Telegram Web Link
ቴዲ አፍሮ ከቦብ ማርሌ እና ከዚጊ ማርሌ ጋ ባለሙያዎችን እንደተጋራ ያውቃሉ?
ካወቁ መልካም ያላወቁ እንደው ለአገራችን ሙዚቀኞችም ጥሩ መነቃቃትን ይፈጥራልና ነገሩን ላጋራችሁ። የምነግራችሁ ነገር ለኢትዮጵያ የሙዚቃ እድገት ትልቅ ምክኒያት ይሆናል። የአገራችን ሙዚቃም የሆነ የኪነ-ጥበብ ሰው ምን ያህል ርቆ መጓዝ እንደሚችልም ያመለክታል።

የቦብ ማርሌን ቅንብሮች የሚሰራው ክሪስ ብላክዌል የተባለው የዓለማችን አንጋፋው እና እውቁ አቀናባሪ ከቴዲ አፍሮ ጋ ተገናኝቶ ለቴዲ አፍሮም አድናቆቱን ገልጾለታል። ይኼ የሆነው አቦጊዳ አልበም እንደወጣ ቴዲ አፍሮ ለመድረክ ስራ አሜሪካን አገር በሄደበት ወቅት ነበር።

ሌላው ዚጊ ማርሌ እራሱ ፈልጓቸው መጥቶ አብረውት ይጫወቱ ከነበሩ ኢትዮጵያዊ ሙዚቀኞች ውስጥ ሩፋኤል የተባለውን ድራመር የአቦጊዳ ባንድ አባል ያደረገው ሲሆን አሁንም አብሮት ያለ ትልቅ ድራመር ነው። በተጨማሪም ከዚጊ ማርሌ ጋ አልበም ሰርቶ ሁለት ግራዊ አዋርዶችን ያነሳው ሁሉንም የሙዚቃ መሳሪያ ከሚጫወተው ከዝነኛው አቀናባሪ ደረጄ መኮንን ጋ ስራ ጀምረው መኮንን ህይወቱ በማለፉ ምክኒያት ሊቀር ችሏል። በነገራችን ላይ ሩፋኤል ወልደ ማሪያም ከነ-ዚጊ ማርሌይ ጋ አብሮ ግራሚ ያነሳ አንጋፋ ድራመር ነው።

አሜሪካ ላይ ትልቁ የሬጌ ክለብ ዋይልድ የሚባል ነው። እዚህ ክለብ ውስጥ በወቅቱ እነ ዚጊ ማርሌ እየሄዱ ይዘፍኑበት የነበረ ሲሆን ቴዲ አፍሮ በልጅነቱ 120 በተሰኘ የቲቪ ፕሮግራም ላይ ስለ ክለቡ ግዙፍነት ሰምቶ አንድ ቀን እዛ ሄዶ ለመጫወት ተመኝቶ ነበር። ምኞቱም ተሳክቶ ከዛው የባንድ አባል ውስጥ ብቁ ያለውን መርጦ በአፍሪካ ብቻ ሳይሆን በዓለም ላይም ተወዳዳሪ የሆነ ግዙፍ ባንድ መመስረት ችሏል። ዋይልድ ክለብ ላይ የተጫወተ አንድ የጀማይካዊ ዘፋኝ አገሩ ሲገባ ስለዛ ሁኔታ ሲያወራ በትግል ሜዳ ላይ ጠላቶቹን የማረከ ያህል በኩራት ሆኖ ነው።

ሌላው የቦብ ማርሌን ላንድ-ሮቨር መኪና እየነዳ የቦብ ማርሌን ሙዚየም ያቋቋመው በዓለም አቀፍ ደረጃ የአርቲስቶች ማናጀር የሆነው አዲስ ገሰሰ የመጀመሪያው የቴዲ አፍሮ ማናጀር የነበር ሲሆን ለአስር አመታትም አብረው ሰርተዋል። ይኼ ሰው በቦብ ማርሌ ቤተሰብ ውስጥ ኢትዮጵያዊ በመሆኑም ጭምር ትልቅ ክብር የሚሰጠው ሰው ነው። እንዲሁም የቦብ ማርሌን የታክስ ወረቀት ይሰራ የነበረው ግለሰብ በተመሳሳይ ሁኔታ የቴዲ አፍሮን የታክስ ወረቀት ይሰራ ነበር። ሌላው በቦብ ማርሌ በተቋቋመው "ታፍ ጎን" በተሰኘው የቦብ ቤተሰብ የሙዚቃ ስቱዲዮ ውስጥ "ደሞ በአባይ" የተሰኘውን ነጠላ ዜማ የቀዳ ሲሆን የዚህን ሙዚቃ ሚክስና ማስተሩንም እዛው አሰርቶት ነበር። ሆኖም ግን ወደ ህዝብ ሚክስ ሆኖ የወጣው በራሱ በቴዲ አፍሮ የግል ስቱዲዮ ውስጥ የተሰራው ዘፈን /Track/ ነው።

በእርግጠኝነት ከጠቀስኳቸው ነጥቦች ውስጥ በዚህ ልክ ይኼንን እድል ያገኙ አልያም ያለሙት አርቲስቶች ስለመኖራቸው እጠራጠራለሁ። ቴዲ አፍሮ ግን ማሰብ ብቻ ሳይሆን መዳሰስና መጨበጥም ችሏል። በነገራችሁ ላይ በዲጄ ከሚጫወቱ አርቲስቶች ይልቅ ከባንድ ጋ የሚጫወቱ አርቲስቶች የሙዚቃ ችሎታቸው እጅግ የላቀ ነው።

#ታታ_አፍሮ /ነፃ ብዕር/

ከታች የተቀመጠውን ሊንክ በመጫን የዩትዩብ ቻናሌን እንድትቀላቀሉ እጠይቃለሁ።

https://youtube.com/channel/UCQKyrC0xnEk1KhSQqrv2JBg
ለውዴ ውዱ ነሽ

በጎደለ ሞልተሽ፤ በጠፋው ተክተሽ፣
ሲዝል አበርትተሽ፤ ግራውን ደግፈሽ፣
የብቸኝነት ጉዞውን፤ በጥንድ ቀይረሽ፣
ባብሮነትሽ አጅበሽ፤
ሙሉ አደረግሽው፤ መልኩን አሳቅፈሽ
እራሱን ደግመሽ፣ እራስሽን ደግመሽ።

መኑ ከመ ሄዋን፤ እንደ ሚካኤል እናት፣
መኑ ከመ ሄዋን፤ እንደ ብሩክቲ እናት?
ሁሌም አብራው ያለች፤ እየሆነች ብርታት፣
ለብላቴናው ክብሩ፤ ለልቡም ዘውድ ናት።

እንደ ግጥሜ ርዕስ፤ እንደ ስንኝ ቋጠሮ፣
እንደ ጠቢብ ቅኔ፤ እንደ ፀሐይ ኑሮ፣
ልብሽ ብሩህ ነው፤ ዘውትር የሚፈካ፣
መልክሽ በለስ ነው፤ ውዴ ባንቺ 'ረካ።

የሰጠሽው ፀጋ፤ የሰማይ ላይ መና፣
ከምድር ሃመልማል፤ የፈካ ነውና፣
ልቡን ፍቅር ሞላው፤ ደስታውም አበበ፣
ለውዴ ውዱ ነሽ፤ በመልክሽ ተዋበ!

እንደ ከዋክብ ብዙ፤ እንደ ጀምበር ውብ፣
አንድ ሰው እልፍ ነው፤ ከተቸረው ልብ!!
አንድ ሳለሽ ብዝተሽ፤ ሁሉን የሆንሽለት፣
ጤና ይስጥሽ አምላክ፤ ዘላለም ኑሪለት!

እንደ ምድር አሸዋ፤ እንደ አባይ ጅረት፣
አንድ ሰው ብዙ ነው፤ ፍቅር ከሞላበት!
በዝተሽ አበዛሽው፤ በርተሽ አፈካሽው፣
ከፊትም ከኋላም፤ በሁሉም ከበሽው።

#ታታ_አፍሮ /ነፃ ብዕር/

የዩትዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ በማድረግ ይወዳጁን
👍

https://youtube.com/channel/UCQKyrC0xnEk1KhSQqrv2JBg
ሞዴል፣ የፊልም ተዋናይት፣ ዳይሬክተር፣ የማስታወቂያ ባለሙያ እና ደራሲ እንዲሁም የሶስት ልጆች እናት የክቡር ዶ/ር ቴዎድሮስ ካሳሁን /የቴዲ አፍሮ/ ባለቤት። አምለሰት መጬ

https://youtube.com/channel/UCQKyrC0xnEk1KhSQqrv2JBg
"ገጥሞሽ የሳባ ሞገስ የኪሊዮፓትራ
አምረሽ ትታዪ ጀመር በራስሽ ተራ
በዓለም የውበት ፀሐይ ወቶ እንደገና
ባንቺ ዘመን ላይ ዋለ ዛሬ ቁንጅና
ያንስብሻል መባል ቆንጆ የማር ክዳኔ
ከንፈርሽ ላይ ሰም አለ ወርቅ የፍቅር ቅኔ
ያንስብሻል የኔ መልካም የአመል ሙዳይ
ሰው አለ ወይ ውብ እንዳንቺ ፀባየ ሰናይ..."

https://youtube.com/channel/UCQKyrC0xnEk1KhSQqrv2JBg
የቴዲ አፍሮ #አርማሽ የተሰኘው ሙዚቃ ነገ ይለቀቃል...
ቀና በል!

ለመላው የቴዲ አፍሮ አድናቂዎች እና ለኢትዮጵያውያን በሙሉ ይኼንን ፎቶ ፌስቡክን ጨምሮ በሁሉም የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ላይ የProfile ፎቶ /የፊት ገጽ ምስል/ እንዲሆን አዘጋጅተናል። ዓላማው አንድ ጠንካራ ህዝብ አንዲት ኢትዮጵያ ነው። ይኼ መልዕክት ለመላው የዓለም ህዝብ እኛ ኢትዮጵያውያን በአገራችን እና በሰንደቅ ዓላማችን የማንደራደር ቆራጥ ዜጎች ስለመሆናችን የምንገልጽበት ታላቅ አጋጣሚ ነው። አባቶቻችን በአንድነታቸው ጠላትን አጥፍተው ወራሪን አንበርክከው ያቆዩልንን አገር እኛም በክንዳችን አንድ አድርገን ለመጪው ትውልድ የምናስተላልፍ እንጂ ስትፈርስ ከአፍራሽ ሀይሎች ጋ የምንተባበር አይደለንም። ቀን እስኪያልፍ የአባትህ ባሪያ ይግዛ የሚሉት ቢህልም በዚህ ዘመን ዋጋ የሚሰጠው አይደለም። ይልቁንም ክንዳችን እንደ አፄ ቴዎድሮስ ክንድ የሚፋጅ ስለመሆኑ ለማረጋገጥ በአንድነት ቆመን በዓለም ዙሪያ ያሉ ጠላቶቻችን እንፈጃቸዋለን። /እናሳፍራቸዋለን!/ ይኼንን ሀሳብ በላቀ መልኩ የሚገልጽ ብሔራዊ አንድነታችንን የሚሰብክ ለዓለም ህዝብም ኢትዮጵያ ማለት ሉዓላዊት አገር ስለመሆኗ የሚያስረግጥ ታላቅ ሙዚቃ ነገ ጥቅምት 24/2014 ዓ.ም በቴዲ አፍሮ ህጋዊ ዩትዩብ ቻናል ላይ ይለቀቃል።

ከታች የተቀመጠውን ሊንክ በመጫን የቴዲ አፍሮን ህጋዊ የዩትዩብ ቻናል Subscribe ያድርጉ!
https://youtube.com/c/TeddyAfroOfficial

ፎቶውን በሁሉም ስፍራ ላይ
ከሚከተሉት ሀሽታጎች ጋ ይለጥፉ

#አርማሽ #ቀናበል

#ታታ_አፍሮ /ነፃ ብዕር/
Channel photo updated
"እኔማ ላይሽ በቶሎ ምኞት ነበረኝ
ግን ባባሁ ናፈኩሽና እንባ ቀደመኝ
እኔማ አለሁ እስካሁን ተስፋ ሰንቄ
በወንዜ ባገሬ እያለሁ አገር ናፍቄ..."

ይኼ እልፍ መልዕክት ካላቸው የግጥም ስንኞች መኃል አንዱ ነው። ከዜማው ጋ ላደመጠው ደግሞ አቅምን ይነሳል!
ባገሩ እያለ አገር አልባ ለሆነው ምስኪን ህዝብ... በጦርነት፣ በሽብርተኞች እና በፖለቲከኞች ቁማር ሰላሙን ላጣ፤ እኔን ባይ ለሌለው መከራውን በጫንቃው ተሸክሞ ለሚዞር ምስኪን ህዝብ ትልቅ ትርጉም አለው።

የልባችንን ህመም በልኩ ማዜም ላንተ ብቻ ይቻልኃል። ምክኒያቱም የወገንህን የህመም ጥልቀት ትረዳለ። በህመማችን ማዘን ሳይሆን አብረኸን ትታመማለ! በቁስላችን "እኔን" ማለት ብቻ ሳይሆን ነፍስህ አብራን ትቆስላለች! ይኼንን እውነት ደግሞ የዜማክ ፍሰት እና የግጥምህ ድርድሮች በሚገባ ይገልጹታል...!

አላየሁም፣ አልሰማሁም፣ አልችልም ብለ ለወገንህ ጀርባ የሰጠኽበት ቀን የለም። አገርህ በፈለገችህ ቀን አጉድለህባት አታውቅም።

በብዙ እ...ን...ወ...ድ...ኃ...ለ...ን...!

#ታታ_አፍሮ /ነፃ ብዕር/
አርማሽ (ቀና በል)

አርማሽ ይውለብለብ ከደጄ
ልቤ ናፍቆሻል ወዳጄ
እኔስ እስካይሽ ጨነቀኝ
ሀገሬ መምጫሽ ናፈቀኝ
ቀን እየሄደ ቀን መጣ
ልቤ ከሀሳብ ሳይወጣ
መጥታ ታብሰው እንባዬን
ሀገሬን ጥሯት አርማዬን

መቼም ከዚህ ምድር ላይ ሄዶ ነው ሁሉም ቀሪ
ሀገራ ናት ቋሚ ሰንደቀ ለዘለዓለም ኗሪ
ትላንትም እንደ ጀምበር እያዩት ከዐይን ይርቃል
ኢትዮጵያ እንድትመጪ ስንት ቀን ይበቃል...?

እኔማ ላይሽ በቶሎ ምኞት ነበረኝ
ግን ባባሁ ናፈኩሽና እንባ ቀደመኝ
እኔማ አለሁ እስካሁን ተስፋ ሰንቄ
በወንዜ ባገሬ እያለሁ አገር ናፍቄ...

ወተሽ በምስራቅ አንቺ የዓለም ጀምበር
አንድ አርጊንና ጠላትሽ ይፈር
የቦረኩበት በልጅነቴ
የያኔው መልክሽ ብቅ ሲል ፊቴ
እየመለሰኝ ወደ ትላንቱ
ናፍቆኝ በብርቱ ትዝ አለኝ የጥንቱ

አርማሽ ይውለብለብ ከደጄ
ልቤ ናፍቆሻል ወዳጄ
እኔስ እስካይሽ ጨነቀኝ
ሀገሬ መምጫሽ ናፈቀኝ
አገር ለክብሩ ሲጣራ
ከፍ ያደረገው ባንዲራ
ዘመም ሳይል ቀን ጎሎ
ባክሽ ኢትዮጵያ ነይ ቶሎ

ብዙ ነሽ አንቺ አገሬ የሞላሽ ታምራት
ምኩራብሽ የተፈራ የነጻነት ቤት
የአርበኞች የድል ችቦ ለትውልድ እንዳበራ
መኖር ለአገር ሲሆን ሞትም አያስፈራ

እኔማ ላይሽ በቶሎ ምኞት ነበረኝ
ግን ባባሁ ናፈኩሽና እንባ ቀደመኝ
እኔማ አለሁ እስካሁን ተስፋ ሰንቄ
በወንዜ ባገሬ እያለሁ አገር ናፍቄ...

አመት አውዳመት ድገመን ሲሉ
ልጆች በቀዬው ችቦ እያበሩ
መስቀል ፋሲካው ኢድ እንቁጣጣሽ
አውዳመት አይሆን አንቺ ካልመጣሽ
ዘመን አድሰሽ በፍቅር ቀለም
ብቅ በይ ኢትዮጵያ ሁኚና መስከረም

ሆነሽ መስከረም....."አሲዮ"
ብቅ በይና.............."ቤሌማ"
እንበል አሲዮ..........."አሲዮ"
ናና በሌማ..............."ቤሌማ"
ብቅ በይና..............."አሲዮ"
ሆነሽ ሙሽራ............"ቤሌማ"
ይብቃን ስደቱ............"አሲዮ"
ስቃይ መከራ............."ቤሌማ"
ቤሌ ቤሌማ..............."አሲዮ"
ናና ቤሌማ................."ቤሌማ"
ዘር ያበቀለው .............."አሲዮ"
ታጭዷል መከራው......."ቤሌማ"
የኢትዮጵያዊነት............"አሲዮ"
አሁን ነው ተራው..........."ቤሌማ"
ኢሲዮ አሲዮ.................."አሲዮ"
ናና በሌማ....................."ቤሌማ"
ዘመን አድሰሽ................."አሲዮ"
በፍቅር ቀለም................."ቤሌማ"
ብቅ በይ ቦጢያ.............."አሲዮ"
ሆነሽ መስከረም............."ቤሌማ"

እኛስ ከመንገድ ላይ ጠፍተን መች አወቅነው
ብንሔድ ብንሔድ አንደርስም ገና ነው
በመባረኪያችን ከመንገድ ላይ ዝለን
አይበቃም ወይ ማሳል በዘር ጉንፋን ታመን
በዘር ጉንፋን ታመን
ቀን አለቡ............................."አለ ገና"
ቀን አለ ገና..........................."አለ ገና"
አለ በሉ.................................."አለ ገና"
ቀን አለ ገና............................."አለ ገና"
ለኢትዮጵያውያዊነት ቀን አለው ገና

ስምሽን በክፉ ያነሳሽ ጠፍቶ
አርማሽ ከፍ ሲል ሰማይ ላይ ወቶ
እኛ ልጆችሽ ልናይ ቆመናል
አንድ ቀን መጥቶ አንድ ያደርገናል
ቀን አለ በሉ................................"አለ ገና"
ቀን አለው ገና.............................."አለ ገና"

ስንቱ ተሰደደ ይብቃን ሀዘን ለቅሶ
አንድ ሆነሽ ኢትዮጵያ ባየን ፍቅር ነግሶ
ዘር ያበቀለው ታጭዷል መከራው
የኢትዮጵያዊነት አሁን ነው ተራው

ቀና በል አሁን........................"ቀና በል"
ቀና በል ቀና.........................."ቀና በል"
የጀግኖቹ ልጅ........................"ቀና በል"
አንተ ነህና............................."ቀና በል"
ከአገር ወዲያ ሞት.................."ቀና በል"
ሞት የለምና..........................."ቀና በል"

ዝም ያለ መስሎ ኢትዮጵያዊነት
ማንም አይገታው የተነሳ ዕለት

ቀናበል አሁን..........................."ቀና በል"
ቀና በል ቀና............................"ቀና በል"
ጥንት አባቶችህ......................."ቀና በል"
ያቆዩትን.................................."ቀና በል"
ከፍ አርገ ይዘ ..........................."ቀና በል"
ባንዲራህን................................"ቀና በል"
ቀና በል አሁን............................"ቀና በል"
ቀና በል ቀና.............................."ቀና በል"

ዜማ እና ግጥም የክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮ /
እንዲሁም ተጨማሪ ዜማዎች የሀገረሰብ...

#አርማሽ #ቀናበል
2025/07/01 01:44:17
Back to Top
HTML Embed Code: