Telegram Web Link
#AddisAbaba

የዘረፋ ወንጀል ፈፅመው ለማምለጥ የሞከሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ገለፀ፡፡

ተጠርጣሪዎቹ የፀጥታ አካል የሚመስል የደንብ ልብስ በመልበስ የዘረፋ ወንጀል ፈፅመው በቁጥጥር ስር የዋሉት ጥቅምት 11 ቀን 2018 ዓ/ም በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ጃክሮስ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው፡፡

አብርሃም አሸናፊ እና ዳግም ብርሃን የተባሉት ሁለት ተጠርጣሪዎች ወንጀሉን የፈፀሙት ረድኤት አህመድ በተባለች ግለሰብ ላይ እንደሆነ ፖሊስ ገልጿል።

የግል ተበዳይ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ልዩ ቦታው አባ ሳሙኤል መቶ አርባ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኝ የንግድ ሱቋን ዘግታ በመውጣት የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2B- 88595 አ.አ የሆነ ተሽከርካሪ እያሽከረከረች ስትጓዝ ከጥቂት ሜትሮች ጉዞ በኋላ  እንዳስቆሟት ታውቋል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ የግል ተበዳይን ከሾፌር መቀመጫ ላይ አስወርደው ከኋላ እንድትቀመጥ ካደረጉ በኋላ ተሽከርካሪውን ራሳቸው እያሽከረከሩ በሚፈልጉት አቅጣጫ እንደወሰዷት እና 500 ሺህ ብር ወደ አካውንታቸው እንድታስገባ እንዳስገደዷት የፖሊስ ምርመራ መዝገቡ ያስረዳል፡፡

የግል ተበዳይ የተጠየቀችውን ያህል ገንዘብ እንደሌላት ስትገልፅላቸው በወቅቱ በእጇ ይዛው የነበረውን 8ሺህ 700 ብር ጥሬ ገንዘብ እና ሁለት ሞባይል ስልኮችን ዘርፈው እሷን ካስወረዱ በኋላ መኪናውን እየነዱ በተቃራኒ አቅጣጫ ተጉዘውለማምለጥ ሲሞክሩ ከሌላ ተሽከርካሪ ጋር  ተጋጭተው የትራፊክ አደጋ አድርሰዋል፡፡

ከአደጋው በኋላ ከተሽከርካሪው ወርደው በመሮጥ ሰው ቤት ገብተው ሊሰወሩ ቢሞክሩም ሳጅን ፋንታሁን አለምነህ በተባለ የአዲስ አበባ ፖሊስ ሞተረኛ ትራፊክ እና በህብረተሰቡ ትብብር ከነ ኤግዚቢቱ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

ግለሰቦቹ ከፀጥታ አካል ጋር ተመሳሳይነት ያለው የደንብ ልብስ ይልበሱ እንጂ የፀጥታ አካል እንዳልሆኑ መረጋገጡን እና ከወንጀሉ ጋር ተያይዞ ተጨማሪ ምርመራ እየተካሄደ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ገልጿል፡፡ 

የፀጥታ አካል በመምሰል እና ተመሳሳይነት ያለው የደንብ ልብስ በመልበስ ወንጀል የሚፈፅሙ ግለሰቦች ሊያጋጥሙ እንደሚችሉ ህብረተሰቡ ተገንዝቦ አጠራጣሪ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙት ለሚመለከተው የፀጥታ አካል ጥቆማ እና መረጃ በመስጠት ትብብሩን እንዲያጠናክር ፖሊስ ጥሪውን አቅርቧል።

#AddisAbabPolice

@tikvahethiopia
22.31K👏603🙏157🤔79😱61💔44😭39😡33🕊22😢17🥰16
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ገንዘብ ገቢ ወይም ወጪ ለማድረግ ወደ ባንካችን ቅርንጫፍ ሲሄዱ፣ ቀድመው በአቢሲንያ ሞባይል መተግበሪያ ፎርሙን በመሙላት ጊዜዎን ይቆጥቡ። ሲጨርሱ በእጅ ስልክዎ ልዩ ቁጥር ይደርስዎታል። የባንካችን ቅርንጫፍ እንደ ደረሱም፣ የተላከልዎትን ቁጥር በማሳየት የፈለጉትን የቅርንጫፍ አገልግሎት በቀላሉ ማግኘት ይችላሉ። #ወረቀትአልባየባንክአገልግሎት #Paperlessbranchmodel #BanksinEthiopia #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
50🙏1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#SamiTech

አዳዲስ ላፕቶፕች ከአንድ ዓመት ዋስትና ጋር!!
@samcomptech

በጥራት፣ በብራንድና በባትሪ ቆይታ አስተማማኝ የሆኑ የተለያዩ ሞዴል ላፕቶፖች በፈለጉት ስክሪን መጠን፣ ኮር አይ እና ጀነሬሽን አሉን።

ለቢሮዎች፣ ለተማሪዎች፣ ለዲዛይን ባለሙያዎች፣ ለጌመሮች ወ.ዘ.ተ. ሁሉም አሉን።

የዕቃዎች ዋጋ፣ ዓይነት እና አድራሻ ለማግኘት 👉 @samcomptech

@sww2844
0928442662 / 0940141114

Telgram : https://www.tg-me.com/samcomptech
34🙏1
TIKVAH-ETHIOPIA
‎" ከ6 ዓመታት በፊት የተጀመረዉ መንገድ አለመጠናቀቁ ለዘርፈ ብዙ ችግሮች ዳርጎናል " - የሸካ ዞን ነዋሪዎች ‎ ‎በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ ዞን ነዋሪዎች ፥ የሸካ ዞንን ከተለያዩ ከተሞች የሚያገናኘው መንገድ ተጀምሮ ለረጅም ዘመናት አለመጠናቀቅ ለዘርፈ ብዙ ችግሮች እየዳረገን ነዉ ሲሉ ቅሬታቸዉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሰምተዋል። ‎ ‎ስማቸዉ እንዲገለፅ ያልፈለጉ ሁለት የሸካ ዞን ቴፒ ከተማ …
" የመንገድ ፕሮጀክቱን በፋይናንስ የሚደግፈው የኮሪያው ኤግዚም ባንክ ከፍተኛ አመራሮች በቀጣይ ቀናት አዲስ አበባ ይገባሉ " - የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር

" የጎሬ - ማሻ - ቴፒ መንገድ ፕሮጀክት ወደ ግንባታ ለመመለስ የሚያስችሉ ጉዳዮች እየታዩ ነው "  ሲል የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር አሳወቀ።

መንገዱ በተለያዩ ምክንያቶች ለጊዜው ተቋርጦ እንደሚገኝ ገልጿል።

አስተዳደሩ ፤ 141 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው የጎሬ - ማሻ - ቴፒ መንገድ ፕሮጀክት በዓለም-አቀፉ የሥራ ተቋራጭ ሃይንዳይ ዴቨሎፕመንት ካምፓኒ 4 ቢሊዮን ብር በጀት ተይዞለት ግንባታው ሲከናወን ቆይቷል ብሏል።

ኾኖም የግንባታው አጠቃላይ አፈጻጸም 62 በመቶ ከደረሰ በኋላ ከወሰን ማስከበር ጋር የተያያዙ ችግሮች በወቅቱ አለመቀረፋቸውን እንዲሁም የግንባታ ውል ዝርዝር ጉዳዮች ላይ የነበሩ አለመግባባቶችን በምክንያትነት በማንሳት የሥራ ተቋራጩ ግንባታውን ለጊዜው እንዳቋረጠ አስረድቷል።

" የመንገድ ፕሮጀክቱን በፋይናንስ የሚደግፈው የኮሪያው ኤግዚም ባንክ ከፍተኛ አመራሮች በቀጣይ ቀናት አዲስ አበባ ይገባሉ " ያለ ሲሆን " ግንባታው ዳግም በሚመለስበት ሁኔታ ላይ ከኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች ጋር የሚመክሩ ይሆናል " ብሏል።

" ከዚሁ ጎን ለጎን የትራንስፖርት እንቅስቃሴው እንዳይስተጓጎል አስፈላጊ የጥገና ሥራ በመከናወን ላይ ይገኛል። የመንገድ ግንባታው ዳግም እስኪጀመር ድረስም የጥገና ሥራው የሚቀጥል ይሆናል " ሲል አሳውቋል።

ይህ የመንገድ ፕሮጀክት ኦሮሚያንና ጋምቤላን በኢሉ አባቦር በኩል እና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያን በሸካ ዞን በኩል በቅርበት በማስተሳሰር ከፍተኛ ጠቀሜታ የሚያበረክት ነው፡፡

ከዚህ ባሻገር ስድስት ወረዳዎች እና ከ15 በላይ ቀበሌዎችን በቅርበት በማገናኘት ማኅበራዊ እና ምጣኔ ሀብታዊ ትስስር የሚያጠናክር ነው፡፡

#ERA

@tikvahethiopia
114😭19🤔7🥰4😡3👏1
" እናት ፣ አባት እና ልጃቸው ናቸው በመብረቅ ተመተው የሞቱት " - የወረዳው አስተዳደር

ጥቅምት 11 ቀን 2018 ዓ.ም በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ዛና ወረዳ 4 ሰዎች በመብረቅ ተመተው ህይወታቸው አልፏል።

በዕለቱ ከቀኑ 11:00 - 3:00 ድረስ ኃይለኛ ዝናብ እንደነበር የወረዳው አስተዳደር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አስታውቋል።

መብረቅ የቀላቀለው ሃይለኛ ዝናብ በወረዳው 8 ቀበሌዎች ዘንቧል።

በሓድነት ቀበሌ ታሕታይ ጎና እምባ መንደር የሚኖሩ ሦስት የአንድ ቤተሰብ አባላት ማለትም እናት ፣ አባት እና ልጃቸው በመብረቅ ተመተው ህይወታቸው አልፏል።

ሌላ አንድ ሰውም እንዲሁ በመብረቅ ተሞቶ ሞቷል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
😭37280😢62💔33🙏12
" ነዋሪው እጅጉን ተከፍቷል በቅርቡ ወረዳውን በማመልከቻ በሰፈራ መልክ ወደ ሌላ ስፍራ እንዲያሰፍረው ቢጠይቅም አሁንም መልስ የሚሰጠው አካል ማግኘት አልተቻለም " - የቀበሌው አስተዳደር

በአማራ ክልል ዋግህምራ ዞን ሰሃላ ሰየምት ወረዳ የቢላዛ ቀበሌ ነዋሪዎች  መንግስት ወደ ሌላ ስፍራ እንዲያሰፍራቸው ጠየቁ።

የቢላዛ ቀበሌ አስተዳዳሪ አቶ ማለደ ብሬ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደተናገሩት ቁጥራቸው ከ3 ሺህ 500 በላይ የሚሆኑ ነዋሪዎች እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሱት  በቀበሌው ምንም አይነት የጤና ተቋም ባለመኖሩ ነዋሪው በቀላል ህመም እየሞተና ህክምና ለማግኘትም ብዙ እንግልት እየደረሰበት በመሆኑ ነው ብለዋል።

አክለውም " ከሳህላ ሰየምት ቢላዛ ቀበሌ የሚወስደው መንገድ በመበላሸቱ የትራንስፖርት አገልግሎት አይሰጥም በዚህ ምክንያት ወላዶችንና የታመሙ ሰዎች ለህክምና ይዘን የምንሄደው ' በቃሬዛ ' ተሸክመን ነው ፤ ይህም ለወጣቶች 7 ሰዓት የእግር ጉዞ ሲጠይቅ ለጎልማሶች ደግሞ እስከ 10:00 ይደርሳል " ብለዋል።

በዚህም ከፍተኛ እንግልት በተደጋጋሚ በመከሰቱ ወላዶች መንገድ ላይ እንደወለዱ ሽማግሌዎችም እንደሞቱ ተናግረዋል።

በዚህ የተማረረው የቀበሌው ነዋሪ መንገዱ እንዲሰራለት በተደጋጋሚ ቢያመለክትም በአካባቢው ባለስልጣናት ዘንድ ትኩረት አላገኘም ብለዋል አቶ ማለደ።

" የቀበሌው ነዋሪ እጅጉን ተከፍቷል በቅርቡ ወረዳውን በማመልከቻ በሰፈራ መልክ ወደ ሌላ ስፍራ እንዲያሰፍረው ቢጠይቅም አሁንም መልስ የሚሰጠው አካል ማግኘት አልተቻለም " ብለዋል።

በጉዳዩ ዙሪያ የሰሃላ ሰየምት ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ሲሳይ ብሩን ቲክቫህ ኢትዮጵያ በስልክ ለመነጋገር በተደጋጋሚ ቢደውልም ስልክ ባለማንሳታቸው ምክንያት አስተያየታቸውን ማካተት አልተቻለም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ባሕር ዳር
#TikvahEthiopiaFamilyBahirdar

@tikvahethiopia
185😭119💔24😡10😢8🤔5🕊1
#MinistryofRevenue

" የግብር ክሊራንስ " የምስክር ወረቀት የብድር መከልከያ ምክንያት መሆን የለበትም ሲል የገቢዎች ሚኒስትር ማሳሰቢያ ሰጠ።

የገቢዎች ሚኒስቴር ባንኮች የግብር ክሊራንስ የምስክር ወረቀት ይዘው ለብድር ለሚቀርቡ ደንበኞች የተለመደውን የብድር አገልግሎት እንዳይከለክሉ ማሳሰቢያ መስጠቱ ተመላክቷል።

ሚኒስቴሩ በቅርቡ በሚሰጠው የምስክር ወረቀት ላይ የተቀመጠው የታክስ ቅድሚያ መብት ድንጋጌ የብድር አሰጣጥ ሂደቱን የሚቀይር አዲስ መብት አለመሆኑን በማስታወቅ፣ ባንኮች የምስክር ወረቀቱን ተቀባይነት እንደሌለው ሊያስቡ እንደማይገባ አስታውቋል።

የገቢዎች ሚኒስትር ለብሔራዊ ባንክ እና ለሁሉም ባንኮች በሚል በፃፈዉ ደብዳቤ ላይ እንደተመላከተዉ ግብር ክሊራንስ የምስክር ወረቀት የሚሰጠው ግብር ከፋዩ በሕጉ መሠረት የተጣለበትን ታክስ የመክፈል ግዴታ ሲወጣ መሆኑን ገልጿል።

በተጨማሪም፣ ለታክስ ባለስልጣኑ በቅድሚያ መከፈል እንዳለባቸውና በየትኛውም ህግ ወይም ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ክፍያዎች መሆናቸው በግልጽ ተቀምጧል።

ሚኒስቴሩ እየተሰጠ ባለው የታክስ ክሊራንስ የምስክር ወረቀት ላይ የሰፈረው የቅድሚያ መብት ድንጋጌ፣ ከላይ የተጠቀሰውን የታክስ አስተዳደር አዋጅ ድንጋጌ ለማካተት እንጂ፣ ለባለስልጣኑ ሌላ አዲስ ልዩ መብት ለመስጠት እንዳልሆነ አብራርቷል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የካፒታል ጋዜጣ ነው።

@tikvahethiopia
190👏13🤔8🥰7🙏2😭2
“የ9 ጤና ባለሙያዎች ሕይወት አልፏል። 7ቱ ከአርሲ፣ ሁለቱ ከባሌ ናቸው” - የኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ

➡️ “የተጎዱት ወደ 8 ይደርሳሉ፤ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው አራት ናቸው። በአጠቃላይ 28 ባለሙያዎች ተሳፍረው ነበር” - ዞን ጤና ቢሮ

ከኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ተውጣጥተው ለትምህርት ወደ ሐረማያ ዩኒቨርስቲ ሲጓዙ በነበሩ ጤና ባለሙያዎች በመኪና አደጋ ሞትና የአካል ጉዳት መድረሱን የክልሉና የዞኑ ጤና ቢሮ ባለስልጣናት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

የኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ ተስፋዬ ከበበው (ዶ/ር)፣ “የመኪና አደጋ ነው የደረሰው፤ የዘጠኝ ጤና ባለሙያዎች ሕይወት አልፏል። 7ቱ ከአርሲ፣ ሁለቱ ከባሌ ናቸው” ሲሉ ሰማሁት ያሉትን መረጃ ነግረውናል።

አደጋው የደረሰው ጤና ባለሙያዎቹ ለፈተና ወደ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ እየተጓዙ በነበረበት ወቅት መሆኑንም አስረድተዋል።

ተጨማሪ ማብራሪያ የጠየቅናቸው የአርሲ ዞን ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሱልጣን ሐምዲኖ፣ ጤና ባለሙያዎቹ ለትምህርት (ከዲፕሎማ ወደ ዲግሪ ለኢንትራንስ ፈተና) ወደ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በኮንትራት መኪና እየሄዱ እንደነበር፤ ብዙዎቹ ከአርሲ እንደሆኑና ወለንጪቲ አካባቢ ሲደርሱ አደጋው እንዳጋጣማቸው አስረድተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ ሞትና የጉዳት መጠን የደረሰባቸው ስንት ናቸው? ብሎ ሲጠይቃቸውም፣ “የሞቱት 7 ናቸው፤ ሦስት ወንድና አራት ሴት። የተጎዱት ወደ ስምንት ይደርሳሉ፤ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው አራት ናቸው” ብለዋል።

በመኪናው በአጠቃላይ 28 ሰዎች ተሳፍረው እንደነበር፣ ሁሉም ከተለያዩ ወረዳዎች የተውጣጡ ጤና ባለሙያዎች እንደነበሩ ገልጸው፣ “ሁሉም የጤና ጣቢያ ሠራተኞች ናቸው” ነው ያሉት።

ከተሳፋሪውቹ መካከል፣ “በ4ቱ ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል፤ አራቱ ታክመው ወጥተዋል” ያሉት ኃላፊው፣ አሰላና አዳማ ሆስፒታሎች ህክምና እየተከታሀሉ ያሉ ጤና ባለሙያዎች መኖራቸውንም ጠቁመዋል። 

አደጋው የደረሰው ከአዳማ ወደ ዩኒቨርሲቲው ሲጓዙ ወለንጪቲ እንደደረሱ ትላንት ጥቅምት 12 ቀን 2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 12 ሰዓት ገደማ መሆኑንም ገልጸዋል።

አደጋው የተከሰተው፣ ከሀረርጌ ወደ አዳማ በርበሬ ጭኖ ሲጓዝ የነበረ አይሱዚና ባለሙያዎቹን የጫነው ተሽከርካሪ ተጋጭተው መሆኑም አቶ ሱልጣን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

በጉዳቱ ጥልቅ ሀዘን እንደተሰማቸው አስረድተው፣ “የመኪና አደጋ በጣም እየበዛ ነው፤ ትራንስፓርትና ሎጂስቲክስ ቢሮዎች በደንብ መስራት አለባቸው። በየቀኑ የሰው ሕይወት እየጠፋ ነው፤ ንብረት ላይም ውድመት እየተደረሰ ነው፤ ጥንቃቄ ያስፈልጋል” ሲሉ አሳስበበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
😭24496💔15😢14😱2🕊2🥰1👏1
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

የ2018 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ይዘቶች ይፋ ሆኑ፡፡

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ፤ ተማሪዎች፣ የተማሪ ቤተሰቦች፣ መምህራንና የትምህርት አመራር ለፈተና ዝግጅት በሚያደርጉበት ወቅት ፈተና የሚሸፍናቸው የይዘት አካባቢዎች ይፋ አድርጓል።

የ2018 ትምህርት ዘመን 12ኛ ከፍል ፈተና ዝግጅትና አስተዳደር የሚከተሉትን ያካትታል፡፡ 

1. የትምህርት ዓይነቶችን በተመለከተ

ለተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች ፦
- እንግሊዘኛ፣
- ሒሳብ፣
- እስኮላስቲክ አፕቲትዩድ፣
- ኬሚስትሪ፣
- ፊዝክስና ባዮሎጂ

ለማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ፦
- እንግሊዘኛ፣
- ሒሳብ፣
- እስኮላስቲክ አፕቲትዩድ፣
- ታሪክ፣
- ጂኦግራፊና ኢኮኖሚክስ ናቸው።

2. ፈተናው ከ9ኛ እስከ 12ኛ ከፍል ደረጃዎችን እና በተማሪው መጽሐፍ ላይ ያሉትን ሁሉንም ምዕራፎች ይሸፍናል፡፡

3. ከ10ኛ – 12ኛ ክፍል ሁሉም የትምህርት ዓይነት ፈተና በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት መሠረት እየተዘጋጀ ያለ ሲሆን የ9ኛ ክፍል ደግሞ የሁሉም የትምህርት ዓይነቶች ፈተናዎች ከቀድሞውና ከአዲሱ ሥርዓተ ትምህርቶች የጋራ ይዘቶችን ብቻ አካቶ እየተዘጋጀ ይገኛል፡፡

4. ፈተናው ማንኛውም ተፈታኝ ተማሪ ከተማረው ሥርዓተ ትምህርትና ከተማሪው መጽሐፍ ላይ ብቻ ተመስርቶ እየተዘጋጀ ይገኛል፡፡

5. የፈተናው አስተዳደር በበይነ መረብና በወረቀት ጎን ለጎን የሚሰጥ ሲሆን አብዛኛው ተፈታኝ በበይነ መረብ እንዲፈተን እየተሠራ ያለ በመሆኑ ተፈታኞች እራሳቸውን በበይነ መረብ ለመፈተን ሊያዘጋጁ ይገባል፡፡

#EAES

@tikvahethiopia
264🤔35😭20👏14
2025/10/23 09:32:46
Back to Top
HTML Embed Code: