Telegram Web Link
🇪🇹 በዘንድሮ የመኸር ወቅት 177 ሚሊዮን ኩንታል የስንዴ ምርት ይጠበቃል - የግብርና ሚኒስትር  

ሚኒስትሩ አዲሱ አረጋ በስንዴ እየለማ ከሚገኘው 4.5 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ወስጥ 2 ነጥብ 9 ሚሊዮን ሄክታሩ በኩታገጠም የአስተራረስ መንገድ እየለማ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

🌾 በዘንድሮ የመኸር ወቅት በአገር አቀፍ ደረጃ በተለያዩ ሰብሎች ከተሸፈነው 20 ነጥብ 7 ሚሊየን ሄክታር መሬት 653 ሚሊዮን ኩንታል ምርት እንደሚጠበቅም አክለዋል።

ኢትዮጵያ በየዓመቱ በአማካይ እስከ 1 ቢሊዮን ዶላር በማውጣት የስንዴ ምርት ከውጭ ስታስገባ እንደነበር ያስታወሱት ሚኒስትሩ፤ ባለፉት ዓመታት ስንዴን በበጋና በክረምት በስፋት በማልማት የውጭ ምንዛሬ ወጪውን ማዳን መቻሉንም ተናግረዋል።


የአየር ንብረት የሚቋቋም የስንዴ እሴት ሰንሰለት ልማት ፕሮጀክት፣ ከአፍሪካ ልማት ባንክ እና ከመንግሥት በተገኘ በጀት በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በሶማሌ እና በአፋር ክልሎች በ76 ወረዳዎች እየተተገበረ እንደሚገኝ የግብርና ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል።

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
8😁7👏1🙏1
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
የሩሲያ ጦር በዛፖሮዥዬ እና በድኔፕሮፔትሮቭስክ ክልሎች ሦስት መንደሮች ነፃ አወጡ እነዚህ አካባቢዎች ኖቮኒኮላዬቭካ፣ ፕሪቮልኖዬ እንዲሁም ዬጎሮቭካ መሆናቸውን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል። ከቅርብ ወራት ወዲህ የሩሲያ ጦር ኃይሎች በዶንባስ ክልል እና ባሻገር በልዩ ወታደራዊ ዘመቻ ማዕቀፍ ውስጥ ያሉ መንደሮችን ተራ በተራ ነጻ እያወጣ በከፍተኛ ፍጥነት ወደፊት እየገሰገሰ ነው። 👉 ስለ ዩክሬን…
❗️የሩሲያ ኃይሎች በኩፕያንስክ እና በክራስኖአርሜይስክ የተከበቡትን የዩክሬን ቡድኖች መደምሰሳቸውን ቀጥለዋል - መከላከያ ሚኒስቴር

በልዩ ወታደራዊ ዘመቻው የኩፕያንስክ አካባቢ፣ የዩክሬን ክፍሎች ከክበባው ወደ ኦስኮል ወንዝ ቀኝ ዳርቻ ለመውጣት ያደረጓቸው አራት ሙከራዎች ተመክተዋል፤ በዚህም እስከ 50 የሚደርሱ የዩክሬን ወታደሮች መገደላቸውን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።

በክራስኖአርሜይስክ አካባቢ ደግሞ በዛሬው ዕለት ከ60 በላይ የዩክሬን ወታደሮች መገደላቸውን ሚኒስቴሩ አክሎ ገልጿል።

በትናንትናው ዕለት የሩሲያ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ቫሌሪ ጌራሲሞቭ ለፑቲን ባቀረቡት ሪፖርት፣ የሩሲያ ጦር በክራስኖአርሜይስክ ጠላትን የመክበብ ሥራውን እያጠናቀቀ ሲሆን፣ በኩፕያንስክ ደግሞ በኦስኮል ወንዝ ላይ ያለውን መሻጋሪያ መያዙን ገልጸዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
👏83🫡2
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
ላቭሮቭ ከሰሜን ኮሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቾይ ሰን ሁይ ጋር ባደረጉት ንግግር የሰጡት መግለጫ ዋና ዋና ሐሳቦች፦ 🔸 ሩሲያ ኩርስክ ክልልን ነጻ ለማውጣት የረዱትን የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች የጀግንነት ተግባር ፈጽሞ አትረሳም። 🔸 በሁለቱ አገራት መሪዎች የተደረሱ ስምምነቶች እየተተገበሩ በመምጣታቸው በሞስኮ እና በፒዮንግያንግ መካከል ያለው ግንኙነት ባለፉት ሦስት ወራት ከመንፈቅ ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ ተጠናክሯል።…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
❗️ፑቲን የሰሜን ኮሪያን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቾይ ሰን ሁይ በክሬምሊን ተቀበሉ

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ስብሰባውን ሲጀምሩ ለየኮሪያ ሕዝባዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የአገር ውስጥ ጉዳዩች ሊቀመንበር ኪም ጆንግ ኡን መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል።

"ስለ ግንኙነታችንና ስለልማት ተስፋዎቻችን በቤጂንግ በዝርዝር ተወያይተናል። ሁሉም ነገር በእቅዱ መሠረት እየሄደ ነው፤ እባክዎን የእኔን መልካም ምኞት ለእሳቸው ያስተላልፉልኝ" ሲሉ ተደምጠዋል።


በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
13👏6
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
🇪🇹 በአዲስ አበባ በ2ተኛው ምዕራፍ የተሠሩ አራት የኮሪደር ልማት መስመሮች ለአገልገሎት ከፍት ተደርጉ

🛣 ከመስቀል አደባባይ - መገናኛ - ሳዉዝ ጌት፣  ከአንበሳ ጋራዥ -ጎሮ ፣ ከአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬሽን ማዕከል - ጎሮ -ቦሌ ቪአይፒ ተርሚናል እንዲሁም ከሳር ቤት - ጀርመን አደባባይ - ጋርመንት - ፉሪ አደባባይ መስመሮች ናቸው፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ “የከተማችን ነዋሪዎች... ለጋራ ልማት በመተባበር፣ ቡና እያፈላ፣ ውሃ እያቀረበ ለልማት ሥራዉ ዉጤታማነት ላሳየዉ ከፍተኛ ድጋፍ ልባዊ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።” ሲሉ በማኅበራዊ የትስስር ገጻችው ላይ ጽፈዋል፡፡


🌇 በ1ኛ እና በ2ኛ ዙር የኮሪደር ልማት ሥራዎች ከተጠናቀቁ መሠረተ-ልማቶች መካከል፦

🔸 342 ኪ.ሜ የእግረኛ፣ 185 ኪ.ሜ የተሽከርካሪ እና 241 ኪ.ሜ የሳይክል መንገዶች ተሠርተዋል፡፡

🔸 101 የሕጻናት መጫወቻዎች፣ 155 የስፓርት ማዘውተሪያዎች እና 210 የሕዝብ መፀዳጃዎች ተገንብተዋል።

🔸 153 ዘመናዊ ፓርኪንግ እና ተርሚናሎችም ለአግልግሎት በቅተዋል፡፡

ለፕሮጀክቶቹ መሳካት አስተዋጻኦ ላበረከቱ "ከማዕከል እስከ ወረዳ ያሉ አመራሮች እና ሠራተኞች፣ ኮንትራክተሮች፣ አማካሪዎች፣ ማኅበራት፣ በጎ ፈቃደኞች እና ሌሎችም" ውቅና ተሰጥቷል፡፡

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
🖕76👏4👍2👌2
#viral | በሞስኮ ሰማይ ላይ የታየው ምስጢራዊ አረንጓዴ የእሳት ኳስ፤ የጠፈር አለት ስባሪ ወይስ የጠፈር ቆሻሻ?

ዛሬ ማለዳ ላይ ሞስኮ አቅራቢያ የተቀረፁ እና በማኅበራዊ የትስስር ገፆች ላይ ከፍተኛ ተቀባይነት ያገኙ ቪዲዮዎች የሚያሳዩት ትንሽዬ ሜትሮይት (የጠፈር አለት) ወይም የጠፈር ቆሻሻ ሊሆን እንደሚችል፣ የሩሲያ የጠፈር ምርምር ኢንስቲትዩት የፀሐይ አስትሮኖሚ ላቦራቶሪ ኃላፊ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።

ኃላፊው እንዳብራሩት፣ "ይህ ምናልባት 10 ሴንቲሜትር የሚሆን ሜትሮይት ሊሆን ይችላል... ሰዎች ከ5 እስከ 10 ሴ.ሜ የሚደርሱ ድንጋዮች እንዲህ ያለ ብርሃናማ መስመር መፍጠር መቻላቸው ብዙ ጊዜ ይገርማቸዋል፤ ግን እውነታው ይህ ነው።"


አረንጓዴው ቀለም የተፈጠረው አብዛኛውን ጊዜ በእንደነዚህ ዓይነት አካላት ውስጥ በሚገኝ ከፍተኛ የኒኬል ይዘት ምክንያት ነው ሲሉ ሳይንቲስቱ ገልጸዋል። አክለውም፣ ይህ አካል በከባቢ አየር ውስጥ ሙሉ በሙሉ ተቃጥሎ አልቆ ሊሆን ይችላል ብለዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
👏54👍3
ሩሲያ ማሌዥያ ትላልቅ አቅም ያላቸውን የኒውክሌር ኃይል ማመንጫዎች እና ትናንሽ 'ሞጁላር' ማብለያዎችን በመገንባት ለመርዳት ዝግጁ ነች - ባለሥልጣን

🇷🇺🇲🇾 የሩሲያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አሌክሲ ኦቨርቹክ ከማሌዥያው አቻቸው ፋዲላህ ዩሶፍ ጋር ባደረጉት ስብሰባ ላይ እንደገለጹት፣ በሩሲያ እና በደቡብ ምሥራቅ የእስያ አገራት ማኅበር መካከል ያለውን ውይይት ለማራመድ ኳላ ላምፑር የያዘችው ገንቢ አቋም የሚደነቅ ነው።

ሩሲያ የውጭ ኢኮኖሚያዊ ግንኙነቷን ማስፋፋት እንዲሁም ከማኅበሩ ጋር ያላትን ትብብር ማጠናከር ቁልፍ ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ጉዳዮች አንዱ ሆኖ እንደሚቀጥል የሩሲያው ባለሥልጣን ጠቁመዋል።

👉 ሁለቱ ወገኖች የማደግ እና የአይነተ ብዙ የሁለትዮሽ የንግድ እምቅ አቅም እንዳላቸው አጉልተው አሳይተዋል።

የኦቨርቹክ ጽሕፈት ቤት እንዳለው፣ "ከጥር እስከ ነሐሴ 2017 ባለው ጊዜ ውስጥ የነበረው የሁለትዮሽ ንግድ፣ ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ32.1% ጨምሮ 2.47 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል። ሩሲያ ለማሌዥያ የምታቀርባቸውን የኃይል ምንጮች፣ መድኃኒቶች እና የኢንዱስትሪ ዕቃዎች የሕክምና መሣሪያዎችን ጨምሮ አቅርቦቶች በከፍተኛ ሁኔታ ለማሳደግ ያሉትን ጠንካራ ዕድሎችን በማየት ላይ ትገኛለች።"

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
2👍2
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
❗️❗️❗️ “የአዕምሮ እድገት ዉሱንነት ያለባቸው ልጆች እንደማንኛውም ሰው ሕይወት ይገባቸዋል” - የዲቦራ ፋውንዴሽን ዋና ሥራ አስኪያጅ

ቤኪ አባዱላ በ100ኛው የሩሲያ የሕዝብ ዲፕሎማሲ ቀን አከባባር ላይ እየተሳተፈች ሲሆን፣ በዓለም አቀፍ የጋራ ጥረት ፎረም ላይ "መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እና ዲፕሎማሲ" በሚል ርዕስ ንግግር እንደምታደርግ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግራለች።

🗣"ሩሲያ ውስጥ ካሉ ተመሳሳይ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጋር አጋርነት ለመፍጠር፣ እርዳታ ለማግኘት፣ የእውቀት ሽግግር ለማግኘት፣ የልምድ ልውውጥ ለማድረግ ተዘጋጅተናል ... ሩሲያ ውስጥ የአዕምሮ እድገት ዉሱንነት ላለባቸው ልጆች የሚደረገውን እንክብካቤ እና የሚሰጣቸውን ሥልጠና ኢትዮጵያ ላይ እንዲሰጣቸው ለማድረግ ነው የመጣሁት" ስትል የሁነቱን አስፈላጊነት ገልጻለች።


ፋውንዴሽናቸው ውስጥ ልዩ ልዩ የአዕምሮ እድገት ውሱኑነት ያለባቸው ከ2 ሺህ በላይ ልጆች እንዳሉ በመግለጽም፣ ልጆቹ ከተማሩ፣ ሥልጠናዎችን ካገኙ የራሳቸውን ሕይወት መምራት እንደሚችሉ አብነት በመጥቀስ አስረድታለች፡፡

“... ወደ ትምህርት እንዲገቡ፣ ትምህርት ከተማሩ በኋላ ደግሞ ሥራ እንዲቀጠሩ እናደርጋለን። እስካሁን ወደ 20 ልጆች ገደማ የተቀጠሩ አሉን፡፡ አስራ አንዱ በዲቦራ ፋውንዴሽን ነው፡፡ ሌሎቹ ደግሞ ኢትዮጵያን ኤርላይንስ፣ ኢትዮ ቴሌኮም፣ አዋጭ፣ ሆላንድ ዴይ ቀጥሮልናል።”


🇷🇺 🇪🇹 ቤኪ አባዱላ የሩሲያ መንግሥት ለኢትዮጵያ ተማሪዎች ያደረገውን እና እያደረገ ያለውን ነፃ የትምህርት ዕድሎች እና ሌሎች ድጋፍ በማንሳት ምስጋና አቀርባለሁ ብላለች።

📌 ቤኪ በሞስኮ ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር ያደረገችውን ቆይታ ይመልከቱ 👆

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
6🙏4
ሞስኮ ከዋሽንግተን ጋር ግንኙነት ለመመሥረት ዝግጁ መሆኗን ዲሚትሪ ፔስኮቭ ተናገሩ

👇 የክሬምሊን ቃል አቀባይ የሰጡት መግለጫ ዋና ዋና ይዘቶች፦

🟠 ግልጽነት ቢኖርም ሩሲያም ሆነ ፑቲን የሚመሩት በራሳቸው ብሔራዊ ጥቅም ነው።

🟠 አውሮፓውያን በሩሲያ ጥላቻ እና በኃይለኛ የቁጣ ስሜት  ውስጥ ይገኛሉ።

🟠 ሩሲያ የራሷን ደኅንነት ለማረጋገጥ ያለማቋረጥ እየሠራች ነው፤ እንዲሁም አዳዲስ የጦር መሣሪያዎችን ማልማት ከዚህ ግብ ጋር የሚጣጣም ነው።

🟠ፑቲን በዛሬው ዕለት ዓለም አቀፍ የስልክ ውይይት ያደርጋሉ።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍43
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
❗️❗️❗️ ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በግብርና ቴክኖሎጂ ላይ ያላቸውን ትብብር አጠናክረው ይቀጥላሉ - የግብርና ሚኒስቴር

አገራቱ በቅርቡ የተፈራረሙት የኒውክሌር ልማት ፕሮጀክት ስምምነት፣ ለኢትዮጵያ ግብር ዕድገት ዘርፈ ብዙ አስተዋጽኦ አንዳለው የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ኢፋ ሙለታ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

🗣"የአፈር ለምነት ማረጋገጥ እና የምግብ ጥበቃ ሥርዓትን ማሳደግ ከስምምነቱ ትሩፋቶች ውስጥ ይጠቀሳሉ። የግብር ዘርፋችንን ውጤታማነት ለማሳደግ የሩሲያን የተለያዩ ቴክኖሎጂ ስንጠቀም ቆይተናል።" ብለዋል።


ሚኒስትር ዴኤታው የኢትዮጵያ ብዝኃ ሕይወት ኢንስቲትዩት፣ የአዲስ አበባ አና የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲዎች አንዲሁም ሌሎች ተቋማት፣ ላለፉት 15 ዓመታት የሩሲያን የባዮቴክኖሎጂ ስልተ ምርት ሲጠቀሙ መቆየታቸውንም አንስተዋል።

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👏54😁2
🇪🇹 በ2018 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት 24 ሚሊዮን የሚጠጉ ዜጎችን ከወባ መከላከል መቻሉ ተዘገበ

የአገር ውስጥ ሚዲያ ጤና ሚኒስቴርን ጥቅሶ እንደዘገበው ባለፉት ሦስት ወራት ከ9 ሚሊዮን በላይ የመኝታ አጎበር ለማኅበረሰቡ ተሠራጭቷል፡፡ በ105 ወረዳዎች የፀረ-ወባ ኬሚካል የቤት ለቤት ርጭት መደረጉንም ዘገባው አክሏል።

በሩብ ዓመቱ ከአምና ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር  የወባ ስርጭቱ በ42.1 በመቶ የቀነሰ ሲሆን፤ ከሳምንት እስከ ሳምንት ያለው ልዩነት ከ5 እስከ 10 በመቶ ቅናሽ ማሳየቱ ነው የተገለፀው።

በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለጸገ ምስል

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
2😁2👍1
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
የስፑትኒክ ሚዲያ እናት ድርጅት ሮሲያ ሴጎድኒያ ከቁልፍ የአፍሪካ ሚዲያዎች ጋር ያለውን ትብብር አጠናከረ የሩሲያው የሚዲያ ቡድን ሞስኮ ውስጥ በተካሄደው 'የጋራ ጥረት ፎረም' ላይ ከደቡብ አፍሪካው ኢንዲፔንደንት ሚዲያ 🇿🇦 እና ከኒጀሩ ኤኤንፒ የዜና ወኪል 🇳🇪 ጋር የትብብር ስምምነቶችን ተፈራረመ። የሮሲያ ሴጎድኒያ ዓለም አቀፍ ትብብር ዳይሬክተር ቫሲሊ ፑሽኮቭ ስምምነቶቹን ከፈረሙ በኋላ እንደተናገሩት፣…
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የሩሲያ ሚዲያ አፍሪካ ውስጥ መገኘቱ የምዕራባውያንን የሚዲያ የበላይነት ለመቋቋም ወሳኝ ነው - የኮንጎ ጋዜጠኛ

"ሁሉም ምዕራባውያን ሚዲያዎች በሐሰት መረጃ እየመረዙን ነው። ... በየደቂቃው ግልፅ የሆነ ፕሮፓጋንዳቸውን ይግቱናል " ሲሉ ጋይ ሲምፎሪየን ኦኩላቡካ ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ በቁጭት ተናግረዋል።


እየጨመረ በመጣው የሩሲያ ጥላቻ  መካከል፣ የአገሪቱን የመረጃ ሚዛን ለመጠበቅ እና የተወሰኑ ትርክቶችን ለመቋቋም አፍሪካ ውስጥ የተለያዩ የብሮድካስት ማዕከላትን መክፈት አለባት ሲሉ ሞስኮ ውስጥ በተካሄደው 'የጋራ ጥረት መድረክ'  ጎን ለጎን ተናግረዋል።

ጋዜጠኛው አክለውም ብዛት ያላቸው የኮንጎ ወጣቶች የአገራቸውን ዕድገት በትምህርት እንዲያግዙ ሩሲያ የዩኒቨርሲቲ መቀበያ ኮታዎቿን እንድትጨምር አሳስበዋል። በትንሹ 85 በመቶ የሚሆነው የኮንጎ ልሂቅ በቀድሞዋ የሶቪዬት ሕብረት ወይም በሩሲያ የሰለጠነ መሆኑንም ተናግረዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
6👏3
የደቡብ ለደቡብ ትብብር ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ አገራት መካከል የእውቀት ልውውጥን ያመቻቻል - የፋኦ ምክትል ዋና ዳይሬክተር

🇷🇺🌍 ሩሲያ የአፍሪካ አገራት የቴክኖሎጂ አቅምን በጋራ መፍጠር እንዲችሉ፣ እውቀትን፣ ሳይንስን እና የፈጠራ ሥራዎችን እንዲሠሩ እየረዳቻቸው ነው ሲሉ የተመድ የምግብና እርሻ ድርጅት (ፋኦ) ረዳት ዋና ዳይሬክተር እና የአፍሪካ ቀጣናዊ ተወካይ አበበ ኃይለ ገብርኤል በዓለም አቀፉ የሳይንስ ይፋዊ ኤግዚቢሽን ጎን ለጎን ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

አሁንም ራሷን ለመመገብ እየታገለች ያለችው አፍሪካ ግብርናዋን ማዘመን እንደሚገባት አጽናኦት ሰጥተዋል፡፡

"መፍትሄው የግብርና ምርታማነትን መጨመር ነው ... ይህም ማለት በአነስተኛ ግብዓት ብዙ ምርት ማግኘት። ይህንን ደግሞ ሳይንስን፣ ቴክኖሎጂንና ፈጠራን ተግባራዊ ሳናደርግ ማግኘት አንችልም"


አበበ ኢትዮጵያን ጨምሮ በሌሎች የአፍሪካ አገራት ያለው የወጣት ኃይል ወደ ሥራ ማስገባት መቻል አለብን ሲሉ አክለዋል።

" ... ግብርናውን ዘመናዊ ካደረግነው፤ ዘመናዊ ማድረግም አለብን፤ ወጣቱ በጉጉት ዘሎ በመግባት ተጠቃሚ ይሆናል" ብለዋል፡፡


🇪🇹 ኢትዮጵያ በስንዴ ምርት እጅግ ከፍተኛ አፈፃፀም ማሳየቷን አስመልክቶም፣ የስንዴ ምርት ኢትዮጵያን ከአገር ወስጥ ፍላጎት በተጨማሪ ከሰፊው የአፍሪካ የውጭ ንግድም ተጠቃሚ እንድትሆን ያስችላታል ብለዋል።

በሰው ሠራሽ አስተሎት የበለጸገ ምስል

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
👍43👏1
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
❗️❗️❗️ የሰው ሠራሽ አስተውሎት ልማትን የመደገፍ አቅም በአግባቡ መጠቀም ይገባል - ባለሙያ ኬንያዊት የፈጠራ ባለሙያ ሊኔት ካሞቶ፣ ሰው ሠራሽ አስተውሎት እና ሮቦቲክስ የአፍሪካን ዕድገት እና የሕዝቦቿን ተጠቃሚነት ለማሳደግ የላቀ እገዛ እንዳላቸው ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጻለች። 🗣 "ለምሳሌ በእነዚህ ቴክኖሎጂዎች ለአርሶ አደሮች የአፈር እርጥበት እና ሌሎች መረጃዎችን ማድረስ ትችላለህ። ከልክ ያለፈ…
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
❗️❗️❗️ የሰው ሠራሽ አስተውሎት የመረጃ ግብዓቶች አፍሪካን በአግባቡ ማሳየት አለባቸው - የዝምባቡዌ የፈጠራ ባለሙያ

ታቴንዳ ሙሶድዛ፣ ችግር ፈቺ የሰው ሠራሽ አስተውሎት ሥርዓቶችን ለማስፋት፣ የቴክኖሎጂው የመረጃ አቅርቦት የገጠሩን ማኅበረሰብ እውነታ የዘነጋ አለመሆኑን ማረጋገጥ እንደሚገባ ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልፀዋል፡፡

🗣"የመረጃ ስብስቦቹ ቴክኖሎጂ እምብዛም ባልተስፋፋባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ ወገኖችን የሚወክሉ መሆን አለባቸው። ይህም ሁሉንም አስፈላጊ መረጃዎች በመጠቀም ችግሮቻቸውን ለመፍታት ያግዛል።" ብለዋል።


የፈጠራ ባለሙያው የሚሰበሰቡ መረጃዎች ወደ አውሮፓ የሚላኩ ተጨማሪ ጥሬ ዕቃዎች እንዳይሆኑ ስልቶቸን መንደፍ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
5👍3👏1
🇺🇳🇪🇹 የተባበሩት መንግሥታት ባለሥልጣናት ኢትዮጵያ መሥራች ለሆነችበት ለዓለም ሰላምና ልማት ያላትን ቁርጠኝነት አወድሰዋል

“አገሪቱ የተመድ ዋና ዋናዎቹን የሰላም፣ የደህንነትና የሰብዓዊ ክብር ዓላማዎች ማስጠበቋን ቀጥላለች” ሲሉ የተመድ "ዩኤንኤድስ" የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ክሪታያዋን ቦንቶ የተመድ 80ኛ ዓመት ክብረ በዓልን አስመልክቶ ተናግረዋል።


🌍 አክለውም "ኢትዮጵያ ወደ ብዙ ተልዕኮዎች ወታደሮቿን በመላክ የተመድ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ቀደምት ተሳታፊዎች መካከል ነበረች፤ ዛሬም በንቃት በመሳተፍ ላይ ትገኛለች"" ማለታቸውን የአገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
7👏3👍2👎1
የጆሃንስበርግ ፖሊስ ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር መረብን በጣጥሶ 58 ኢትዮጵያውያን ታደገ

በጆሃንስበርግ በተካሄደ ከፍተኛ ዘመቻ፣ በሊምፖፖ እና በጋውቴንግ ክልሎች መካከል ኢትዮጵያውያን ዜጎችን ሲያዘዋውር የነበረ ሕገ-ወጥ የወንጀለኛ ቡድን መረብ መበጣጠሱን የጆሃንስበርግ ከተማ የሕዝብ ደህንነት የከንቲባ ምክር ቤት አባል ምግሲኒ ትሽዋኩ አሳውቀዋል።

በትክክለኛ መረጃ በመመራት፣ ከተለያዩ ተቋማት የተውጣጣ ቡድን በምሥራቅ ታውን በሚገኝ የተጠረጠረ መጋዘን ላይ ባካሄደው ድንገተኛ ፍተሻ፣ በተጨናነቀና ኢ-ሰብአዊ በሆነ ሁኔታ ታጭቀው ተይዘው የነበሩ 58 ተጎጂዎችን ታድጓል።

⛓️  በድንገተኛ ፍተሻው ወቅት ሦስት የውጭ አገር ዜጎች በቁጥጥር ስር ውለዋል። ይህ ቡድን ተጎጂዎችን ከደቡብ አፍሪካ ማክዶ ግዛት ዚምባብዌ ድንበር አቅራቢያ ወደ ሚገኘው ሊምፖፖ ግዛት በማጓጓዝ በከተማው ውስጥ ወደ ተደበቁ ስፍራዎች ያዘዋውር እንደነበር ይታመናል። ይህ እርምጃ በቡድኑ ላይ ትልቅ ጉዳት ማድረሱን ያመለክታል።

🔫 የፓሊስ መኮንኖች በርካታ ሞባይል ስልኮችን፣ የጥገኝነት መጠየቂያ ሰነዶችን፣ ለወንጀለኛ ቡድኑ አገልግሎት ስትሰጥ የነበረች ሱዙኪ ሰሌሪዮ መኪና እና የውሸት  ሽጉጥ ጨምሮ ቁልፍ ማስረጃዎችን ማግኘት ችለዋል።

🔍 መርማሪዎች አሁንም በኔትወርኩ ውስጥ ያሉ ተጨማሪ ተጠርጣሪዎችን እየተከታተሉ በመሆኑ፣ ተጨማሪ እስራት ሊከተል እንደሚችል ገልጸዋል። 58ቱ ሰዎች ደህንነታቸው  ወደሚጠበቅበት ስፍራ የደረሱ ሲሆን፣ የወንጀል ማጓጓዣ መስመርም ከመነሻው ተቆርጧል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
18👏5
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#viral  | በጋዛ ሰርጥ የሚገኙ ሕጻናት ወደ ትምህርት ቤት ተመለሱ

በከፊል በወደመው የመማሪያ ክፍላቸው ውስጥ ወንበርና ጠረጴዛ ስለሌለ መሬት ላይ ተቀምጠው ለመማር ተገድደዋል።

ምስል ከማኅበራዊ የትስስር ገፆች

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
11👍9🥰3👏1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
❗️❗️❗️ አፍሪካ የግብርና አቅሟን ገና መጠቀም አልጀመረችም - የኡጋንዳ የእንስሳት ጤና ኮሚሽነር

🌍 ዶ/ር አና-ሮዝ ኦኩሩት፣ አኅጉሪቱ ዘመናዊ ስልተ ምርትን በመጠቀም ያላትን እምቅ የግብርና ኃብት ወደ ልማት መቀየር እንዳለባት ለስፑኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

🗣"በመስኖ መልማት የሚችል ሰፊ መሬት አለን። ይህን በአግባቡ ወደ ምርት ማስገባት እና የእንስሳት እርባታ ሥርዓታችንን ማዘመን ይኖርብናል።" ብለዋል፡፡


የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን የግብርና፣ የገጠር ልማት፣ የውኃ እና የአካባቢ ልዩ የቴክኒክ ኮሚቴ ስብሰባ ባሳለፍነው ሳምንት በአዲስ አበባ መካሄዱ ይታወሳል፡፡

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
6👍2😁1
2025/10/28 03:34:45
Back to Top
HTML Embed Code: