Telegram Web Link
1ሺህ አመት የተቀጣጠለው እሳት በነቢዬ መውሊድ ድርግም ጭልም አለ! ሰዪዲ.. ያ ረሱለሏህ!
ካለፈውና ከሚመጣው
አምሳያው የታጣው
صلى الله عليه وسلم
1.የኸሚስ ጀባታ #ከአል #ቡርዳ ጀመአ መልካም የ ኢሽቅ ኸሚስ ይሁንላቹ ውዶቼ😍❤️❤️
❀በቴሌግራም
❀ይ🀄️🀄️ሉን!
👇👇👇
www.tg-me.com/sudayisyeharyifochu
www.tg-me.com/sudayisyeharyifochu
የነገው የሚሊኒየም መውሊድ በላቀ ኢስላማዊ አደብ በደመቀ ሁኔታ ሊከበር ሰአታት ብቻ ቀርተዋል!
አሳዛኝ ዜና

የመውሊዱን ፕሮግራም መሰረዝን ስለማሳወቅ
•••••••••••••••••••••
ህገወጡ የአዲስ አበባ መጅሊስ የሚሊኒየሙን መውሊድ አስቁሙልን ብሎ ለአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት በፃፈው ደብዳቤ መሰረት፣ መስከረም 4/2015 ከንቲባ ፅህፈት ቤቱ በደብዳቤ የፈቀደውን የመውሊድ ፕሮግራም ሰላምና ፀጥታ ፅህፈት ቤቱ በቃል ደረጃ የጸጥታ ችግር ስላለ አቁሙ የሚል ትእዛዝ ሰጥቷል። ነጃሺ እስላማዊ ማህበር እስከዚህ ሰአት ድረት በደብዳቤ የተፈቀደ ፕሮግራም በደብዳቤ ከልክላችሁ አሳውቁን ብሎ እየጠየቀ ያለበት ሁኔታ ላይ ቢሆንም ከሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ምላሽ ማግኘት አልተቻለም።

በመሆኑም አገሪቱ ያለችበትን ሁኔታ በማየት እና ማህበረሰባችን ላይ ሊደርስ ከሚችለው ጉዳት አንፃር በጥልቀት በማየት እና በመወያየት የነገው የመስከረም 15/2015 የሚሊኒየም መውሊድ ፕሮግራም መሰረዙ ለማህበረሰባችን ደህንነት የተሻለ መሆኑን ስላመንን በአስገዳጅ ሁኔታ የነገውን የመውሊዱን ፕሮግራም መሰረዛችንን ለመግለፅ ተገደናል።

ስለሆነም በነገው እለት ወደ ሚሊኒየም አዳራሽ ባለመሄድ ከፀጥታ አካላት ጋር በሚደረግ ግጭት በማህበረሰባችን ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ማስቆም ግዴታችን በመሆኑ የአሽረፈል ኸልቅ ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ወዳጆች ነገ ጠዋት ወደ ሚሊኒየም አዳራሽ ባለመሄድ እንድትተባበሩን በእጅጉ እንማፀናለን።

የተሰረዘው የመውሊድ ፕሮግራም የረቢእ አልአወል ወር ሳይወጣ በተለዋጭ ቀን ማድረግ የምንችልበትን መንገድ ሁሉ የምንሞክር ሲሆን ተለዋጭ ቀኑ ካልተሳካ ከማህበረሰባችን በቲኬት ሽያጭ የተሰበሰበው ገንዘብ ተመላሽ የምናደርግ መሆኑን እናሳውቃለን። ቀጣይ ሂደቶችን በትእግስትና፣ በዱዓ እና በተጠናከረ የትግል ወኔ ፀንታችሁ እንድትጠብቁን አጥብቀን እንጠይቃለን።
#ኸሚስ❤️👏🥁

በጦይባ ቀበሌ ፋኖሱ ቢያበራ
ሐበሻ መሬት ላይ ሙሒቡህ ተጣራ
ወዳጄ መሕቡቤ ይላል ሳያባራ
ዛቱን ያየህ ይላል ባለህበት ስፋራ

የነቢ ወዳጆች ደማቅ ነው ሐድራቸው
ያሉበት አማን ነው ማማሩ ሆዳቸው
ወደ ሙስጦፋ አገር ዳኢም ዘማች ናቸው
መዲና ቀበሌ ተሰርቷል ቤታቸው

የሙሐባው ሸላይ እየነካካቸው
በባጢን ሐድረው መዲና ላይ ናቸው
የውዴታው ጅራፍ እየገረፋቸው፡፡
#መልካም_ኸሚስ

  በቴሌግራም አድራሻችን
   ይቀላቀሉን 👇👇👇
www.tg-me.com/sudayisyeharyifochu
www.tg-me.com/sudayisyeharyifochu
www.tg-me.com/sudayisyeharyifochu
#ኸሚስ_አመሻሹ_ላይ!

ከታላላቆች ሸጋው፣ በብቸኝነት ወደ ሐድረተል‐ፈናእ የበረሩ፣ ለነገሩ እንጂ ከሰው የላቁ እና የኮሩ፣ ጌታቸው ዘንድ ተደላዳይ የሆኑ ነበሩ። ሠይዲ አቡል መዋሒብ አሽ‐ሻዚሊይ ይባላሉ። የዘመናቸው ብቸኛ ወልይ ነበሩ። የማይደፈሩ እጅጉን የታፈሩ። በነብዬ ላይ ሶለዋት ሲያጎርፉ አሳማሪ ገበር ተሰኝተዋል። አንድ ዕለት ነብዬዋ በመናም ተሰየሟቸው። እጅግ አቅፈው ሳሟቸው። እርሳቸውም "የጌታዬ ነብዬዋ ምን ሰርቼ ነው እንዲህ ባለ ሐል የሳሙኝ?" ብለው ጠየቋቸው። የሐቢበሏህ ምላሽ እንዲህ ነበረ «በእኔ ላይ ሶለዋትን ከማብዛት አልፈው አሳማሪ የሆኑትን እንዲህ በመሳም እሸልማቸዋለሁ። ለእኔ መደሰት ሰበብ የሆኑልኝን ከናፍርት አስውባለሁ። በጠዋት አንድ ሺህ፣ በምሽትም አንድ ሺህ ጊዜ በእኔ ላይ ሶለዋት ለሚያወርድ ይህንን አደርግለታለሁ።»

ሠይዳችን በተውሒድ ባህር ይዋልላሉ ፣ እኛ ደግሞ በሶለዋት መርከብ እንንሻለላለን።

በሶለዋት ስንቱ ሻረ? ያላማረበት ያልተዋበ ልብና ጀሰድ የለም። ልቦናዎች ኹሉ ተሰብረው በመንሰቅሰቅ ተናንሰው ወደ አሏህ እና ነብዩ ሐድራ የሚገቡበት ጊዜ ላይ የሚያደርጉት አምልኮ ኹሉ ጠዓም አለው።
ልብህ አዝና ተከፍታ ተሰብራ ፣ ጭንቀት እና ግራ መጋባት በወረረህ ጊዜ ወደ ቂብላ ተቅጣጭና ወደ ነቢ ሰላምታ አድርስ። «በእኔ ላይ ሶለዋት ያወረደ ከጭንቀቱ ይገላገላል» ብለዋል ወለላው ነብዬ። ሃሳብ ሲልግ ሲያንገላታህ ጊዜ በወረቀት ላይ ሶለዋት እየከተብክ ቅራው። ተንቢሑል አናም የተሰኘ የሶለዋት ኪታብ ያዘጋጁልን ታላቅ ዓሊም በዚሁ ኪታብ መቅድም ላይ "ይህንን የሶለዋት ኪታብ ከትቤ ስጨርስ ከቤቶቼ በአንደኛው ግቢ ነብዩ ዘልቀው ግቢው በብርሃናቸው ተሞልቶ ዓይኔ ተጥበረበረ።" ሲሉ የኹነቱን ግርምት አካፍለውናል።

ሀጥያት በዝቶ ቀልብህን ሲጫንህ ሶለዋት አጉረፍርፍባቸው። ከደጋጎቹ እንዲህ ተብሎ ተሰምቷል "በዱንያ ላይ በሀጥያት የተጠመቀ ሰው ነበረ። በሞተ ጊዜ ፊቱ ጠቆረ። በቅፅበት ሰይዳችን መጥተው ፊቱን አብሰው አበሩት። ምክንያታቸውንም ሲጠየቁ «ምንም ሀጥያተኛ ቢሆን በእያንዳንዱ እርምጃው በእኔ ላይ ሶለዋት ያወርድ ነበረ።» ነው ያሉት። ስሙን ያደረገው ለወንጀል ሳሙና እንዴት ያለው ነብይ!!

#ሶሉ_ዓለል_ሐቢብ!
አሏሁመሶሊ ወሰሊም ወባሪክ ዓላ ሰይዲና ወመውላና ሙሐመድ ወዓላ አሊሂ ወሶህቢሂ ወሰለም!💚💚💚

✍️ Atiqa Ahmed Ali
አላህ ይዘንለት አላህ ይርሀመው
የመሻኢሆቻችን መንገድ የሠይዲ ( ሠዐወ) መንገድ ነው። ተቀዳሚ ሙፍቲ በአለም ተፅዕኖ ከፈጠሩ 500 ዑለሞች አንዱ ሁነው ተመርጠዋል። እንኳን ደስ አለን !!!
ነቢ ሰዐወ
የቲሞች እንዳያዝኑ ዘንድ የቲም ሁነው ተወለዱ። ድሃዎች ይፅናኑ ዘንድ ድሃ ሁነው ኖሩ። ስራ እንዳንንቅ ተምሳሌት ሊሆኑን ዘንድ ከንግድ እስከ እረኝነት ተቀጥረው ስሩ።

አግብታ የፈታችን ሴት ማግባት ክብር መሆኑን ሊያሳዩን ዘንድ ከእድሜያቸው ምትበልጥን ሴት በወጣትነታቸው አገቧት።

ወጣት አግብተው ልጅ ያልወለዱ ጥንዶች ይፅናኑባቸድ ዘንድ ዓኢሻ የተሰኘች ልጃገረድ አግብተው ሳይወልዱ ቀሩ።

በፍቺ ትዳራቸውን የሚያጡ ሴቶች ይፅናኑ ዘንድ ሁለት ሴት ልጆቻቸው ከትዳር ተፈቱ። ህመምተኛ ይፅናና ዘንድ ራስን ሚያስት ህመም ታመሙ።

ባይተዋሮች እና ዘመድ አልባዎች ይፅናኑባቸው ዘንድ በገዛ ሀገራቸው ባይተዋር ሁነው ተገለሉ። ልጅ የሞተባቸው ወላጆች እንዳያዝኑ ዘንድ እኚህ ነቢይ ልጆቻቸውን እንደ ጉድ በሞት ተነጠቁ።

ስደተኞች ይፅናኑ ዘንድም እስከ እለተ ፍፃሜያቸው ድረስ ህይወታቸውን በስደት አጠናቀቁ።

ጀግኖች ይማሩባቸው ዘንድ በ23 አመት እንቅስቃሴ ብቻ የአለምን ህዝብ ቀይረው ለሁሉም ሰው በሁሉም ዘርፍ ተምሳሌት ሆኑ።

ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም

ለሌሎች እንዲደርስ #ላይክ #ሼር አድርጉ

https://www.tg-me.com/sudayisyeharyifochu
2024/05/14 20:21:47
Back to Top
HTML Embed Code: