የሀዘን መግለጫ!
ኢትዮጵያ ለተባለች ውድ አገር ትልቅ ስጦታን ከሰጡን አባቶች መኃል አንዱ የሆኑት የሁላችን አባት አባ በቀለ አይናለም ነበሩ። የህልፈተ ህይወታቸውን ዜና በመስማታችን የተሰማን ሀዘን ጥልቅ መሆኑን እየገለጽን ለመላው ህዝባችን መጽናናትን እንዲሰጥልን እንመኛለን።
የብዙ ዜጎችን ምኞት ለመፈጸም በርኻ የወረደው የእርሳቸው የአብራክ ክፋይ የሆነው ጀግናው ኢንጂነር ስመኘው በቀለ ነው። አገራችን ኢትዮጵያ የኒህን ታላቅ አባት ስም በፍጹም አትዘነጋም። የአብራካቸው ክፋይ ለአገሩና ለወገኑ ኩራት ሆኖ አልፏል። በእርግጥም እኒህ አባት በህይወታቸው ብዙ አሳዛኝ ነገር አልፏል። ብዙ ያልተቋጨ እና ያልተመለሰ የፍትህ ጥያቄም እንዳላቸው ግልጽ ነው። ቢሆንም ግን ይኼን ስሜታቸውን ሁላችን እንደምንጋራቸው ያውቁ ከነበር ብቻቸውን እንዳልተከፉና እንዳላዘኑ ስለሚያውቁ ይኼ መልካም ነው ብለን እናምናለን። የእርሳቸው የአብራክ ክፋይ የሁላችን ጀግና ነውና....
አባታችን እንደሚረዱት እርግጠኞች ነን። አገራችን ኢትዮጵያ እንደ ጽጌሬዳ አበባ ነች። የሚወዷት ዜጎቿ መስዋዕትነትን ሲከፍሉላት እያበበች ማራኪ ጠረኗንም እያበዛች የምትመጣ ስትሆን ሊቀጥፏት ቢጠጓት የጀግኖቿ መስዋዕትነት በዘንጓ ላይ እንዳለው እሾህ ይዋጋልና እንደ እሾህ በከበባት የልጆቿ በመስዋዕትነት ታፍራ እና ተከብራ ትኖራለች። ለዚህች ውድ አገር መስዋዕትነት ከከፈሉላት ጀግኖች መኃል የአባ በቀለ አይናለም ልጅ የሆነው ኢንጂነር ስመኘው በቀለ አንዱ ነው።
የአባት እና የልጁን ነፍሥ በሰላም ያሳርፍልን ዘንድ የእስራኤል አምላክ መልካም ፍቃዱ ይሁን!

👍3❤1
ዜና ኪነጥበብ
የክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮ/ ከሐምሌ 1/2011 ዓ.ም - ሰኔ 30/2013 ዓ.ም ድረስ ከወጡ ነጠላ ዜማዎች ጋ በለዛ አዋርድ ላይ 'ምርጥ ነጠላ ዜማ' በሚል ዘርፍ "ደሞ በአባይ" የተሰኘው ነጠላ ዜማው እጩ ሆኖ ቀርቧል። ስለሆነም ከታች በተቀመጠው ማስፈንጠሪያ እየገባችሁ ድምጻችሁን ለቴዲ አፍሮ እንድትሰጡት ለመጠቆም እንወዳለን።
#ማሳሰቢያ
አንድ ሰው በአንድ ዘርፍ ከታጩ ሙዚቃዎች ውስጥ ከአንድ ጊዜ በላይ መምረጥ ስለማይችል ስለአመራረጥ ሂደቱ ግልጽ ያልሆነ ነገር ከገጠምዎ ከአንድ ደቂቃ በታች የሆነ የአመራረጥ ሂደቱን የሚያስረዳ ቪዲዮ ከሰዓታት በኋላ ስለምናደርስዎ እንዲጠብቁን እንጠቁማለን።
https://vote.lezashow.com/

👍5❤2
ክቡር ዶክተር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሣሁን (ቴዲ አፍሮ)
ቤተልሔም፣ ኒው ኢራ እና የካቲት 12 የተማረባቸ ትመህርት ቤቶች ናቸው፡፡ ክስተቶችን፣ ስሜቶችን፣ እውነቶችን ኹሉ ይዘፍናቸዋል ብቻም ሳይኾን ይተርካቸዋል፣ ይሰንዳቸዋልም። ለበርካታ ድምፃውያንም ግጥም እና ዜማ ደርሶ አበርክቷል። በአቡጊዳ፣ በያስተሠርያል እና በጥቁር ሰው (በ 2004 ዓ/ም በለዛ ምርጥ አድማጮች ምርጫ፥ የዓመቱ ምርጥ አልበም ተሸላሚ ነበር።) ኢትዮጵያ የተሰኘው አልበሙም ባለፈው ዓመት በለዛ ምርጥ አድማጮች ምርጫ፥ የዓመቱ ምርጥ አልበም ተሸላሚ ነበር።) ከላይ የተዘረዘሩት ክቡር ዶክተር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን የሠራቸው የአልበሞች ስያሜዎች ናቸው፡፡ በ2007 ዓ/ም ደግሞ የዓመቱ ምርጥ ነጠላ ዜማ በሚል ዘርፍ በሰባ ደረጃ ተሸላሚም ነበር። ዘንድሮም የሁለት አመት ሙዚቃዎች በአንድ ተሰብስበው ለውድድር ሲቀርቡ እጩ ሆኖ የቀረበው ደሞ በአባይ የተሰኘው ነጠላ ዜማው ነው።
የአመቱ ምርጥ ነጠላ ዜማ በሚል ዘርፍ እጩ ሆኖ የቀረበውን ቴዲ አፍሮን እዚህ ይምረጡ👇

👍2
Forwarded from ታታ አፍሮ -Tata Afro
የመልካም ልደት መግለጫ!
ውዷ አምለሰት ሙጬ እንኳን ተወለድሽ! እንኳንም በሰላምና በጤና ለዚህች ዕለት አደረሰሽ! ኤሚዬ ብሩ እና መልካም ልደት ይሁንልሽ። ቀሪው ዘመንሽ በደስታና በብዙ በረከቶች የተሞላ ይሁን። የልጆችሽን ወግ ማዕረግ የባለቤትሽንም የስኬት ጥግ በዘመንሽ እንዲያሳይሽና የልብሽም መሻቶች በዘመንሽ የተፈጸሙ እንዲሆኑልሽ እመኛለሁ።
ከአክባሪ ወንድምሽ ✎✍#ታታ_አፍሮ /ነፃ ብዕር/

👍14
ቴዲ አፍሮ ከእስር ከተፈታ በኋላ ጥቁር ሰው የተሰኘ ግዙፍ አልበም ነበር የገነባው። ይህ ድንቅ አልበም ሚያዝያ 6/2004 ዓ.ም በገበያ ላይ የዋለው። ሚያዝያ 6/2014 ዓ.ም ይህ አልበም 10ኛ አመቱን ደፍኗል። እልፍ ሰዎች በጉጉት ሲጠብቁት የነበረው አርቲስት ቴዲ አፍሮ ከሰባት አመት ቆይታ በኋላ ነበር አልበም ይዞ ብቅ ያለው። በመሆኑም በኢትዮጵያ እና በመላው ዓለም ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ለሌሎች የሙዚቃ አፍቃሪያን እንዲሁም የአርቲስቱ የኪነ ጥብብ ቱርፋት ወዳጅ ለሆኑ ሁሉ ይኽ አልበም መለቀቁ እጅግ አስደሳች ዜና ሲሆን በአልበሙ የተካተቱት ሙዚቃዎችም ተወዳጅ ነበረ። በወቅቱ ትልቅ የገበያ መነቃቃትን የፈጠረው ጥቁር ሰው አልበም በአገር ውስጥ እና በዓለም ዙሪያ ሁሉ ታላላቅ ኮንሰርቶች እንዲዘጋጁ ትልቅ እድልን ያመቻቸ ነበር። ጥቁር ሰው አልበም እንደሌሎቹ የአርቲስቱ የጥበብ ቱርፋቶች ዛሬም ድረስ እንደ አዲስ ዜማ ይደመጣል። እንደ ወይን እያደር ጣዕሙ ይጎመራል።
#Ethiopia
ኢትዮጵያ የተሰኘው ነጠላ ዜማ በቴዲ አፍሮ ህጋዊ የዩትዩብ ቻናል ከተለቀቀ ዛሬ አምስተኛ አመቱን ደፈነ። ይኼ ሙዚቃ ሚያዝያ 7/2009 ዓ.ም ምሽት ላይ ነበር የተለቀቀው። በተለቀቀ በሰዓታት ውስጥ ግን ድፍን አዲስ አበባ በዚህ ሙዚቃ ዳንኪራ ስትረግጥ አምሽታለች። ከተማይቱ አዲስ ዘመንን የምታከብር ያህል በየ ስፍራው እንደ ብሔራዊ መዝሙር ይኼ ሙዚቃ ብቻ ሲደመጥ አነጋ... በዕለቱ በተለያዩ ስፍራዎች እየተዘዋወርኩ ለሊቱን ሙሉ ስሜቱን ለማጣጣም የሞከርኩ ሲሆን በየ ቦታው የሚታየው የህዝቡ ስሜት እጅግ ልዩ ነበር። የአገር ፍቅር ልኩ የገባው የአገሬ ሰው ዛሬም ድረስ በዚህ ሙዚቃ ኢትዮጵያን ከፍ ከፍ ያደርጋታል። ዘፈኑ ከተለቀቀ በአምስት አመታት ውስጥ በዩትዩብ ብቻ 23 ሚልየን አድማጭን አግኝቷል። በተጨማሪም ይኼው ሙዚቃ በምስል ተቀናብሮ በአርቲስቱ ህጋዊ የዩትዩብ ቻናል ላይ 5.7 ሚሊየን ጊዜ መታየት ችሏል። በጥቅሉ ኢትዮጵያ የተሰኘው ነጠላ ዜማ በዩትዩብ ብያ ከ28.7 ሚሊየን በላይ አድማጮችን አግኝቷል። ይኼ ደግሞ በኢትዮጵያ ያለ ተንቀሳቃሽ ምስል ተለቆ ብዙ አድማጮችን ያገኘ የመጀመሪያው ነጠላ ዜማ ነው።
✎✍#ታታ_አፍሮ /ነፃ ብዕር/
Teddy Afro🤴 ደረጃቸውን ስለጠበቁ ውብ የሙዚቃ አልበሞችህ ከልብ እናመሰግናለ

👍16
Forwarded from ታታ አፍሮ -Tata Afro
የክቡር ዶ/ር ቴዎድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮ/ አንተ ጽኑ እና ጀግና አባት ነህ። ከአብራኮችህ ለወጡ ልጆችህ ብቻ ሳይሆን ለብዙዎች ምርጥ አባት ሆነህ በመቆምህ ከልብ እናመሰግንኃለን።
የአገሬ ማህጸን እንዳንተ አይነት ቅን ሰዎችን ስለምታፈራ ክብር ሊሰማት ይገባል።
መልካም የአባቶች ቀን ይሁንልህ!
በጽኑ መውደድ እ...ን...ወ...ድ...ኃ...ለ...ን!

❤156👍37🥰26👎4👏4
የኢትዮጵያ ሙዚቃ በዓለም ጆሮዎች...
ድምጻችን በዓለም እየተሰማ ነው። "ናዕት" አርባ ሺ Subscribers፣ ከ90 ሺህ በላይ መውደዶች እና ከአንደ ሚሊየን በላይ ተመልካቾችን በአስራ ሰባት /17/ሰዓታት ውስጥ ብቻ አግኝቷል። ይኽ የህዝብ ድምጽ የሆነው የክቡር ዶ/ር ቴዎድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮ/ አዲስ ሙዚቃ ዓለማችን ላይ በዚህን ሰዓት በስፋት እየተደመጡ ካሉ ሙዚቃዎች ውስጥ የሁለተኛ ደረጃነትን የያዘ ሲሆን በዘመናዊ የሙዚቃ ማድመጫ ድረገጽ /You Tube/ ላይ ከእራሱ ከቴዲ አፍሮ በቀር በኢትዮጵያ በዚህ ፍጥነት የተደመጠ ሙዚቃ በፍጹም የለም።
ናዕት /እያመመው ቁ፪/ ሙዚቃ ገና 24 ሰዓት ሳይሞላው በዚህ ፍጥነት በዓለም ደረጃ መዳረስ መቻሉ እጅግ ሊደነቅ የሚገባ ክስተት ነው። የህዝብ ድምጽ ሁሌም ኃያል ነው። ናዕት የኢትዮጵያውያን ድምጽ ነው። እንደ አገር ከገባንበት ማጥ ለመውጣት እንደ ዜጋ ከተረገጥንበት ትቢያ ለመነሳት እንዲህ ያሉ አስገምጋሚ ድምጾች ያሹናል። እንደ ሰማይ ማስገምገም እንደ ነጋሪት ጉሰማ የአምባ ገነኖችን ልብ የሚያሸብር የነፍስ ጩኸት።
✎✍#ታታ_አፍሮ /ነፃ ብዕር/
አሁንም ከፍ ብሎ ይደመጥ
የሚያዜም ይመስላል ሲያጣጥር ተጨንቆ
ውስጡን ሲሰብቅለት ኡ... እያለ ማሲንቆ
ኡ...ኡ...
https://youtu.be/1hMVeENjVew

❤159👍59🥰29🔥17👏4