Telegram Web Link
በአክሱም ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተከሰተው የእሳት አደጋ በሚሊዮኖች የሚገመት ጉዳት አስከትሏል

መንስኤው ያልታወቀው አደጋ በሆስፒታሉ ዋና የመድኃኒት መጋዝን ውስጥ የነበሩ የሕክምና መሣርያዎችንና ግብዓቶችን ማውደሙን ዩኒቨርሲቲው አስታውቋል።

ከዩኒቨርሲቲው ይፋዊ የማኅበራዊ ሚዲያ ገጽ የተገኙ ምስሎች

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
👏3😢31🙏1
🇪🇹 🇸🇩 የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ፖርት ሱዳን ዳግም በረራ መጀመሩን አስታወቀ

🛫 አየር መንገዱ ከትናንት ጥቅምት 5 ቀን 2018 ጀምሮ በየቀኑ ወደ ፖርት ሱዳን (PZU) እንደሚበር ይፋ አድርጓል፡፡

ከጥቅምት 22 ቀን 2018 ጀምሮ ደግሞ ዕለታዊ በረራውን በእጥፍ እንደሚያሳድግ ገልጿል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
👍51
ፑቲን በሩሲያ እና ቶጎ መካከል የተደረገውን የወታደራዊ ትብብር ስምምነትን የሚያፀድቅ ሕግ ፈረሙ

ይህ አጋርነት፣ በመጋቢትና ሚያዝያ 2025 በሎሜ እና በኋላም በሞስኮ ፊርማዎች የታተመ ሲሆን፣ በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ወታደራዊ ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ ነው።

ስምምነቱ የሚከተሉትን ዘርፎች ያካትታል፦

🟠 የገንዘብ ድጋፍ ሂደቶች፣
🟠 የመረጃ ጥበቃ ሁኔታዎች እና እርምጃዎች፣
🟠 የሕክምና አገልግሎት አቅርቦት፣
🟠 የዳኝነት ሥልጣን እና
🟠 የሕጋዊ ጥበቃ።

ላልተወሰነ ጊዜ የሚቆየው ስምምነቱ፣ ሁለቱ አገራት የውስጥ አሰራራቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ተግባራዊ ይሆናል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍72
ፑቲን በዛሬው የሩሲያ የኢነርጂ ሳምንት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ይሳተፋሉ

🌐 ከ60 በላይ የንግድ ዝግጅቶችን ያካተተው ዓለም አቀፉ ስብሰባ የመንግሥት ባለሥልጣናትን፣ የኢነርጂ ኩባንያ መሪዎችን፣ ባለሙያዎችን እና የሳይንስ ማኅበረሰብ ተወካዮችን ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች በሞስኮ አገናኝቷል።

👉 በስፑትኒክ ኢትዮጵያ ሁነቱን ይከታተሉ!

በእንግሊዝኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
4👍3
🚨የእንግሊዝ እና የዩክሬን የስለላ አገልግሎቶች የቱርክ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመርን ለማደናቀፍ እየተዘጋጁ ነው - የሩስያ ደህንነት አገልግሎት

“እንግሊዞች ከዩክሬን የስለላ ድርጅት ጋር በመሆን በቱርክ ጋዝ ማስተላለፊያ ቧንቧ ላይ ብልሽት ለመፍጠር እየተዘጋጁ እንደሆነ መረጃ አለን" ሲሉ የፌደራል ደህንነት አገልግሎቱ ዳይሬክተር አሌክሳንደር ቦርትኒኮቭ ተናግረዋል።


በተጨማሪም የእንግሊዝ ጦር ኤስኤኤስ እና ኤምአይ6 አዛዦች በካስፒያን የማስተላለፊያ ቧንቧ መስመር ጥምር ድርጅቶች ላይ ተከታታይ የድሮን ጥቃቶችን ለማድረግ ማቀዳቸው ተዘግቧል።

የጥምር ድርጅቱ ባለድርሻዎች ከሩሲያ፣ ከካዛኪስታን እና ከአሜሪካ የተወጣጡ ኩባንያዎች መሆናቸውን ቦርትኒኮቭ አክለዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
7👏2🤯1😈1
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
የኢትዮጵያን የኤሌክትሪክ ትራንስፖርት የማስፋት ቁርጠኝነት አብነት ማድረግ ይገባል - የአፍሪካ ኢ-ሞቢሊቲ ጥምረት 📌 ኢትዮጵያ ወደ ኤሌክትሪክ ትራንስፖርት ሥርዓት ለመሸጋገር መሠረተ ልማት ሥራ ላይ በትኩረት እየሠራች እንደምትገኝ የጥምረቱ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ዋረን ኦንዳንጄ ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል። "የኢትዮ ቴሌኮምን የሕዝብ የመኪና መሙያ ማዕከላት ተመልክቻለሁ። በሥፍራዎቹ ቻርጅ ለማድረግ የተሰለፉ…
🇪🇹 ኢትዮጵያ ከ50 - 120 ኪሜ ርቀት ላይ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች የባትሪ መሙያ ጣቢያዎችን እንደምትተክል አስታወቀች

🔌 በዋና ዋና አውራ ጎዳናዎች ላይ የሚተከሉት ጣቢያዎቹ በከተሞች መካከል የኤሌክትሪክ ጉዞን ለማሳለጥ ያለሙ መሆናቸውን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ገልጿል።

ሚኒስትሩ ዶ/ር ዓለሙ ሥሜ፣ መንግሥት በ2030 የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ቁጥር ግማሽ ሚሊዮን ለማድረስ ማቀዱን በመግለጽ፣ በዚህ ረገድ በመንግሥትና የግል አጋርነት የሚከናወነው የመሠረተ ልማት ዝርጋታ ጉልህ ሚና እንደሚኖረው አፅንኦት ሰጥተዋል።


🚘 በአሁኑ ወቅት በመላ አገሪቱ ያለው የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ቁጥር ከአንድ መቶ ሺህ መሻገሩን የአገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል፡፡

በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለጸገ ምስል

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
👍4😁42🤔1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
❗️❗️❗️ አፍሪካውያን ዓለምን በተለየ ሁኔታ እንዲመለከቱ ስፑትኒክ እገዛ ያደርጋል - የሱዳን ሚኒስትር

“በእርግጥም አፍሪካውያን ሁለተኛ፣ ሦስተኛ ዕይታ ሊኖራቸው ይገባል፡፡ አንድ ወገንን ብቻ ስታዳምጡ፣ ያ የተዛባ አመለካከት ይሆናል፤ ነገር ግን የተለያዩ የመረጃ ምንጮችን እና የአንድን ክስተት የተለያዩ ትንታኔዎችን ስታዳምጡ፣ ስለሚፈጠረው ነገር ሰፋ ያለ ግንዛቤ ይኖራችኋል” ሲሉ የሱዳን የገንዘብ ሚኒስትር ዶ/ር ጂብሪል ኢብራሂም መሐመድ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።


ስፑትኒክ በአኅጉሪቱ ዕይታዎችን በማስፋት ረገድ ላበረከተው አስተዋጽኦ አድናቆት እንዳለቸውም ገልፀዋል፡፡

“የስፑትኒክ ሥራ ግንዛቤያችንን እያበለጸገ፣ የአፍሪካ ህዝቦች የተለየ ዕይታ እንዲኖራቸው እየረዳ እንደሆነ እናምናለን።” ብለዋል፡፡


በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍65
🇪🇹🇷🇺 ኢትዮጵያ የሩሲያ-አፍሪካ ፎረምን የኢኮኖሚ ዕድሎችን ለማስተዋወቅ እያዋለችው መሆኑ ተገለፀ

ጥቅምት 5 እና 6 በሞስኮ እየተካሄደ ባለው ዓለም አቀፍ ፎረም እና ኤክስፖ ላይ አገሪቱ የኤክስፖርት ምርቶቿን፣ የኢንቨስትመንት ዕድሎቿን እና የቱሪዝም መስህቦቿን ተደራሽነት ለማስፋት እያስተዋወቀች መሆኑን በሩስያ የኢትዮጵያ ኢምባሲ አስታውቋል፡፡

ኤምባሲው፣ "በኤክስፖው ላይ ከዓለም አቀፍ የንግድ ተቋማት ጋር ለመገናኘት እና የአገሪቱን የኢኮኖሚ አቅም ለጉባኤው ተሳታፊዎችና ባለሀብቶች ለማስረዳት እየሠራ" መሆኑን ጠቁሟል።


በሩሲያ ፌዴሬሽን የንግድና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት የሚዘጋጀው ፎረም፣ በሎጂስቲክስና ባንኪንግ ላይ የሚደረገውን ዋነኛ የጋራ ስብሰባ ጨምሮ በርካታ የፓናል ውይይቶችን ያካትታል። ከተለያዩ ዘርፎች የተውጣጡ በርካታ የሩሲያ ኩባንያዎችም በመድረኩ ተገኝተዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
5👍5
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
❗️የማዳጋስካር መፈንቀለ መንግሥት መሪ ሚካኤል ራንድሪያኒሪና ራሳቸውን ገዜያዊ ፕሬዝዳንት አድርገው ሾሙ የሀገሪቱን ፕሬዝዳንት ከሥልጣን ለማውረድ የተደረገውን ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት የመሩት ኮሎኔል ሚካኤል ራንድሪያኒሪና፤ አንድሪ ራጆሊና ከሀገር መሸሻቸውን ተከትሎ በሕገ-መንግሥቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጥያቄ መሠረት የመንግሥትን ሥልጣን እንደሚረከቡ አስታውቀዋል። የተሰናባቹ ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት…
❗️የማዳጋስካር ወታደራዊ ኃይል ሲቪሎችን ያሳተፈ መንግሥት መምሥረቱን አስታወቀ

ሀገሪቱን በሽግግር ፕሬዝዳንትነት ለመመራት እጩ የሆኑት ሚካኤል ራንድሪያኒሪና ዓርብ ዕለት ቃለ መኃላ ከፈፀሙ በኋላ የጋራ አስተዳደር እንደሚመሰረት መገናኛ ብዙኃን የራንድሪያኒሪናን መግለጫ ጠቅሰው ዘግበዋል።

👉 በማዳጋስካር የተከሰተው የአስተዳደር ለውጥ በሕግ ማዕቀፍ ውስጥ የተፈጸመ እንጂ መፈንቅለ መንግሥት አልነበረም ሲሉም ወታደራዊ ኃላፊው ተናግረዋል። ኮሎኔሉ አክለውም ምንም ዓይነት ኃይል እንዳልተጠቀሙ እና ማንም ሰው የፕሬዚዳንቱን ቤተ መንግሥት እንዳልወረረ ጠቁመዋል።

በተጨማሪም ወታደራዊ እና ሲቪል ሠራተኞችን ያካተተ ብሔራዊ የሽግግር መከላከያ ምክር ቤት መቋቋሙን አስታውቀዋል።

📄 በቅድሚያ አጠቃላይ ምርጫ ለማካሄድ ዕቅድ እንደሌለ ራንድሪያኒሪና ተናግረዋል። ግልጽ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያለው የምርጫ ሂደት ለማረጋገጥ የምርጫ ኮሚሽኑን ማሻሻል እና የመራጮች ዝርዝርን ማዘመን አስፈላጊ መሆኑን አስታውቀዋል።

ራንድሪያኒሪና የአዲሱ መንግሥት ዋነኛ ግብ ለፕሬዚዳንት አንድሪ ራጆኤሊና ከሥልጣን መውረድ ምክንያት የሆኑትን የሕዝቡን ማኅበራዊ ጥያቄዎች መመለስ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።

🤝 ራንድሪያኒሪና አፍሪካ ኅብረት ማዳጋስካርን ከአባልነት ለማገድ የወሰነውን ውሳኔ በአሁናዊ ሁኔታ ውስጥ “መደበኛ ምላሽ” ነው በማለት ገልጸውታል። ከኅብረቱ ጋር ውይይቶች መጀመራቸውን የጠቆሙ ሲሆን ከደቡብ አፍሪካ ልማት ማኅበረሰብ የተወጣጣ ልዑክም ጥቅምት 10 ቀን ወደ ማዳጋስካር ለመምጣት ቀጠሮ ተይዞለታል ብለዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉
4👍2
2025/10/27 15:19:06
Back to Top
HTML Embed Code: