Telegram Web Link
ዚክርና ጥቅሞቹ
🕯አላህን ማሥታወሥ ያለዉ ጥቅም እና ትሩፋት

🔸አላህን ማሥታወሥ ነፍሥያ እና ሸይጧን ላይ ድል የመቀዳጃ ትልቅ በር ነው
🔹 ወደ አላህ ሡብሀነ ወተዓላ መዳረሻ መንገድ ነው
🔸 አላህ ሡብሀነ ወተዓላ የዚክርን በር የከፈተለት ሰው የሁሉንም የኸይር በሮች አግኝቷል
🔹የዚክር በር የተዘጋበት ሰው የኸይር በሮች ተዘግተውበታል
🔸ዚክርን አላህ ሡብሀነ ወተዓላ ያገራለት ሠው ዒባዳዎች ሁሉ ይገሩለታል
🔹ዚክር የከበደውና ከዚክር የሠነፈ ሰው ከዒባዳዎችም ይሠንፋል
🔸 ዚክር ማብዛት ሸይጧንን ከሰው ልጆች ያርቃል
🔹ዚክር አላህን ሡብሀነሁ ወተዓላ ያሥደሥታል፣የአዱንያን ጭንቀት ያሥወግዳል
🔸በልብ ውሥጥ ደሥታን ይፈጥራል፣የደረቁ ቀልቦችን ያረጥባል
🔹ወንጀሎችን ያራግፋል የብቸኝነትን ስሜት ያሥወግዳል ከአላህ ሡብሀነሁ ወተዓላ ቅጣትም ይጠብቃል
🔸 ዚክር የሚያበዛ ሠው ከሙናፊቅነት ይድናል
🔹የቂያማ ቀን ከመፀፀት እና ከመቆጨትም ያድናል
🔸ጀነት ላይ የሰው ልጆች አትክልት እና ፍራፍሬ የሚያገኙትም በአዱንያ በሚያደርጉት ዚክር ልክ ነው፡፡

🔹የህሊናን እረፍት ይሠጣል

🔸ዚክር የሚል ሰው ላይ የአላህ ራህመት ይወርድበታል፣ መላኢኮች ዙሪያውን ይከቡታል
🔹 በአዱኒያ ዚክር ለሚያበዛ ሰው አላህ ግንባሩ ላይ ኑርን ይሠጠዋል፣
ቀብር ውስጥም አላህ ብርሃንን ይፈጥርለታል፡፡
🔸የቂያማ ቀንም በአዱኒያ ያደርገው የነበረው ዚክር ሲራጥን በሠላም እንዲሻገር ያደርገዋል፣ ፊቱም ያበራል፡፡ለዚህም ነው አላህ ሡብሀነሁ ወተዓላ የሠው ልጆች ዚክርን እንዲያበዙ በተለያዩ የቁርኣን አያዎች (አንቀፆች) ያዘዛቸው፣ ረሡልም ሠለላሁ አለይሂ ወሠለም በብዙ ሀዲሶች ዚክርን ማብዛት እንዳለብን ገልፀዋል፣ ዚክር የሚያበዙ ሰዎች የሚያገኙትን ትሩፋትም ጠቅሠዋል፣
🚩አላህ ሡብሀነ ወተዓላ በቁርኣኑ
يَا أَيُّهَا الَّذَ آمَنُوا اذْكُرُوا اللَّهَ ذِكْرًا كَثِيرًا
وَسَبِّحُوهُ بُكْرَةً وَأَصِيلًا
(ሡረቱል አህዛብ፡41-42)
[ "እናንተ ያመናችሁ ሰዎች ሆይ :—አላህን ሡብሀነሁ ወተዓላ ብዙ ማሥታወሥን አሥታውሡት ጠዋትና ማታም አጥሩት"] ይላል
🚩በሌላውም የቁርአን አያ የሡን ትክክለኛ ባሮችን መገለጫ ሢገልፅ
እነዚያ ያመኑ አላህን በማሥታወሣቸው ልባቸዉ ይረጋጋል የሠው ልጆች ሆይ አላህን በማሥታወሥ የልብ ሠላም እና እርጋታ ይገኛል፡፡ብሏል ፣
🚩በሌላኛው የቁርኣን አያም "አሥታውሡኝ አሥታውሣችኋ
ለሁ "ብሏል፡፡
ሐጅ ሥርአት ላይ ዒባዳችሁን ሥትጨርሡ አላህ ሡብሀነ ወተአላ አሥታውሡ ቤተሠቦቻችሁን እና ዘመዶቻችሁን ከምታሥታውሡት የበለጠ ይላል "
"አላህን ሡብሀነ ወተዓላ በብዛት አሥታውሡት ፣እነሆ ይህን ያደረጋችሁ እንደሆነ ትድናላችሁ" ይላል
🔸በተለያዩ የቁርኣን አያዎች ላይ የዚክርን ጥቅሞች አላህ ገልጿል።
📎ዐብዱሏህ ኢብኑ ዐባስ ረዲየሏሁ ዐንሁ የሚከተለውን ብለዋል("አላህ ሡብሀነ ወተዓላ ባሮቹ ላይ ማንኛውንም አይነት ዒባዳ አልደነገገም ዒባዳው በግልፅ በውል የሚታወቅ ገደብና መጠን ቢያደርግለት እንጂ!" )
ይህን ዒባዳ የታዘዙ እና የተደነገገላቸው ሰዎችን ኡዝር ባላቸው ሠአት ይህን ዒባዳ ቢተውት ምንም ችግር የለውም ብሎም ቢያሣውቅ እንጂ ፡፡ ዚክር ሢቀር 👌
📌ዚክርን በተመለከተ ይሄን ያህል ብቻ ዚክር አድርጉ ብሎ አላህ አልገደበውም ፣እንዲሁ ዚክርን መተውም አላህ ሡብሀነ ወተዓላ ለማንም አልፈቀደም ለመተዉም ኡዝር አልሰጠም። አእምሮውን የሣተ፣ ራሡን መቆጣጠር ያቃተው ሰው ካልሆነ በሥተቀር ዚክርን ለመተው አላህ ለማንም ኡዝር አልሠጠም፡፡
እንዲሁም ዚክርንም በዚህ ሠአት በሉ ብሎ አላህ አልገደባቸውም፡፡በጊዜ የተገደቡ ዚክሮች ቢኖሩም በዛ ወቅት እነዚህ ዚክሮች መባል አለባቸው በዚህ ሠአት ቢባሉ ይመረጣል ፣በማለት ነብያችን ሠለላሁ አለይሂ ወሠለም የተናገሩት ካልሆነ በስተቀር! እንጂ ከዚህ ሠአት ውጭ አላህን ማሥታወሥ አይቻልም ማለት አይደለም፡፡
ቆማችሁም፣ተቀምጣችሁም ተኝታችሁም አላህን አሥታውሡ፡፡ቀንም ሌሊትም ባህርም ውስጥ የብሥም
ላይ አላህን አሥታውሡ፣ ሀገርም ላይ ይሁን መንገድ ላይ ፣በድንጋጤና በሀዘንም ሆነ በደሥታ ጊዜ በህመምም ሆነ በጤንነት ጊዜ አላህን አሥታውሡ! በገሀድም በሚሥጥርም በየትኛውም ሁኔታ ላይ ብትሆኑ አላህን አሥታውሡት!

ኡስታዝ አህመድ ኣደም
20/12/1437 ዓ.ሂ
@theamazingquran
@theamazingquran
@theamazingquran
➧መልካም_ጓደኛ

ሁለት ውብ የሂወት ኡደቶችን ይለግሰሀል…"አንደኛው አዚህ ዱንያ ላይ ሲሆን" "ሁለተኛው ደግሞ ጀነት ውስጥ ይሆናል"

መልካም_ጓደኞች «ወደ አሏህ መንገድ… ይጠሩሀል…» «ከጠፋህባቸው… ይፈልጉሀል…» ከተዘናጋህ… አስታውሱሀል»

«…በዱአቸው ውስጥ…ያካቱሀል»
«ልክ እንደ ከዋክብቶች… መርከብህ መንገድ ከሳተች…ይመሩሀል…» «ነገ ከአሏህ አርሽ ስር…ኢንሸአላህ…አብረው ይጎዳኙሀል…» «ጀነት ውስጥ ፈልገውህ ካጡህ…

አሏህን ወደነሱ እንዲቀላቅልህ ይለምኑልሀል» "አሏህ ሶሊሆቹን አድርጎ ከሶሊሆቹ ያወዳጀን ከሶሊሆቹ ጓደኞቻችን አይነጥለን በያሉበት ይጠብቅልን " አሚን

https://www.tg-me.com/YereSulwedajoch_12


http://www.tg-me.com/SUNAJOIN
وَلَا تَحْسَبَنَّ اللَّهَ غَافِلًا عَمَّا يَعْمَلُ الظَّالِمُونَ ۚ إِنَّمَا يُؤَخِّرُهُمْ لِيَوْمٍ تَشْخَصُ فِيهِ الْأَبْصَارُ

አላህንም በደለኞች ከሚሠሩት ግፍ ዘንጊ አድርገህ አታስብ፡፡ የሚያቆያቸው ዓይኖች በእርሱ እስከሚፈጡበት ቀን ድረስ ብቻ ነው፡፡
14፥42
ሙስሊሞችን ከመተዋወቄ በፊት ቁርአንን ተምሬያለሁ! ኢስላምንም ተቀብያለሁ! ምናልባትም ሙስሊሞችም ቀድሜ አውቄ ቢሆን ሙስሊም ያለመሆን ሰፊ እድል ይኖረኝ ነበር! (ይህም የሙስሊሞች ባህሪ ከቁርአን በጣም ስለራቀ ነው)

ዝነኛው እንግሊዛዊ!
የቀድሞ ታዋቂ ሙዚቀኛ ካት ስቲቨንስ ( ዩሱፍ ኢስላም)
አንተ ሶላትን የተውክ ሆይ!!
አንተ ሶላትን የተውክ ሆይ!! አንተ ሶላትን የተውክ ሆይ! ሶላትን
ትተህ ከእስልምና ምን ቀረህ? ሶላት የኢስላም ምሰሶ ፤
የኢማን መገለጫ -ካባ- መሆኑን አታውቅምን!? አንተ ሶላትን
የተውክ ሆይ! አንተ ስትቀር ሁሉም ፍጥረታት ለጌታቸው
ሰጋጆች ናቸው። አላህ እንዲህ ብሏል፡-
“በሰማያት ያለው ሁሉ፤ በምድርም ያለው ሁሉ፤ ፀሀይና፣
ጨረቃም፣ ከዋክብትም፣ ተራሮችም፣ ዛፎችም፣
ተንቀሳቃሶችም፣ ከሰዎች ብዙዎችም ለአላህ የሚሰግዱ
መሆናቸውን አታውቅምን!? ብዙዎችም ቅጣት ተገባቸው።
አላህ የሚያዋርደው ሰው ለርሱ ምንም አክባሪ የለውም፤
አላህ የሻውን ይሰራልና።” አንተም የማትሰግድ ከሆነ ከነዚያ
ቅጣት ከተወሰነባቸው አንዱ ትሆነናለህ።አ ንተ ሶላትን የተውክ
ሆይ! ሶላትን መተው ክህደትና (በአላህ ላይ) ማጋራት
መሆኑን አታውቅምን!? ነቢዩ < አንዲህ ብለዋል፡-
« ﺑﻴﻦ ﺍﻟﺮﺟﻞ ﻭﺑﻴﻦ ﺍﻟﺸﺮﻙ ﻭﺍﻟﻜﻔﺮ ﺗﺮﻙ ﺍﻟﺼﻼﺓ ‏» ‏[ﺭﻭﺍﻩ
ﻣﺴﻠﻢ]
«በሰውየውና በሽርክ ወይም በክህደት መሀል (ያለው) ሶላትን
መተው ነው።”
« ﺍﻟﻌﻬﺪ ﺍﻟﺬﻱ ﺑﻴﻨﻨﺎ ﻭﺑﻴﻨﻬﻢ ﺍﻟﺼﻼﺓ : ﻓﻤﻦ ﺗﺮﻛﻬﺎ ﻓﻘﺪ
ﻛﻔﺮ ‏» ‏[ﺃﺧﺮﺟﻪ ﺃﺣﻤﺪ ﻭﺍﻟﺘﺮﻣﺬﻱ ﻭﺻﺤﺤﻪ ﺍﻷﻟﺒﺎﻧﻲ ].
“በኛና በነሱ (በካህዲያን) መሀል ያለው ቃል-ኪዳን (ድንበር)
ሶላትን መተው ነው። (ሶላትን) የተወ በእርግጥ ካደ።”
አንተ ሶላትን የተውክ ሆይ! ሶላትን መተው እንዲሁም
(ከሶላት) መዘናጋት ሙናፊቅነት መሆኑን አታውቅም!?
አላህ እንዲህ ብሏል፡-
ﺍﻟﻨﺴﺎﺀ : ١٤٢
“ሙናፊቆች አላህን ሊያታልሉ ይፈልጋሉ፤ እሱ አታላያቸው
ሲሆን። ወደ ሶላት ሲቆሙ እየሰለቹ፣ ለሰዎች የሚያሳዩ ሆነው
ይቆማሉ። አላህንም ጥቂትን እንጂ አያወሱም።”
ነቢዩም < ይህን ማስተላለፋቸው ተዘግቧል።
« ﺃﺛﻘﻞ ﺍﻟﺼﻼﺓ ﻋﻠﻰ ﺍﻟﻤﻨﺎﻓﻘﻴﻦ ﺻﻼﺓ ﺍﻟﻌﺸﺎﺀ ﻭﺻﻼﺓ
ﺍﻟﻔﺠﺮ، ﻭﻟﻮ ﻳﻌﻠﻤﻮﻥ ﻣﺎ ﻓﻴﻬﻤﺎ ﻷﺗﻮﻫﻤﺎ ﻭﻟﻮ ﺣﺒﻮًﺍ‏» ‏[ﻣﺘﻔﻖ
ﻋﻠﻴﻪ ].
“በሙናፊቆች ላይ እጅግ የሚከብደው ሶላት ኢሻዕ እና ሱብሂ
ነው። (ሁለቱን በመስገድ) የሚገኘውን ምንዳ ቢያውቁ ኖሮ
እየዳሁም ቢሆን (ወደ መስጊድ) ይመጡ ነበር።”
አንተ ሶላትን የተውክ ሆይ! እስቲ አስተንትን ሙናፊቆች
ለይዩልኝ (ሪያዕ) ቢሆንም እንኳ ይሰግዳሉ፤ አንተ ግን
በፍጹም አትሰግድም!!
አንተ ሶላትን የተውክ ሆይ፡- ሶላትን መተው ዝንጉነት እና
የልብ መድረቅ መሆኑን አታውቅምን!? ነቢዩ < እንዲህ
ብለዋል፡-
« ﻟﻴﻨﺘﻬﻴﻦ ﺃﻗﻮﺍﻡ ﻋﻦ ﻭﺩﻋﻬﻢ ﺍﻟﺠﻤﻌﺎﺕ، ﺃﻭ ﻟﻴﺨﺘﻤﻦ ﺍﻟﻠﻪ
ﻋﻠﻰ ﻗﻠﻮﺑﻬﻢ، ﺛﻢ ﻟﻴﻜﻮﻧﻦ ﻣﻦ ﺍﻟﻐﺎﻓﻠﻴﻦ ‏» ‏[ﺭﻭﺍﻩ ﻣﺴﻠﻢ ].
“ህዝቦች የጁምዓ ሶላትን ከመተው ይከልከሉ! ወይም አላህ
በልቦቻቸው ላይ ያሽግባቸዋል። ከዚያም ከዝንጉዎች
ይሆናሉ።”
አንተ ሶላትን የተውክ ሆይ፡- ሶላትን መተው ስራን ሁሉ
እንደሚያበላሽ አልሰማሐሃምን!? የሚከተለውን የነቢዩን <
ንግግር ተመልከት።
« ﻣﻦ ﺗﺮﻙ ﺻﻼﺓ ﺍﻟﻌﺼﺮ ﺣﺒﻂ ﻋﻤﻠﻪ ‏» ‏[ﺭﻭﺍﻩ ﺍﻟﺒﺨﺎﺭﻱ ].
“የአስርን ሶላት የተወ ስራው በርግጥ ተበላሸበት።”
አንተ ሶላትን የተውክ ሆይ! ሶላትን መተው ከከሀዲያንና
ወንጀለኞች ጋር ለእሳት ቅጣት እንደሚዳርግ አታውቅምን!?
የጀነት ሰዎች የጀሀነም ሰዎችን (ጀሀነም የገቡበትን
ምክንያት) ሲጠይቋቸው የሚሰጧቸውን ምላሽ ሲናገር አላህ
እንዲህ ይላል፡-
“ሰቀር (የገሀነም ጉድጓድ) ውስጥ ምን አስገባችሁ?
(እነሱም) ይላሉ፡- ከሰጋጆች አልነበርንም…።”
እንዲሁም በሌላ ምዕራፍ፡-
“ከነሱም በኋላ ሶላትን ያጔደሉ፣ ስሜታቸውንም የተከተሉ
ምትኮች ተተኩ። ለወደፊት ገይን (የገሀነም ሸለቆ) ይገባሉ።”
አንተ ሶላትን የተውክ ሆይ! ሶላትን በመተውህ ከባድ መዓት
(ጥፋት) ያረፈብህ መሆኑን አታውቅምን!?
ነቢዩ < እንዲህ ብለዋል፡-
« ﺍﻟﺬﻱ ﺗﻔﻮﺗﻪ ﺻﻼﺓ ﺍﻟﻌﺼﺮ، ﻓﻜﺄﻧﻤﺎ ﻭﺗﺮ ﺃﻫﻠﻪ
ﻭﻣﺎﻟﻪ‏» ‏[ﺭﻭﺍﻩ ﺍﻟﺒﺨﺎﺭﻱ ]
“የአስር ሶላት ያመለጠው ቤተሰቦቹንና ንብረቱን እንደ አጣ
(እንደ ተነጠቀ) ነው።”
የአምስቱንም ወቅት ሶላት መተውህስ ምን ያስከትል ይሆን!?
አንተ ሶላትን የተውክ ሆይ! ሶላትን መተው መረበሽን፣
አለመረጋጋትን፣ ጭንቀትን፤ የኑሮ ጥበትን (እንደሚያመጣ)
አታውቅምን!?
አላህ እንዲህ ይላል፡-
«ከግሳጼዬ የዞረ፤ የጥበት ህይወት አለለት፤ የትንሳኤም ቀን
እውር ሆኖ እንቀሰቅሰዋለን። ጌታይ ሆይ ለምን እውር
አድርገህ ቀሰቀስከኝ? በርግጥ አይናማ የነበርኩ ስሆን
ይላል። (ነገሩ) እንደዚሁ ነው። ተዓምራችን መጥቶልህ ሳለ
እንደዘነጋኀው አንተም ዛሬ ትዘነጋለህ ይለዋል።»
ዋ ንዴትህ! ዋ ፀፀትህ! አንተ ሶላትን የተውክ ሆይ። እንዴት
ጊዜ ያልፋል፤ እድሜህ (ያለ አግባብ) ይገባደዳል; ልብህ
ከጌታህ ተጋርዶ ሳለ!? እንዴትስ በቅርቢቱ አለም (ዱንያ)
ከሚገኙት ነገሮች ሁሉ ይበልጥ ጣፋጭ እና ማራኪ የሆነውን
ነገር ሳትቀምስ ዱንያን ትሰናበታታለህ!? ይህም አላህን
በማምለክ፣ በማውሳት፣ በማመስገን እና ለርሱም በመስገድ
የሚገኝ ሲሆን።
አንተ ሶላትን የተውክ ሆይ! ለሶላትህ ቀላል ስፍራ የሰጠኀው
አንተ ዘንድ ታላቅ ስፍራ የሚሰጠው ምን ይሆን? ሶላቱን ያጓደ
ሌሎች ስራዎቹን ይበልጥ እንደሚያጓድል አታውቅምን!?
ሀሰን እንዲህ ብሏል፡- “የአደም ልጅ ሆይ! ሶላትህ አንተ ዘንድ
ጥሩ ስፍራ ከሌለው ምንድን ነው አንተ ዘንድ ጥሩ ስፍራ
ሊኖረው የሚችለው!?”
አንተ ዝንጉ የሆንክ ሆይ! ወደ ጌታህ ተመለስ! ሶላትህን
ትተህ ሞት ከመምጣቱ በፊት።
አንተ ሶላትን ችላ የምትል ሆይ!
• የታላቁን ሶላት ደረጃ ካወቅክ
• የሰጋጆችን ቁጥር ስፍር የሌለውን ሽልማት መመልከት
ከቻልክ (እና)
• ሶላትን የሚያጓድሉ ሰዎችን ብርቱ ቅጣት ከተገነዘብክ በኋላ
አሁንስ ምላሽህ ምን ይሆን?
ሶላትን በማጓደልና ችላ በማለት ትቀጥላለህን!?
ሶላትን ትቶ መተኛትንና ከወቅቱ ማዘግየትን ትገፋበታለህን!?
ወንድሜ ሆይ!
የት አለ ከፍ ያለው ሞራልህ?
የት አለ ጠንካራው ቁርጠኝነትህ?
የቱ ላይ ነው ለጀነት ታጥቆ መነሳት?
የት አለ የሶላትን ወቅት መጠባበቅ?
(ኧረ) የት አለ ወደ ጁምዓ እና ወደ ጀምዓ ሶላት በጊዜ
መሄድ?
<<ለሰዎች ከተገለጸች ሕዝብ ሁሉ በላጭ ኾናችሁ በጽድቅ ነገር ታዛላችሁ፤ ከመጥፎም ነገር ትከለክላላችሁ፤ በአላህም (አንድነት) ታምናላችሁ፡፡.....>>3፥110


.
.


ለአስተያየት @quraniccbot

የምንለቃቸው ማስታወቅያዎች እኛን አይወክሉንም!

Find as on:
👉FB
https://bit.ly/3bCWvtY

👉youtube
https://bit.ly/2MmQqpq
ሰለዋት እናብዛ‼️

ምን ያህሎቻችን ነን ጁምዓ ተጠባብቀን በረሱል [ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም] ላይ ሰለዋት የምናወርደው
ለምንድን ነው ከዚህ ትልቅ ስራ የምንዘናጋው

📚እስኪ አላህና መልዕክተኛውን ምን እንደ ሚሉን እንመልከት


قال الله تعالى ﴿إِنَّ اللَّهَ وَمَلائِكَتَهُ يُصَلّونَ عَلَى النَّبِيِّ يا أَيُّهَا الَّذينَ آمَنوا صَلّوا عَلَيهِ وَسَلِّموا تَسليمًا﴾
[الأحزاب: ٥٦]
አላህ እንዲህ ይላል፦
{አላህና መላዒካዎቹ በነብዩ ላይ ሰለዋት ያወርዳሉ; እናንተ ያመናችሁ ሆይ በእሱ (በነብዩ) ላይ ሰለዋትና ሰላምን አውርዱ}


📖የአላህ መልዕክተኛም እንዲህ ይሉናል👇👇

"أكثروا الصلاة علي يوم الجمعة وليلة الجمعة فمن صلى علي صلاة صلى الله عليه عشرا "
و حـسـنه الألباني في السلسلة الصحيحة 1407
{ጁምዓ ቀንና ጁምዓ ሌሊት በእኔ ላይ ሰለዋት አብዙ። በእኔ ላይ አንድ ጊዜ ሰለዋት ያወረደ ሰው በእሱ ላይ አላህ አስር ጊዜ ሰለዋት ያወርድበታል}

"من صلى علي مرة كتب الله له بها عشر حسنات"
وصـحــحه العلامة الألباني رحمه الله في السلسلة الصحيحة (٣٣٥٩)
{በእኔ ላይ አንድ ጊዜ ሰለዋት ያወረደ ሰው አላህ ለእሱ በዚህ ምክንያት አስር ምንዳ ይፅፍለታል}

" من صلى علي من أمتي صلاة مخلصا من قلبه صلى الله عليه بها عشر صلوات ورفعه بها عشر درجات وكتب له بها عشر حسنات ومحا عنه عشر سيئات "
وصـحــحه العلامة الألباني رحمه الله في السلسلة الصحيحة ( ٣٣٦٠)
{ከኡመቶቼ ውስጥ ከቀልቡ ጥርት አድርጎ በእኔ ላይ ሰለዋት ያወረደ የሆነ ሰው; አላህ በእሷ ምክንያት አስር ሰለዋት ያወርድበታል፣ አስር ደረጃም ከፍ ያደርግለታል፣ አስር ምንዳም ይፅፍለታል፣ አስር ወንጀልም ይሰርዝለታል}

" من صلى علي واحدة صلى الله عليه عشرا "
رواه أبو داود في سننه (١٥٣٠)
وصححه الألباني رحمه الله
{በእኔ ላይ አንድ ሰለዋት ያወረደ በእሱ ላይ አላህ አስር ያወርድበታል}


"اللهم صل على محمد وعلى آل محمد كما صليت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد، اللهم بارك على محمد وعلى آل محمد كما باركت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد"🌺
@theamazingquran
የጁሙዓ ማስታወሻ

★ለወሬ የለውም ፍሬ★

★የተሰማ ሁሉ አይወራም
★የተሰማ ሁሉ አይታመንም
★የሰሙትን ሁሉ ሳያጣሩ ማውራት የሰይጧን አጫፋሪነት ነው።
★የማጣሪያው መንገድ ኡለሞች ናቸው ።

قال الله تعالى: (وَإِذَا جَاءَهُمْ أَمْرٌ مِّنَ الْأَمْنِ أَوِ الْخَوْفِ أَذَاعُوا بِهِ ۖ وَلَوْ رَدُّوهُ إِلَى الرَّسُولِ وَإِلَىٰ أُولِي الْأَمْرِ مِنْهُمْ لَعَلِمَهُ الَّذِينَ يَسْتَنبِطُونَهُ مِنْهُمْ ۗ وَلَوْلَا فَضْلُ اللَّهِ عَلَيْكُمْ وَرَحْمَتُهُ لَاتَّبَعْتُمُ الشَّيْطَانَ إِلَّا قَلِيلًا)

[ ከጸጥታ፣ከድል ወይም ከፍርሃት አንዳች (ወሬ) በመጣላቸውም ጊዜ እርሱን ያጋንናሉ ያሰራጫሉ ፡፡ ወደ መልክተኛውና ከእነርሱ ወደ ትዕዛዙ ባለቤቶች (ወደ ዐዋቂዎቹ) በመለሱት ኖሮ እነዚያ ከእነርሱ (ነገሩን) የሚያውጣጡት ባወቁት ነበር ፡፡ በእናንተም ላይ የአላህ ችሮታና እዝነቱ ባልነበረ ኖሮ ከጥቂቶች በስተቀር ሰይጣንን በተከተላችሁ ነበር፡፡]
(ሱረቱ አል-ኒሳእ - 83)

قال الله تعالى: {يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِن جَاءَكُمْ فَاسِقٌ بِنَبَإٍ فَتَبَيَّنُوا أَن تُصِيبُوا قَوْمًا بِجَهَالَةٍ فَتُصْبِحُوا عَلَىٰ مَا فَعَلْتُمْ نَادِمِين}َ

እላንተ ያመናችሁ ሆይ! ነገረኛ ወሬን ቢያመጣላችሁ በስህተት ላይ ኾናችሁ ሕዝቦችን እንዳትጎዱና በሠራችሁት ነገር ላይ ተጸጸቾች እንዳትኾኑ አረጋግጡ፡፡)
(ሱረቱ አል-ሁጁራት - 6)

የመንደር ወሬ ፣አሉባልታ፣መሰለኝና ሳይሆን አይቀርም እየተባሉ ሚወሩ ወሬዎች ሸይጣንን ከማስደሰት በስተቀር አይጠቅሙም አላህም ፊት ያስጠይቃሉ ።
ተቀያየመ፣ታጣላ፣ተዋጋ!
በወሬ ስንቱ ከሰረ!

ሳያዩ ፣ሳይሰሙ ፣ ሳያጣሩ ፣ሳያረጋግጡ ከማውራት አላህ ይጠብቀን
@theamazingquran
ሁላችንም የአላህ ነን፤ወደ እርሱም ተመላሾች

የሱመያ መስጂድ ኢማም የሆኑት ሸይኽ ሰዒድ በጠና ታመው በካዲስኮ ሆስፒታል ህክምና ሲደረግላቸው ቆይቶ ወደማይቀረው ዓለም አኼራ ሄደዋል።

የቀብር ስነስርዓቱ በርካታ ኡለማዎች፣ ዱዐቶችና ምዕመናን በተገኙበት በመስጅዳቸው ሱመያ መስጅድ ሶላተል ጀናዛ ተሰግዶ፣ ስርዓተ ቀብሩ በኮተቤ መካነ መቃብር ይፈፀማል።

እኛ የአላህ ነን፣ ወደ እርሱም ተመላሾች ነን!

T.me/ahmedin99
❤️💘የኛ ነብይ ﷺ እኮ 💘❤️

የኛ ነብይ ዝምታቸው ብዙ ሳቃቸው ትንሽ ነበር።

የኛ ነብይ ﷺ በህፃናት ጎን ሲያልፉ ሰላም ይሏቸው ነበር።

የኛ ነብይ ﷺ ለሰው ልጆች ለእንስሳት ሳይቀር ያዝኑ ነበር።

የኛ ነብይ ﷺ ሰዎችን አክባሪና ተናናሽ ነበሩ።

የኛ ነብይ ﷺ ይቅር ባይና ይቅር ማለት የሚወዱ ነበሩ።

የኛ ነብይ ﷺ ከቅርቧ አለም ብልጭልጭ ይልቅ የመጨረሻውን አለም የሚናፍቁ ዛሂድ ነበሩ።

የኛ ነብይ ﷺ ጌታቸውን አመስጋኝ ሰዎችንም አመስጋኝ ነበሩ።

የኛ ነብይ ﷺ እግራቸው እስኪሰነጣጠቅ ለጌታቸው ይሰግዱ ነበር።

የኛ ነብይ ﷺ ሰኞና ሐሙስን ይፆሙ ነበር።

የኛ ነብይ ﷺ በፈተናዎች ላይ ታጋሽ ነበሩ።

የኛ ነብይ ﷺ ሚስቶቻቸውን የሚወዱ ፍቅርም ይሰጡ ነበር።

የኛ ነብይ ﷺ ውሸትን በጣም ይጠሉ ነበር።

የኛ ነብይﷺ ስድብንም ሆነ እርግማን ይጠሉ ነበር።

የኔ ዉድ ነብይ💘ሩሄም ገንዘቤም እናቴም አባቴም ለአንቱ ፊዳ ይሁኑሎት😭😭

💝ሶለዋቱ ረቢ ወሰላሙን አለይክ ያረሱለላህ 💝

አላመሁመ አሚን ያረበል አለሚን 🙌🙌🙌 🙌🙌🙌🙌



በረሱልﷺ ሰለዋት አውርድ ወዳጄ!
Channel photo updated
ሱረቱ ሉቅማን❤️


ለሉቅማንም ጥበብን በእርግጥ ሰጠነው፡፡ (አልነውም)፡«አላህን አመስግን፡፡» ያመሰገነም ሰው የሚያመሰግነው ለራሱ ብቻ ነው፡፡ የካደም ሰው (በራሱ ላይ ነው)፡፡ አላህ ተብቃቂ ምስጉን ነውና፡፡(12)
ሉቅማንም ለልጁ እርሱ የሚገሥጸው ሲኾን «ልጄ ሆይ! በአላህ (ጣዖትን) አታጋራ፡፡ ማጋራት ታላቅ በደል ነውና» ያለውን (አስታውስ)፡፡(13)
ሰውንም
በወላጆቹ (በጎ እንዲያደርግ) በጥብቅ አዘዝነው፡፡ እናቱ ከድካም በላይ በሆነ ድካም አረገዘችው፡፡ ጡት መጣያውም በሁለት ዓመት ውስጥ ነው፡፡ ለእኔም ለወላጆችህም አመስግን በማለት (አዘዝነው)፡፡ መመለሻው ወደኔ ነው፡፡ (14)
ለአንተ በእርሱ ዕውቀት የሌለህን ነገር በእኔ እንድታጋራ ቢታገሉህም
አትታዘዛቸው፡፡ በቅርቢቱም ዓለም፤ በመልካም ሥራ ተወዳጃቸው፡፡ ወደእኔም የተመለሰን ሰው መንገድ ተከተል፡፡ ከዚያም መመለሻችሁ ወደእኔ ነው፡፡ ትሠሩት የነበራችሁትንም
ሁሉ እነግራችኋለሁ፤ (አልነው)፡፡ (15) (ሉቅማንም አለ) «ልጄ ሆይ! እርሷ የሰናፍጭ ቅንጣት ክብደት ያህል ብትሆንና በቋጥኝ ውስጥ ወይም በሰማያት ውስጥ ወይም በምድር ውስጥ
ብትሆን አላህ ያመጣታል፡፡ አላህ ሩኅሩኅ ውስጥ ዐዋቂ ነውና፡፡(16)
«ልጄ ሆይ! ሶላትን አስተካክለህ ስገድ፡፡ በበጎ
ነገርም እዘዝ፡፡ ከሚጠላም ሁሉ ከልክል፡፡ በሚያገኝህም መከራ ላይ ታገስ፡፡ ይህ በምር ከሚያዙ ነገሮች ነው፡፡ (17)
«ጉንጭህንም (በኩራት) ከሰዎች አታዙር፡፡ በምድርም ላይ ተንበጥርረህ አትሂድ፡፡ አላህ ተንበጥራሪን ጉረኛን ሁሉ አይወድምና፡፡ (18)
«በአካኼድህም መካከለኛ ኹን፡፡ ከድምጽህም ዝቅ አድርግ፡፡ ከድምጾች ሁሉ አስከፊው
የአህዮች ድምጽ ነውና፡፡» (19)


https://www.tg-me.com/theamazingquran
#መልካም_ሥራ_ተቀባይነት_እንዲያገኝ #መሟላት_ያለባቸው_ነገሮች_ምንድ ናቸው* ?!

"መልካም ሥራ በአላህ ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኝ ሶስት (3) ነገሮች መሟላት አለባቸው ።

. እነሱም:-
በአላህ አንድነትና ብቸኛ አምላክነት በትክክል ማመን።!

. (ቁርአን እንዲህ ይላል😊



«إن الذين امنوا وعملوا الصالحات كانت لهم جنات الفردوس نزلآ » سورة الكهف.

እነዚያ ያመኑና መልካም ሥራዎንም የሠሩ " የፈርደውስ ገነቶች ለነሱ መስፈሪያ ናቸው።!


و قال صلى الله عليه و سلم قل امنت بالله ثم استقم « رواه مسلم. »
📰 የአላህ መልእክተኛ " ሰለሏህ ዓለይሂ ወሰለም )

"እንዲህ ብለዋል :- በአላህ አመንኩ በልና በፍቃዱም ቀጥ በል።
. (ሙስሊም)

2} ሥራው የጠራና ከልብ የመነጨ መሆን:- ይህም ማለት የሚሰራው መልካም ሥራ ለአላህ ውዴታ ተብሎ መሆን " እንዳለበት የሚያስገነዝብ ነው።

📰ሥራው" ስዎች ለማስደሰት ከሰው ፊት አክብሮትንና አድናቆትን ለማትረፍ ተብሎ የተሰራ 😞የይስሙላ ሥራ) መሆን የለበትም።!


📜 «‌ و ما أمروا الا ليعبدوا الله مخلصين له الدين حنفاء. » سورة البينة.

አላህን ፡- ሀይማኖትን ለርሱ ብቻ አጥሪዎች " ቀጥተኞች ሆነው ሊገዙት፦ (98:5)

*ሰራዎች መከናወን ያለበት የአላህ መልእክተኛ (ሰ ዐ ወ) ባስተማሩት መሰረት መሆን አለበት*።

📜 «وما اتاكم الرسول فخذوه وما نهاكم عنه فانتهوا واتقوا الله إن الله شديد العقاب» سورة الحشر.
📜መልዕክተኛው የሰጣችሁን (ማንኛውንም) ነገር ያዙት። ከእርሱም የከለክላቹሁን ነገር ተከልከሉ። አላህንም ፍሩ ፦ አላህም ቅጣተ ብርቱ ነውና።(59፡7)

📜 و قال صلى الله عليه و سلم من عمل عملآ ليس عليه امرنا فهو رد » رواه مسلم.
የአላህ መልዕክተኛ ሰለሏህ ዓለይሂ ወሰለም)
የእኛ ፍቃድ ያልሆነን ነገር ያከናወነ ሰው ተግባሩ ውድቅ ነው። ሲሉ ተናግረዋል። (ሙስሊም)
አንድ ቀን እንዲህ ሆነ…
ረሱል ሰ,አ,ወ ቢላልን ጠርተው ያ ቢላል አሰላቱ ጃሚአ ብለህ ህዝቤን ሰብስብልኝ አሉት ያኔ ቢላል ረ,ዐ ወዲያውኑ አሰላቱ ጃሚአ ብሎ ህዝቡን ሰበሰበ ረሱል ሰ,ዐ,ወ ወደ ሚንበር ላይ ወጡና እሚገርም ቁጥባ ማድረግ ጀመሩ ረሱል ሰ,ዐ,ወ ይጠይቃሉ ሰሀባወች ይመልሳሉ ።
.
ረሱል ሰ,ዐ,ወ የእኔ ነብይነት ለእናንተ እንዴት ነበር ???
በደንብ አስተምሬአችሆለሁን ?
ሀቃችሁን ሁሉ ተወጥቻለሁ ወይን? ብለው ጠየቁ።
.
ሰሀባወችም አንቱማ በጣም ረሂም አባት ነበሩ እንዲሁም መካሪ ወንድም እናት ነውት እኮ ለእኛ አሎቸው በሉ እንግዲያውስ በአላህ ይዧችሆለሁ ምናለልባት የበደልኩት ሰው ካለ ነገ አኼራ ላይ እንዳይጠይቀኝ ዛሬ ላይ ይኸው የበደልኩት ካለ ንብረቱን የወሰድኩበት ሰውም ካለ የመታሁት ዛሬ ነውና እድሉ ይምጣ እና ይበቀለኝ ብለው አሉ።
.
ሁሉም ፀጥ አሉ ማንም አልተነሳም አሁንም ለ2ኛ ጊዜ ደገሙና በአላህ ይሁንበት የበደልኩት ይምጣና ይበቀለኝ ይሄው አለሁ ሁሉም ፀጥ አሉ።
.
ለ3ኛ ጊዜ ደገሙና ያመእሸረል ሙስሊሚን አስኪ ማነው እኔን መበቀል እሚፈልግ ትላንት በእኔ የተከፋ አለን? በአላህ ይሁንባችሁ ይኸው እኔ እዚህ አለሁ የበደልኩት ሰው ይምጣና ይበቀለኝ ሲሉ ይህኔ በእድሜ የገፋው ኡካሻ የሚባሉ ሰሀባ ተነሱና ፊዳከ ቢአቢ ወኡሚ ወላሂ ያረሱለላህ በአላህ ይሁንባችሁ አያልክ ደጋግመው ባይጋብዙ
ኖሮ ወላሂ እኔ ለእዚህ ጉዳይ እምቆም አልነበርኩም ።
በእርግጥ አንድ ቀን ከእርስዎ በደል ደርሶብኛል ፊዳክ አቢ ወኡሚ ያረሱለላህ☞ ከእለታት አንድ ቀን አንቱ ጋር ጦርነት ላይ አላህ ማሸነፍን አድሎን ሰጥቶን ወደየቤታችን ልንመለስ እያልን ሳለን ያንቱ ግመል ከእኔ ግመል አጠገብ ለአጠገብ ሆነው ነበር።
እናም እኔ የእግረዎትን ጡንቻ ለመሳብ ከግመሌ ወረድኩ ወደ እግረዎ ዝቅ ስል በእጅዎ የያዙትን አለንጋ ዝቅ ሲያደርጉ ወገቤን እስከ ሆዴ
ጭምር መቱኝ ሆን ብለው ነው የመቱኝ ወይስ አለንጋውን ከፍ ለማድረግ አላቸው?
☞ረሱል ሰ,ዐ,ወ አሉ ኧረ አውቄ እማ ከመምታት አላህ ይጠብቀኝ አላወኩም አሉት ።
.
እና አሁን ምን ትፈልጋለክ ሲሉት እኔማ እምፈልገው የመቱብኝ ቦታ መምታት ነው አላቸው ለረሱል (ሰዐወ)
☞ረሱል ሰ,ዐ,ወ ቢላልን ጠሩትና ያ ቢላል በል ከፋጡማ ረ,ዐ ቤት ሂድና አለንጋዋን አምጣ ብለው አሉት።
.
ቢላልም ሄዶ ያ ፋጡማ ቢንት ረሱል ሰ,ዐ,ወ
ረሱል ሰ,ዐ,ወ አንቺ ጋር ያስቀመጡትን አለንጋ ላኪ ብለውሸል አላት።
ያ ቢላል ዛሬ የሀጅ ቀን ወይም የዘመቻ ቀን አይደለም ምን ሊያደርጉት ነው አለችው።
ቢላልም ቀጠለና ያ ፋጢማ አልሰማሽም እንዴ ነብዩ ሰ,ዐ,ወ የደረሰባቸውን የተባሉትን አልሰማሽምን?
.
ነብዩ ሰ,ዐ,ወ ከዚህ አለም አየሞቱ ወደ እዛኛው አለም እየተሸጋገሩ እኮ ነው ። ያ ፋጡማ አልሰማሽም እንዴ መሄዴ ነው እና በቀል ካላችሁ ተበቀሉኝ አሉ እኮ ታዳ ማነው ነብዩን እሚመታ እሳቸውን እሚገርፍ?
ያ ቢላል ማነው ሀሰን እና ሁሴንን ውሰድ እና በረሱል ቦታ ይገረፉው እነሱ እያሉ ረሱል ሰ,ዐ,ወ አይገረፉውም አለች አለንጋውን ለረሱል ሰ,ዐ,ወ ወስዶ ሰጣቸው።
.
እሳቸውም ተቀበሉና ያ ኦካሻ በል ወገቤም ሆዴም የሄው ምታኝ አሉት ኦካሻም ሊመታቸው ተነሳ ያኔ አቡበከር ረ,ዐ ቆሙ ኡመርም ረ,ዐ ተነሱ ያ ኦካሻ እኛ እያለን ረሱልን እንዳትነካብን አሉ ።
.
ይሄው እኛ ቆመናል እኛን ግረፍ አሉት ።
እሳቸውን እንዳትመታብን ያ ኦካሻ እያሉ የማፀኑት ጀመር።
ረሱል ሰ,ዐ,ወ እንቢ ያ አቡበከር እንቢ ያ ኡመር አላህ ሱ,ወ ለእኔ ያላችሁን ቦታ አውቋል አይቷል ወዶታል እና ተቀመጡ አሉ ።
ምታኝ ያ ኦካሻ ሲሉት አልይ ኢብን አቡጣሊብ ረ,ዐ ተነሳና ያው እኔን እንደፈለክ ወገቤም ሆዴም አደራ ብየሀለሁ ረሱልን እንዳትነካብኝ እኔን እንደፈለክ አርገኝ አለ።
ረሱል ሰ,ዐ,ወ ያ አልይ አላህ ያንተንም ለእኔ ያለህን ቦታ ወዶታል ቁጭ በል አሉት ።
.
የዛኔ የፋጡማና አሊ ረ,ዐ ልጆች ሀሰንና ሁሴን ተነሱ እና ያ ኦካሻ የረሱል ሰ,ዐ,ወ የልጅ ልጆች መሆናችንን አታውቅምን ነብዩን እንዳትነካ እኔን እኔን ግረፍ አማና ያ ኦካሻ እያሉ የማፀኑ ጀመር ።
ይህኔ ረሱል ሰ,ዐ,ወ ያ ቁረተል እዩኒና አይደለም ተቀመጡ አሎቸው።
.
☞ያ ኦካሻ እምትመታኝ ከሆነ ምታኝ አሉት።
ያረሱለላህ እርስወ እኮ የመቱኝ ሆዴ ክፍት ሆኖ ነው እንዴት አድርጌ ከእነ ልብስዎ ልምታወት ይህኔ የኸው ሆዴ በለው ገለጡለትና ምታኝ አሉት ።
.
ይህኔ ሰሀባዎች በእንባ ተራጩ ። ያ ኦካሻ አይከብድህም አታፍርም ነብዩን ልትመታ ነው? እያሉ ይጮሀሉ ።
.
የነብዩ ሰ,ዐ,ወ ሆድ በሚያይ ሰአት በሚገርም ሁኔታ ፊዳከ ቢአቢ
ወኡሚ ፊዳከ ቢአቢ ወኡሚ እያለ ይስማቸው እየላሳች ይጮሀል ።
ይህኔ ረሱል ሰ,ዐ,ወ ያ ኦካሻ ወይ ምታ ወይ አፉው በል አሉት።
አላህ የውመል ቂያማ አፉዉ እንዲለኝ አፉው ብየዎታለሁ እኔ እኮ ልመታወት ፈልጌ አይደለም ቆዳየ ከቆዳወ ጋር አንዲላተም እንዲገናኝ ብየ ነው።
.
ረሱል ሰ,ዐ,ወ ተናገሩ ጀነት ውስጥ የእኔ ጎደኛ የሆነን ሰው ማየት እሚፈልግ ካለ ወደ እዚህ ሽማግሌ ይይ አሉ። እንዳለ ሰሀባዎች የኡካሻን ግንባር እየሳሙ የረፊቅል አእላ ባለቤት እያሉ ያለቅሳሉ ኦካሻም ያለቅሳል
ሰሀባዎች ይህን ያህል ነብዩ ሰ,ዐ,ወ ያፈቅሮቸው ነበር ።
እኛስ?
@theamazingquran
@theamazingquran
ረሱል ሰ.ዐ.ወ ከሶሃቦቻቸው ጋር ቁጭ ብለው በዱኒያ ላይ በጣም ስለሚዎዷቸው ነገሮች
አየተጨዋወቱ እያሉ ነብዩ አቡበክርን "ያ አባ በከር አንተ በዱኒያ ላይ በጣም የምትወደው
ነገር ምንድነው?" ብለው ጠየቁት።
አቡበክርም "3 ነገሮችን እወዳለሁ:-
1.ከአንተ ጋር መቀመጥ፣
2.አንተን ማየት፣
3.አንተ ባዘዝካቸው ነገሮች ላይ በሙሉ ገንዘቤን መለገስ" ብሎ መለሰ።
°
ዑመርን በተራው ጠየቁት "አንተስ ያዑመር ?"
"በዱኒያ ላይ 3 ነገሮችን እወዳለሁ
1.በድብቅ እንኳን ቢሆን በመልካም ነገር ማዘዝ፣
2.በግልጽ እንኳን ቢሆን ከመጥፎ ነገር መከልከል፣
3 መራራ እንኳን ቢሆን እውነትን መናገር።" ብሎ መለሰ።
°
ዑስማንን ጠየቁት "አንተስ ያዑስማን?
በዱኒያ ላይ 3 ነገሮችን እወዳለሁ:-
1.ሰዎችን ማብላት፣
2.ሰላምታን ማብዛት፣
3.ሰዎች በተኙ ጊዜ ሶላትን ማብዛት፣
°
አልይን በተራው ጠየቁት "አንተስ ያአልይ ?"
"በዱኒያ ላይ 3ነገሮችን እወዳለሁ:-
1.እንግዳን ማክበር፣
2.በሙቀት ወቅት ፆምን መፆም፣
3.ጠላቴን በሰይፍ መቅላት፣
°
አባ ዘርን በተራው ጠየቁት "አንተስ ያአባ ዘር?"
"በዱኒያ ላይ 3 ነገሮችን እወዳለሁ :-
1.እርሃብን እወዳለሁ፣
2.በሽታን እወዳለሁ፣
3.ሞትን እወዳለሁ፣
ነብዩም "ያ አባ ዘር ለምን እነዚህን ወደድክ?"
አቡዘር መለሰ "ረሃብን ወደድኩት ቀልቤን ፈሪ ሊያደርግልኝ ዘንድ፣
በሽታን ወደድኩት ወንጀሌን ሊያቀልልኝ ዘንድ፣
ሞትን ወደድኩት ከጌታየ ጋር ሊያገናኜኝ ዘንድ።" ብሎ መለሰ።
°
ነብዩ ሰለላሁ አለየሂ ወሰለም " እኔም በዱኒያ ላይ
3 ነገሮችን እወዳለሁ:-
1.ሽቶን እወዳለሁ፣
2.ሚስቶቼን እወዳለሁ፣
3.የአይኔ ማረፊያ ሶላቴን እወዳለሁ፣
በዚህ መካከል ድንገት ጅብሪል ዱብ አለ ሰላምታ ካወረደ በኋላ እንዲህ አለ
"አንቱ የአላህ መልዕክተኛ በዱኒያ ላይ እኔም 3 ነገሮችን እወዳለሁ
ነብዩም ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም "ምንድናቸው ያ ጀብሪል?" ብለው ጠየቁት።
1.መልዕክትን ማድረስ፣
2. አማናን አደራን መጠበቅ፣
3.ሚስኪኖችን መውደድ፣
ጅብሪል ተመልሶ ወደ ሰማይ ከወጣ በኋላ ረሱልና ሱሃቦቻቸው ከመቀመጫቸው ሳይነሱ
ተመልሶ ወደ መሬት ዱብ አለ አሁንም ሰላምታውን አቅርቦ:-
"አላህም ሰላም ብሏችኋል ካለ በኋላ አላህም እንዲህ ብሏል:-
በዱኒያ ላይ 3 ነገሮችን እወዳለሁ:-
1.አላህን አውሺ የሆነችን ምላስ፣
2.አላህን ፈሪ የሆነችን ቀልብ፣
3.መከራ የበዛበት ታጋሽ የሆነችን ጀሰድ።
አላህ ታጋሾች አድርጎ ነብዩና ሱሃቦች የወደዱትን ያስወድደን
አሚን ያረበልአለሚን
🖐 كلام اعجبني ..................
ካስገረሙኝ ንግግሮች 🖐

🔲 عندما تولد لا تعلم
من الذي أخرجك من بطن أمك
🔲በምትወለድበት ጊዜ ከእናትህ ሆድ ያወጣህን ፈፅሞ አታውቅም።

🔳 وعندما تموت لا تعلم
من الذي أدخلك إلى قبرك
🔳 በምትሞትበት ጊዜ ማን ወደ ቀብርህ እንዳስገባህ ፈፅሞ አታውቅም።

*🔲 عجبا لك ياابن آدم*ትዝ ባለ ትዝ
*🔲 የአደም ልጅ ሆይ! ትገርማለህ።*

🔳 عندما ولدت تغسل وتنظف
🔳 በተወለድክ ጊዜ ትታጠባለህ፣ ትፀዳለህ።

🔲 وعندما تموت تغسل وتنظف
🔲 በምትሞትበት ጊዜ ትታጠባለህ፣ ትፀዳለህ።
*🔳 عجبا لك ياابن آدم*
*🔳 የአደም ልጅ ሆይ! ትገርማለህ።*

🔲 عندما تولد لاتعلم من فرح واستبشر بك
🔲 በተወለድክ ጊዜ በውልደት ማን እንደተደሰተ እና እንደተበረሰ አታውቅም።

🔳 وعندما تموت لاتعلم من بكى عليك وحزن
🔳 በሞት ጊዜ በመሞትህ ማን እንዳለቀና እንደአዘነ አታውቅም።


*🔲 عجبا لك ياابن آدم*
*🔲 የአደም ልጅ ሆይ! ትገርማለህ*

🔳 في بطن أمك كنت في مكان ضيق ومظلم
🔳 በእናትህ ሆድ ውስጥ በጠባብ ቦታና በጨለማ ውስጥ ነበርክ።

🔲 وعندما تموت تكون في مكان ضيق ومظلم
🔲 በምትሞትበት ጊዜ በጠባብ ቦታና በጨለማ ውስጥ ትሆናለህ።

*🔳 عجبا لك ياابن آدم*
*🔳 የአደም ልጅ ሆይ! ትገርማለህ*

🔲 عندما ولدت تغطى بالقماش ليستروك
🔲 ስትወለድ በጨርቅ ትጠቀለላህ ሊሸፍኑህ!

🔳 وعندما تموت تكفن بالقماش ليستروك
🔳 ስትሞት በከፈን ይጠቀልሉሃል ሊሸፍኑህ!

🔲 عجبا لك ياابن آدم
🔲 የአደም ልጅ ሆይ! ትገርማለህ

🔳 عندما ولدت وكبرت يسألك الناس
عن شهادتك وخبراتك
🔳 በተወለድክና በአደግክ ጊዜ ሰዎች ስለምስክር (ወረቀትህና) ስለሙያህ ይጠይቁሃክ።

🔲 وعندما تموت تسألك الملائكة عن عملك الصالح
🔲 በሞትክም ጊዜ መልዓይኮች ስለመልካም ስራህ ይጠይቁሃል።

*🔳 فماذا أعددت لآخرتك ؟*
*🔳 ለመጨረሻው ሃገርህ ምን አዘጋጀህ?*

🔲 جرب تقولها من قلب :
آشهد آن لآ آله آلآ آلله
واشهد آن محمد رسول آلله
🔲 ከልብህ ይህችን (ቃል) ለመናገር ሞክር! ።ከአላህ ሌላ በፍፁም የሚመለክ አምላክ እንደሌለ መስክር። እንዲሁም ሙሃመድ የአላህ መልክተኛ መሆናቸውን መስክር።

🔳 مستحيل تقرآها بدون ما ترسلها
🔳 (ይህን መልእክት) በፍፁም ሳታነባድ እንዳትልካት!!

& & &
‏ بسم الله الرحمن الرحیم
*{ قل هو الله أحد * الله الصمد * لم يلد ولم يولد * ولم يكن له كفواً أحد }*


*ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ*
*{ በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው። አልወለደም፤ አልተወለደምም። ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።}*

@theamazingquran
🔻ትልቁ ቅሌት ሌሎችን ያነወርንበትን ወንጀል እኛ ስንሠራው ነው።
🔷ትልቁ እፍረት ሌሎችን ያሽማቀቅንበትን ድርጊት እኛ ስንደግመው ነው።
ኢላሂ
ሌሎች ላይ አይተን በጠላነው ወንጀል አትፈትነን።
ሌሎችን ባነወርንበት ነውር ላይ አትጣለን።
ሌሎች ሲሠሩት አይተን በሳቅንባቸው ስህተቶች አታዳልጠን።
اللهم امين يا رب برحمتك نعش
ተጋበዙልኝ አጭር ግን አስተማሪ ታሪክ

☞መግባት እና መውጣት☜

አንድ ገበሬ የሚወደው ፈረሱ ይታመምበትና ወደ እንስሳት ሀኪም ጋር ይዞት ይሄዳል። ሀኪሙም ፈረሱ ጉረኖ ድረስ በመሄድ በሚገባ መረመረው።

ለገበሬውም - "ተላላፊ በሽታ ስላለበት ለሶስት ቀን መድሀኒት እንስጠውና
ካልተሻለው ወደሌሎቹ ፈረሶች እንዳይዛመት እንገለዋለን" ብሎት ሄደ።

ይሄንን ሲያወሩ ፍየል ተደብቃ ሰምታቸው ኖሯል ለፈረሱ እያለቀሰች ያወሩትን ነገረችውና "እንደምንም ብለህ ተነስ!
ያለበዛ ይገሉሀል" እያለች ተንሰቀሰቀች።
የመጀመርያው ቀን ሀኪሙ መጥቶ መድሀኒቱን ሰጥቶት ወጣ። ወድያው ፍየል ለምለም ሳርና አተላ ይዛለት መጣች ና "እንደምንም ተነስ!" ብላ ተማፀነችው።


በሁለተኛውም ቀን ሀኪሙ ሲመጣ ፈረሱ ምንም ለውጥ አላመጣም መድሀኒቱን ወግቶት እስከ ቀጣዩ ቀን ጠብቆት ካልተሻለው እንደሚገለው ለገበሬው ነግሮት ሄደ።

ይሄን ግዜ ፍየል ለምለም ሳር ፈልጋ ለፈረሱ በማምጣት አፅናናችው። የመጨረሻ ቀን ሀኪሙ ሲመጣ አሁንም ፈረሱ ምንም ለውጥ አላመጣም ይሄን ጊዜ ከገበሬው ጋር ቢገሉት እንደሚሻል በር ላይ ቆመው ሲያወሩ ፍየል ቀስ ብላ ተደብቃ ፈረሱ ጋር ገብታ እየተንሰቀሰቀች-
"በናትህ አኔንም ጓደኛ አታሳጣኝ ካልተነሳህ ይገሉሀል" ብላ አለቀሰች።
ፈረሱ በፍየሏ ግፊት ቀስ ብሎ ተነሳ።
ፍየል ደስ አላት። "ጎበዝ አስኪ እሩጥ" እያለች አበረታችው። ፈረሱ በወኔ በፊት
ከሚሮጥበት ፍጥነት በላይ ሮጠ። ይሄን ጊዜ ፍየል በደስታ ጮኸች።
ገበሬውና ሀኪሙ የምን ጩኸት ነው ብለው ሲያዩ
ያዩትን ማመነን አቃታቸው።ፈረሱ በሓይል አየሮጠ ነው። ገበሬው በደስታ ብዛት ሀኪሙን አንቆ ሳመው።
*
*
*
*
እረኛውን ጠርቶት "ዛሬ እኔ ቤት ትልቅ ድግስ አለ! ስለዚህ ቶሎ በሉ ፍየሏን እረዱልኝ! ምሳ እዚህ ነው" አለ።

አንዱ የሌላው መሰላል ነው።
ለአንዱ ሂወት ለሌላው ሞት ነው። ለሀብታም ሂወት የደሀው ችግር ግድ ነው።
ለአንዱ ማለፍ የሌላው ውድቀት ወሳኝ ነው።
አለም የምትመራበት ህግ ነው።

መግባት እና መውጣት፡፡
▪️▪️▪️▪️▪️▪️▪️▪️▪️▪️▪️▪️▪️
<<ለሰዎች ከተገለጸች ሕዝብ ሁሉ በላጭ ኾናችሁ በጽድቅ ነገር ታዛላችሁ፤ ከመጥፎም ነገር ትከለክላላችሁ፤ በአላህም (አንድነት) ታምናላችሁ፡፡.....>>3፥110


.
.


ለአስተያየት @quraniccbot

የምንለቃቸው ማስታወቅያዎች እኛን አይወክሉንም!

Find as on:
👉FB
https://bit.ly/3bCWvtY

👉youtube
https://bit.ly/2MmQqpq
🤔ለፈገግታ😁

👱አንዱ ሰውዬው ወንዝ ዳር ቁጭ ብሎ ያለቅሳል😭😭😭

👀ይህንን የተመለከተ አንድ🙎‍♂ ሰው ወደ እርሱ ይመጣና "ለምንድነው የምታለቅሰው?" ይለዋል

👱ሰውዬውም " አንድ ማንኪያ ሙሉ ስኳር እዚህ ወንዝ ውስጥ ጨምሬ የወንዙን ውሃ ብቀምሰው ምንም አይጣፍጥም"😢ሲለው

🙎‍♂፡ ሌላኛው ሰውዬ ሳቁን ይለቀዋል😂፡፡

👱ሰውዬው----"ምን ሆነህ ነው የምትስቀው?"😡ይለወን

 " " " " " " " "
🙎‍♂አንተ ጅል! መጀመሪያ አታማስለውም ነበር ብሎ ቁጭ
እኛስ ቁርኣን ስንቀራ ምን አይነት ስሜት ይሰማናል?

"የነብዩ ﷺ ሶሐቦች ቁርኣንን ሲሰሙ እንዴት ነበር?" ተብላ የተጠየቀችው አስማእ ቢንት አቡበክር መልሷ እንዲህ የሚል ነበር:–
"تدمع أعينهم وتقشعر جلودهم، كما نعتهم الله".
"አይኖቻቸው ያነባሉ። ቆዳዎቻቸው ይኮማተራሉ። ልክ አላህ እንደገለፃቸው!" 📚أخرجه البيهقي ٢/٣٦٥.
እኛስ በምንድን ነው የምናለቅሰው? ለመሆኑ ቁርኣንን ስንቀራ በዛቻው እንፈራለን? በተስፋ ቃሉ እንቋምጣለን? ታሪኩን እናጣጥማለን? ኧረ ይህም ይቅር ለመሆኑ ቁርኣን እንቀራለን? መልሱ "አዎ" የሆነ ሰው ምንኛ የታደለ ነው? ግን መቼ ነው የምንቀራው?
በየቀኑ?
በሳምንት?
ጁሙዐ?
በአመት ረመዳን ወር? መቼ?
አላህ ይድረስልን።

ነገ አዋጅ አለ! እንዲህ የሚል ነብያዊ አዋጅ!
(وَقَالَ الرَّسُولُ يَا رَبِّ إِنَّ قَوْمِي اتَّخَذُوا هَٰذَا الْقُرْآنَ مَهْجُورًا)
[ الفرقان 30]

"መልክተኛውም ‘ጌታዬ ሆይ! ሕዝቦቼ ይህንን ቁርኣን የተተወ ነገር አድርገው ያዙት’ አለ፡፡" [አልፉርቃን: 30]
@theamazingquran
2025/07/10 00:03:53
Back to Top
HTML Embed Code: