Telegram Web Link
For those of you who want an online easy payment system and bank this is easy one to have and use. Good luck

@talentofmedstu

Join me and over 28 million users who love Revolut. Sign up with my link below: https://revolut.com/referral/?referral-code=dagmawoef6!SEP2-23-AR-PROMPT-AE
ደግሜ ደስተኛ እሆን ይሆን?
-----

እንደነዛ ቀናት፣
ሳይክል እየነዳሁ፣ በረፋድ ተሲያት
በምትጠልቅ ጀምበር፣ በለምለም አማጋ
ትናጋዬ እስኪደርቅ፣ ከሆዴ እየጮህኩ፣ እንደበረርኩበት።

ዶፍ እየጣለ አሁን
ብርድ እና እርጥበት፣ ሳያጎሳቁለኝ
ስካር እና ፍዝዘት፣ ሳያነበርረኝ፣
እንደነዛ ቀናት
ኩልል ያለ ውኃ፣ ጅረት ሳያጠልቀኝ
ከአብሮአደጎቼ ጋር፣ እንደዋልኩት ዋና፣
ዛፍ እንደወጣሁት፣ እንደ አምና ካቻምና...

ትመልሰኝ ህይወት? ወደ እናቴ ኩታ?
ወደ ሰላም ጠረን? ወደ ተረት ማታ?

Dr. Ermiyas Gp)
@Ad_mino
@talentofmedstu
👍63
"The normie scan"

Uptight
hysteria
Past life
Bacteria
Tortured
Lust
Cortex
Deluxe
Colored
Cults of
Wretched
Maya

Egyptian firstborn
Gory
Saklas' glory
Solitude is
Purity

Team Marry
Team Mohammed
Team Jesus
Team Dawkins

Bonafide
Creeper type
Too ironic to rant
convo-post-avant-garde
My left hand
Laughs at you

Dr. ቅዱስ
Jimma uni
JU-MI
@talentofmedstu
👍2👏2👎1🔥1
ማንነት...
ስማኝ ልጠይቅህ
አለው በለኝ እህ...
ስለምን ይሆን ራስህን የጠላህ
ኋላህን ረስተህ አንተነትክን የተውህ
ቡቱቶውን ትላንት በዛሬ ቀይረህ
ከአድባር ምትሸሽ ቀዬህን ረግጠህ
ዝቅ ማለትን ማህበረሰብህን ትተህ
ምን የሚሉት ጊዜ እንዲ የቀየረህ
ይሄን ነው ምትለኝ መለወጥ መሰልጠን
ማንነትን ትቶ በሌላ መሸፈን
ስማኝ ወንድምአለም ተመለስ ግዴለም
ባታውቀው ይሆናል ከንቱ ናት ይቺ አለም


ናትናኤል ኃይሌ
Sante medical college
c-2
@talentofmedstu
👍31
HOMETOWN

As you look through the town
The place you were born in,
You see eternity
On a dusty afternoon.

The air is sorrow, the winds despondent
But it's not your feelings,
Nor is it the sad songs, that play from the small souqs.

It comes from people, the withered living
Resenting the dead,
For, in the depths of their demise,
They've finally caught solace.


Dr. Ermiyas A (GP)
@talentofmedstu
👍41👏1
From Arsi University
@talentofmedstu
12
By Dr. Kirubel
a Must!!!
@talentofmedstu
1
ማን ነው የተረዳው?
ደፋ ቀና ብሎ ለነገው ሚተጋ
አንድ ምስኪን ሩሕሩሕ ወጣት ባለፀጋ
የሰፈሩ አውራ ሁሉ የሚያከብረው
ለጠራው ደራሽ እጅ የማያጥረው
የለኝምን አያውቅ ከቶ እንዴት ብሎ
ያለውን የሚለግስ ምስጋናን ተቀብሎ
ከራሱ አሳልፎ ያለውን የሚቸር
ንፉግነትን ማያውቅ አንድ ፍጡር ነበር
እንዲህ እንደዚህ እያለ ኑሮውን ሲገፋ
አእምሮውን ሳተና ከሰውነት ጠፋ
ጨርቁንም ጣለና መማታት ጀመረ
አላፊ አግዳሚውን ያባርር ጀመረ
በድንጋይ ቢያቅተው በስድብ እያለ
ቃላትን ሳይመርጥ ሰውን አያጮለ
ሲዘባበቱበት ጣት እየቀሰሩ
እንደሱ መች አዩት አልገባቸው ችግሩ
ፊታቸውን አጥቁረው ሊያዩት አልወደዱ
ጠጋ ብለው እንኳን እርሱን አልተረዱ።

Nathaniel
C-2
መታሰቢያነቱ በ አእምሮ ህመም ላሉ
ተፃፈ ጥቅምት 26/2016
👍102
From Arsi University
@talentofmedstu
8👍1
We are deeply saddened by the death of our fellow brother. A fatal shooting that resulted in the killing of Dr. Israel Tilahun occurred near Bole Atlas Road. The incident reportedly followed a collision between Dr. Tilahun's vehicle and another car. RIP... our condolence to his family.

@talentofmedstu
📷📷📷
Dr. Hilina Gosaye
JU intern
@talentofmedstu
12🔥4
የፍቅር ቃል
እራሴን ባደርገው ብሆን ባንቺ ቦታ
ምን ይሰማኝ ይሆን የጠየቅሺኝ ለታ
አቤት ያቺ እለት ልዩ ናት የምትሆን
አንቺን ለኔ አድርጎሽ ታየኝ መቼም ያ ቀን
ያ ቀን መቼ ነው? ወራት ወይስ አመታት
ወይስ ነው በቅርቡ አልያም በሳምንታ
ቃሉን ባትይውም ድፍረቱ ባይኖርሽ
በምልክት እንኳ አሳይኝ እባክሽ
እንደ ሀሩር ንዳድ እኔም ከምቃጠል
ወይ ተይኝ ልተውሽ አቦ እፎይ ልበል
ቃሉ ከባድ ሆኖ ከአፍሽ ካልወጣ
ዳገት ከሆነብሽ እኔም አንቺን ልጣ
ስቃዬም አይብዛ መቋጫ ይኑረው
መታደል የመሰለኝ ለካ መረገም ነው
ብቻ ብቻ እኔ ላፍቅርሽ ደሕና ሁኚ ውዴ
ልውጣ ከሕይወትሽ ዞር በይ ከመንገዴ
Natnael H.
SMC (sante)
C-2
@talentofmedstu
3👍3
እምቢታ
እንባ ባቀረረው ዓይንሽ፣
በሚንቀጠቀጠው ከንፈርሽ፣
ሀዘን ባወየበው በገረጣው ፌትሽ፣
ልብሽ የሸሸገው ገፅሽ ሚያሳብቀው፣
ከባድ ህመም አለ መደበቅ ያቃተው።
ቀና ማለት ከብዶት ዝቅ ያለው አካልሽ፣
ሰው ማየትከብዷቸው ያፈሩት አይኖችሽ፣
አጉልተው ይነግሩኛል የውስጥሽን ጥቃት፣
ገፍቶ የጣለሽን የጎረምሳ ጉልበት፣
ያስጎነበሰሽን የባህሉን ጭነት፣
ድምፅሽን የዋጠውን የልማዱን ጬኸት።
አሁን ግን ይበቃል!
የዝምታሽ ልኩ ከገደፉ አልፏል፥
የተረገጥሽበት ዝቅ ያልሽበት ግዜ ከእንግዲህ ያከትማል፥
የእምቢታ ጬኸትሽ ከዛሬ ይጀምራል።
ያንቺ ቀና ማለት ልጆችን ያድናል፣
የነገውን ትውልድ ከእንግዲህ ይታደጋል።

           Say no to GBV  (DEC 10 , 2023)

                ✍️ smr
AMU CII
@talentofmedstu
20👍1
Dear medicos
እንኳን አደረሳችሁ
@talentofmedstu
4
ማን ነው የተረዳው (ቁ.2)
ልትለው ፈልገህ የተውከው
ምን ይሉኝን ፈርተህ ያልተናገርከው
ብቸኝነትን መርጠህ የተደበከው
ሳትፈልግ ባዶነትክን የመረጥከው
ከሰዎች ሸሽተህ ጉዞህን የጀመርኸው
ፍርሃትህን ሸሽገህ ወይ አልተነፈስከው
ጥርሶችህን ላየ ደስተኛ ምትመስለው
ሁሉ የሞላለት ሀብቱ እንደ ተረፈው
ከላይ ለተመለከተህ ህመም ያልበገረው
በፈተና ብዛት ድንዝ ድብት ያልከው
ሌላውን ለመምሰል ብለህ ማንነትክን የቀየርከው
መገለልን ፈርተህ በማስመሰል የኖርከው
እንደዛ ስትባዝን ጭንቀትንክን ማን አየው
የአንተን መውጣት መውረድ ማንስ አስተዋለው
ማንስ እህ ብሎ ጆሮዉን አዋሰው
ማንስ ነበር ቀርቦ እንባህን ያበሰው
ከማንጓጠጥ ይልቅ ማን ነው የተረዳው
ከትቢያ አግኝቶት ተጠይፎ ቢያልፈው
በአንተ ጨርቅ መጣል ዛሬ የተሳለቀው
አርሱ እኮ ለየለት ብሎ የተጠየፈው
ቆሞ መሄዱን እንጂ ነገህን መች አየው
ህመምክን አንኳን ቀርቦ ሳይረዳህ
ባሳለፍከው ትላንት ሲዘባበትብህ
እርሱ ምን ጎድሎበት እያለ ሲያማህ
የኔ ያልከው ወዳጅ ምነው አልተረዳህ


ቁስልህ ባይሰማቸው ከሃኪም ባይወስዱህ
በቃ እንደማያቁህ ምናለ ቢረሱህ
አንተን መርዳት ትተው ከቶ አያስታውሱህ
እብደትክን እንኳ ለአንተ ቢተዉልህ።

ተፃፈ ታኅሣሥ 28/2016
ናትናኤል ኃይሌ
SMC (sante)
C-2
@talentofmedstu
4👍1
👍84
2025/10/22 16:12:50
Back to Top
HTML Embed Code: