Telegram Web Link
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Earthquake

ዛሬ ጥቅምት 10 ቀን 2018 ዓ.ም ምሽት ላይ ከዓዲግራት ደቡባዊ ምስራቅ 43 ኪሎሜትር የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ በበርካታ አከባቢዎች ላይ ንዝረት ተሰምቷል።

ከምሽቱ 1:30 የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ በሬክተር ስኬል 4.5 የተለካ እንደሆነ የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቨይ መረጃ ያሳያል።

የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረቱ ከተሰማባቸው አካባቢዎች አንዷ የትግራይ መዲና መቐለ ስትሆን ንዝረቱ በተለይም በፎቅ/ህንፃዎች ላይ አስፈሪ ስሜት እንደነበር የቲክቫህ ኢትዮጵያ መቐለ ቤተሰብ አባል ገልጿል።

ከጥቅምት 2 ቀን 2018 ዓ.ም ወዲህ ንዝረቱ ትግራይ እና አፋር በርካታ አካባቢዎች ጎልቶ የሚሰማ የተለያየ ልኬት ያለው መሬት መንቀጥቀጥ እየተሰማ ነው።

በተለይ እሁድ ጥቅምት 2/2018 ዓ.ም የተከሰተው በሬክተር ስኬል 5.6 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ አፋር ክልል የሰው ህይወት ቀጥፎ በርካታ ቤቶችን አፍርሶ ከ40 ሺህ በላይ ሰዎች ያለመጠለያ እንዲቀሩ አድርጓል። በተመሳሳይ በትግራይ ምስራቃዊ ዞን አፅቢ ወምበርታ ወረዳ ቤቶች እንዲፈርሱ ምክንያት ሆኗል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
473😭160🙏38😱24🕊22💔16😢15👏10🥰3😡2
TIKVAH-ETHIOPIA
" ኢትዮጵያ በጣት ከሚቆጠሩ አረጋውያን፣ አፈ ማር ከሆኑ መካሪዎችዋ መካከል አንዱ የሆኑትን፣ ለመወደድ የታደሉትን የዘመናችን ጌጥ አጥታለች። ይህንን የድካም ዓለም መገላገል ለእርሳቸው ዕረፍት ቢሆንም ለአገር ግን ታላቅ ጉዳት ከመሆኑም በላይ ዕድሜን ከጥበብ ጋር ያዋሐዱ በሁሉ ዘመን አይገኙምና ኀዘናችን ጥልቅ ነው። " - ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ  ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ…
" ሀገራችንን አላህ ሰላም ያድርግልን። ሀገራችንን አላህ አማን ያድርግልን።

እኛም የምንዋደድ አላህ ያድርገን። የምንከባብር አላህ ያድርገን። የምንረዳዳ አላህ ያድርገን። የምንመካከር አላህ ያድርገን።

ጥላቻን ከውስጣችን አላህ ያጥፋው።

በሃይማኖትም ሆነ በፖለቲካ መገዳደልን፣ መጋጨትን፣ መለያየትን ከሀገራችን ከውስጣችን አላህ ያንሳልን።

እንደ አባቶቻችን ከዛም በበለጠ የምንተባበር ፣ የምንከባበር፣ የምንዋደድ ፣ የምንረዳዳ አላህ ያድረገን። " - ታላቁ አባት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ

@tikvahethiopia
🙏2.79K994😭640💔156🕊114😢61🥰30👏30😡21😱16
ዛሬውኑ የባዮሜትሪክ (የጣት አሻራና የፊት ገጽታ) ምዝገባ ያድርጉ

ውድ ደንበኛችን

ባንካችን አቢሲንያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለደንበኞቹ ቀላል፣ አመቺና ደህንነቱ የተጠበቀ እጅግ ዘመናዊ የወረቀት አልባ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል። ታዲያ ለዚህ አገልግሎት መሳካት የደንበኞች የጣት አሻራና የፊት ገጽታ ዋነኛ ግብዓት በመሆኑ፣ እርስዎም በአቅራቢያዎ ወደሚገኝ የባንካችን ቅርንጫፍ በመሄድ የባዮሜትሪክ ምዝገባ እንዲያደርጉ በአክብሮት እንጠይቃለን። አንዴ ከተመዘገቡም፣ በየጊዜው ማንነትዎን የሚገልጽ ሰነድ ማቅረብ ሳይጠበቅብዎ፣የሚፈልጉትን የባንካችንን አገልግሎት በጣት አሻራዎ ወይም በፊት ገጽታዎ ብቻ ማግኘት ይችላሉ።                                                                                                                                                  
#ወረቀትአልባየባንክአገልግሎት #Paperlessbranchmodel #BanksinEthiopia #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
274😡22🙏15🤔8😢4
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#SamiTech

አዳዲስ ላፕቶፕች ከአንድ ዓመት ዋስትና ጋር!!
@samcomptech

በጥራት፣ በብራንድና በባትሪ ቆይታ አስተማማኝ የሆኑ የተለያዩ ሞዴል ላፕቶፖች በፈለጉት ስክሪን መጠን፣ ኮር አይ እና ጀነሬሽን አሉን።

ለቢሮዎች፣ ለተማሪዎች፣ ለዲዛይን ባለሙያዎች፣ ለጌመሮች ወ.ዘ.ተ. ሁሉም አሉን።

የዕቃዎች ዋጋ፣ ዓይነት እና አድራሻ ለማግኘት 👉 @samcomptech

@sww2844
0928442662 / 0940141114

Telgram : https://www.tg-me.com/samcomptech
103🤔11😡11😭3🥰2
" ባቡሩ የተጋጨው ከዚህ ወደ ጂቡቲ ሲሄድ ሳይሆን ከደወሌ ወደ ሽንሌ እየመጣ ነው አደጋው የደረሰው " - የድሬዳዋ ኮሚኒዩኬሽን

በሶማሌ ክልል ሲቲ ዞን ሽንሌ ወረዳ በደረሰ የባቡር አደጋ እስካሁን ባለው መረጃ 12 ሰዎች መሞታቸውን የድሬዳዋ ከተማ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

የሽንሌ ወረዳ አስተዳደር በበኩሉ፣ የሟቾቹን ቁጥር 14 ነው ያለ ሲሆን ከ28 የሚልቁት ደግሞ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው አሳውቋል።

ወረዳው " አደጋው የደረሰው ከደወሌ መነሻውን አድርጎ ወደ ድሬዳዋ በመጓዝ ላይ የነበረ የድሬዳዋ ደወሌ የምድር ባቡር ድርጅት የህዝብ ማመላለሻ ባቡር ትላንት ሌሊት 8:00 አካባቢ በሶማሌ ክልል ሺኒሌ ወረዳ አካባቢ አነስተኛ ዳገታማ ስፍራ ላይ የኋለኛው ፉርጎ ተነጥሎ ወደ ኋላ በመመለሱ ለጥገና ከቆመ ሌላ ባቡር ጋር በመጋጨቱ ነው " ብሏል።

ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃላቸውን የሰጡት አንድ የድሬዳዋ ከተማ ኮሚኒኬሽን አካል " አደጋው ደርሷል። እስካሁን ባለው መረጃ ወደ 12 የሚሆኑ ሰዎች ሞተዋል። ከባድና ቀላል የአካል ጉዳትም ደርሷል " ብለዋል።

አደጋው የደረሰው ባቡሩ " ወደ ጂቡቲ ሲጓዝ ነው " ሲባል የተስተዋለ ሲሆን፤ የቢሮው አካል ግን " ባቡሩ የተጋጨው ከዚህ ወደ ጂቡቲ ሲሄድ ሳይሆን ከደወሌ ወደ ሽንሌ እየመጣ ነው አደጋው የደረሰው " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

" አደጋው የደረሰበት ትክክለኛ ቦታ ሽንሌ ነው፤ ባቡሩ ከደወሌ ወደ ሽንሌ ከዛ ወደ ድሬዳዋ ነው የሚገባው " ሲሉም አክለው አስረድተዋል። ዝርዝር መረጃውን ወደ ስፍራው የተላኩ አካላት እንዳደረሷቸው እንደሚያሳውቁ ገልጸዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተጨማሪ ማብራሪያ የጠየቃቸው የከተማ አስተዳደሩ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ብሩክ ፈለቀ፣ ጉዳዩን አጣርተው ማብራሪያ እንደሚሰጡ ገልጸዋል። 

ለተጨማሪ መረጃ ወደ ሽንሌ ወረዳ ያደረግነው መኩራ ስልክ ባለመነሳቱ ለጊዜው አልተሳካም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
😭871710💔65😢44🕊38😱20🤔9🥰7🙏5😡4
#BenishangulGumuz

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግሥት ከዘንድሮ ዓመት ጀምሮ የክልሉ የትምህርት ቋንቋ #አማርኛ እንዲሆን እና ሰባት የአፍ መፍቻ ቋንቋዎች " እንደ አንድ የትምህርት ዓይነት" እየተሰጡ እንዲቀጥሉ ወስኗል።

" ጊዜያዊ ነው " የተባለው ይህ አሠራር በዚህ ዓመት በቅድመ መደበኛ (ኬጂ) እና በአንደኛ ክፍል ተማሪዎች ላይ የሚተገበር ሲሆን በየዓመቱ ወደ ሌሎች የክፍል ደረጃዎች እያደገ እንደሚሄድ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገልጿል።

የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች መኖሪያ የሆነው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ፤ በክልሉ በሚነገሩ አፍ መፍቻ ቋንቋዎች ትምህርት መስጠት የጀመረው በ2001 ዓ. ም. ነበር።

የመማር ማስተማሪያ ቋንቋ ሆነው ከሚያገለግሉት አፍ መፍቻዎች መካከል ፦
- ቤኒሻንጉልኛ፣
- ጉምዝኛ፣
- ሽናሽኛ እና ማኦኛ ይገኙበታል።

ኮሞኛ፣ ጓምኛ፣ ኦሮምኛ እና አማርኛም ትምህርት ይሰጥባቸው ከነበሩ የአፍ መፍቻ ቋንቋዎች መካከል ናቸው።

በክልሉ የሚገኙ ተማሪዎች ከአንደኛ ክፍል ጀምሮ ሒሳብ እና የሳይንስ ትምህርት አይነቶችን በእነዚህ ቋንቋዎች የሚማሩ ሲሆን ሰባተኛ ክፍል ላይ የመማር ማስተማሪያ ቋንቋው እንግሊዘኛ ይሆናል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ትምህርት ቢሮ በክልሉ ላሉ የወረዳ፣ ልዩ ወረዳ ከተማ አስተዳደር መዋቅሮች በጻፈው ደብዳቤ ከዘንድሮ የ2018 ትምህርት ዘመን አንስቶ ይህ አሠራር መቀየሩን አስታውቋል።

የቢሮው ኃላፊ ዶ/ር ተመስገን ዲሳሳ ውሳኔው መተላለፉን ለቢቢሲ አማርኛ አረጋግጠዋል።

በቢሮ ኃላፊው የተጻፈው ደብዳቤ እንደሚያስረዳው ላለፉት 17 ዓመታት ተግባራዊ ሲሆን የቆየው አሠራር የተቀየረው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግሥት ካቢኔ ባለፈው ወር መስከረም 10/2018 ዓ. ም. ያሳለፈውን ውሳኔ ተከትሎ ነው።

ከሁለት ሳምንት በፊት በመስከረም 21 ለክልሉ ትምህርት ቢሮ የደረሰው የካቢኔው ውሳኔ የተመሠረተው፤ በ2017 ዓ. ም. በተደረገ ጥናት ላይ እንደሆነ ተጠቅሷል።

ደብዳቤው፤ የአፍ መፍቻ ቋንቋዎቹ በመማሪያ ማስተማሪያነት ጥቅም ላይ በሚውሉበት ጊዜ "የሚፈለገውን ውጤት ማምጣት እንዳልተቻለ" ይገልጻል።

ይህ የሆነውም "ከሚያስፈልገው የመምህራን ቁጥር እና ብቃት፣ ከግብአት እና ከሌሎች ችግሮች" ጋር በተያያዘ እንደሆነ ይገልጻል።

የትምህርት ቢሮው ኃላፊው ዶ/ር ተመስገን፤ " መምህራን በቂ አይደሉም፤ እንደውም የሉም ማለት ይቻላል። ያሉትም ላይ የአቅም ማነስ አለ " ሲሉ ተናግረዋል።

" ሕጻናት በራሳቸው ቋንቋ በሚማሩበት ጊዜ አካባቢውን በአግባቡ ይረዳሉ፣ የትምህርት ይዘቱንም ይረዳሉ ተብሎ ይታሰባል " ያሉት ዶ/ር ተመስገን፤ " ይህ ሊሆን የሚችለው ግን ሊያስተምር የሚችል፣ በራሱ ብቁ የሆነ መምህር ሲኖር ነው " ብለዋል።

ቋንቋዎቹን እንደ አንድ የትምህርት ዓይነት ለመስጠት የሚሆን የመምህር እጥረት አለመኖሩን የሚናገሩት ኃላፊው፤ ሒሳብ እና ሌሎች የሳይንስ ትምህርቶችን በአፍ መፍቻ ለማስተማር የተመረቀ መምህር ግን አለመገኘቱን ገልጸዋል።

" ያሉትም ቢሆን በሌላ ከተማሩ በኋላ ሁለት ወር ወይም አንድ ወር ቋንቋ ትርጉም እና ተያያዥ ሥልጠና የወሰዱ ናቸው " ብለዋል።

ይህ ጉዳይ " የተማሪዎች ውጤት ላይም ተጽዕኖ እያሳየ " መምጣቱን አክለዋል።

ቢሮው፤ ይህንን " ችግር ለመፍታት እና የተማሪዎችን የመማር ውጤት ለማሻሻል በ2017 ዓ. ም. ያጠናውን " ጥናት ለክልሉ ካቤኒ እንዳቀረበ ደብዳቤው ያስረዳል።

ካቤኒውም፤ " የክልሉ አቅም እስኪጎለብት እና ያሉ ችግሮች በሂደት እስኪፈቱ ድረስ በክልሉ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት መማሪያ ማስተማሪያ ቋንቋ አማርኛ እንዲሆን " ወስኗል ተብሏል።

" የአፍ መፍቻ ቋንቋዎች ደግሞ አንድ አንድ የትምህርት ዓይነት ሆነው ብቻ እንዲቀጥል " ካቢኔው ወስኗል።

የሽግግር ሂደት ዝርዝር የአፈጻጸም መመሪያ እየተዘጋጀ ነው ተብሏል።

ዶ/ር ተመስገን በዚህ ዓመት ይህ ውሳኔ መተግበር የሚጀምረው በቅድመ መደበኛ (ኬጂ) እና በአንደኛ ክፍል ተማሪዎች ላይ እንደሆነና በሚቀጥለው ዓመት ሁለተኛ ክፍል ተማሪዎች ይህንን አሠራር መተግበር እንደሚጀምሩ እና በቀጣዮቹ ዓመታት ሌሎቹም የክፍል ደረጃዎች እንደሚቀላቀሉ አብራርተዋል።

ቢሮው ይህንን አካሄድ የመረጠው ከአንደኛ ክፍል አንስቶ በአፍ መፍቻ ቋንቋ እየተማሩ ያሉ ተማሪዎች ላይ አዲስ አሠራር ላለመተግበር በማሰብ መሆኑንም ገልጸዋል።

አማርኛን በክልሉ የትምህርት ቋንቋነት የመጠቀም አሠራር የሚቀጥለው በአፍ መፍቻ ቋንቋዎቹ ብቁ የሆኑ፣ ፍላጎት ያላቸው ሠልጣኝ እና መምህራን እስከሚዘጋጁ ድረስ እንደሆነ ጠቅሰዋል።

መረጃ የቢቢሲ አማርኛ ነው።

@tikvahethiopia
11.94K👏308😡96🙏54😭31🤔28🕊19💔6😱1😢1
ዘኔክሰስ፡-
☑️ ለተጠቃሚ ምቹ የሆኑ (keypad + touchscreen) በመጠቀም የተጠቃሚዎችን ልምድ ያቀላል
☑️ ለገጠራማ እና አነስተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ላላቸው አካባቢዎች ረጅም የባትሪ ዕድሜ አለው
☑️ በተገጠመ የቴሌስቶሬጅ (teleStorage) አማካኝነት የፋይል ማከማቻ ገደቦችን ያስወግዳል
☑️ እንደ ቴሌብር፣ የትምህርት ይዘት፣ ሚዲያዎች ያሉ ወሳኝ አፕሊኬሽኖችን ተጭኖባቸዋል
☑️ ከሁሉም በላይ ደግሞ የመጀመሪያ ጊዜ ተጠቃሚዎች በቀላሉ አገልግሎቶችን እንዲጠቀሙ ያስችላል

ዘኔክሰስ ስማርት ስልክ ላይ የሚገኙ ወሳኝ መተግበሪያዎችን በክላውድ አማካይነት በማቅረብ በኢትዮጵያ ብሎም በአፍሪካ የዲጂታል ተጠቃሚነት ተግዳሮት የሆነውን የዋጋ ውድነት በዘላቂነት በመፍታት የDigital-First ማኅበረሰቦችን ዕውን ለማድረግ ያስችላል።

ለበለጠ መረጃ፡ https://bit.ly/3Wb9TgX

#Ethiotelecom #Znexus #NextHorizon #telebirr #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
164👏14🙏6🥰1💔1
ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ የኩላሊት እጥበት ህክምና መስጫ ሀዋሳ ማዕከል ማስመረቁን ገልጾልናል።

በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ተገኝተው የነበሩት የጤና ሚኒስቴር ሚንስትር ክብርት ዶ/ር መቅደስ ዳባ " የኩላሊት በሽታ ከዕድሜ መግፋት ጋር ተያይዞ የሚመጣ ነገር ግን ነው በአሁኑ ወቅት ግን ወጣቶች ጭምር በበሽታው በስፋት እየታየዙ እና ህይወታቸውን እያጡ ነው " ብለዋል።

ዶ/ር መቅደስ ዳባ ዲጂታል ኤክስ ሬይ(Digital x-ray) እንዲሁም ምርቃቱ ላይ የተገኙት የሲዳማ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ደስታ ሌዳሞ በክልሉ መንግስት እና ህዝብ ስም 10 ሚሊዮን ብር እና የሲዳማ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ ለሜሪጆይ ኢትዮጵያ ሀዋሳ ማዕከል የአምቡላንስ መኪና ድጋፍ አድርገዋል፡፡

ሌሎች የተደረጉ ድጋፎች ፦
• የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ፦ 5 ሚሊዮን ብር
• ሲዳማ ልማት ማህበር፦ 300,000 ብር
• ያኔት ሆስፒታል፦ 500,000 ብር
• ይርጋለም ኮንስትራክሽን፦ 1 ሚሊዮን ብር
• ሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ፦ 500,000 ብር

የሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ መስራች እና ስራ አስኪያጅ የሆኑት ሲ/ር ዘቢደር ዘውዴም ለተደረገው ድጋፍ እንዲሁም በእዚህ ላይ ስማቸው ያልተገለፀ እና ለፕሮግራሙ መሳካት እገዛ ያደረጉትን በሙሉ አመስገነዋል፡፡

@tikvahethiopia
649🙏103👏51🥰12🤔7😱2🕊2😭1
" የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከ9-12ኛ ክፍል ይሸፍናል " - ትምህርት ሚኒስቴር

ትምህርት ሚኒስቴር የ2018 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን በተመለከት ለሁሉም ክልሎች እና ለሁለቱ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች እንዲሁም ለትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ትናንት ጥቅምት 10/2018 ዓ.ም ደብዳቤ ልኳል፡፡

የደብዳቤውን ትክክለኝነት ቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጧል።

በሚኒስቴሩ የስርዓተ ትምህርት ማበልጸጊያ መሪ ሥራ አስፈጻማ ቴዎድሮስ ሽዋርገጥ (ዶ/ር) የተፈረመው ደብዳቤው፤ የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ከ9-12ኛ ክፍል እንደሚሸፍንና ተማሪዎች የተማሩትን ይዘቶች የሚፈተኑ መሆኑን ይገልጻል፡፡

ብሔራዊ ፈተናው ከ10ኛ እስከ 12ኛ ክፍሎች የአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ይዘቶችን መሠረት ያደረገ እንደሚሆን ተጠቁሟል፡፡

በ2015 ዓ.ም የሙከራ ትምህርት ቤቶች 9ኛ ክፍልን በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት፤ ሌሎቹ ደግሞ በቀድሞው ስርዓተ ትምህርት የተማሩ በመሆኑ ፈተናው ከሁለቱ ስርዓተ ትምህርቶች የጋራ የሆኑ ይዘቶች ተጣጥሞ የሚወጣ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በአጠቃላይ ትምህርት ስርዓተ ትምህርት ሪፎርም መሠረት የሁለተኛ ደረጃ አዲሱ ስርዓተ ትምህርት በ2015 ዓ.ም የሙከራ ትግበራ በማካሔድ ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ሙሉ ትግበራ መገባቱ ይታወቃል፡፡

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ

Via @tikvahuniversity
418😭113😡46😱20🤔19👏17🙏13💔11🕊8😢6🥰5
‎" ከ6 ዓመታት በፊት የተጀመረዉ መንገድ አለመጠናቀቁ ለዘርፈ ብዙ ችግሮች ዳርጎናል " - የሸካ ዞን ነዋሪዎች

‎በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ ዞን ነዋሪዎች ፥ የሸካ ዞንን ከተለያዩ ከተሞች የሚያገናኘው መንገድ ተጀምሮ ለረጅም ዘመናት አለመጠናቀቅ ለዘርፈ ብዙ ችግሮች እየዳረገን ነዉ ሲሉ ቅሬታቸዉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሰምተዋል።

‎ስማቸዉ እንዲገለፅ ያልፈለጉ ሁለት የሸካ ዞን ቴፒ ከተማ  ነዋሪዎች " ዞኑን ከጎሬ ቴፒ ማሻ፣ ከጪዳ ታርጫ፣ ዋቻ ጀሙ፣ ሚዛን ቴፒ  የሚያገናኘው መንገድ ከ6 እና 7 ዓመታት በፊት የተጀመረ ቢሆንም እስካሁን አልተጠናቀቀም " ብለዋል።

" በዚህም ምክንያት በንግድ እንቅስቃሴ፣ በሕዝብ ትራንስፖርትና በከተማዋ ሁለንተናዊ ዕድገት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ አሳርፏል " ሲሉ ተናግረዋል።

‎የአከባቢዉ ነዋሪዎች በተለይም የዞኑ አርሶአደሮች ዞኑ ካሽ ክሮፕ ከመሆኑም በላይ የቡና፣ የሻይ ቅጠል፣ የኮረሪማ፣ ዝንጅብል፣ እርድና ሌሎችም የግብርና ምርቶችን ለገበያ ለማቅረብ መቸገራቸዉን ገልፀዋል።

‎ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሀሳባቸውን ያጋሩ ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ አንድ የቴፒ ከተማ አመራር የሸካ ዞን የመንገድ ጉዳይ ከዞኑ መንግስት አቅም በላይ ነዉ ያሉ ሲሆን ከሕዝቡ ጩኸት በዘለለ አመራሩ በተደጋጋሚ በተለያዩ መድረኮች የሚያነሳው ቢሆንም የዞኑ መንግስት የማስፈፀም አቅም ስለሌለው ለዘመናት እልባት ሊያስገኝ አልቻለም ብለዋል።

ሌላ ስማቸዉ እንዲገለፅ ያልፈለጉ የሸካ ዞን የቀድሞ አመራር " ከመንገድ ችግሮች ጋር በተያያዘ ጥያቄዎች ሲበረቱ ማዘናጊያ እንቅስቃሴዎች የማድረግና ' ከኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ጋር እየተነጋገርን ነዉ ' የሚሉ ዜናዎችን በዞንና ወረዳ የሕዝብ ግንኙነት ገፆች ማሰራጨት ልማድ በዞኑ ተደጋግሞ ይስተዋላል " ሲሉ ገልጸዋል።

ሰሞኑንም ይኸው ድርጊት እየተስተዋለ መሆኑን አንስተዉ ይህ ተደጋጋሚ ድርጊት አሁን ላይ ሕዝቡን አስመርሯል ሲሉ ተናግረዋል።

" ‎አሁን ላይ ለሸካ ዞን የመንገድ መሰረተ ልማት ጉዳይ የህልውና ጉዳይ ነዉ " የሚሉት ቅሬታ አቅራቢዎቹ " በየትኛውም መመዘኛ የሕዝብ የመሠረተ ልማት ጥያቄ በአግባቡ ሊመለስ እንጂ ሌላ ትርጉም ሊሰጠው አይገባም " ብለዋል።

በማህበራዊ ሚዲያዎች የአከባቢውን የመንገድ ችግር ጥያቄ ያስተጋቡ ግለሰቦችን የማስፈራራት ሁኔታዎች በመንግስት አመራሮች ሲፈጸሙ እንደሚስተዋልም ጠቁመዋል።

‎ቲክቫህ ኢትዮጵያ በጉዳዩ ዙሪያ የሸካ ዞን መንገድ ልማትና ትራንስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሀብታሙ ሀራን ለማነጋገር ያደረገዉ ሙከራ በተደጋጋሚ ቀጠሮ ምክንያት ሳይሳካ ቀርቷል። ሀሳባቸውን ማግኘት ስንችል የምናካትት ይሆናል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
1799😡97🙏68😭66💔28🕊27👏16😢13🤔9
2025/10/22 21:04:45
Back to Top
HTML Embed Code: