TIKVAH-ETHIOPIA
" ይህንን የድካም ዓለም መገላገል ለእርሳቸው ዕረፍት ቢሆንም ለአገር ግን ታላቅ ጉዳት ነው " - ቅዱስነታቸው " እግዚአብሔር በየዘመናቱ አገርን ያለ መካሪ፣ ሕዝብን ያለዘካሪ አይተወውም ! " ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ እረፍት የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል።…
ፎቶ፦ የታላቁ አባት የተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ አስክሬን ፒያሳ በሚገኘው ኑር መስጂድ የዱዓ እና የሽኝት ሥነ-ሥርዓት ተካሄደ።
የተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ አስከሬን ለ40 ዓመታት ባስተማሩበት ኑር መስጂድ ሶላተል ጀናዛ ተሰግዶበታል።
ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ ሥርዓተ ቀብራቸው የሚፈፀም ይሆናል።
Photo Credit - EBC & ENA
@tikvahethiopia

2😢988❤361😭200🕊49🙏41🥰7😡7💔5🤔4😱2👏1
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የ2018 የቲክኒክና ሙያ ሰልጣኞች መግቢያ ነጥብ ይፋ አድርጓል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመለከተው የተቋሙ ደብዳቤ፣ በ2018 ዓ/ም የስልጠና ዘመን ወደ ቲክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት የሚገቡ ሰልጣኞች የመግቢያ ነጥብ በ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ውጤታቸው መሰረት ለተፈጥሮና ማህበራዊ ሳይንስ የመግቢያ ውጤት ከደረጃ 1 እስከ 5 በዝርዝር አስቀምጧል።
የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ እና ቅድመ ዝግጅት (12ኛ ክፍል) ላጠናቀቁ ደረጃ 1 እና ደረጃ 2 ሰልጣኞች መቁረጫ ነጥብ፦
-ለወንዶች አርብቶ አደር አካባቢዎችን ሳይጨምር 134 እና ከዚያ በታች፣
-ለወንዶች አርብቶ አደር አካባቢዎች 132 እና ከዚያ በታች፣
-ሴቶች አርብቶ አደር አካባቢዎችን ሳይጨምር 121 እና ከዚያ በታች፣
-ሴቶች አርብቶ አደር አካባቢዎች 120 እና ከዚያ በታች፣
-ለሁሉም ክልል አካል ጉዳተኞች 120 እና ከዚያ በታች ሆኖ ተቆርጧል።
የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ እና ቅድመ ዝግጅት (12ኛ ክፍል) ላጠናቀቁ ደረጃ 3 እና 4 ሰልጣኞች መቁረጫ የጥብ፦
-ወንዶች አርብቶ አደር አካባቢዎችን ሳይጨምር 135 እና ከዚያ በላይ፤
-ወንዶች አርብቶ አደር አካባቢዎች 133 እና ከዚያ በላይ፤
-ሴቶች አርብቶ አደር አካባቢዎችን ሳይጨምር 122 እና ከዚያ በላይ፤
-ሴቶች አርብቶ አደር አካባቢዎች 121 እና ከዚያ በላይ፤
-ለሁሉም ክልል አካል ጉዳተኞች 121 እና ከዚያ በላይ ሆኖ ተቆርጧል።
እንዲሁም፣ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ እና ቅድመ ዝግጅት (12ኛ ክፍል) ላጠናቀቁ ደረጃ 5 ሰልጣኞች መቁረጫ ነጥብ፦
-ወንዶች አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር 179 እና ከዚያ በላይ፤
-ወንዶች አርብቶ አደር አካባቢዎች 168 እና ከዚያ በላይ፤
-ሴቶች አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር 168 እና ከዚያ በላይ፤
-ሴቶች አርብቶ አደር አካባቢ 157 እና ከዚያ በላይ፤
-ለሁሉም ክልል አካል ጉዳተኞች 142 እና ከዚያ በላይ ሆኖ ተቆርጧል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

1❤897😭47🙏43🤔22😡20👏17🕊15💔15🥰6😱4😢2
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ፦ የታላቁ አባት የተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ አስክሬን ፒያሳ በሚገኘው ኑር መስጂድ የዱዓ እና የሽኝት ሥነ-ሥርዓት ተካሄደ። የተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ አስከሬን ለ40 ዓመታት ባስተማሩበት ኑር መስጂድ ሶላተል ጀናዛ ተሰግዶበታል። ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ ሥርዓተ ቀብራቸው የሚፈፀም ይሆናል። Photo Credit - EBC & ENA @tikvahethiopia
የታላቁ የሃይማኖት አባት የቀድሞው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ሥርዓተ ቀብር ተፈጽሟል።
ከስርዓተ ቀብራቸው ቀደም ብሎ በሚሊኒየም አዳራሽ ሽኝት ተደርጓል።
ታላቁ የሃይማኖት አባት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር በታላቁ አንዋር እና በኑር (በኒ) መስጂዶች ከአራት አስትርት ዓመታት በላይ ኢስላማዊ ሃይማኖታዊ ትምህርት አስተምረዋል።
ከ50 በላይ ሃይማኖታዊ መጽሐፍትንም ጽፈዋል፡፡
ቅዱስ ቁርአንንም ተርጉመዋል፡፡ የቁርአን ትርጉም ሥራቸውን በሲዲ በማሳተም አሰራጭተዋል፡፡
ከ50 ዓመታት በላይ በዘለቀ የአዲስ አበባ ቆይታ ቅዱስ ቁርአንን ከ300 ጊዜ በላይ በትርጉም (ተፍሲር) አስተምረዋል፡፡
ተቀዳሚ ሙፍቲ በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች የተፈጠሩ ሃይማኖታዊ አለመግባባቶችን በመፍታት የሃይማኖታዊ አባትነታቸውን ሚና ተወጥተዋል።
በ1967 ዓ.ም የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ሲመሰረት የምክር ቤቱ አባልና የዑለማ ሊቀመንበር በመሆን አገልግለዋል።
ከ2010 መጋቢት እስከ ግንቦት ወር 2014 ዓ.ል ድረስ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትን በፕሬዚዳንትነት እንዲሁም የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ በመሆን አገልግለዋል፡፡
ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ባለትዳርና የአምስት ወንዶችና የአራት ሴቶች አባት እንደነበሩ ከጠቅላይ ምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

❤1.85K😭777🕊102💔86🙏54😢44🥰23🤔19😱15😡11