Telegram Web Link
ሚሊዮን ፍቅር በአንድ ልብ። ♥️

ሀገሬን እወዳለሁ ካልክ በትንሽዬ ቀበሌ ውስጥ የሚኖሩ ምስኪን ወገኖችህን በእውነተኛ የመውደድ ስሜት መውደድ ይጠበቅብሃል። ምክኒያቱም ሀገር ያለነሱ ትንሽዬ ተሳትፎ ከወርቅነት ወደ መዳብነት ታንሳለች። (ሙሉ አይደለችም።) ወገኔን እወዳለሁ ስትል የፍቅርህ እውነትነት የሚጸናው በሙዚቃህ ዳንኪራ የሚረግጠውን (የሚዲያ ተደራሽነት አግኝቶ ማንነትህን የለየውን በመውደድ ብቻ ሳይሆን) ከተፈጠርክበት አፈር ተፈጥሮ ነገር ግን ማንነትህን ፈጽሞ የማያውቀውን ባላገር ጭምር ለመውደድ ብቁ ስትሆን ነው። (እንደ ቴዎድሮስ ካሳሁን።)

መቶ ሚሊዮን ህዝብ ምልክታችን ነህ ብሎ ከፊት ያሰለፈው የኔው ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ጠጋ ብለ ‘ይሄ ድሃ ህዝብ ምንህ ነው?’ ብትለው “ወገኔ ለኔ ክብሬና ኩራቴ ነው ለዚህ ህዝብ ሁለት ነፍስ ቢኖረኝ ሁለቱንም ነፍሴን ለመስጠት አልሰስትም ይልሃል።”

ነፍስህ በጥበብ ስትመላ የድሃ ወገኖችህ እንባ አያስተኛህም። ሀዘናቸውም ሰላም ይነሳሃል። ምክኒያቱም ጥበብ ከግብዝነት መንፈስ የራቀች ነች። ቴዲ አፍሮ ደግሞ ለዚህ ህዝብ ዋጋ ከፍሏል። ታግሏል፣ ታስሯልም። ስለዚህ ሚሊዮኖች በአንድ ልብ ይወዱታል! እሱም ሚሊዮኖችን በአንድ ልብ ይወዳል። ♥️

#ታታ_አፍሮ (ነፃ ብዕር)
ቢቂላ ሽልማት (Bikila Award 2024)

በሀገራችን እንቁ አትሌት የተሰየመው “ቢቂላ አዋርድ” ትልቅ ክብር ከሚሰጣቸው የሽልማት ተቋሞች ውስጥ አንዱ ሲሆን እስካሁንም ለበርካታ የሀገር ባለውለታዎች እውቅናን በመስጠት ሲሸልም ቆይቷል። ቢቂላ ሽልማት (Bikila Award) ከሀይማኖታዊ፣ ፖለቲካዊ እና ከምንም አይነት ትርፍ እራሱን ባገለለ መልኩ በካናዳ ከ50 አመታት በላይ በኖሩ ኢትዮጵያውያን ነው የተቋቋመው። ይህ ተቋም በትምህርታቸው፣ በንግዳቸው፣ በሙያቸው ብሎም በበጎ አድራጎት ስራ ተሰማርተው ልዩ ስኬት ያስመዘገቡ እና አርአያ የሆኑ ኢትዮጵያውያንን በየአመቱ በመሸለም እውቅናን የሚሰጥ ትልቅ ኢትዮጵያዊ መድረክ ነው።

በዚህ አመት አስረኛ (10) የምስረታ በአሉን የሚያከብረው የቢቂላ አዋርድ ተቋም፥ መስከረም 11 (21 September 2024) በሚያደርገው መርሃ ግብር ላይ በሙዚቃው ዘርፍ በዚህ አመት የሚሸልመው የግጥምና የዜማ ደራሲ ብሎም የሰብአዊ መብት ተሟጋች የሆነውን የክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁንን መሆኑን በህጋዊ ድህረገጾቹ በይፋ አሳውቋል።

አርቲስቱም በዕለቱ በዚህ ግዙፍ መርሃግብር ላይ በመገኘት ሽልማቱን እንደሚቀበል ተገልጿል።

#ታታ_አፍሮ (ነፃ ብዕር)
በሀገር ውስጥና በመላው ዓለም ለምትገኙ የክርስትና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያውያን ወገኖች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሳችሁ።

መልካም በዓል።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
ፍቅር ያሸንፋል!
ቴዎድሮስ ካሳሁን
(ቴዲ አፍሮ)
ከ10 አመታት በኋላ በTroxy Music Hall ቴዲ አፍሮ 💪🔥

በሀገረ እንግሊዝ ግዙፍ የመድረክ ሥራዎች ከሚካሄድባቸው ጥቂት የሙዚቃ ፌስቲቫል ማቅረቢያ ቦታዎች ውስጥ Troxy Music Hall (ትሮክሲ የሙዚቃ አዳራሽ) አንዱ ነው። ይህ ታሪካዊ የጥበብ አዳራሽ ግዙፍ አዳራሾችን በመገንባት በሀገሪቷ ትልቅ እውቅናን ባተረፈው አርክቴክት ጆርጅ ኮልስ እ.ኤ.አ በ1932 ዓመተ ምህረት የተገነባ ነው። Troxy Music Hall (ትሮክሲ የሙዚቃ አዳራሽ) በእንግሊዝ ሎንዶን ከተማ ውስጥ የሚገኝ ግዙፉና እድሜ ጠገብ ዘመናዊ አዳራሾች መካከል አንዱ ነው።

በዚህ ግዙፍና ታሪካዊ የሙዚቃ አዳራሽ ውስጥ የዓለማችን አንጋፋ እና ተፅዕኖ ፈጣሪ አቀንቃኞች የመድረክ ስራዎቻቸውን አቅርበውበታል። ከነዚህም ውስጥ በእንግሊዝ የሙዚቃ ሰንጠረዥ ላይ በነጠላ ዜማ አንደኛ ደረጃን በመያዝ ቀዳሚዋ ሴት የሆነችው ትውልደ እንግሊዛዊቷ የሶሎ ሙዚቃ አቀንቃኟ ሊታ ሮዛ ተጠቃሽ ስትሆን ሌሎችም ምዕራባውያን እና ነጭ አሜሪካውያን ጥበበኞች ለበርካታ አመታቶች ስራዎቻቸውን አቅርበውበታል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ጥቁሮችም በመድረኩ መታየት ጀምረዋል።

እነሆ ከአፍሪካ ኢትዮጵያን በመወከል ለመጀመሪያ ጊዜ እውቁ የኪነጥበብ ባለሙያ የክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) “ፍቅርን እንጋራ” በሚል መሪ ቃል የሙዚቃ ስራዎቹን February 1/2025 የሚያቀርብ ይሆናል።

የክቡር ዶክተር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ለመጨረሻ ጊዜ በሎንዶን ከተማ የሙዚቃ ስራውን ያቀረበው እ.ኤ.አ በJuly 25/2015 ነበር። እነሆ ከ10 አመታቶች በኋላ በሚዘጋጀው በዚህ ታላቅ የሙዚቃ ድግስ ላይ ከኢትዮጵያ፣ ከአሜሪካ እና ከአውሮፓ ግዛቶች የቴዲ አፍሮ አድናቂዎች የሙዚቃ ኮንሰርቱን ለመታደም ይገኛሉ።

#ታታ_አፍሮ (ነፃ ብዕር)
2025/07/03 04:12:56
Back to Top
HTML Embed Code: