Telegram Web Link
ደሞ በአባይ የተሰኘው የቴዲ አፍሮ ሙዚቃ ዛሬ አንድ ወር መሙላቱን ተከትሎ 22 አከባቢ ሰማዐትነትን የተቀበሉ ወንድሞቻችን ሚሊዮን እና ሚኪያስን ለማሰብ እና ለማስታወስ በመፈለግ አዲሱ 22 የታነጸውን የቅዱስ ገብርኤልን እና የቅድስት አርሴማን ምርዓበ ሰማዕታት ቤተ ክርስቲያን ተሳልመን ቀኑን አስበን ወለናል። ከዚሁ ጋ ተያይዞ የዛሬ ስድስት አመት ሰበዓ ደረጃ የተሰኘው ሙዚቃ የተለቀቀበት ወቅት በመሆኑ ያንንም አስበን ውለናል።

ማን ዝም ይላል ሆኖ ዜጋ ደሞ በአባይ...
/እጅ አንሰጥም በአባይ/

#ቼ_በለው
#ደሞ_በአባይ
#ቴዲአፍሮ

https://youtu.be/btuC2IfwmfQ
✔️አንተ ከግዜ እኩል አትራመድም። ምክኒያቱም ግዜን ቀድመኸው ሄዳኃል።
✔️ባንተ ፊት "የግዜ እንጂ የሰው ጀግና የለውም" ይሉት ፈሊጥ ትርጉም የለውም። ምክኒያቱም በጀግና ግዜ ላይ ሰልጥነሃል። ድልም ተቀዳጅተኃል።
✔️አንተን የሰሞንኛ ቀውስ፤ ለይስሙላ የተሽቀረቀረ የፖለቲካ እንፋሎት አያገኝህም። ውቂያኖሱም አይደንቅህም። ምክኒያቱም አንተ ከጥንት ዘመን ጥበብን የተቀዳጀኸ ማስተዋልን የተቀባህ ንጹህ ፍጡር ነህ።
✔️በእጅህ ደግነት እንጂ ስስት የለም። ከአንደበትህ መልካም እንጂ ክፋት አይወጣም። ከልብህ ፍቅር እንጂ ጠብ የለም።
✔️ዘውትር ለጥበብ ትደክማለኽ! የዛሬ 19 ዓመት የቋጠርከው ቅኔ ሰሙ እንጂ ወርቁ ሳይፈታን ይኸው ዛሬ ማለዳ ከጆሯችን እንደመጣ ከ6,840 ቀናት በኋላም አዲስ ሆኖ ያስደስተናል።
✔️ብዙ አውቀኽ በብዙ ተከብረኽ "እኔ ልቅደም እኔን እዪኝ" ሳትል ዝቅ ብለክ ከኋላ ሆነ ተናንሰህ የምትኖር ምስጉን ነህ።
✔️በድግስ ሲጠብቁህ ለማህተሙ ሲል ከወደቀ ሰማዕት ቤት ትገኛለኽ።
✔️ድሃ ተገፋ ቢሉህ እኔ ልጎሳቆል ብለ ትደርስለታለ።
✔️ባካበትከው ዝና እኛን ሳትረሳ ከእኛው እኩል በእኛ ሀዘን ቆዝመ አንሰክ እኛን ሆነህ የኖርክ ወገናችን ነህ።

አንተን መግልፅ የሚችል አቅም ቢኖረኝ ነፍሴን አስደስታት ነበረ። ግና አንተም አትገለፅ እኔም አቅሙ የለኝ። ብቻ ስላንተ በኔ ልብ ካለው መውደድ እና በኔ ልብ ካለው ፍቅር ቃሉ የሚቀራረብ ደረጃውም ከፍ ያለ ነውና አንተን እንደኔ እወድኃለው!! እንደ ራሴ እሳሳልሃለሁ!!
👍1
Forwarded from Amleset Muchie
የደን አፀድ ጌጥ የሶሪት ላባ
ማን አበቀለሽ መኃል አዲስ አበባ

የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://www.tg-me.com/Amlesetmuchie/
2025/07/10 11:41:59
Back to Top
HTML Embed Code: