Telegram Web Link
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የሩሲያ ቶርናዶ-ኤስ ባለ ብዙ ሮኬት ማስወንጨፊያ በካርኮቭ ክልል የሚገኙ የጠላት ቦታዎች ላይ ከፍተኛ ጥቃት ፈፀመ

በሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር የቀረበ ተንቀሳቃሽ ምሥል

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
👍146👎1
🇸🇩 በሱዳን መዲና እና አውሮፕላን ማረፊያ ላይ ያነጣጠሩ የድሮን ጥቃቶች ለሶስተኛ ተከታታይ ቀን ተፈፀሙ

ድሮኖቹ በካርቱም ሰማይ ላይ በከባድ የፀረ-አውሮፕላን ተኩስና በከፍተኛ ፍንዳታዎች ታጅበው በዝቅተኛ ከፍታ ላይ ሲበሩ እንደነበር የአካባቢው ነዋሪዎች ለአረብ ሚዲያ ተናግረዋል።

ጥቃቶቹ መፈፀም የተጀመሩት የሀገር ውስጥ በረራዎች ዳግም እንደሚጀመሩ በተገለጸበት ዋዜማ፤ በአማፂው ፈጥኖ ደራሽ ኃይል እንደሆነ የሱዳን ምንጮች ገልፀዋል።

የካርቱም አውሮፕላን ማረፊያ ከሁለት ዓመት በላይ በጦርነቱ ምክንያት ሥራ ካቆመ በኋላ የመጀመሪያውን የሲቪል አውሮፕላን በትናንትናው ዕላት እንዳስተናገደ ከላይ የተያያዘው ተንቀሳቃሽ ምሥል ያሳያል። ይሁን እንጂ የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ መሪ ወደ ሱዳን የሚመጡ ማናቸውንም አውሮፕላኖች መትተው እንደሚጥሉ ዝተዋል።

ከማሕበራዊ ሚዲያ የተገኘ ምሥል

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
7👍5
በስፑትኒክ ቱርኪዬ ብራንድ የደመቁ የከተማ አውቶብሶች በኢስታንቡል ጎዳናዎች ጉዟቸውን ጀመሩ

🛰🛰🛰🛰 “ራዲዮዎን ይከፈቱ። ከእርስዎ የተደበቀውን ይስሙ” የሚል መሪ ቃል ያነገቡት ፈጣን አውቶቡሶች፤ ቦስፎረስ ስትሬት እና ጎልደን ሆርን በተባሉ ታዋቂ ሥፍራዎች ጨምሮ የአውሮፓ፣ የእስያ እና የኢስታንቡል ክፍሎችን በሚያገናኙ የትራንስፖርት መስመሮች በማለፍ አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል።

🚇 ወሳኝ የመጓጓዣ መንገድ የሆነው ሜትሮ ባስ — 52 ኪ.ሜ በመሸፈን በኢስታንቡል የሚገኙ ቁልፍ አካባቢዎችን ያገናኛል። በየቀኑ 1 ሚሊዮን በዓመት ደግሞ 375 ሚሊዮን የሚጠጉ መንገደኞች ሜትሮባሱን ይጠቀማሉ።

📌 ስፑትኒክ ዓለም አቀፍ የዜና ወኪል እና ሬዲዮ በሮሲያ ሰጎድኒያ የሚዲያ ቡድን ስር ከ30 በላይ ቋንቋዎች የሚሠራ ሲሆን በዓለም ዙሪያ ከ20 በላይ የመልቲሚዲያ ማዕከላት አሉት። የሬድዮ ስርጭቶቹ በ20 ሀገራት ውስጥ በ14 ቋንቋዎች ተደራሽ ይሆናሉ።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👏138👍2
ዚምባብዌ የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭና ማከፋፈልን ለግል ኩባንያዎች ክፍት አደረገች

በዚምባብዌ የኃይል ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን ይፋ የተደረገው እርምጃ አገልግሎትን ለማሻሻል እና በ2030 ሀገር አቀፍ ተደራሽነትን ለማሳካት ታስቦ የተዘጋጀ ነው።

👉 ውሳኔው ለሀገር ውስጥ የኤሌክትሪክ ኃይል ማሰራጪያ መሠረተ ልማት ኢንቨስትመንት ለመሳብ፣ ቅልጥፍናን ለማሻሻል እና አገልግሎት የሌላቸውን አካባቢዎች ተደራሽ ለማድረግ ያለመ መሆኑን የሀገሪቱ ባለሥልጣናት ገልፀዋል።

ኢንቨስትመንቱ የሚከተሉትን ማፋጠን አለበት፦

🟠 የመሠረተ ልማት ግንባታ፣
🟠 የመንግሥትን ወጪ መቀነስ፣
🟠 ታዳሽ ኃይልን ከብሔራዊ የኃይል ፍርግርግ ጋር ማዋሃድ።

በአዲሱ ሞዴል መሠረት የግል ኩባንያዎች በተለይም አገልግሎት የሌላቸውን እና አዳዲስ የመኖሪያ አካባቢዎችን ለመሸፈን፤ ከዚምባብዌ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያና ስርጭት ኩባንያ ጋር በመተባበር የኤሌክትሪክ ኃይልን ለማከፋፈልና ለመሸጥ ፈቃድ ሊያገኙ ይችላሉ።

ፈቃድ የተሰጣቸው ኢንቨስተሮች የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ስርዓቶችን በዚምባብዌ ደንቦች መሠረት ለማስተዳደር የሚያስችል የቴክኒክ እና የፋይናንስ አቅም ማሳየት ይጠበቅባቸዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
6👍5
❗️የሩሲያ ኃይሎች የዩክሬን መከላከያ ኢንዱስትሪ ተቋማትን የሚደግፉ የኃይል ማመንጫዎችን እንዳወደሙ የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ

የሩሲያ የጦር ኃይሎች በልዩ ወታደራዊ ዘመቻው ስር በዶንባስ ክልል እና ባሻገር ከቅርብ ወራት ወዲህ በፍጥነት በመገስገስ በተከታታይ የተለያዩ ሥፍራዎችን ነፃ እያወጡ ይገኛሉ።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
👍7👎1🫡1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሩሲያ በሰብዓዊ መብቶች ዘርፍ ከውጭ አጋራት ጋር ልምድ ለመለዋወጥ ዝግጁ ናት - ቭላድሚር ፑቲን

"ሀገራችን የዜጎችን የዲጂታል መብቶች ለመጠበቅ በተከታታይ የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰደች ነው" ሲሉ የሩሲያ ፕሬዝዳንት በጽሑፍ ባስተላለፉት መልዕክት ገልፀዋል።


የእምባ ጠባቂዎች ምርጥ ተሞክሮዎችን መለዋወጥ በሚል በሞስኮ እየተካሄደ በሚገኘው 9ኛው ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ጥበቃ ጉዳዮች ጉባኤ ለሚሳተፉት እንኳን ደህና መጣችሁ ብለዋል።

👉 ብሔራዊ እምባ ጠባቂዎች፣ የመንግሥት ተወካዮች፣ ባለሙያዎች እና የሕግ ምሁራንን ጨምሮ ከ60 በላይ ሀገራት የተውጣጡ ልዑካን በሩሲያ ዋና ከተማ መሰባሰባቸውን ፑቲን አስታውቀዋል።

🖥 በዲጂታል ሽግግር ዘመን የሰብዓዊ መብቶች ጥበቃ የጉባኤው አጀንዳ ነው። የመረጃና ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂዎች፤ በተለይም የሰው ሠራሽ አስተውህሎት ፈጣን እድገት አዳዲስ ምልከታዎችን ገቢር ከማድረግ ባለፈ በጣም ከባድ አደጋዎችም እንዳሉት ፑቲን አስጠንቅቀዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
11🥰1😁1
ኪን ኢትዮጵያ፡ ለዓለም የቀረበ የባህልና ጥበብ ትዕይንት
Sovereignty Sources
🇪🇹🤝 🌏 #SovereigntySources |ኪን ኢትዮጵያ፡ ለዓለም የቀረበ የባህልና ጥበብ ትዕይንት

ኪን-ኢትዮጵያ የጥበብና ባህል ጉዞ ኢትዮጵያን ለዓለም የማስተዋወቅ ዓላማ አድርጎ ብሪክስ አባል ሀገራት እያቀረበ ነው፣ በቻይና እና ሩሲያ ስራዉን ያቀረበው ቡድኑ፣ በቅርቡም ወደ ብራዚል ያቀናል ፡፡

''ኪን - ኢትዮጵያ ትልቅ የባህል፣ የጥበብ እና የዲፕሎማሲ፣ የብዙ የኪነጥብ  ባለሙያዎች ስብስብ ነው። ኅብረትን መሠረት ያደረገ ሥራ በመሥራታችን ውጤቱ እጅግ የሚደነቅ ነው [...] ብሪክስ የዓለምን ሚዛንን ለማስተካከል የተፈጠረ አቅም ስለሆነ አባል መሆናችን በብዙ ይጠቅመናል።'' ሲል የኪን ኢትዮጵያ ቡድን መሪ፣ አሰልጣኝና ድምፃዊ ወንድዬ አበበ (ወንድዬ ኮንታ) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግሯል ።


📻 ሶቨርኒቲ ሶርስስ በዛሬው መርሃ ግብሩ በክፍል አንድ ኪን ኢትዮጵያ ቡድን በዓለም አቀፍ ደረጃ እያደረገ ያለው ጉዞ በብሪክስ ማዕቀፍ ስር የባህል ዲፕሎማሲ እና ዓለም አቀፍ አጋርነትን ለመወያየት የኪን ኢትዮጵያ ቡድን መሪ፣ አሰልጣኝና ድምፃዊ ወንድዬ አበበ (ወንድዬ ኮንታ) በእንግድነት ጋብዘነዋል። በክፍል ሁለት ደግሞ ወደ ኢትዮጵያ የፊልም ስራዎች ጠልቀን ፣ ዘርፉ ለአንድነት እና ቀጠናዊ ትስስር ስላለው ሚና ከዳይሬክተር፣ ኤዲተርና ፕሮዲውሰር ክብሮም በርሄ  ጋር የተደረገው ቆይታ ያደርጋል።

🔊 ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን  ያዳምጡ:

⚡️ከቴሌግራም ሳይወጡ ፕሮግራሙን ያዳምጡ                                          

⚡️ በድረ ገጻችን

👉 ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple Podcasts AfripodsDeezerPocket CastsPodcast Addict Spotify

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
3👍2🍾1
የሀገራዊ ምክክር ጉባዔ በትግራይ ክልል ያሉ ቀሪ ጉዳዮች መፍትሄ ማግኘታቸው ላይ የተመረኮዘ ነው - የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

ይህ በእንዲህ እንዳለ ምክክሩ በሁለት ወራት ጊዜ ውስጥ ይጀመራል ተብሎ እንደሚጠበቅ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ አስታውቀዋል።

በተጨማሪም በትግራይ ክልል የማህበረሰብ ተወካዮችን የመምረጥ ሂደትን ጨምሮ ለአንዳንድ ላልተፈቱ ጉዳዮች መፍትሄ ለማበጀት በቅርቡ ወደ ትግራይ ለማቅናት ማቀዳቸውን ለሀገር ውስጥ ሚዲያ ገልፀዋል።

የዋና ኮሚሽነሩ ጉብኝት በክልሉ ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት ጄነራል ታደሰ ወረደ ተቀባይነት ማግኘቱንም አስረድተዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
8😁5
❗️ ሞስኮ የኔቶ ሀገራትን የኒውክሌር ልምምዶች ችላ እንደማትል እና ይህንንም በወታደራዊ እቅዷ ታሳቢ በማድረግ ላይ እንደምትገኝ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ተናገሩ

የማሪያ ዛካሮቫ ተጨማሪ መግለጫዎች፦

የኔቶ የኒውክሌር ልምምዶች አለመረጋጋትን የሚፈጥሩ እና ውጥረቶችን የሚያባብሱ እንዲሁም የሞስኮን ከፍተኛ ትኩረት የሚሹ ናቸው።

የሩሲያ እና የአሜሪካ ስብሰባ መሰረዝን አስመልክቶ ትራምፕ በሰጡት መግለጫ ዙሪያ ክሬምሊን አስተያየት ይሰጣል።

ሞስኮ የሩሲያ-ዩናይትድ ስቴትስ የውይይት መለኪያዎችን ግልፅ ለማድረግ ከአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ጋር ለመገናኘት ዝግጁ ናት፡፡

በሩሲያ ላይ የተጣለው አዲስ የአሜሪካ ማዕቀብ በጅ የማይል ነው፡፡

የአውሮፓ ህብረት በሩሲያ ላይ የጣለው ማዕቀብ ብዙ ግዜ ተሞክሮ ውጤት ያላመጣ እና የማይሠራ ነው፤ ሞስኮ በጥቅሞቿ ላይ በመመሥረት ምላሽ የመስጠት መብቷ የተጠበቀ ነው፡፡

የሩሲያ ንብረቶችን ለመውረስ በአውሮፓ ህብረት የሚደረጉ የትኛውም እርምጃዎች በሕግ ፊት ዋጋ ቢስ እና ከሞስኮ ጥብቅ ምላሽ የሚያስከትሉ ናቸው፡፡

በዩክሬን የሰላም ሂደት ዙሪያ ሩሲያ እና አሜሪካ የሚሠሩት ሥራ ከባድ እና አድካሚ ነው፤ ከማይክራፎን ጀርባ ሳይሆን በዲፕሎማሲ መከናወን አለበት።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍112😁1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#viral|🏍🗞 በቦሊውድ የታቀኘ ተሰጥኦ፦ ሞተር ሳይክሉን በፍጥነት እየነዳ ጋዜጦችን በቄንጥ የሚያደርሰው ህንዳዊ መልዕክተኛ

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
13😁4🔥3
❗️ሩሲያ ተጨማሪ 1 ሺህ የዩክሬን ወታደሮችን አስከሬን ለኪዬቭ አስረክባ፤ በምላሹ 31 የተዋደቁ ወታደሮቿን እንደተቀበለች የስፑትኒክ ምንጭ ገለጹ

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
🔥10🙏53👎1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🇷🇺 ቤተሰብ ለሩሲያ የወደፊት እጣ ፈንታ መሠረት ነው - ፑቲን

ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በሥነ-ሕዝብና በቤተሰብ ፖሊሲ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ የሩሲያን የሥነ-ሕዝብ አወቃቀር ስትራቴጂ ለማጠናከር ቀጣይ እርምጃዎችን በማስቀመጥ፤ የቤተሰብ ድጋፍ "በሁሉም ብሔራዊ ፕሮጀክቶች ቅድሚያ የሚሰጠው ቁልፍ ጉዳይ" እንደሆነ አፅንዖት ሰጥተዋል፡፡

ተጨማሪ ቁልፍ መግለጫዎች፦

🔶 ቤተሰቦችን መደገፍ ፍፁም ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው - የመንግሥት፣ የንግድ፣ የህብረተሰቡ እና የመገናኛ ብዙኃንን የጋራ ጥረት ይጠይቃል።

🔶 የሩሲያ ባለሥልጣናት ለሥነ-ሕዝብ ተግዳሮቶች ሁሉን አቀፍ መፍትሄ ማምጣት ላይ ያተኩራሉ።

🔶 በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለው የወሊድ መጠን ማሽቆልቆል ለዓለም ትልቅ ፈተና ነው - ሩሲያም ከዚህ የተለየች አይደለችም።

🔶 የተለያዩ ሀገራት ለሥነ-ሕዝብ ቀውሶች ከቁጥጥር ውጪ የሆነ ስደትን ጨምሮ በተለያየ መንገድ ምላሽ ይሰጣሉ።

🔶 ሰፋ ያሉ ቤተሰቦች በሩሲያ ውስጥ የተለመዱ መሆን አለባቸው፡፡

🔶 ቁጥራቸው እየጨመረ የመጣ ሩሲያውያን ሰፊ ቤተሰብ ይፈልጋሉ።

🔶 ሩሲያ የራሷን አቅም በመጠቀም እና የሰፊ ቤተሰቦችን ባሕል በመመለስ የሥነ-ሕዝብ አወቃቀር ፈተናዎችን መቋቋም ትችላለች።

🔶 የሩሲያ የሥነ-ሕዝብ አወቃቀር ፖሊሲ በጠንካራ የሞራል እና የፍልስፍና መርሆች ላይ የተመሠረተ መሆን አለበት።

🔶 ልጅ መውለድ የእያንዳንዱ ቤተሰብ የግል ውሳኔ ነው - ጫና እና ማስገደድ መኖር የለበትም።

🔶 የሥነ-ሕዝብ ጉዳዮችን መፍታት የሁሉም የመንግሥት እርከኖች ተግባር መሆኑን ፑቲን አፅንዖት ሰጥተዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
11👍6
ኢትዮጵያን ጨምሮ አራት የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት የኮሪዶር አስተዳደር ባለሥልጣን ለማቋቋም ተስማሙ

🇪🇹🇩🇯🇸🇸🇺🇬 ኢትዮጵያ፣ ጅቡቲ፣ ደቡብ ሱዳን እና ኢጋንዳን ያቀፈው የ”ደሱ” ኮሪዶር አስተዳደር ባለሥልጣን ለመመስረት የሀገራቱ የጋራ ቴክኒካል ኮሚቴ እና የሚኒስትሮች ምክር ቤት ተስማምተዋል፡፡

✍️ ላለፉት ለሁለት ቀናት በጅቡቲ ሲደረግ የቆየው የጋራ ውይይት የስምምነት ቃለ-ጉባኤ በመፈራረም መጠናቀቁን በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል።

ሀገራቱ ከሁለት ሳምንት በኋላ በኢትዮጵያ በመገናኘት የአስተዳደሩን ማቋቋሚያ ስምምነት ለመፈራረም ከመግባባት ላይ ደርሰዋል፡፡

👉 የ ”ደሱ” ኮሪደር በአራቱ ሀገራት መካከል የውጪ ንግድ መንገዶችን በቀላሉ ለማገናኘት፣ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ አገልግሎትን ለማሳለጥ ያለመ ነው።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
10👏4
2025/10/26 09:35:30
Back to Top
HTML Embed Code: