈሳዊ ጉባኤ ኃላፊ በተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ

“ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ጥበበኛ፣ እውነተኛ አማኝ ሙስሊም፣ ራሳቸውን ለእስልምና መሠረታዊ አገልግሎቶች አሳለፈው የሰጡ እና ለእስልምና ትምህርት እድገት የደከሙ ናቸው። ሁሉን ቻይ የሆነው አላህ ነፍሳቸውን ከወሰን የለሽ ፀጋው ስር እንዲያሳርፍ እንፀልያለን” ሲሉ የሞስኮ ሙፍቲ አልቢር ካዝራት ክርጋኖቭ፤ ለኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ባስተላለፉት መልዕክት ገልፀዋል።


ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ በአጋጠማቸው ድንገተኛ ሕመም ምክንያት እሁድ እለት በ94 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። ሥርዓተ ቀብራቸው ዛሬ በአዲስ አበባ ተፈፅሟል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
28👏5👍4
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በእኛ ምርት ከሁለት ዓመት በላይ የተነዱ መኪናዎች አሉ - ከከብት አጥንት የፍሬን እና ፍሪሲዮን ሸራ የሚያመርተው ወጣት

በሃይሉ ሰቦቃ "አስኬማ" ብሎ የሰየመውን ከከብት አጥንት፣ ከሴራሚክ ቁርጥራጮች እና ከሌሎች የተጣሉ ዕቃዎች የፍሬን እና ፍሪሲዮን ሸራ የሚያመርተውን ድርጅት የመሰረተው ከ3 ዓመት በፊት ነበር።

ከተጣሉ ዕቃዎች 1ሺ 400 አይነት የመኪና ፍሬን አካላትን በማምረት ላይ መሆኑን የሚናገረው ወጣቱ፤ ባሳለፍነው ዓመት ብቻ ከ30 ቶን በላይ የከብት አጥንት ከተለያዩ ቦታዎች ላይ ማንሳቱን ገልጿል።

"እስካሁን ከ6ሺህ 400 በላይ መኪናዎች የእኛኝ ምርት ተጠቅመዋል። ጥሬ ዕቃዎችን በቀላሉ ስለምናገኝ እየጠየቅን ያለነው አንድ ሦስተኛ የገበያውን ዋጋ ብቻ ነው" ብሏል።


📌ስፑትኒክ አፍሪካ ጋር በነበረው ቆይታ ለወጣቶች የሥራ ዕድል እንደፈጠረ አጫውቶናል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
22👏13
በናይጄሪያ የብያፍራ ተገንጣይ መሪን በመደገፍ የተቃውሞ ሰልፎች ተቀሰቀሱ

እስካሁን የታወቁ ጉዳዮች፦

🔙 መነሻ

🇬🇧 የብያፍራ ሕዝቦች ቡድን መሪ የሆኑት የእንግሊዝ እና ናይጄሪያ ጥምር ዜጋ ተሟጋቹ ናምዲ ካኑ ከእስር እንዲፈቱ የሚጠይቁ ሰልፎች ሰኞ ዕለት በመላው ናይጄሪያ ተቀስቅሰዋል ሲሉ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። ካኑ ከ2021 ጀምሮ ውድቅ ባደረጉት የአሸባሪነት እና ሀገር ክህደት ወንጀል ተከስሰው ታስረዋል።

➡️ ምን ተፈጠረ?

◻️ በተሟጋች ኦሞዬሌ ሶዎሬ በሚመራው ‘ናምዲ ካኑ አሁኑኑ ይፈቱ’ ዘመቻ ስር የተደራጁ መሰባሰቦችን ለማስቆም የጸጥታ ኃይሎች በአቡጃ አስለቃሽ ጋዝ ተኩሰው እስር መፈጸማቸው ተዘግቧል።

◻️ ፖሊስ ዋና ዋና መንገዶችን ዘግቷል፤ ወታደሮች እና የሀገሪቱ የደህንነት ኃይሎች ደግሞ ቁልፍ መገናኛዎችና የፌዴራል ቦታዎች ላይ ተሰማርተዋል።

◻️ በሌጎስ፣ እንደ ሌኪ እና ኦጆታ ባሉ ችግር ያለባቸው ቦታዎች ላይ ‘የኃይል ማሳያ’ ተካሂዷል የተባለ ሲሆን ፖሊስ ይህ እርምጃ ዓላማው አለመረጋጋትን ለመከላከል እና ‘የነዋሪዎችን ደህንነት ለማረጋገጥ’ እንደሆነ ገልጿል።

➡️ ባለሥልጣናት ምን አሉ?

◻️ መንግሥት የተቃውሞ ሰልፎቹ ፍርድ ቤቶች ላይ ጫና ለማሳደር የተደረጉ ሕገ-ወጥ ሙከራዎች እንደሆኑ ይገልጻል።
◻️ የፕሬዝዳንቱ አማካሪ ባዮ ኦናኑጋ በአቡጃ የተደረገውን የተቃውሞ ሰልፍ ‘የተመሳቀለ’ ሲሉ በመገለጽ፤ የካኑ ጠበቃ በሰልፉ በመቀላቀል የሕግ ሥነ-ምግባር ጥሰዋል ብለዋል።
◻️ የፖሊስ ኃላፊዎች ሰልፎቹ ‘የሕዝብን ሰላም እስካላስተጓጎሉ ድረስ’ እንደሚፈቀዱ አጽንኦት ሰጥተዋል።
◻️ የአናምብራ ገዥ ቻርለስ ሶሉዶ ተገንጣይነትን እንደማይደግፉ ገልጸው፤ “የኢግቦ ሰው ናይጄሪያን ይፈልጋል፤ ናይጄሪያም የኢግቦን ሰው ትፈልጋለች” በማለት ካኑ ከተፈቱ በኋላ ውይይት እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

➡️ አውድ

◻️ የካኑ የብያፍራ ሕዝቦች ቡድን የ1967–1970 ብያፍራ ጦርነት ቅሬታዎች በማስተጋባት ለደቡብ ምስራቅ ናይጄሪያ ነፃነትን ይሟገታል።
◻️ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ቡድኖች ባለሥልጣናት ከባድ እርምጃ ወስደዋል ሲሉ ይከሳሉ፤ የጸጥታ ኤጀንሲዎች ደግሞ የወሰዱት እርምጃ የሀገሪቱን መረጋጋት ለመጠበቅ እንደሆነ አጥብቀው ይናገራሉ።

➡️ አሁናዊ ሁኔታ

◻️ በአቡጃ እና ሌጎስ ከባድ የጸጥታ ጥበቃ እንደቀጠለ ሲሆን ባለሥልጣናት ያልተፈቀዱ ስብሰባዎች የሕዝብን ሥርዓት እንደጣሱ ተደርገው እንደሚወሰዱ አስጠንቅቀዋል ሲሉ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

◻️ ከማኅበራዊ ሚዲያ የተገኙ ምስሎች፤ ከናምዲ ካኑ ጠበቆች አንዱ የሆኑት አሎይ ኤጂማኮር በመጨረሻው ቪዲዮ (ቀይ ሸሚዝ ለብሰው) ይታያሉ።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
5🤔3
ሞሮኮ ካለፈው ዓመት 16 በመቶ ከፍ የሚል በጀት ለ2026 የጤና እና ትምህርት ዘርፍ መደበች

🇲🇦 ለእነዚህ ዘርፎች የተመደበው 140 ቢሊዮን ድርሃም (15 ቢሊዮን ዶላር) የሞሮኮን አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት 10 በመቶ ይሆናል። ውሳኔው በንጉሥ መሐመድ ስድስተኛ ከተመራው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ በኋላ ይፋ ሆኗል።

የንጉሣዊው ቤተ-መንግሥት የዘንድሮው የ4.8 በመቶ ጠንካራ የኢኮኖሚ ዕድገት ትንበያ ለጭማሪው ምክንያት እንደሆነ ገልጿል።

👉 ይህ ውሳኔ በቅርቡ የተሻሉ የመንግሥት አገልግሎቶችን በመጠየቅ ከተካሄዱት የወጣቶች ተቃውሞ በኋላ የተላለፈ ነው።

ምክር ቤቱ ከ35 ዓመት በታች ለሆኑ እጩዎች የምርጫ ውድድር ማቅለያ ደንብ እና 75 በመቶ የምርጫ ዘመቻ ወጪን የሚሸፍን የገንዘብ ድጋፍን ጨምሮ የወጣቶችንና የሴቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ ያለሙ የምርጫ ማሻሻያዎችን በተናጠል አጽድቋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
4
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
❗️❗️❗️ አዲሱ የማዳጋስካር ፕሬዝዳንት ሚካኤል ራንድሪያኒሪና ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር ልዩ ቃለምልልስ አደረጉ

ራንድሪያኒሪና የስፑትኒክን "ፓን አፍሪካኒዝም" አጉልተው ለአፍሪካ እያደረገ ለሚገኘው "ድጋፍ" አመስግነዋል።

ይህ ፕሬዝዳንቱ ቃለ መሐላ ከፈጸሙ ወዲህ ከዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኃን ጋር ያደረጉት የመጀመሪያ ቃለምልልስ ነው።

ቃለ ምልልሱን በቅርቡ በቴሌግራም፣ በኤክስ እና በድረ-ገጽ አማራጮቻችን ላይ ያገኙታል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
9
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ከብድር ይልቅ የሕዝብን የልማት አቅም ለማስተባበር ቅድሚያ መስጠት ይገባል - የናይጄሪያ ትራንስፖርት ባለሥልጣን

በተለይ የሀገር ውስጥ ባንኮች የሕዝቡን ሐብት ወደ ልማት መቀየር በሚያስችሉ ንቅናቄዎች ላይ በስፋት መሳተፍ እንዳለባቸው የናይጄሪያ ትራንስፖርት ባለሥልጣን የሕዝብ ኦፕሬሽን አስተዳደር ስፔሻሊስት አዴፖጁኤ ፎውካን ጠቁመዋል።

"ሕዝቡን ማስተባበር ከቻልን ዓለም አቀፍ ተቋማትን ለብድር ደጅ እንድንጠና የሚያስገድደን ምክንያት አይኖርም። ይህም ትራንስፖርትን ጨምሮ አኅጉሪቱ በሁሉም ዘርፎች ራሷን ለመቻል የምታደርገውን ጥረት በእጅጉ ይደግፋል" ብለዋል።


📌ስፑትኒክ አፍሪካ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ መሰል ሥራዎች በሕዝብ ዘንድ ተዓማኒነት እንዲኖራቸው ሊመሩበት ስለሚገባቸው መርሆችም አንስተዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
6
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ዩክሬን ከሩሲያ ጋር የምታደርገውን ጦርነት ታሸንፋለች ብዬ አላምንም - ትራምፕ

በተመሳሳይ የዩክሬንን ድል ከጨዋታ ውጪ እንደማያደርጉም ተናግረዋል፡፡

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
👏84🔥1
ኢትዮጵያ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የእዳ ጫና እና የአየር ንብረት ለውጥ ስጋት ላለባቸው ሀገራት የሚያደርገውን የፋይናንስ ድጋፍ መጠን እንዲያሳድግ ጠየቀች

ለአየር ንብረት ለውጥ ተጋላጭ የሆነችው ኢትዮጵያ ድርቅ፣ ጎርፍ እና የእዳ ጫና የልማት ጉዞዋን እየፈተነ እንደሚገኝ የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ በዋሽንግተን ለአየር ንብረት ተጋላጭ 20 ሀገራት ጥምረት (V20) የሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ተናግረዋል።

"ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ ፕሮግራም፣ የታዳሽ ኃይል በማስፋት እና የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን በማስተዋወቅ ለአረንጓዴ እድገት ያላትን ቁርጠኝነት በተግባር አሳይታለች" ብለዋል።


ከዓለም አጋሮች ጋር በመሆን ፍትሐዊ እና የማይበገር ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ስርዓት ለመገንባት ዝግጁ ነን ሲሉ ማከላቸውንም የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
5😁1🙏1
ጋና በሕገ-ወጥ የደን ሥራዎች ላይ በተደረገ ዘመቻ የማዕድን ቁፋሮ መሳሪያዎችን መያዟ ተዘገበ

🇬🇭 በአካባቢ ጥበቃ ልዩ ሥፍራ በሚሰጠው የኒዩንግ ደቡብ ጥብቅ ደን ውስጥ የፀጥታ የጋራ ግብረ ኃይል በሕገ-ወጥ የማዕድን ቁፋሮ ሥራዎች ላይ ባደረገው ድንገተኛ ፍተሻ ሰባት ኤክስካቫተሮችን እና 18 የውሃ ፓምፖችን መያዙን የአካባቢው መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

ይህ ዘመቻ ለደኖች ውድመት እና ለወንዞች ብክነት ምክንያት የሆነውን "ጋላምሴይ" ወይም ሕገ-ወጥ አነስተኛ የማዕድን ቁፋሮዎችን ለመዋጋት እየተደረጉ ያሉ ጥረቶች አካል እንደሆነ ተዘግቧል።

⛏️ የኒዩንግ ደቡብ ደን በዓለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ ጠቀሜታ ያለው የብዝሀ ሕይወት ሥፍራ የሚል ስያሜን ያገኘ ሲሆን ሕገ-ወጥ የማዕድን ቆፋሪዎች ከባለሥልጣናትና ከሕጋዊ የማዕድን ሥራ ፈቃድ ባለቤቶች ጋር የሚጋጩበት መነሻ ምክንያት ሆኗል ሲሉ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

መንግሥት በመደበኛ ፍተሻዎች እና መሳሪያዎችን በመያዝ የሕግ ማስከበር ሥራውን ቢያጠናክርም፤ የአካባቢ ውድመት ግን ቀጥሏል። ተሟጋቾች የደን ክምችቶችን ከማዕድን ቁፋሮ ሥራዎች ለመጠበቅ ጠንካራ ሕግ እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
9🙏3
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
❗️❗️❗️ አዲሱ የማዳጋስካር ፕሬዝዳንት ሚካኤል ራንድሪያኒሪና ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር ልዩ ቃለምልልስ አደረጉ ራንድሪያኒሪና የስፑትኒክን "ፓን አፍሪካኒዝም" አጉልተው ለአፍሪካ እያደረገ ለሚገኘው "ድጋፍ" አመስግነዋል። ይህ ፕሬዝዳንቱ ቃለ መሐላ ከፈጸሙ ወዲህ ከዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኃን ጋር ያደረጉት የመጀመሪያ ቃለምልልስ ነው። ቃለ ምልልሱን በቅርቡ በቴሌግራም፣ በኤክስ እና በድረ-ገጽ አማራጮቻችን…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
❗️❗️❗️ አዲሱ የማዳጋስካር ፕሬዝዳንት ሚካኤል ራንድሪያኒሪና ለሀገሪቱ መልሶ ማገገም ቅድሚያ እንደሚሰጡ አስታወቁ

“ይህን ከፍተኛ ንቅናቄ ያጎላው ጉዳይ የኤሌክትሪክ ኃይልና የውሃ አቅርቦት እጥረት መኖሩ ነው። ስለዚህ በቀጣይ የምናደርገው መፍትሄ በማፈላለግ፤ በአጭር ግዜ ውስጥና በተቻለ ፍጥነት በዚህ ረገድ ሊረዳን የሚችል አጋር ማግኘት ነው” ሲሉ ፕሬዝዳንት ከስፑትኒክ ጋር ባደረጉት የመጀመሪያ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ቃለ ምልልሳቸው ተናግረዋል፡፡


🔸 በመስከረም አጋማሽ በሀገሪቱ የተቀሰቅሰው ከፍተኛ ተቃውሞ የአንዲሪ ራጆሊና ዘመነ መንግሥት እንዲያበቀ አድርጎታል፡፡ ኮኖሌል ራንድሪያኒሪና የአዲሱ አስተዳደር መሪ ሆነው ጥቅምት 7 ቀን በከፍተኛ ሕገ-መንግሥታዊ ፍርድ ቤት ተሹመዋል፡፡

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔥53
2025/10/24 05:48:10
Back to Top
HTML Embed Code: