Telegram Web Link
Live stream finished (21 minutes)
❗️የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ከአሜሪካ አቻቸው ማርክ ሩቢዮ ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች እና በፑቲን-ትራምፕ ንግግር ቅድመ ዝግጅት ዙሪያ መወያየታቸውን ገለፁ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
6
በድሬዳዋ ደወሌ ባቡር ላይ በደረሰ አደጋ 14 ሰዎች ሲሞቱ 29 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሰ

ከደወሌ መነሻውን አድርጎ ወደ ድሬዳዋ በመጓዝ ላይ የነበረ የሕዝብ ማመላለሻ ባቡር ትላንት ሌሊት 8:00 አካባቢ በሶማሌ ክልል ሺኒሌ ወረዳ ላይ አደጋው እንደደረሰበት የአካባቢው ሚዲያ ዘግቧል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
😢24🤔5🙏32🔥1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
❗️የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ስፑትኒክ በሀገሪቱ እያከናወነ ያለውን ሥራ አወደሱ

“ከአዲሱ የትብብር መስኮች አንዱን ማለትም በሩሲያ እና በኢትዮጵያ ሚዲያ መካከል ያለውን ግንኙነት ተወያይተናል። ሚኒስቴሩ በከፍተኛ ደረጃ ተወዳጅነት እያገኘ ስለመጣው የስፑትኒክ ኤጀንሲ ሥራ በአድናቆት አንስተዋል። ተከታዮቹ እየጨመሩ ነው። ይህ በእርግጥ በጣም የሚያስደስት ነው፤ ምክንያቱም በዛሬው ዓለም እውነትን በተለያዩ ሀገራት ለታዳሚዎች ማድረስ በጣም ጠቃሚ ተግባር ነው" ሲሉ የሁለትዮሽ ውይይቱን ተከትሎ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከኢትዮጵያ አቻቸው ጌዲዮን ጢሞቲዮስ ጋር በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተናግረዋል።


ስፑትኒክ ባለ ብዙ አገልግሎት የኤዲቶሪያል ማዕከሉን በአዲስ አበባ ባለፈው ዓመት የካቲት ወር መክፈቱ ይታወሳል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
8👍8😁1
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
❗️የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ስፑትኒክ በሀገሪቱ እያከናወነ ያለውን ሥራ አወደሱ “ከአዲሱ የትብብር መስኮች አንዱን ማለትም በሩሲያ እና በኢትዮጵያ ሚዲያ መካከል ያለውን ግንኙነት ተወያይተናል። ሚኒስቴሩ በከፍተኛ ደረጃ ተወዳጅነት እያገኘ ስለመጣው የስፑትኒክ ኤጀንሲ ሥራ በአድናቆት አንስተዋል። ተከታዮቹ እየጨመሩ ነው። ይህ በእርግጥ በጣም የሚያስደስት ነው፤ ምክንያቱም በዛሬው ዓለም እውነትን በተለያዩ…
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
🇪🇹🇷🇺ኢትዮጵያ ከሩሲያ ጋር የተፈረመው የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ግንባታ ስምምነት በቀጣናው ቀዳሚ የኃይል አቅራቢነቷን እንደሚያጠናክር ተስፋ ታደርጋለች - ጌዲዮን ጢሞቲዮስ ለስፑትኒክ አፍሪካ

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከላቭሮቭ ጋር በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ከስፑትኒክ አፍሪካ ዘጋቢ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፤ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ግንባታን ለማካሄድ ከሩሲያ ጋር የተደረሰው የቅርብ ጊዜ ስምምነትን የተመለከቱ በርካታ ቁልፍ ነጥቦችን አብራርተዋል።

🟠 የቀጣናዊ ሚናን ማሳደግ፦ ፕሮጀክቱ በሁለትዮሽ ግንኙነት ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ ከመሆኑም በላይ የላቀ የኒውክሌር ቴክኖሎጂን ከሰሃራ በታች ላሉ የአፍሪካ ሀገራት ያስተዋውቃል። ይህ ኢትዮጵያን በክልሉ የኃይል ፈጠራ ዘርፍ ግንባር ቀደምት እንድትሆን ያደርጋታል።

🟠 የኤልክትሪክ ኃይል ወደ ውጭ ስለመላክ፦ ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቅ ጋር ተያይዞ ኢትዮጵያ እንደ ኬንያ፣ ጅቡቲ እና ሱዳን ላሉ ጎረቤት ሀገራት የኤሌክትሪክ ኃይል መላክ ጀምራለች። የኒውክሌር ኃይል መጨመር፤ የኤሌክትሪክ ኃይል ወደ ውጭ መላክን የበለጠ ለማጠናከር እና የቀጣናዊ ውህደትን ለማሳደግ ያለመ ነው።

🟠 የኢንዱስትሪ ልማት መነሳሳት፦ ንጹህ ኃይል ከማቅረብ ባለፈ አዲሱ የኒውክሌር ተቋም የኢትዮጵያን ሰፋፊ የኢንዱስትሪ ልማት እና በተለያዩ ዘርፎች ያሉ ቴከኖሎጂዎችን የማዘመን ጥረቶችን ከማፋጠን ጋር የተጣጣመ ነው።

🟠 የቴክኖሎጂ እድገት፦ የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ሃብቶችን እና አዳዲስ የኒውክሌር መፍትሄዎችን አጣምሮ በመጠቀም፤ ኢትዮጵያ ለአፍሪካ የወደፊት እድገት ውስጥ ወሳኝ በሆኑት አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እና አዳዲስ የቴክኖሎጂ ዘርፎች ግንባር ቀደም መሆን ትፈልጋለች።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
👍91😁1
ሩሲያ በአላስካው የትራምፕ-ፑቲን ስብሰባ ላይ በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት ለመንቀሳቀስ ዝግጁ ናት - ላቭሮቭ

👇ሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በዩክሬን ግጭት አፈታት ዙሪያ ያነሷቸው ተጨማሪ ነጥቦች፦

🟠 የጦርነቱ መሠረታዊ መንሳኤዎች መፍትሄ ሳያገኙ የተኩስ አቁም እንዲደረግ የሚቀርቡ ጥሪዎች ፑቲን እና ትራምፕ በአላስካ ከተስማሙባቸው ጉዳዮች ጋር ይቃረናሉ።

🟠 በዩክሬን ውስጥ አፋጣኝ የተኩስ ማቆም ከተደረገ አብዛኛው የዩክሬን ክፍል በናዚ ቁጥጥር ስር ይቆያል ማለት ነው።

🟠 የሩሲያ ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ ግቡን እያሳካ ነው፤ ያለምንም ጥርጥር ስኬታማ ይሆናል።

🟠 በሩሲያ-አሜሪካ የመሪዎች ጉባኤ ዝግጅት ላይ ሀሳባቸውን የሰጡት ላቭሮቭ ዋናው ነገር በአላስካ የተደረሱ ስምምነቶችን ወደፊት እንዴት መውሰድ አለብን የሚለው ነው ብለዋል።

🟠 ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሩቢዮ ጋር የስልክ ግንኙነት ለማስቀጠል ተስማምተናል።

🟠 ፖላንድ በፑቲን አውሮፕላን ዙሪያ የሰነዘረችው ማስፈራሪያ የሽብር ጥቃቶችን ለመፈጸም ፈቃደኝነቷን ያሳያል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
8
አፍሪካ ከውጭ ለሚገቡ ምግቦች በዓመት ከ50 እስከ 100 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ታደርጋለች - ኮሚሽነር ሞሰስ ቪላካቲ

6ኛው የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን የግብርና፣ የገጠር ልማት፣ የውኃ እና የአካባቢ ልዩ የቴክኒክ ኮሚቴ ስብሰባ በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ነው።

ውይይቱን በንግግር የከፈቱት የኅብረቱ ኮሚሽን የግብርና፣ የገጠር ልማት፣ የብሉ ኢኮኖሚ እና የዘላቂ አካባቢ ኮሚሽነር ሞሰስ ቪላካቲ አፍሪካ የምግብ ዋስትና ችግር ውስጥ ነች ብለዋል።

“አፍሪካ ምንም እንኳ የተትረፈረፈ የተፈጥሮ ሃብት ቢኖራትም በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የአህጉሪቱ ነዋሪዎች የምግብ ዋስትናቸውን አላረጋገጡም።"


የአየር ንብረት ለውጥ፣ የብዝኃ ሕይወት ውድመት እና የመሬት መራቆት ለአህጉሪቱ የምግብ ዋስትና ችግር በምክንያትነት የጠቀሷቸው ጉዳዮች ናቸው።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
3👍2😱2
ማላዊ ነፃ ትምህርት እና ርሃብን ለመዋጋት የአደጋ ግዜ የምግብ አቅርቦት ይፋ አደርገች

🇲🇼 ከመጪው ጥር 2026 ጀምሮ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ለሁሉም የማላዊ ዜጎች ነፃ እንደሚሆን አዲስ ተሿሚው ፕሬዝዳንት ፒተር ሙታሪካ አስታውቀዋል።

"ወላጆች አሁን ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት ላለመላክ ምንም ምክንያት አይኖራቸውም" ሲሉ የተናገሩት ሙታሪካ፤ ትምህርት ለብሔራዊ ልማት መሠረት መሆኑን ገልጸዋል።


🇿🇲🤝 በተመሳሳይ ስለ ሀገሪቱ የምግብ ቀውስ ያነሱት ፕሬዝዳንቱ፤ የምግብ እጥረት ላለባቸው ሰዎች የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ አቅርቦት ከውጭ እንደሚገባ ይፋ አድርገዋል፡፡ መንግሥት ከአራት ሚሊዮን በላይ የምግብ እጥረት ያለባቸውን ሰዎች ለመመገብ 200ሺህ ቶን በቆሎ ከዛምቢያ እየገዛ መሆኑንም ጠቁመዋል።

ፕሬዝዳንቱ ስምምነቱን ለመፈፀም "ሁሉም ነገር ዝግጁ" እንደሆነና የግብርና ሚኒስትሩም በዛምቢያ ቅድመ ዝግጅቶች እያጠናቀቁ እንደሚገኙ ለዜጎቻቸው አረጋግጠዋል፡፡

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
7👍6
🇪🇹🇨🇳 ኢትዮጵያ ለቻይና መንግሥት የምትከፍለውን የ5.38 ቢሊዮን ዶላር ዕዳ በከፊል ወደ ቻይና ገንዘብ (ዩዋን) ለመቀየር ንግግር ጀመረች

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ እዮብ ተካለኝ በቅርቡ በቤጂንግ ባደረጉት ጉብኝት ከቻይና ኤክስፖርት-ኢምፖርት ባንክ እና ከቻይና ሕዝብ ባንክ ጋር በዚሀ ረገድ ውይይት መጀመራቸውን አስታውቀዋል።

ኢትዮጵያ በዚህ ጥያቄዋ ቀደም ሲል ለተመጣጣኝ ክፍያ ወደ ዩዋን ፊታቸውን እያዞሩ ያሉትን እንደ ስሪላንካ፣ ሃንጋሪ እና ኬንያ ያሉ ሀገራትን ተቀላቅላለች፡፡

“ቻይና አሁን ለኛ በጣም አስፈላጊ አጋር ናት፤ የንግድና ኢንቨስትመንት መጠኑ እያደገ ነው፡፡ ስለዚህ የተወሰነ የመገበያያ ልውውጥ መኖሩ ምክንያታዊ ነው፡፡ በትክክልም ይህ በሂደት ያለ ነገር ነው፤ በይፋ ጠይቀናል እናም እየሠራንበት ነው” ሲሉ የብሔራዊ ባንክ ገዥው ከዓለም አቀፋ የገንዘብ ተቋም ዓመታዊ ስብሰባ ትይዩ በሰጡት ቃለ ምልልስ ተናግረዋል።


ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
6👍6😁2
🇷🇺 ምዕራባውያን ወሬ ያሠራጫሉ፤ ከዚያም ራሳቸው ያስተባብላሉ - ሩሲያ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ በሰርጌ ላቭሮቭ እና በአሜሪካ አቻቸው ማርኮ ሩቢዮ መካከል ይካሄዳል የተባለው ውይይት መዘግየቱን በሚገልጹ ዘገባዎች ዙሪያ አስተያየታቸውን አጋርተዋል፡፡

💬 "እነሱ ራሳቸው ወሬ ያሠራጫሉ፤ ከዚያም ራሳቸው ያስተባብላሉ" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡


በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
9
አዲሱ የማዳጋስካር ፕሬዝዳንት የሩሲያን አምባሳደር ተቀብለው አነጋገሩ

ሚካኤል ራንድሪያኒሪና እና አንድሬ አንድሬየቭ በሽግግር ወቅት በሩሲያ እና በማዳጋስካር መካከል ስለሚኖረው ወዳጃዊ ትብብር ተወያይተዋል።

ጥቅምት 7 ሥልጣን ከያዙ ወዲህ ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር ባደረጉት የመጀመሪያ ቃለ ምልልስ አዲሱ ፕሬዝዳንት ከዚህ ቀደሙ አካሄድ "ሙሉ በሙሉ ፍቺ መፈፀም እንደሚገባ" አስታውቀዋል።

"የምናደርገው ከእኛ ጋር በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የሚሠሩ አጋሮችን መፈለግ ነው" ሲሉም ገልፀዋል።


በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
6👏6👍4
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
“እኛጋ የሚሸጡ ሸራዎች የገበያውን አንድ ሶስተኛ ዋጋ ነው የሚጠይቁት” - ሥራ ፈጣሪው ወጣት

📌 ከከብት አጥንት የፍሬን እና ፍሪሲዮን ሸራ የሚያመርተው በሃይሉ ሰቦቃ፤ ሸራ ከውጭ ሲመጣ በጣም ውድ እንደሆነ ገልጾ፤ “እኛ ጥሬ እቃውን በቀላሉ ተጥሎ ስለምናገኘው” ዋጋው ሊቀንስ ችሏል ሲል ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግሯል፡፡

“ከግምሽ በመቶ በላይ አጥንት ሆነ እንጂ ሌሎቹም የምንጠቀማቸው ጥሬ እቃዎች የሚጣሉ ነገሮች ናቸው፡፡ ለምሳሌ ሴራሚክ እንጠቀማለን፡፡ ሴራሚክ ስንጠቀም ግን አዲሱን ገዝተን ሳይሆን ተሰባብሮ የወደቀውን ሰብስበብን ነው የምንጠቀመው፡፡ ሌሎች ፊለር ማተሪያሎችም አሉ፡፡ እንደ ቆዳ የመሳሰሉ ነገሮች፡፡ እነዚህ ሲደመሩ ትልቅ ስትራክቸራል ጥንካሬ ያለው ለፍሬን አገልግሎት የሚውል ቁጥር ያመጣሉ፡፡ አይ ኤስ ኦ ሰርቲፋይድ ነን፡፡ ምርታችን አገልግሎት ላይ ከመዋሉ በፊት በጣም ብዙ ጊዜ ተሞክሯል፡፡”


ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔥9👏92
ወደሀገር ውስጥ ከሚገቡ ተሽከርካሪዎች 99 በመቶዎቹን የኤሌክትሪክ ለማድረግ ታቅዷል - የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር

አሁን ላይ በሀገሪቱ ከሚገኙ አጠቃላይ ተሽከርካሪዎች ሰባት በመቶ ያህሉን የሚሸፍኑ 115 ሺህ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች በእንቅስቃሴ ላይ እንደሚገኙ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ በርኦ ሀሰን ለሀገር ውስጥ ሚዲያ ተናግረዋል፡፡

ከ10 ዓመታት በኋላ በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ቁጥር ከግማሽ ሚሊየን በላይ ለማድረስ መታቀዱን ጠቁመው፤ በሀገር ውስጥ የሚገጣጠሙ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ከቀረጥ ነጻ እንዲሆኑ መደረጉንም አንስተዋል።

በተጨማሪም የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች በቀላሉ እንዲገቡ ሂደቱን የማቅለልና ተደራሽነታቸውን ለማስፋት እንደሚሠራ አስታውቀዋል፡፡

በሰው ሠራሽ አሰተውህሎት የበለፀገ ምሥል

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
👏6👍43👎3
“ሩሲያ አፍሪካውያን በነጻነት ፖሊሲያቸውን እንዲያወጡና እንዲተገብሩ የማድረግ ልምዱ አላት” - የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር

📌 በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ጌድዮን ጢሞቲዮስ እና የሩሲያ አቻቸው ሰርጌ ላቭሮቭ መካከል ዛሬ በሞስኮ የተካሄደውን ውይይት አስመልክቶ ለስፑትኒክ አፍሪካ አስተያየታቸውን የሰጡት የፖለቲካ ሳይንስ ባለሙያው እንዳለ ንጉሴ፤ ለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ፣ ኃይል እና ዲፕሎማሲ ውጥኖች የሩሲያ ድጋፍ ቁልፍ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

“የአንድ ሀገር ዲፕሎማሲ በኢኮኖሚ መደገፍ አለበት፤ በኢነርጂ ነጻነት መደገፍ አለበት፤ ጥራት ባለው መከላከያ ኃይል መደገፍ አለበት፡፡ ከዚህ አንጻር እንግዲህ በዓለም ወሳኝ ድጋፍ ከሚሰጡ ሀገሮች ደግሞ ሩሲያ ከግንባር ቀደሞቹ አንዷ ናት፡፡ ስለዚህ ሩሲያ የኢትዮጵያን መከላከያ ለመደገፍ የወሰደችው ተነሳሽነት የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ ባስተማማኝ መልኩ እንዲተገበር፤ ነጻነቷንም የበለጠ እንድታስቀጥልና በሌሎች ሀገራት ለሚኖራት ክብርም ፋይዳው የላቀ ነው፡፡”


🇷🇺 ላቭሮቭ ሩሲያ ‘ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄዎች’ የሚለውን መርህ ሁሌም ታከብራለች ሲሉ በዛሬው ስብሰባቸው ገልፀዋል፡፡ ባለሙያው በዚህ ዙሪያ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል 👇

“የአፍሪካ ፍላጎት ችግሮቿን በራሷ ለመፍታት፤ ፖሊሲዎቿን በነጻነት እንድታወጣ ነው፡፡ ሩሲያም ቻይናም እንደዚህ አይነት ፖሊሲዎችን በመደገፍ ተግባራዊ በማድረግ ይታወቃሉ፡፡ ከዚህ አንጻር ፖሊሲን በነጻነት የማውጣት ችግር...ጣልቃ ገብነቱ ስላለ ሁልጊዜ የሆነ ቦታ ይሄዳል፣ ይቆማል፡፡ ይሄ እንዳይሆን የሩሲያ ድጋፍ በጣም አስፈላጊ ነው” ብለዋል፡፡


ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👏52
ፈረንሳይ እና ጀርመን አፍሪካን ለማተራመስ፤ ጥላቻ ቀስቃሾችን እያበረታቱ ነው - የኢኳቶሪያል ጊኒ ምክትል ፕሬዝዳንት

🇬🇶 ፓሪስ "ከሃዲ" አፍሪካውያንን እየደገፈች ነው በማለት በይፋ የከሰሱት ቴዎዶሮ ንጉዌማ ኦቢያንግ ማንጌ፤ በርሊን እንዲህ አይነቱን ዘመቻ በመቀላቀሏ ውግዘት ሰንዝረዋል።

"ሰላምን እንዲያደፈርሱ እና የራሳቸውን ባሕልና ወንድም እንዲቃወሙ" ለጥቅም የተገዙ ግለሰቦችን በማነሳሳቷ ምክትል ፕሬዝዳንቱ ፈረንሳይ ላይ "ቁጣቸውን" ገልጸዋል።

🇫🇷🇩🇪 ባለፈው ሳምንት በአውሮፓ የሚኖር "ሀገሩን የካደ የኢኳቶሪያል ጊኒ ዜጋ"፤ ከማድሪድ የጀርመን አምባሳደር እና ከከፍተኛ የፈረንሳይ ዲፕሎማት ጋር በመሆን የፈጠረውን ክስተት ጠቅሰዋል።

👉 ባለሥልጣኑ የትኛውን ክስተት ማለት እንደፈለጉ ባይገልጹም፤ ይፋዊ መግለጫቸው የተሰጠው የኢኳቶሪያል ጊኒ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች አልፍሬዶ ኦኬንቬ ለፍራንኮ-ጀርመን የሰብዓዊ መብት ሽልማት ከታጨ በኋላ ነው።

ፈረንሳይ ሀገራቸውን ለማተራመስ "ስልታዊ የትንኮሳ ፖሊሲ" እየተከተለች ነው ያሉት ምክትል ፕሬዝዳንቱ፤ ፓሪስ በማሊ፣ ኒጀር እና ቡርኪና ፋሶ ባሉ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ላይ ይህንን ዘዴ ተጠቅማበታለች ብለዋል።

"አፍሪካ እንደዚህ አይነት ሴራዎች መረዋታል!" ሲሉ ሀሳባቸውን አጠቃለዋል።


በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
9👏9
2025/10/26 08:04:45
Back to Top
HTML Embed Code: