Forwarded from Profile pictures
Forwarded from Profile pictures
Forwarded from Profile pictures
Forwarded from Profile pictures
Forwarded from @ወደብ_ፔንሲዮን (@DMULLERB21)
Forwarded from @ወደብ_ፔንሲዮን (@DMULLERB21)
Forwarded from @ወደብ_ፔንሲዮን (@DMULLERB21)
Forwarded from @ወደብ_ፔንሲዮን (@DMULLERB21)
Forwarded from @ወደብ_ፔንሲዮን (@DMULLERB21)
📝📚 ስለ መጽሐፍ 📚📚📒
☑️ የኔን የግል ህይወት ብቻ ሳይሆን በዙሪያዬ ያሉ ሰዎችን ህይወት መለወጥ
የቻሉ ሀሳቦችን መተግበር የቻልኩት መጽሐፍ በማንበብ ነው ።(ቤልሑክስ)

☑️አላዎቂነትንና ችኩልነትን የምንዋጋበት ብቸኛው ወሳኝ መሳሪያ ቢኖር ማንበብ ነው ። (ሌኖርድ ቤይንስ ጆንሰን)

☑️በህይወቴ ማወቅ የምፈልጋቸው ነገሮች በሙሉ መጽሐፍ ውስጥ አሉ ።
የኔ ምሪጥ ጓደኛ ብዬ የምመሪጠው ሰው
ያላነብኩትን መጽሐፍ "እንካ አንብብ "
ብሎ የሚሰጠኝ ሰው ነው ። (አብርሃም ሊንከን)

☑️መጽሐፍትን በሚገባ ማንበብ ማለት
በድሮ ዘመን ይኖር ከነበረ በጣም አስተዋይ ሰውጋ መወያየት ማለት ነዉ ።
(ሬኒ ዲካርቴሥ)

☑️ መጽሐፍትን ከማቃጠል የባሰ በርካታ
ወንጀሎች አሉ ። ከነዚህም መሀል መጽሐፍትን አለማንበብ አንዱ ትልቁ ወንጀል ነው ። ( ጆሴፋ ብሮድስኪ)
@tgprofile2
@tgprofile2
#የበታችነት_ስሜት
(Inferior complex)

ሰው በሁለት ነገሮች ተጠምዶ ህይወቱን ያባክናል። ወይ በበታችነት ስሜት ወይ ደግሞ በበላይነት ስሜት ይሰቃያል።

አንድ ሰው በበታችነት ስሜት ከተያዘ ውስጡ በጥልቀት ይታመማል፡፡ ከንቱ እንደሆነ እያሰበ ከኖረ በህይወት የመቆየቱ ጉዳይ አስቸጋሪ ይሆናል። በህይወት እየኖረ ቢሆንም ሙት ነው፡፡ እስከ እለተ ሞታቸው ድረስ በህይወት የሚቆዩ በጣም ጥቂት ሰዎች አሉ። አብዛኞቹ ግን ከመሞታቸው በፊት የሚሞቱ ናቸው። በሰባ አመታቸው ቢቀበሩም የሞቱት ግን ቀደም ብለው ነው። በሞታቸውና በቀብራቸው መሀል የሰላሳ፣ የአርባ ወይም የሃምሳ ዓመታት ክፍተት ሊኖር ይችላል፡፡

በዙሪያችሁ የተንሰራፋውን ግዝፈተ ተፈጥሮ ስትመለከቱ የበታችነት ሊሰማችሁ ይችላል። ከዚህ አንፃር ሲታይ ሰው ምንም ነው። በውቅያኖስ ሞገዶች ላይ እንደተንሳፈፈ ገለባ ነው። ምንም አይነት ሃይልም ሆነ አቅጣጫ የለውም፡፡ እንደዚህ አይነት የበታችነት ስሜት አይምሮን ጨምድዶ ከያዘ የሰው ህይወት በመከፋት የተሞላ ይሆናል። በህይወት የሚኖር ሙት ይሆናል፡፡ ህይወቱ አመድና ትቢያ ይሆናል። የህይወታችሁ ነበልባል ከውስጣችሁ ከጠፋ፣ የፋኖሳችሁ ነበልባል ከጠፋ፣ በፀሃይ ብርሃንም ምንም ማድረግ አትችሉም፡፡ ለናንተ ፀሃይ ምንም ጥቅም አይኖራትም፡፡

በሰው ውስጥ መላው ግዝፈተ ተፈጥሮ እንደሚገኝ ማስታወስ ያስፈልጋል፡፡ በሰው ውስጥ መለኮት እንደሚገኝ ማስታወስ ያስፈልጋል፡፡ በዚህም ሰው የበታች አይሆንም፡፡ በጣም የሚገርመው ሰው የበታችነት ስሜቱን ለማውደም አስቦ በበላይነት ስሜት መጃጃሉ ነው። የበታችነት ስሜቱን ለማፈን የተለያዩ መንገዶችን መፈለግ ይጀምራል። ውስጡን የበታችነት ስሜት ሲሰማው ሃብት በማከማቸት ለአለም ህዝብ ከንቱ አለመሆኑን ሊያሳይና ከሌላው የበላይ የመሆን ስሜት ሊሰማው ይችላል። ከበታችነት ስሜቱ የተነሳ ጭንቅላቱ ላይ ዘውድ ደፍቶ ከንቱ አለመሆኑን ለማሳየት ይሞክራል። የበላይነት ፉክክር ውስጥ የሚከተው የበታችነት ስሜት ነው። እናም የበላይ ለመሆን በሚደረግ የእብዶች እሽቅድምድም ውስጥ ያሉ ሰዎች ያለጥርጥር ውስጣቸው በበታችነት ስሜት እየተሰቃየ ነው።

ከዚህ አንፃር አድለር ብዙ አስገራሚ ነገሮችን ተናግሯል። ገለፃዎቹ አስፈላጊ ናቸው። እንደ አድለር ገለፃ ከሆነ በሩጫ ውድድር አንደኛ የሚወጡ ሰዎች በልጅነታቸው በትክክል መራመድ የማይችሉ ነበሩ። ልዩ የሙዚቃ ክህሎት ያላቸው በልጅነታቸው መጠነኛ የመስማት ችግር የነበረባቸው ናቸው፡፡ ርዕሰ ብሔር፣ ጠቅላይ ሚኒስትር የሚሆኑት ደግሞ በትምህርት ቤት ህይወታቸው ኋላ ወንበር ላይ የሚቀመጡ የነበሩ ናቸው፡፡ እነዚህ ሰዎች በልጅነት በደረሰባቸው የበታችነት ስሜት ጉዳት ሳቢያ ከንቱ አለመሆናቸውን ለዓለም ለማሳየትና ለማረጋገጥ ይፈልጋሉ። አንድ ፖለቲከኛ በበታችነት ስሜት ቢሰቃይ አያስገርምም፡፡ ከንቱ ነኝ የሚል የበታችነት ስሜት ውስጡን እንደ ትል ይበላዋል፡፡ በዚህም አይምሮው ተጐድቶ ችግር ውስጥ ይከተውና የበላይ መሆኑን ለማሳየት ወደ ውድድር እንዲገባ ያነሳሳዋል።

ሌኒን ወንበር ላይ ሲቀመጥ እግሮቹ ወደ ወለሉ አይደርሱም ነበር፡፡ ከወገቡ በላይ ያለው የሰውነቱ ክፍል ከወገቡ በታች ካለው ይረዝም ነበር። እናም ወንበር ላይ ሲቀመጥ እግሮቹ ወደ ወለሉ መድረስ አይችሉም፡፡

ሂትለር ደግሞ ተራ ንቃተ ህሊና የነበረው ወታደር ነበር። በዚህም የጦር ሰራዊቱ አባል ለመሆን አትመጥንም ተብሎ ተባሮ ነበር። ስታሊንና ሊንከንም የጫማ አዳሽ ልጆች ነበሩ፡፡

የአለማችንን ፖለቲከኞች የኋላ ታሪክ ብንመለከት እንገረማለን። የእሽቅድምድማቸው መንስኤ በልጅነታቸው የገጠማቸው የበታችነት ስሜት ጉዳት ነው፡፡ በዚህም ሳቢያ እንደ እብድ መሽቀዳደም የጀመሩ ናቸው፡፡ ወደ አንድ የከፍታ ጫፍ ላይ መውጣት ካልቻሉ አይረኩም፡፡ እዛ የከፍታ ጫፍ ላይ በመውጣት ከንቱ አለመሆናቸውን ለአለም አሳይተዋል። በውስጣቸው ግን ምንም ነበሩ። ከዚህ አንፃር ሁሉም ስልጣን፣ ሃብት፣ ወይም ዝና ለባለቤታቸው ትርጉም አልባ ናቸው፡፡ ምክንያቱም ግለሰቡ የፈለገውን በእጁ ቢያስገባም ውስጡን ግን ያው እንደ በፊቱ ሆኖ ያገኘዋል። የበታችነት ስሜቱ አሁንም እንደ ትል ይበላዋል። ትልቁ የስልጣን እርከን እንኳ እርካታን አያመጣም፡፡ እናም ቀድሞ መገኘት ያለው እሽቅድምድም አይጠፋም፡፡ አንድ ሰው አሌክሳንደርን፡- “አለምን ለመቆጣጠር እንደምትፈልግ ሰምቻለሁ፡፡ ነገር ግን አለምን ከተቆጣጠርክ በኋላ ምን እንደምታደርግ አስበህበት ታውቃለህ?ምክንያቱም ያለው አንድ አለም ብቻ ነው።” ሲል ጠይቆት ነበር፡፡ እንደሰማሁት ከሆነ እሌክሳንደር በጣም ተከፍቶ፡- “በዚያ መልኩ አስቤ አላውቅም፤ ትክክል ነህ፡፡ መላውን አለም ከተቆጣጠርኩ በኋላ ምን አደርጋለሁ? ሌላ አለም ያለው የት ነው?” በማለት መልሷል። አለምን ከተቆጣጠረ በኋላ እንኳ አይምሮውን ጠፍሮ ከያዘው የበታችነት ስሜት ማምለጫ አይኖረውም፡፡ ሌላ አለም ቢኖርና ቢቆጣጠረው እንኳ ማምለጫ አይኖረውም፡፡ የበላይነት ስሜት የበታችነት ስሜት ነፀብራቅ ነው።

በኩራት የሚኮፈስና ሌሎች እንዲታዘዙት ሃይል የሚጠቀም ስው ሊታዘንለት ይገባል፤ ምክንያቱም በበታችነት ስሜት እየተሰቃየ መሆኑን ነው፡፡ በዚህ የአይምሮ ጭንቀት ሳቢያም የበላይ ለመሆን በሚደረጉ የእብዶች እሽቅድምድም ውስጥ ተካፋይ ይሆናል።

የበታችነት ስሜት በሽታ ነው፤ ይህን የበታችነት ስሜት ለመደበቅ የሚመጣው የበላይነት ስሜት ደግሞ የባስ በሽታ ነው፡፡ አብዛኛውን ጊዜ መድሃኒቱ ከበሽታው ይልቅ አደገኛ ነው።

ምንጭ ፦ የንቃት ፀሀይ (ኦሾ)
ተርጓሚ ፦ መርሻ በነበሩ

@tgprofile2
Tg profile picture pinned «https://www.tg-me.com/Yefkermaed»
Hi there!
Ready to score some cash?
Join me at Pawns.app and kick-start your money-making journey with $3 just for signing up:
- $1 when you join
- $1 on your first payout
- $1 on your second payout

Use the magic link below:👇👇
https://discoverpawns.eu/2211649
Tg profile picture pinned «Hi there! Ready to score some cash? Join me at Pawns.app and kick-start your money-making journey with $3 just for signing up: - $1 when you join - $1 on your first payout - $1 on your second payout Use the magic link below:👇👇 https://discoverpawns.eu/2211649»
2024/05/15 22:53:51
Back to Top
HTML Embed Code: