ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
❗️ የእስራኤል የብሔራዊ ደህንነት ሚኒስትር የተኩስ አቁም ስምምነቱ መጣሱን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ጋዛ ውስጥ ሙሉ ወታደራዊ ዘመቻ መልሰው እንዲያስጀምሩ ጠየቁ በእንግሊዘኛ ያንብቡ ✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
ሐማስ አሜሪካን የተኩስ አቁም ስምምነቱን ጥሷል በማለት ያቀረበችበትን ክስ አስተባበለ
ፍልስጤማዊው ንቅናቄ በመግለጫው የሚከተሉትን ነጥቦችንም አስታውቋል፡-
🔶 በመሬት ላይ ያለው እውነታ እንደሚያሳየው የወራሪው አካል ባለሥልጣናት "በጋዛ ሰርጥ የወንጀል ቡድኖችን አደራጅተዋል፣ አስታጥቀዋል እንዲሁም በገንዘብ ደግፈዋል"።
🔶 ሐማስ የአሜሪካን አስተዳደር "የወራሪውን አካል ትርክት ማስተጋባት እንዲያቆም እና በምትኩ የተኩስ አቁም ስምምነትን መጣስ ላይ እንዲያተኩር" አሳስቧል።
🔶 በንቅናቄው ላይ የሚሰነዘሩት የሐሰት ክሶች "ከእስራኤል ፕሮፓጋንዳ ጋር የሚጣጣሙ እና የወራሪው አካል ባለሥልጣናት ለሚፈጽሟቸው ተከታታይ ወንጀሎችና ጥቃቶች እንደ ሽፋን ሆነው ያገለግላሉ"።
በትናንትናው ዕለት የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት እንዳስታወቀው፤ አሜሪካ ስለ ሐማስ "በቅርቡ የሚፈፀም" የተኩስ አቁም ስምምነት ጥሰት ለጋዛ ሰላም ስምምነት ዋስትና ለሰጡ አገሮች አሳውቃ ነበር።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X

❤5🕊3🥰2👎1
ሉቭረ ያጋጠመው ስርቆት በፈረንሳይ ሙዚየሞች ያለውን የደህንነት ጉድለት አጋልጧል - የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር አምኗል
ከሉቭረ ሙዚየም የተሰረቀው ጌጣጌጥ "ትክክለኛ ባሕላዊ ቅርስ" ነው ሲሉ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ሎውረንት ኑኜዝ ተናግረዋል።
ስለ ስርቆቱ የተሰሙ ተጨማሪ ዝርዝሮች፡-
◻️ ሌቦቹ ዛሬ ማለዳ የሉቭረን ሙዚየም ሰብረው በመግባት የንጉሠ ነገሥት ናፖሊዮን ቀዳማዊ ባለቤት የነበሩት የእቴጌ ጆሴፊን ስብስብ የሆኑ ዘጠኝ ጌጣጌጦችን እንደሰረቁ የአገሪቱ ሚዲያዎች ዘግበዋል።
◻️ የንጉሠ ነገሥት ናፖሊዮን ሳልሳዊ ባለቤት የነበሩት የእቴጌ ዩጂኒ ደ ሞንቲጆ የተሰበረ አክሊል በሉቭረ ሙዚየም አቅራቢያ ተገኝቷል (በምስል ላይ የሚታየው) ሲሉ የፈረንሳይ ሚዲያ ገልጿል።
◻️ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው፣ "ሦስት ወይም አራት" ሌቦች ስርቆቱን ያከናወኑት በ"ሰባት ደቂቃዎች" ውስጥ ነው። ሙዚየሙ ውስጥ ከውጭ በመግባት "አፖሎ ጋለሪ" ወደሚባለው ቦታ ለመድረስ በጭነት መኪና ላይ የተገጠመ ግንባታ እቃ ማቀበያ ማሽን ተጠቅመዋል (ቪዲዮ 2)።
◻️ የፓሪስ ዓቃቤ ሕግ ቢሮ በጉዳዩ ላይ በተደራጀ ስርቆት እና በወንጀል ሴራ ምርመራ መጀመሩን አስታውቋል።
📹 በፑትኒክ አፍሪካ ዘጋቢ የተቀረጸው ቪዲዮ ከዝርፊያው በኋላ በፓሪስ ሉቭረ ሙዚየም አካባቢ ያለውን ሁኔታ ያሳያል፡፡
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
ከሉቭረ ሙዚየም የተሰረቀው ጌጣጌጥ "ትክክለኛ ባሕላዊ ቅርስ" ነው ሲሉ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ሎውረንት ኑኜዝ ተናግረዋል።
ስለ ስርቆቱ የተሰሙ ተጨማሪ ዝርዝሮች፡-
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤7👍5
🇪🇹 የአፍሪካ ልማት ባንክ በኢትዮጵያ የመሠረተ ልማት ሥራዎች ላይ መዋዕለ ነዋይ ፈሰስ እንደሚያደርግ አስታወቀ
የባንኩ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሲዲ ኦልድ ታህ፣ ባንኩ በበጀት ድጋፍ፣ በግብርና እና በመሠረተ ልማት እና በተለይም ለቀጣናዊ ውህደት ወሳኝ ለሆነው የአየር ትራንስፖርት መሠረተ ልማት ድጋፍ ለማድረግ ያላቸውን ዝግጁነት አረጋግጠዋል።
🤝 የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ ከዓለም ባንክና ከዓለም ከአይኤምኤፍ ዓመታዊ ጉባኤ ጎን ለጎን ከባንኩ ፕሬዝዳንት ጋር ተወያይተዋል።
በውይይቱም የገንዘብ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያን ማክሮ ኢኮኖሚያዊ እና የኢንቨስትመንት ሁኔታን ለማሻሻል፣ በዐቢይ ዘርፎች ላይ ምርታማነትን ለማሳደግ እና የመንግሥታዊ ዘርፍን ውጤታማነት ለማጠናከር ተግባራዊ የሆኑ የሪፎርም ጥረቶችን ለፕሬዝዳንቱ አስረድተዋል።
🛬 የልማት ባንኩ ዋና መሪ አመቻች እና ገንዘብ አቅራቢ በመሆን ቁልፍ ሚና እየተጫወተ ስላሚገኝበት አዲሱ የቢሾፍቱ አየር ማረፊያ ፕሮጀክት የተመለከቱ መረጃዎችም በውይይቱ ውስጥ ተካተዋል ሲል ሚኒስቴሩ በማኅበራዊ የትስስር ገፁ ላይ አስነብቧል።

👍4❤3
የቀይ ባሕር እና የናይል ወንዝ ተጠቃሚነት ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ኅልውና እና ስትራቴጂያዊ ነፃነት ወሳኝ ነው - የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት
🇪🇹 የአገሪቱ ብልጽግና ከቀይ ባሕር እና ከናይል ተፋሰስ ጋር በመሠረታዊነት የተቆራኘ መሆኑን ያብራራው የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት፣ ይህ ተጠቃሚነት "የማንነት፣ የእርቅ እና የታሪካዊ ቀጣይነት" ጉዳይ መሆኑን አጽናኦት ሰጥቷል፡፡
ይህ አቋም የተንፀባረቀው "የናይል-ቀይ ባሕር ትስስር" በሚል ርዕስ በአፋር ክልል ዋና ከተማ በሰመራ በተደረገው ስትራቴጂያዊ ጉባኤ ላይ መሆኑን የአገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።
👉 የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ጃፋር በድሩ፣ በቀይ ባሕር ጂኦፖለቲካ ላይ ለዘመናት የቆየውን ዝምታ ማብቃቱን አስታውቀዋል። የኢትዮጵያ ወደ ባሕሩ መቅረብ "ኃይል እና ራዕይዋ እንደሚሰፋ" አመላክተዋል።
በመድረኩ የአገሪቱን ጥቅም ለማስጠበቅ የኢትዮጵያን የባሕር ኃይል ዘመናዊና ብቁ ኃይል እንዲሆን ለማደራጀት እየተደረገ ያለውን ጥረትም ተገልጿል።
ሁለቱን የውኃ ሥርዓቶች በኢትዮጵያ ስትራቴጂያዊ አጀንዳ ውስጥ ለማዋሃድ ያለመው ይህ ጉባኤ፣ በከፍተኛ የመንግሥትና የጦር መኮንኖች ተሳትፎ መካሄዱን ሚዲያው ገልጿል።
በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለጸገ ምስል

❤11👍1👎1🥰1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#viral | 100 ደረጃ ያለውን ሕንጻ ከመውረድ ቢሮ ውስጥ መኖር ይሻል ይሆን 🤔
በቅርቡ በኳላ ላምፑር ጊዜአዊ የሌክትሪክ መቆራረጥ አጋጥሞ ነበር። ይህ ክስተት 106 ፎቆች ካሉት ከከተማዋ ሰማይ ጠቀስ ሕንጻዎች በአንዱ ውስጥ የነበሩ ሰዎች በአስቸኳይ እንዲለቅቁ አስገድዷቸዋል። ይህ ስፍር ቁጥር የሌለው ደረጃ የመውረድ ድራማዊ ክስተት በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በፍጥነት መነጋገሪያ ሆኗል።
የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ብዛት ያላቸው ሠራተኞች በድንገቴው ከባድ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በጣም ስለደከሙ በማግስቱ ወደ ሥራ መመለስ አልቻሉም በማለት ቀልደዋል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
በቅርቡ በኳላ ላምፑር ጊዜአዊ የሌክትሪክ መቆራረጥ አጋጥሞ ነበር። ይህ ክስተት 106 ፎቆች ካሉት ከከተማዋ ሰማይ ጠቀስ ሕንጻዎች በአንዱ ውስጥ የነበሩ ሰዎች በአስቸኳይ እንዲለቅቁ አስገድዷቸዋል። ይህ ስፍር ቁጥር የሌለው ደረጃ የመውረድ ድራማዊ ክስተት በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በፍጥነት መነጋገሪያ ሆኗል።
የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ብዛት ያላቸው ሠራተኞች በድንገቴው ከባድ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በጣም ስለደከሙ በማግስቱ ወደ ሥራ መመለስ አልቻሉም በማለት ቀልደዋል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
❤14😱2
🇪🇬 የግብፅ ፕሬዝዳንት የዓለምን 'መራጭነትና መንታዌ አሠራርን ኮንነው የተባበሩት መንግሥታት ማሻሻያን ጠይቀዋል
አብደል ፈታህ ኤል-ሲሲ የአስዋን የዘላቂ ሰላምና ልማት ጉባኤን ሲከፍቱ ባደረጉት ንግግር፣ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ከፍተኛ ሰብአዊ ቀውሶችን "መፍታት ባለመቻሉ እና ብቃት በማጣቱ" ወቅሰዋል።
🌍 ኤል-ሲሲ አፍሪካ የከፉ ግጭቶች፣ የልማት ፈተናዎች እና የአየር ንብረት አደጋዎች ተጋርጠውባት፣ የእነዚህ ውድቀቶች ገፈት ቀማሽ ሆናለች ብለዋል፡፡
የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በድር አብደላቲ ይህን አቋም አስተጋብተዋል፤ አሁን ያለውን የዓለም እውነታ እና የደቡባዊ ዓለም ምኞቶችን በተሻለ ሁኔታ ለማንፀባረቅ የዓለም አቀፍ ተቋማት፣ የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት እና ዓለም አቀፍ የፋይናንስ አካላትን ያካተተ ማሻሻያ እንዲደረግ አሳስበዋል።
🇸🇩 "በተለዋዋጭ ዓለም፣ በእንቅስቃሴ ላይ ያለች አኅጉር" በሚል መሪ ቃል የተሰባሰበው ፎረሙ፣ የሱዳን ቀውስ ላይም ትኩረቱን አድርጓል፡፡ ግብፅ ሱዳናውያን-መር የፖለቲካ እልባት እና ዘላቂ የተኩስ አቁም አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥታለች።

❤12👎5🤮3
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#viral | የሊዮፓርዱ የተዝናኖት ጊዜ፤ የዱር ርጋታን የማጣጣም አፍታ
🐆 በአንድ ቀን ውስጥ 25 ኪሎ ሜትር መጓዝ የሚችለው እና በሩቅ ምስራቅ ሩሲያ "የነብር ምድር የሚገኘው የአሙር ሊዮፓርድ (በተለምዶ የአፍሪካ ነብር በመባል የሚታወቀው ዝርያ) ፤ አንዳንድ ጊዜ ግን ፀጥታን ይመርጣል ሲሉ ነብሩ የሚገኝበት የመጠለያ አስተዳደር ገልፀዋል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
🐆 በአንድ ቀን ውስጥ 25 ኪሎ ሜትር መጓዝ የሚችለው እና በሩቅ ምስራቅ ሩሲያ "የነብር ምድር የሚገኘው የአሙር ሊዮፓርድ (በተለምዶ የአፍሪካ ነብር በመባል የሚታወቀው ዝርያ) ፤ አንዳንድ ጊዜ ግን ፀጥታን ይመርጣል ሲሉ ነብሩ የሚገኝበት የመጠለያ አስተዳደር ገልፀዋል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
🥰7👎2❤1
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
ሐማስ አሜሪካን የተኩስ አቁም ስምምነቱን ጥሷል በማለት ያቀረበችበትን ክስ አስተባበለ ፍልስጤማዊው ንቅናቄ በመግለጫው የሚከተሉትን ነጥቦችንም አስታውቋል፡- 🔶 በመሬት ላይ ያለው እውነታ እንደሚያሳየው የወራሪው አካል ባለሥልጣናት "በጋዛ ሰርጥ የወንጀል ቡድኖችን አደራጅተዋል፣ አስታጥቀዋል እንዲሁም በገንዘብ ደግፈዋል"። 🔶 ሐማስ የአሜሪካን አስተዳደር "የወራሪውን አካል ትርክት ማስተጋባት እንዲያቆም…
ኔታንያሁ ጋዛ በሚገኙ የሐማስ ዒላማዎች ላይ 'ጠንካራ እርምጃ' እንዲወሰድ ማዘዛቸውን ጽሕፈት ቤታቸው አስታወቀ
የጠቅላይ ሚኒስትሩ መመሪያ ለእስራኤል ጦር የተሰጠው የፍልስጤሙ ንቅናቄ በእስራኤል መከላከያ ሠራዊት ላይ ጥቃቶችን ከፍቷል ከሚሉ ዘገባዎች በኋላ ነው ሲል ጽሕፈት ቤታቸው ጨምሮ አስታውቋል።
👉 እንደ እስራኤል ሚዲያዎች፣ በዛሬው ዕለት አገሪቱ በመከላከያ ሠራዊቷ ላይ ተፈፅሟል ለተባለው ጥቃት የአጸፋ ምላሽ ለመስጠት በደቡባዊ ጋዛ ሰርጥ በምትገኘው ራፋህ ላይ የአየር ድብደባ ፈጽማለች። የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት ሐማስ በእስራኤል ወታደራዊ ይዞታዎች ይ በርካታ ጥቃቶችን ፈጽሟል ሲል ገልጿል።
በእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ሥራ ላይ የዋለው መስከረም 30 ቀን ነበር። ያለፈው ሰኞ የአሜሪካ፣ የግብፅ፣ የኳታር እና የቱርክ መሪዎች በጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ አዋጅ መፈራረማቸው ይታወሳል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
የጠቅላይ ሚኒስትሩ መመሪያ ለእስራኤል ጦር የተሰጠው የፍልስጤሙ ንቅናቄ በእስራኤል መከላከያ ሠራዊት ላይ ጥቃቶችን ከፍቷል ከሚሉ ዘገባዎች በኋላ ነው ሲል ጽሕፈት ቤታቸው ጨምሮ አስታውቋል።
መግለጫው ሲያትት፣ "የተኩስ አቁም ስምምነቱ በሐማስ መጣሱን ተከትሎ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ከመከላከያ ሚኒስትሩ እና ከደህንነት ተቋማት ኃላፊዎች ጋር ምክክር አድርገዋል፤ እንዲሁም በጋዛ ሰርጥ በሚገኙ የአሸባሪው ዒላማዎች ላይ ጠንካራ እርምጃ እንዲወሰድ መመሪያ ሰጥተዋል" ብሏል።
👉 እንደ እስራኤል ሚዲያዎች፣ በዛሬው ዕለት አገሪቱ በመከላከያ ሠራዊቷ ላይ ተፈፅሟል ለተባለው ጥቃት የአጸፋ ምላሽ ለመስጠት በደቡባዊ ጋዛ ሰርጥ በምትገኘው ራፋህ ላይ የአየር ድብደባ ፈጽማለች። የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት ሐማስ በእስራኤል ወታደራዊ ይዞታዎች ይ በርካታ ጥቃቶችን ፈጽሟል ሲል ገልጿል።
በእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ሥራ ላይ የዋለው መስከረም 30 ቀን ነበር። ያለፈው ሰኞ የአሜሪካ፣ የግብፅ፣ የኳታር እና የቱርክ መሪዎች በጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ አዋጅ መፈራረማቸው ይታወሳል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
👎6👏4
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
ሉቭረ ያጋጠመው ስርቆት በፈረንሳይ ሙዚየሞች ያለውን የደህንነት ጉድለት አጋልጧል - የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር አምኗል ከሉቭረ ሙዚየም የተሰረቀው ጌጣጌጥ "ትክክለኛ ባሕላዊ ቅርስ" ነው ሲሉ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ሎውረንት ኑኜዝ ተናግረዋል። ስለ ስርቆቱ የተሰሙ ተጨማሪ ዝርዝሮች፡- ◻️ ሌቦቹ ዛሬ ማለዳ የሉቭረን ሙዚየም ሰብረው በመግባት የንጉሠ ነገሥት ናፖሊዮን ቀዳማዊ ባለቤት የነበሩት…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሉቭረ ሙዚየም ውስጥ የተፈጸመውን ዝርፊያ የሚያሳይ ቪዲዮ ተለቀቀ
ቪዲዮው ባለኮፍያ ሹራብ የለበሰ ግለሰብ በአፖሎ ጋለሪ ውስጥ ያለውን የማሳያ (ዲስፕሌይ) መስታወት ሲቆርጥ ያሳያል። ዝርፊያው በተፈጸመበት ወቅት ሙዚየሙ ክፍት ስለነበር ጎብኚዎችም በቪዲዮው ላይ ይታያሉ።
ከማኅበራዊ ሚዲያ የተገኘ ቪዲዮ
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
ቪዲዮው ባለኮፍያ ሹራብ የለበሰ ግለሰብ በአፖሎ ጋለሪ ውስጥ ያለውን የማሳያ (ዲስፕሌይ) መስታወት ሲቆርጥ ያሳያል። ዝርፊያው በተፈጸመበት ወቅት ሙዚየሙ ክፍት ስለነበር ጎብኚዎችም በቪዲዮው ላይ ይታያሉ።
ከማኅበራዊ ሚዲያ የተገኘ ቪዲዮ
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
🙉2👍1
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
የሩሲያ ጦር በዶኔትስክ ህዝቦች ሪፐብሊክ እና በዛፖሮዥዬ ክልል ሁለት መንደሮችን ነጻ አወጣ - የመከላከያ ሚኒስቴር ነፃ የወጡት መንደሮች ቹኒሺኖ እና ፖልታቭካ መሆናቸውን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል። በቅርብ ወራት ውስጥ የሩሲያ የጦር ኃይሎች በዶንባስ ክልል እና ከዚያም በላይ ባሉ አካባቢዎች በሚካሄደው ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ ማዕቀፍ ውስጥ መንደሮችን ተራ በተራ እያስለቀቁ ፈጣን ግስጋሴ እያደረጉ…
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የሩሲያ ወታደሮች በዛፖሮዥዬ ክልል ፖልታቭካን ነጻ በማውጣት ከ12 ካሬ ኪሎ ሜትር በላይ ያለውን አካባቢ አጽድተዋል - የመከላከያ ሚኒስቴር
የሩሲያው “ቮስቶክ” (ምስራቅ) ክፍል በዘመቻው ወቅት ከ500 በላይ ሕንጻዎችን እንዳጸዳ (ነጻ ማድረጉን ) የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።
የተለቀቀው ቪዲዮ በዛሬው ዕለት ቀደም ሲል ነጻ መውጣቱ በተገለፀው መንደር ውስጥ ወታደሮች ሰንደቅ ዓላማ ሲያውለበልቡ ያሳያል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
የሩሲያው “ቮስቶክ” (ምስራቅ) ክፍል በዘመቻው ወቅት ከ500 በላይ ሕንጻዎችን እንዳጸዳ (ነጻ ማድረጉን ) የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።
የተለቀቀው ቪዲዮ በዛሬው ዕለት ቀደም ሲል ነጻ መውጣቱ በተገለፀው መንደር ውስጥ ወታደሮች ሰንደቅ ዓላማ ሲያውለበልቡ ያሳያል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
❤4👍4
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አሜሪካ "ሁሉንም የጦር መሣሪያ ለዩክሬን መስጠት አትችልም" ሲሉ ትራምፕ ተናገሩ
ከኪዬቭ ለቀረበው የአቅርቦት ጥያቄ ምላሽ ሲሰጡ፣ አሜሪካ እራሷ የቶማሃውክ ክሩዝ ሚሳኤሎች እንደሚያስፈልጓት ደጋግመው አስረግጠዋል።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት የዩክሬን ግጭት በሰላማዊ መንገድ መፍታት እንደሚችሉ ሙሉ እምነት እንዳላቸውም ተናግረዋል።
አሜሪካ እና ሩሲያ "እጅግ በጣም ጥሩ አቅም" የንግድ አላቸው ሲሉ ትራምፕ ጠቁመዋል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
ትራምፕ "አሜሪካን ለአደጋ ማጋለጥ አልችልም" በማለት ለአሜሪካ ሚዲያ ገልጸዋል፡፡
ከኪዬቭ ለቀረበው የአቅርቦት ጥያቄ ምላሽ ሲሰጡ፣ አሜሪካ እራሷ የቶማሃውክ ክሩዝ ሚሳኤሎች እንደሚያስፈልጓት ደጋግመው አስረግጠዋል።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት የዩክሬን ግጭት በሰላማዊ መንገድ መፍታት እንደሚችሉ ሙሉ እምነት እንዳላቸውም ተናግረዋል።
አሜሪካ እና ሩሲያ "እጅግ በጣም ጥሩ አቅም" የንግድ አላቸው ሲሉ ትራምፕ ጠቁመዋል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
❤9👍6
❗️ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ “የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ፕሬዚዳንት የነበሩት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ በማረፋቸው ኀዘን ተሰምቶኛል” ሲሉ በማኅበራዊ ሚዲያቸው ላይ ጽፈዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ለቤተሰቦቻቸው እና ለመላ ኢትዮጵያ ሙስሊሞች መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡
ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ባደረባቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ሕልፈት ሕይወታቸው ተሰምቷል፡፡
✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ “የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ፕሬዚዳንት የነበሩት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ በማረፋቸው ኀዘን ተሰምቶኛል” ሲሉ በማኅበራዊ ሚዲያቸው ላይ ጽፈዋል።
“ሐጂ ዑመር በአመራር ዘመናቸው የተለያዩ ወገኖች ወደ አንድነት እንዲመጡ እና የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በሕግ ዕውቅና እንዲኖረው ያደረጉትን አስተዋጽዖ ሁሌም እናስታውሰዋለን።” ብለዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ለቤተሰቦቻቸው እና ለመላ ኢትዮጵያ ሙስሊሞች መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡
ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ባደረባቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ሕልፈት ሕይወታቸው ተሰምቷል፡፡
✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
😢70💔30❤12😱9🙏3
🇲🇱 የማሊ ሕዝብ ቁጥር በ25 ዓመታት ውስጥ በእጥፍ ሊጨምር እንደሚችል ተገለፀ
በ2050 የሀገሪቱ ሕዝብ ቁጥር 51፣670፣490 ይደርሳል ተብሎ እንደሚጠበቅ የኢኮኖሚ ሚኒስቴር አካል የሆነው የብሔራዊ ሕዝብ ዳይሬክቶሪት ገልጿል።
በአሁኑ ወቅት የሀገሪቱ ሕዝብ ቁጥር 24፣738፣480 ነው።
ይህ አዝማሚያ በከፍተኛ የወሊድ መጠን እና የዕድሜ ጣሪያ መሻሻል እንደመጣ ተጠቁሟል።
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
በ2050 የሀገሪቱ ሕዝብ ቁጥር 51፣670፣490 ይደርሳል ተብሎ እንደሚጠበቅ የኢኮኖሚ ሚኒስቴር አካል የሆነው የብሔራዊ ሕዝብ ዳይሬክቶሪት ገልጿል።
በአሁኑ ወቅት የሀገሪቱ ሕዝብ ቁጥር 24፣738፣480 ነው።
ይህ አዝማሚያ በከፍተኛ የወሊድ መጠን እና የዕድሜ ጣሪያ መሻሻል እንደመጣ ተጠቁሟል።
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
😁1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሩሲያ እና ዩክሬን አሁን ባለው የጦርነት ግንባር ግጭቱን ማቆም አለባቸው - ትራምፕ
“78 በመቶ የሚሆነው መሬት በሩሲያ ተይዟል ያሉት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት፤ ”የግጭቱ ተዋናይ ወገኖች ሌሎች አስቻይ ስምምነቶችን ጦርነቱ ከቆመ በኋላ መደራደር ይችላሉ” ሲሉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል፡፡
ዩክሬን መላውን የዶንባስ ክልል ለሩሲያ እንድትሰጥ አለመወያየታቸውንም ትራምፕ ጠቁመዋል።
አንድ የእንግሊዝ ሚዲያ በውይይቱ የተሳተፉ ሰዎችን ዋቢ በማድረግ ሰኞ ዕለት እንደዘገበው፤ አርብ በተደረገው ስብሰባ ትራምፕ ዘለንስኪ ሰፊ ግዛቶችን ለሞስኮ እንዲሰጡ ገፋፍተዋቸዋል።
በዩክሬን ያለው ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ “በኪየቭ አገዛዝ የዘር ማጥፋት የተፈጸመባቸውን ሰዎች ለመጠበቅ” ያለመ ሲሆን የመጨረሻው ግብ ደግሞ ዶንባስን ሙሉ በሙሉ ነፃ ማውጣት እና የሩሲያን ደህንነት የሚያረጋግጡ ሁኔታዎችን መፍጠር መሆኑን ሞስኮ ደጋግማ ገልፃለች።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
“78 በመቶ የሚሆነው መሬት በሩሲያ ተይዟል ያሉት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት፤ ”የግጭቱ ተዋናይ ወገኖች ሌሎች አስቻይ ስምምነቶችን ጦርነቱ ከቆመ በኋላ መደራደር ይችላሉ” ሲሉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል፡፡
ዩክሬን መላውን የዶንባስ ክልል ለሩሲያ እንድትሰጥ አለመወያየታቸውንም ትራምፕ ጠቁመዋል።
አንድ የእንግሊዝ ሚዲያ በውይይቱ የተሳተፉ ሰዎችን ዋቢ በማድረግ ሰኞ ዕለት እንደዘገበው፤ አርብ በተደረገው ስብሰባ ትራምፕ ዘለንስኪ ሰፊ ግዛቶችን ለሞስኮ እንዲሰጡ ገፋፍተዋቸዋል።
“ውይይቱ በትራምፕ ‘ጦርነቱን አሁን ባለበት የድንበር መስመር ላይ በማቆም ስምምነት’ እንዲደረግ በመወሰን ተጠናቋል” ሲል አንድ ምንጭ ለጋዜጣው ተናግረዋል፡፡
በዩክሬን ያለው ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ “በኪየቭ አገዛዝ የዘር ማጥፋት የተፈጸመባቸውን ሰዎች ለመጠበቅ” ያለመ ሲሆን የመጨረሻው ግብ ደግሞ ዶንባስን ሙሉ በሙሉ ነፃ ማውጣት እና የሩሲያን ደህንነት የሚያረጋግጡ ሁኔታዎችን መፍጠር መሆኑን ሞስኮ ደጋግማ ገልፃለች።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
👍3🙏2
🇲🇦 ሞሮኮ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድኗ የተቀዳጀውን ታሪካዊ የዓለም ዋንጫ ድል በሀገር አቀፍ ደረጃ አከበረች
⚽️ የሞሮኮ ከ20 ዓመት በታች የእግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን እሁድ ምሽት በቺሊ በተደረገው የፍጻሜ ጨዋታ አርጀንቲናን 2 ለ 0 በማሸነፍ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የዓለም ሻምፒዮንነት ዘውድ ጭኗል፡፡
በተጨማሪም ሞሮኮ ከ42 ዓመት በኋላ በፊፋ ከ20 ዓመት በታች የዓለም ዋንጫ ፍጻሜ አርጀንቲናን ያሸነፈች የመጀመሪያዋ ብሔራዊ ቡድን ሆናለች።
🎉 ሞሮኳውያን በጭፈራ፣ በእንባ፣ በእልልታ፣ በዝማሬ እና በመኪና ጥሩምባ በከፍተኛ የደስታ ስሜት ውስጥ ሆነው የአንበሶቹን ድል አክብረዋል።
ከማህበራዊ ሚዲያ የተገኙ ምሥሎች

❤7