Telegram Web Link
#ቀናበል ቲሸርት

ይኼንን ትሸርት የፈልጋቹ አዲስ አበባ የምትገኙ ሀያ ሁለት ጎላጎል አከባቢ ከቦሌ ታክሲ መያዣ ወረድ ብሎ ፓሪስ ካፌ ፊትለፊት ታገኙናላችሁ። ከአዲስ አበባ ውጪ የምትገኙ አልያም ከኢትዮጵያ ውጪ ለምትገኙ በጠቅላላ ያላችሁበት አገር በፖስታ ቤት ይላክላችኋል። ለበለጠ መረጃ ከታች የተቀመጠውን የስልክ አድራሻ ተጠቀሙ።

የቲሸርት ዋጋ 350 ብር

#ማሳሰቢያ

አብዛኛው የታተሙ ሳይዞች እያለቁ ስለሆነ ከታች በተቀመጠው የቴሌግራም ወይንም Whats App አድራሻ በውስጥ መስመር የምትፈልጉትን ሳይዝ ማዘዝ ትችላላቹ። ትሸርቱ ጥራቱን የጠበቀ ህትመቱ በፍጹም በእጥበት አልያም በሌላ ምክኒያት የማይለቅ ነው።
በትሸርቱ ላይ ከፊት "ቀና በል" አርማ ከጀርባ ደግሞ የቴዲ አፍሮ ምስል ይገኝበታል።

+251911979634
https://www.tg-me.com/NegusMultimedia
#ቀናበል

በስድስት ቀናቶች ውስጥ ብቻ 3 ሚሊየን አድማጭ!! ይኼ በኢትዮጵያ የዲጂታሉ ዓለም ሌላ አዲስ ሪከርድ ነው!
በነዚህ ቀናቶች 3 ሚሊየን አድማጭ፥ ከ82 ሺ በላይ አዲስ Subscribers እንዲሁም ከ129ሺህ በላይ መውደዶች ብሎም ዓለም ላይ በዩትዩብ ከተለቀቁ ሙዚቃዎች ውስጥ በወቅቱ እየተደመጡ ከሚገኙ 23 ሙዚቃዎች መሃል አንዱ ሆኗል።

ቀና ስንል ዓለም እኛን ያደምጠናል። አርማችንን ይዘን ሆ ካልን በዓለም ላይ አዲስ ታሪክ ይኖረናል።
ስለዚህ
የብላቴናውን ሙዚቃ እያደመጥክ........👉 "ቀና በል"
የአባቶችህን የድል አርማ ይዘህ........……👉 "ቀና በል"
ኢትዮጵያ አገርህ በክብር ታሸንፋለችና...👉 "ቀና በል"
የጀግኖቹ ልጅ አንተ ሐበሻውነህና..........👉"ቀና በል"
አገር ወዳድ ድንቅ ትውልድ ነህና............👉 "ቀና በል"
የጠላቶችህን ዛቻ የማትፈራ ነህና.........👉 "ቀና በል"
ጥቁር ኢትዮጵያዊ ነህና ደግመ ዳጋግመ👉 "ቀና በል"

አዎ በሳምንት 7 ቀን "ቀና በል" 💚💛

አሁንም ደግሞ ደጋግሞ ይደመጥ! ሺ ጊዜ፥ ኧረ ብዙ ዕልፍ ጊዜ ይደመጥ! ሼርም ይደረግ! ላይክ ይሰጠው...! የአገር ክብር የወገን ኩራት ነው! ብላቴናውን ለተረዳው እያነባ ዘፍኖ አገራችንን "ቀና" ነው ያደረገው።

#አርማሽ
https://youtu.be/PkOstq4GuLk

#ታታ_አፍሮ /ነፃ ብዕር/
@Binu_Graphics
#ቀናበል

''ሀገር ለክብሩ ሲጣራ
ከፍ ያደረግነው ባንዲራ
ዘመም ሳይል ቀን ጎሎ
እባክሽ ኢትዮጵያ ነይ ቶሎ...?

#አርማሽ
https://youtu.be/PkOstq4GuLk
#ቀናበል

አርማሽ የተሰኘው የክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን ሙዚቃ 4 ሚሊየን አድማጮችን በአስር ቀናቶች ሊያገኝ 300 ሺ አድማጮች ብቻ ቀርተውታል። አሁን ካለንበት ወቅታዊ ሁኔታ አንጻር ይኼንን ሙዚቃ ሁሉም ቢያዳምጠው ከስነ ልቦና አንጻር ትልቅ ለውጥ መፍጠር የሚችል ግዙፍ ሀሳብ የሰነቀ እጅግ ረቂቅ ሙዚቃ በመሆኑ በስፋት ተደረሽ እንዲሆን እመኛለሁ። ኢትዮጵያ ትፍረስ አልያም እየፈረሰች ነው ያሉ ሁሉ በዚህ ሙዚቃ ስሜታቸው መነካት ችሏል። ይኼ ደግሞ ትልቅ ተስፋ ነው። ሰላምን የሚወድ፥ የጦርነት ዜናን የሰለቸ፥ የብሔርተኝነት መንፈስ ያደቀቀውን አገራዊ ስሜት ሲመለከት የሚያዝን፥ የሰንደቅ አላማው ክብር ማጣት የሚያንገበግበው፥ የነጮችን ፉከራ መስማት የታከተ ሁሉ "አንድ ቀን መጥቶ አንድ ያደርገናል..." ሊል ይገባል። በአንድነታችን ውስጥ ዓለምን አደብ የሚያስገዛ ትልቅ ሀይል አለን።

ስለዚህ ሙዚቃ ከተለያዩ የኪነ ጥበብ ሰዎች ጋ ሳወራ ቴዲ አፍሮ ምን ያህል አስተዋይና ዛሬም ድረስ በአቋሙ የጸና ትልቅ አርቲስት መሆኑን አጫውተውኛል! አንዳዶቹ ደግሞ ቴዲ አፍሮ እነሱ ከገመቱት ፍጹም ተቃራኒ ሙዚቃ መልቀቁን ነግረውኝ በዚህ መልኩ መዝፈኑ እንዳስገረማቸው ለመረዳት ችያለሁ። ሙዚቃው ወደማንም የወገነ ባለመሆኑ ብቻ ሳይሆን የቀዘቀዘ የሚመስለውን አገራዊ ስሜት የሚቀሰቅስ ተስፋን የሚያጭር ሙዚቃ በመሆኑም ጭምር ተደስተውበታል። አብዛኛው የሙዚቃ አፍቃሪም ሆነ አገር ወዳድ የሆነው ወገናችንም ተሰመሳሳይ ስሜቱን በተለያየ መልኩ አጋርቷል።

ከዚህ ሙዚቃ መለቀቅ በኋላ እኔም ስለ ቴዲ አፍሮ የተዛባ ሀሳብ ሲነሳ እንደ-ወትሮው ስለሱ መሞገት ሳይሆን ቀድመው ከሞገቱኝ ሰዎች አንደበት ጭምር ቴዲ አፍሮ ትልቅ የኪነ-ጥበብ ሰው ስለመሆኑ የማዳመጫ ጊዜ ሆኖልኛል። ዛሬም ድረስ የኔ ቴዲ አፍሮ በቆምኩባቸው ሰዎች ፊትለፊት የሚያኮራኝን ተግባር እየፈጸመ ይገኛል። ለመንቀፍ ቃል ያላጠራቸው ቴዲ አፍሮን ሲረዱት ለማድነቅ አቅም አንሷቸው ሳይ ተደስቻለሁ። አገር መውደድ ስራን ማክበር ላመኑበት መጽናት እንደ ቴዲ አፍሮ የታፈረ ሰው ያደርጋል።

ሙዚቃው ከፍ ብሎ ከአጥናፍ አጥናፍ ይደመጥ!! ህዝቤም በተስፋ ቀና ይበል! በኢትዮጵያ እና በህዝቦቿ ላይ ጨልሞ የሚነጋ ቀን እንጂ እንደመሸ የሚቀር የመከራ ዘመን በፍፁም አይኖርም! የጥንቷ ኢትዮጵያ ትመጣለች!

መልዕክቱ ይዳረስ ዘንድ Share በማድረግ እንበርታ!

#አርማሽ

https://youtu.be/PkOstq4GuLk

#ታታ_አፍሮ /ነፃ ብዕር/
Channel photo updated
"ቀን እየሄደ ቀን መጣ
ልቤ ከሀሳብ ሳይወጣ..."

አገር ማለት ትርጉሙ ሰው መሆኑ ከገባኝ ዕለት ጀምሮ የሰው ልጅ ስቃይ ያስጨንቀኛል። ባነበብኳቸው የአገሬ ታሪኮች ውስጥም ሆነ በኖርኩበት ዘመን የአገሬ ህዝብ እረፍት አልባ መሆኑን ሳስብ ልቤን ይነደዋል።

ከቤት ወጥቼ ሰው የሚበዛበት ስፍራ ድንገት ብገኝ በየመንገዱ በድዊ ተመቶ ለህክምና ሳንቲም የሚለምን እልፍ ወገን አያለሁ። ማልዶ በብርድ የወጣ ምስኪን ታማሚ የጠዋት ፀሐይ እስከ ቀኑ ማምሻ ፈንጭታበት ማታ ለብርድ አጋፍጣው ስትሄድ እርሱ ከወደቀበት መሬት የሚነሳው ቸር እጆች የጣሉለትን ሳንቲም ሰብስቦ ወደ ድሃ ጎጆው ለመግባት ነው። ሌላው ደሞ የዕለት ጉርስ ያጣ እባካችሁ የዳቦ ስጡኝ የሚል ቁጥር ስፍር የለውም! በርሃብ ይሁን በኑሮ አለመመቻቸት የገረጣ ፊታቸው ሆድ ያባባል። ነገ ትልቅ አገር ያስቀጥላሉ የተባሉ ህጻናት በርሃብና በችግሮ ቆፈን ይሰቃያሉ። እኔ በቀን ሶስቴ ጥጋብ እስኪያስጨንቀኝ መመገቤ እንዲጸጽተኝ የሚያደርግ እልፍ ክስተቶች አጋጥመውኛል። 'ርቦኝ ለሰዓታት መታገስ የማልችል እኔ የራበው ሳይ ሰውነቴ ይደነግጣል። መቼ ነው ከዚህ ማጥ የምንወጣው እላለሁ።

አራስ እናት ፀሐይ ላይ ተቀምጣ ስትለምን አይቻለሁ። ቢሞላላት ጨቅላ ልጇን ተሸክማ ባልተንከራተተች። በመጦሪያቸው በምርኩዝ ተደግፈው ምፅዋት የሚጠይቁ እናቶች ብሎም አዛውንት አባቶችን አስተውያለሁ! ዓለም ላይ ከኛ በኋላ የነቁ አገራት የህክምና፣ የምግብ፣ የመኖሪያ ቤት ብሎም የአልባሳት ሁኔታ በፍፁም አያሳስባቸውም። እነዚህ እንደ ሰብዓዊ መብት የሚታዩ ጉዳዮች ናቸው። እኛ ግን በተጠቀሱት ነገሮች ፍፁም ስቃይ ውስጥ ነን። ሀይማኖቱ ያለው እኛጋ ባህልና ወጉ ያለው እኛ ጋ የምንራበውም የምንቸገረውም እኛው ነን። ይደንቃል እኮ!

የወገኔን ስቃይ አብራርቶ ለመፃፍ አቅሙ ቢኖረኝ ብዬ ተመኘሁ! አንዳዴ ከእምነቴ አንፃር ይሁን ከአቅሜ በላይ ስለሆነ፤ እራሴን ከጸጸቱ ለማዳን ባላውቅም "ከኔ በላይ ለፍጡራኑ የሚጨነቅ እግዚአብሔር አለ! እሱ እንደፈቀደ ነው የምንኖረው" እላለሁ እግዚአብሔር ግን የመከራ ኑሮን በእኛ በልጆቹ የማያጸና ቸር አምላክ እንደሆነ አውቃለሁ። ታዲያ ለምን ወገኔ ላይ መከራ በመከራ ላይ እየተደራረበ ትልቅ የችጋር ህንፃ ተገነባበት?

በዚህ መሰል ሀሳብ ለምብሰለሰል ለኔ "ቀና በል" የተሰኘው የቴዲ አፍሮ ሙዚቃ አንዴ ቁስሌን እያባሰ አንዳዴ ደግሞ እንደ መድኃኒት ሆኖ ቆጥቋጭ ስሜቴን እያስታገሰልኝ ይገኛል። የሰው ልጅ ተስፋ ባይኖረው ትውልድ ከአዳም ተስቦ ዛሬ ባልደረሰ ነበር። እኔም "ቀን እየሄደ ቀን መጣ
ልቤ ከሀሳብ ሳይወጣ"
ከሚለው የትካዜ ዜማ "ቀን አለ በሉ ቀን አለ ገና..." በሚለው አጽናኝ ዜማ በአገሬ መሰረታዊ የሆኑ ነገሮች እንደ ሰብዓዊ መብቶች ወደሚቆጠሩበት ዘመን እነጠቃለሁ። ለወገኔ ለአገሬ ያንን ቀን እመኛለሁ። ግን ያ ቀን ለኢትዮጵያ እስኪመጣ ኢትዮጵያም ለህዝቦቿ በረከቷን አንግባ እስክትመጣ ስንት ቀን ይፈጅ ይሆን...? ኢትዮጵያ እንድትመጪ ስንት ቀን ይበቃል...?

ይኼ ሙዚቃ ከተለቀቀበት ቅጽበት ጀምሮ ይኼንን ጽሁፍ እስካጠናከርኩበት እስከ አሁኗ ቅጽበት ያላዳመጥኩበት ቀን በፍጹም ትዝ አይለኝም።

#ታታ_አፍሮ /ነፃ ብዕር/

https://youtu.be/PkOstq4GuLk
አርማሽ የተሰኘው የክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮ/ ሙዚቃ በተለቀቀ በ25 ቀናቶች ውስጥ በዩትዩብ ብቻ ከ5 ሚሊየን ጊዜ በላይ የተደመጠ ሙዚቃ ሲሆን በዚህ ዓመት ከተለቀቁ ነጠላ ዜማዎችም ትልቅ ተቀባይነትን ያገኘ ሙዚቃ ለመሆን በቅቷል። እንደሚታወሰው ይኼ ሙዚቃ በተለቀቀበት ተከታታይ 5 ቀናቶችም ዓለም ላይ እየተደመጡ ካሉ 20-28 ሙዚቃዎች ውስጥ የተካተተ አንዱ ሙዚቃ ለመሆን በቅቷል።

የሙዚቃው ይዘትና ጭብጥ ሀሳብ እየደበዘዘ የመጣውን የኢትዮጵያዊነት ስሜት ማንቃት ላይ ያተኮረ ሲሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ እንደሌሎች የአፍሪካ አገራት ኢትዮጵያን ለማውደም ታጥቀው የተነሱ አካሎችን ኢትዮጵያዊነት ዝም ያለ /የደበዘዘ/ ቢመስልም በአንድ ልብ "ሆ" ብሎ የተነሳ ዕለት ምድር ላይ ያለ ምንም አይነት ሀይል እንደማይችለው አሳስቧል። አክሎም እንደ ጠላቶቻችን ሀሳብ አገራችን ፈራርሳ ሳይሆን ይልቁንም የዓለማችን ልዕለ ሀያል አገር ሆና አርማዋ ከሁሉ ከፍ ብሎ ሰማይ ላይ ሲውለበለብ ለማየት የቆምን መሆናችንን አስረግጦ የተናገረበት ሙዚቃ ነው። ያ ቀን ደግሞ ጊዜው አሁን መሆኑን ለዓለም ህዝብም ሆነ ለኢትዮጵያውያን ወገኖቹ ያበሰረበት ጭምር ነው።

ቀና በል አሁን ቀናበል ቀና
የጀግኖቹ ልጅ አንተ ነህና!

የአፍሪካ ጠላቶችም ሆኑ የኢትዮጵያ ጠላቶች ዳግም በኢትዮጵያ ክንድ ተንደው መውደቃቸው አይቀርም። ኢትዮጵያ በዳግማዊ አጤ ምኒልክ ዘመን የቀኝ ገዢዎችን ታግላ ጥላ ጥቁሮችን ያነቃች ኃያል አገር ነች። ዛሬም በእኛ ዘመን ለመላው ዓለም ኢትዮጵያውያን በአንድነት ቆመን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የጥቁሮችን እኩልነት አረጋግጠን የነጮችን የበላይ ነን ባይነት መንፈስ ቀብረን፤ ሁሉም ሰው በማንነቱ ተከብሮ እንዲኖር የሚያስችል ገድል የምንፈጽምበት ጊዜው ተቃርቧል። የአባቶቻችንን ገድል የምንደግመው እነሱ ያቆዩልንን ባንዲራ ይዘን ቀና ስንል ነውና ጥንት አባቶቻችን በፈጸሙት ገድል በመኩራት የዓለማችን ኃያላን አገራት የከፈቱብንን የዘመኑን ጦርነት በአንድነት መክተን ዳግም አፍሪካንና መላውን የጥቁር ህዝብ ከመጨቆን እንታደገዋለን። ይኼንን ገድል ደግሞ የመፈጸም ኃላፊነቱም ሆነ አቅሙ ያለን እኛ ኢትዮጵያውያኖች ነን። አባቶቻችን ይኼንን እውነት ፈጽመውት አልፈዋል። እኛም በዘመናችን እንደግመዋለን። ዓለም ላይ ያለውን እውነት የምንለውጥበት ቀኑ ተቃርቧል። አዎ የኢትዮጵያዊነት ተራው አሁን ነው።

ቴዲ አፍሮ ብቻ ሳይሆን በነጮች የተጨቆነች አፍሪካም "እባክሽ ኢትዮጵያ ነይ ቶሎ" እያለች ትገኛለች።

https://youtu.be/PkOstq4GuLk

#ታታ_አፍሮ /ነፃ ብዕር/
አርማሽ

አርማሽ የተሰኘው የአንጋፉውና የተወዳጁ ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ ሙዚቃ በአርቲስቱ ህጋዊ የዩትዩብ ቻናል ከተለቀቀ ዛሬ ህዳር 23 ቀን /2014 ዓ.ም አንድ ወር ሞላው። ይኽ ሙዚቃ ከተለቀቀበት ቅጽበት ጀምሮ በህዝብ ዘንድ ትልቅ ተቀባይነትን ማግኘት የቻለ በመሆኑ በአርቲስቱ በኩል ሊኖር የሚችል ማንኛውም አይነት ግምት ግቡን የመታ እንደሆነ አልጠራጠርም።

አገራችን ካለችበት ወቅታዊ ሁኔታ በፍጥነት ትላቀቅ ዘንድ ብሎም ህዝባችን ከገባበት አሰልቺና አዝጋሚ ከሆነ የህይወት ግብ ግብ በድል አድራጊነት ይላቀቅ ዘንድ የኪነጥበብ ባለሙያዎች በዚህ መልኩ የተቀነቀኑ ሙዚቃዎችን ማበርከታቸው እጅጉን መልካም ተግባር ነው። እንዲህ ያሉ ስራዎች የማህበረሰባችንን፣ በአመራር ደረጃ የተቀመጡ የህዝብ አገልጋዮችን፣ በጦር ግንባር ለኢትዮጵያ ክብር የሚዋደቁ ነፍጥ አንጋቢዎችንና በመላው ዓለም የሚገኙ የታላቂቷ ኢትዮጵያ ወዳጆችን ስሜት የሚያነቃና የመፍትሄ አቅጣጫ የሚጠቁም ብቻ ሳይሆን፥ ህዝብ በአንድ ልብ በአንድነት ፀንቶ ከቆመ፤ ሁሉም በተሰማራበት ሙያ ጊዜው የሚፈልገውን ተግባር በኃላፊነት ስሜት ከፈጸመ እንደ ህዝብም እንደ ሀገርም አሸናፊዎች እንደምንሆን አበክሮ የሚመሰክርና የሚያሳስብ ጭምር ነው።

የተለያዩ የአገራችን አርቲስቶች በወቅታዊው የአገራችን ጉዳይ ላይ ብዙ ስራዎችን በመስራት ወደ ህዝብ እያደረሱ የሚገኙ ሲሆን ሌሎችም በተመሳሳይ መልኩ ስራዎቻቸውን በማጠናቀቅ ላይ ይገኛሉ። የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ከምንም ጊዜው በላይ በዚህ ወቅት ህዝባቸውን የማነቃቃትና በግንባር የሚገኘውን የኢትዮጵያን ሰራዊት በቻሉት መልኩ እየደገፉ በመገኘታቸው ምስጋናዬን ላቀርብላቸው እወዳለሁ። ሁሉም በሙያው ይኼንን ተግባር እንዲፈጽምና የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያደርግ በታላቅ አክብሮት ለማሳሰብ እወዳለሁ።

እንደ አገር የተጫነብንን የሴራ ክምር ንደን ዳግም በአባቶቻችን መንፈስ ተሞልተን በአሸናፊነት ስሜት ቀና ብለን ልንቆም ግድ ይለናል። በአባቶቻችን ዘመን ያልተፈጸመ ሽንፈት በኛ ዘመን እንዲፈጸም አንፈቅድም። ምክኒያቱም እኛ የጀግኖቹ ልጆች ነን። እኛ የአሸናፊዎቹ ልጆች ነን። በአንድ ልብ ለማሸነፍ ጥንት አባቶቻችን ያቆዩትን ባንዲራ ከፍ አድርገን ይዘን የቆምን የዚህ ዘመን ሰው ነን።

ለማሸነፍ ተፈጥረናልና እናሸንፋለን። ከአሸናፊዎች ወገን በአሸናፊዎች ምድር ተገኝተናልና እናሸንፋለን!
ዳግም ቀና እንላለን!

#ቀናበል

#ታታ_አፍሮ /ነፃ ብዕር/
Forwarded from Amleset Muchie
"አረጀች እያሉ ሰዎቹ ሲያሙሽ
ሙሽራ ነሽ ጎንደር ይሰፋል ልብስሽ"
2025/06/29 12:44:33
Back to Top
HTML Embed Code: