Telegram Web Link
🇨🇲 ካሜሮናውያን ፕሬዝዳንታቸውን ለመምረጥ ወደ ምርጫ ጣቢያ እየተመሙ ነው

🟠 ከ8 ሚሊዮን በላይ መራጮች ድምጻቸውን ለመስጠት ብቁ ናቸው፡፡

🟠 በዛሬው ዕለት ለሚካሄደው የአንድ ዙር ምርጫ በጠቅላላው 31 ሺህ 653 የምርጫ ጣቢያዎች ተከፍተዋል።

🟠 ተመራጩ ፕሬዝዳንት ለሰባት ዓመት የሥልጣን ዘመን ያገለግላሉ።

🟠 ለ43 ዓመታት በሥልጣን ላይ የቆዩት የአሁኑ ፕሬዝዳንት ፖል ቢያ፤ ለምርጫ ከቀረቡት 12 እጩዎች መካከል አንዱ ናቸው።

🟠 ፕሬዝዳንቱ ከዋናዎቹ የተቃዋሚ እጩዎች ኢሳ ቺሮማ ባካሪ እና ቤሎ ቡባ ማይጋሪ ጋር ይፎካከራሉ።

🟠 ሕገ-መንግሥታዊ ምክር-ቤት የምርጫውን የመጨረሻ ውጤት እስከ ጥቅምት 16 ድረስ የማወጅ ግዴታ አለበት።

🗳 የሀገሪቱ ምርጫ የበላይ አካል 'ኤሌካም'፤ ሕገ-መንግሥታዊ መመዘኛዎችን የሚያሟላ፣ ግልጽና ሁሉን አቀፍ የምርጫ ሂደት ለማረጋገጥ ሁሉም አስፈላጊ እርምጃዎች መወሰዳቸውን አጽንዖት ሰጥቷል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
4👍1👎1
🇪🇹 የመፅሀፍ ቅዱስ የኤደን ገነት ባህር ዳር ናት የሚል ዓለም አቀፍ ጥናት ይፋ ተደረገ

📄 አሜሪካዊው ምሁር መሐሙድ ጀዋይድ መጽሐፍ ቅዱስን እና ቅዱስ ቁርዓንን ጨምሮ በርካታ መዛግብትን በማመሳከር ያካሄዱት ሳይንሳዊ ጥናት ትክክለኛው የገነት መገኛ ባህር ዳር መሆኗን አረጋግጧል ብለዋል፡፡

👉 ይህም በመፅሐፍ ቅዱስ ላይ የተጠቀሱት ግዮን፣ ኤፍራጥስ፣ ጤግሮስና ፒሶን ታላላቅ ወንዞች በዘመናዊቷ ኢራቅ ውስጥ ስለሚጓዙ ኤደን በዚያ አካባቢ መሆን አለበት ከሚለው እምነት ጋር የተቃረነ ነው፡፡

በአቻ-ያልተገመገመው ጥናት የብሉ ናይል ወንዝ የመጽሐፍ ቅዱሱ ግዮን አቻ ሊሆን እንደሚችል እና የጣና ሀይቅ ፈሳሾች ወደ ብዙ የውሃ መስመሮች ተከፍለው በዘፍጥረት የተገለጹትን አራቱን ወንዞች ሊፈጥሩ እንደሚችሉ ጠቁሟል።

"ሁሉም ፍንጮች ወደ ባሕር ዳር፣ ወደ ጣና ሐይቅ አቅራቢያ ይጠቁማሉ፡፡ አስደናቂ ውበት፣ አያሌ ዕፅዋት እና የብሉ ናይል ምንጭ፤ ይህም ከጥንቱ የኤደን ወንዞች ገለጻ ጋር የሚገጥም ነው” በማለት መሐሙድ ጀዋይድ ፅፈዋል።


❗️ጃዋይድ በመጽሐፍ ቅዱስ እና ቅዱስ ቁርዓን የሰፈሩት የአዳም (አደም) እና ሄዋን (ሀዋ) ዘፍጥረት በመተንተን አዳም (አደም) የተፈጠረበት ትክክለኛ ቦታ ከዓባይ (ግዮን) ወንዝ እና የጣና ሐይቅ ደቡባዊ ጫፍ አካባቢ መሆኑን የሚያሳዩ ማስረጃዎችን አቅርበዋል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
36😁31🤔4👍3🙉1
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
❗️ የማዳጋስካር ፕሬዝዳንት አንድሪ ራጆሊና በሀገሪቱ ውስጥ 'ሥልጣን በሕገ-ወጥ መንገድ ለመያዝ ሙከራ' እየተካሄደ እንደሆነ ገለፁ "የሪፐብሊኩ ፕሬዝዳንት ከሕገ-መንግስቱ እና ከዲሞክራሲያዊ መርሆዎች በተቃራኒ በሕገ-ወጥ መንገድ እና በኃይል ሥልጣን ለመያዝ የሚደረግ ሙከራ በአሁኑ ጊዜ በሀገሪቱ ውስጥ እየተካሄደ መሆኑን ለሕዝቡ እና ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ለማሳወቅ ይፈልጋሉ" ብለዋል በመግለጫቸው። …
🇲🇬 የማዳጋስካር ቀውስ፦ እስካሁን የታወቁ ጉዳዮች

▪️ፖሊሶች ዛሬ ከተቃዋሚ ሰልፈኞች ጎን መቆማቸው ተዘግቧል። የአካባቢው መገናኛ ብዙኃን እንደዘገበው ፖሊሶች “እኛ እዚህ ያለነው ለመጠበቅ እንጂ ለማሸበር አይደለም” የሚል መግለጫ አውጥተው የጦር ሠራዊቱ ኃይል እንዳይጠቀም አሳስበዋል።

▪️አንድ የጦር ሠራዊቱ ክንፍ ትናንት ሰልፈኞቹን መቀላቀሉ ተሰምቷል። በማዳጋስካር ዋና ከተማ አቅራቢያ የሚገኘው የአስተዳደር እና ቴክኒካል ሠራተኞችና አገልግሎት የጦር ኃይል አባላት (ካፕሳት)፤ ወታደሮች “በተቃዋሚዎች ላይ ተኩስ የመክፈት ትዕዛዝ እንዳይቀበሉ” ጥሪ አቅርበዋል።

▪️የማዳጋስካር ጦር ኃይል ባለፈው እሁድ ባወጣው መግለጫ፤ የመሬት፣ የአየር እና የባሕር ኃይሎችን ያካተተው የጦር ኃይሎች አመራር ቅንጅት ከአሁን በኋላ የሚመራው በካፕሳት የትዕዛዝ ማዕከል መሆኑን አስታውቋል።

▪️በዚያው ምሽት የካፕሳት ወታደሮች ወደ ዋና ከተማው በመግባት ከፕሬዝዳንቱ ታማኝ የደህንነት ኃይሎች ጋር ለአጭር ጊዜ የተኩስ ልውውጥ ካደረጉ በኋላ መሀል አንታናናሪቮን በመቆጣጠር ሰልፈኞቹን ተቀላቅለዋል።

▪️ፕሬዝዳንቱ ድርጊቱን “ሥልጣንን በኃይል ለመንጠቅ የተደረገ ሕገ-ወጥ ሙከራ” ሲሉ አውግዘው፤ ሁሉም ብሔራዊ ባለድርሻ አካላት “ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓትን እና ብሔራዊ ሉዓላዊነትን ለመከላከል” እንዲተባበሩ ጥሪ አቅርበዋል።

▪️የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ኤር ኦስትራልን እና ኤር ፍራንስን ጨምሮ በርካታ አየር መንገዶች ከቅዳሜ እስከ ሰኞ ወደ ማዳጋስካር የሚደረጉ በረራዎች ወደፊት መተላለፋቸውን ወይም መሰረዛቸውን አስታውቀዋል።

▪️አንታናናሪቮ ተቃውሞዎች ከተጀመሩበት ከመስከረም ወር አጋማሽ ወዲህ ትልቁን ሰልፍ አስተናግዳለች። በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ግንቦት 13 ተብሎ በሚጠራው አደባባይ እንደተሰበሰቡ ተዘግቧል። የእንቅስቃሴው ዋና አካል ፕሬዝዳንት አንድሪ ራጆሊናን እና የሴኔት ፕሬዝዳንቱ ሥልጣን እንዲለቁ የሚጠይቀው የ "ጀን ዚ" ስብስብ ነው።

▪️በርካታ መገናኛ ብዙኃን አንድሪ ራጆሊና ሀገሪቱን ለቀው እንደወጡ ቢዘግቡም፤ የፕሬዝዳንቱ ፅሕፈት ቤት “ፕሬዝዳንቱ አሁንም በሀገሪቱ ክልል ውስጥ ይገኛሉ” ሲል ትናንት አስተባብሏል።

ከማኅበራዊ የትስስር ገፆች የተገኙ ምሥሎች

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
13
ሜጀር ጄኔራል ዴሞስቴን ፒኩላስ በካፕሳት የማዳጋስካር ጦር ኃይሎች መሪ ሆነው ተሾሙ

“ሁሉም የሚሰጠውን ኃላፊነት ይወጣ” ሲሉ መናገራቸውን የአካባቢው መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

❗️የተልዕኮ ክፍፍል ቀጣይ የሚጠበቅ ጉዳይ እንደሆነም ዘገባዎቹ ጨምረው አመላክተዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
4👍1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#viral | በሞስኮ መካነ አራዊት የምትገኘውን ብርቅዬ የምዕራብ አፍሪካ የዳያና ጦጣ ግልገል ይተዋወቁ

🙈 በመካነ አራዊቱ ተወልዳ አንድ ወር ያለፋት ግልገሏ መጀመሪያ ከእናቷ ጉያ አትወጣም ነበር። አሁን በማወቅ ጉጉትና ንቁ እንቅስቃሴ - በግቢው ውስጥ እየተንጠላጠለች፣ ከትልቅ እህቷ ጋር እየተጫወተች እንዲሁም ከሰላጣ እስከ እርጎ ያሉ የአዋቂ ምግቦችን በደስታ እየቀመሰች የጎብኚዎችን ልብ እያሸነፈች ነው ሲል መካነ አራዊቱ አስታውቋል።

በቀይ መዝገብ (ከምድረ ገፅ ሊጠፉ የተቃረቡ ብርቅዬ እንሰሳት) ውስጥ የተካተትው የዳያና ጦጣ ዝርያ መጠሪያ ከሮማን የውበት እና አደን ጣኦት የመጣ ነው፡፡ የጦጣዎቹ መገኛ የምዕራብ አፍሪካ ጫካዎች ናቸው።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
👍43
🇪🇹🇮🇳 ኢትዮጵያና ህንድ በድንበር ተሻጋሪ የጤና ክብካቤ ትብብር ለማጠናከር እንደሚፈልጉ ገለፁ

በኢትዮጵያ የህንድ ኤምባሲ “በእሴታዊ የህክምና ጉዞ የግንኙነት ድልድይ መፍጠር" በሚል መሪ ቃል የጤና ክብካቤ ጉባኤ አዘጋጅቷል።

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሑሪያ አሊ ህንድ የላቀ ህክምና ለሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን ተመራጭ እንደሆነች በዚህ ወቅት ተናግረዋል።

ህንድ በህክምናው ዘርፍ ያካበተችውን እውቀት ከኢትዮጵያ ራዕይ ጋር በማጣመር ጠንካራ፣ ተደራሽ እና ሕዝብ ተኮር የጤና ክብካቤ ሥርዓቶችን መፍጠር ይቻላልም ብለዋል።

የህንድ አምባሳደር አኒል ኩማር ራይ በበኩላቸው በህንድ አቅራቢዎችና በኢትዮጵያ ባለድርሻ አካላት መካከል ትብብር ለማስፋት ጥረት እየተደረገ እንደሆነ ገልፀዋል።

ህንድ በኢትዮጵያ የመድኃኒት ማምረት አቅምን በማጠናከር ተመጣጣኝ እና ጥራት ያለው ህክምና ለማረጋገጥ እየተባበረች እንደሆነም አስታውቀዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
7🙏7👎1
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
ሜጀር ጄኔራል ዴሞስቴን ፒኩላስ በካፕሳት የማዳጋስካር ጦር ኃይሎች መሪ ሆነው ተሾሙ “ሁሉም የሚሰጠውን ኃላፊነት ይወጣ” ሲሉ መናገራቸውን የአካባቢው መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። ❗️የተልዕኮ ክፍፍል ቀጣይ የሚጠበቅ ጉዳይ እንደሆነም ዘገባዎቹ ጨምረው አመላክተዋል። በእንግሊዘኛ ያንብቡ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
የአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበር ለማዳጋስካር ቀውስ ሰላማዊና በስምምነት ላይ የተመሰረተ መፍትሄ ቅድሚያ እንዲሰጠው አሳሰቡ

🇲🇬 ማህሙድ አሊ ዩሱፍ መንግሥት ለውይይት ቁርጠኛ መሆኑን በደስታ ተቀብለው ሁሉም የማዳጋስካር ባለድርሻዎች፤ ሲቪል እና ወታደራዊ አካላት፤ እርጋታና መታቀብን ተግባራዊ  እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

ሁሉም ወገኖች “ኃላፊነትና ሀገር ወዳድነትን በማሳየት የሀገሪቱን አንድነት፣ መረጋጋትና ሰላም ለመጠበቅ እንዲሠሩ” አሳስበዋል።


በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
4👍1
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
🇸🇨 ከአፍሪካ በነፍስ ወከፍ እጅግ ሀብታም ስለሆነችው ሲሼልስ አጠቃላይ ምርጫ ማወቅ ያለብዎት ነገር 🗳 ከ77 ሺህ በላይ የሲሼልስ ዜጎች ከመስከረም 25 እስከ 27 በሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊና የሕግ አውጪ ምርጫ ድምጽ እየሰጡ ነው። በርቀት ባሉ ደሴቶች የሚኖሩ ነዋሪዎችና አስፈላጊ ሠራተኞች ሐሙስ ዕለት ድምጽ መስጠት የጀመሩ ሲሆን ዋናው ድምጽ አሰጣጥ ቅዳሜ በሶስቱ ትላልቅ ደሴቶች ላይ ይካሄዳል። 8️⃣
🇸🇨 በሲሼልስ ምርጫ በሥልጣን ላይ የሚገኙት ፕሬዝዳንት በተቃዋሚ መሪው ተሸነፉ

የሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን የቀድሞ የፓርላማ አፈ-ጉባኤ እና የሕክምና ዶክተር ፓትሪክ ሄርሚኒ ከማጣሪያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫው 52.7 መቶ ድምፅ በማግኘት ፕሬዝዳንት ዋቨል ራምካላዋን ድል እንዳደረጉ አስታውቋል።

ሄርሚኒ በድል ንግግራቸው “ይህንን ሥልጣን በአመስጋኝነት፣ በታላቅ የኃላፊነት ስሜት እና በሲሼልስ ሕዝብ ጥንካሬና ፅናት የማያወላውል እምነት እቀበላለሁ” ብለዋል።


የሄርሚኒ ፓርቲ ዩናይትድ ሲሼልስ፤ ራምካላዋን እ.ኤ.አ በ2020 ከማሸነፋቸው በፊት ከ40 ዓመታት በላይ ሀገሪቱን የመራ ሲሆን አሁን በፓርላማ አብላጫ መቀመጫ መልሶ በማግኘት ወደ ሥልጣን ተመልሷል።

ዩናይትድ ሰይሼልስ በምርጫ ማኒፌስቶው ላይ የሚከተሉትን አቅዷል፦

🟠 የማህበራዊ ድጋፍ እርምጃዎችን እንደገና ማስጀመር፣
🟠 ሥራ አጥነትን መቀነስ እና
🟠 የጡረታ ማህበራዊ ዋስትና ጥቅማጥቅሞችን መጨመር ናቸው።

🇮🇳 የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ለሄርሚኒ ድል የእንኳን ደስ አለሆት መልዕክት አስተላልፈዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
3👍3
እስራኤል በጋዛ ዳግም ወታደራዊ ዘመቻዋን ካበረታች ሀገሪቱ ላይ የሚፈፅሙትን ጥቃት እንደሚያጠናክሩ ሁቲዎች አስታወቁ

"ወታደራዊ ዘመቻችንን የምናቆመው ጠላት እስራኤል የጋዛ ተኩስ አቁም ስምምነትን ስታከብር ነው፤ ሆኖም ትግበራውን መከታተላችንን እንቀጥላለን" ሲሉ የሁቲ የፖለቲካ ቢሮ አባል ሔዛም አል-ዐሳድ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።


❗️የጋዛ ሰርጥ ውጊያ ዓርብ ከሰዓት ቆሟል። ቀደም ብሎ የፍልስጤም ንቅናቄ ሐማስ እና እስራኤል ግጭቱን ለመቋጨት የተዘጋጀውን የመጀመሪያ ደረጃ ዕቅድ ለመተግበር ተስማምተው ነበር።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
😁23🥰106👎1🔥1
🇪🇹 በአዲስ አበባ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ፋብሪካ ለመገንባት ከአውሮፓ ኩባንያ ጋር ስምምነት ተደረሠ

የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ በረኦ ሐሰን መሠረቱን አውሮፓ ካደረገው ባትስዋፕ አውቶሞቲቭ ኃላፊዎች ጋር በጉዳዩ ዙሪያ ተወያይተዋል።

ትብብሩ አዲስ አበባ ውስጥ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ማምረቻ ፋብሪካ መትከል፣ የባትሪ ማምረቻ እና ጥናትና ምርምር እንዲሁም የአረንጓዴ ትራንስፖርት ዘርፍ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ማቋቋምን ያካትታል።

በ2026 በሚጀምረው የስምምነቱ የመጀመሪያ ምዕራፍ 240 የሙከራ የኤሌክትሪክ ጭነት ተሽከርካሪዎች ሲገነቡ፤ 10 አውቶማቲክ የባትሪ መለዋወጫ ጣቢያዎች በአዲስ አበባ ይዘረጋሉ።

ስምምነቱ ኢትዮጵያ በአፍሪካ የአረንጓዴ እንቅስቃሴ ዘርፍ ቁልፍ ተዋናይ ከመሆን ራዕይዋ ጋር የተጣጣመ ነው ተብሏል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
👏22😁87🔥4👍1
🇸🇩 ፈጥኖ ደራሽ ኃይል በአል-ፋሸር መጠለያ ላይ በፈፀመው የድሮን ጥቃት 57 ሰላማዊ ሰዎች ተገደሉ - የሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

❗️የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት የፈጥኖ ደራሽ ኃይል የአል-ፋሸር ከበባውን በአፋጣኝ እንዲያቆም እና በከተማዋ ላይ የሚሰነዝራቸውን ጥቃቶች በሙሉ እንዲያቆም የሚጠይቀውን ውሳኔ እንዲያስከብር ውጭ ጉዳዩ አሳስቧል።

🔊  ሁሉም ዓለም አቀፍ እና ቀጣናዊ ተዋናዮች ለአማፂው የሚቀርበውን ጦር መሳሪያና ቅጥረኞች በአስቸኳይ እንዲያስቆሙ፣ የመንግሥትን የሰላማዊ ዜጎችን መከራ የማቃለል ጥረት እንዲደግፉ እንዲሁም የአርኤስኤፍ አመራሮችን ለድርጊታቸው ተጠያቂ እንዲያደርጉ አሳስቧል።

አል-ፋሸር ከግንቦት 2016 ዓ.ም ጀምሮ  የሱዳን ጦር ኃይሎች እና አርኤስኤፍ ዋነኛ የጦር ፍልሚያ ሜዳ ሆና ቆይታለች።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
😱21😁1
በእስራኤል ጥቃቶች በከፍተኛ ሁኔታ የወደመችው ጋዛ

በጋዛ ከተማ ምዕራባዊ ክፍል አል-ናስር አውራጃ የሚገኘው አል-ረንቲሲ የሕጻናት ሆስፒታል ሙሉ በሙሉ ወድሟል የሚባልበት ደረጃ ላይ ይገኛል (ቪዲዮ 1)።

በማዕከላዊ ጋዛ ከተማ የሚገኘው አል-ጃላእ ጎዳና ሙሉ በሙሉ ወደ ፍርስራሽነት ተቀይሯል (ቪዲዮ 2)።

ከማኅበራዊ የትስስር ገፆች የተገኙ ተንቀሳቃሽ ምሥሎች

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
3💔3👏2😱2
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ሩሲያ ለዓለም አቀፍ ገበያ የምግብ ምርት ከሚያቀርቡት ውስጥ ዋነኛዋ ነች - ፑቲን

👨🏼‍🌾 የሩሲያ ፕሬዝዳንት የሩሲያ የግብርና ሠራተኞችን ቀን በማስመልከት በቪዲዮ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ሀገሪቱ የግብርና ዘርፉን ዕድገት መደገፏን፣ ተወዳዳሪነቱን እና የቴክኖሎጂ ነጻነቱን ማሳደጓን እንደምትቀጥል ገልጸዋል።

"የእኛ ከፍተኛ ጥራት ያላቸው ምርቶች፤ እህል፣ የአትክልት ዘይቶች፣ ዓሣ፣ ጣፋጭ ምግቦች እና ሌሎች ሸቀጦች በዓለም ዙሪያ ከ160 በላይ ሀገራት ዘንድ ይታወቃሉ፤ ተፈላጊዎችም ናቸው" ሲሉ ፑቲን ተናግረዋል።


🔸 የሩሲያ የግብርና ሚኒስቴር የግብርና ኤክስፖርት ልማት ማዕከል ባወጣው መረጃ መሠረት፤ ከጥር እስከ ነሐሴ 2017 ዓ.ም ሩሲያ ከ2.8 ቢሊዮን ዶላር በላይ ዋጋ ያላቸውን 11 ሚሊዮን ቶን የሚጠጉ የግብርና ምርቶች ለአፍሪካ ሀገራት ልካለች።

🔸 እህል እና የጥራጥሬ ሰብሎች የሩሲያ ዋነኛ የውጭ ንግድ ምርቶች ሲሆኑ ባለፈው ዓመት ብቻ ከ75 ሚሊዮን ቶን በላይ ምርት ለውጭ ገበያ ተልኳል። ሩሲያ በስንዴ፣ ገብስ እና በክዊት ከዓለም ቀዳሚ፤ በአተር እና በሽምብራ ምርት ደግሞ ከዓለም ሁለተኛ ትልቋ ላኪ ሀገር ናት።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
6🙏6👍2🥰1
2025/10/22 02:09:44
Back to Top
HTML Embed Code: