ልዩ የትምህርት ድጋፍ እድል ከፋዌ ኢትዮጵያ
ፋዌ ኢትዮጵያ እና ፋዌ አፍሪካ ከ ማስተርካርድ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር በ 2018 ዓ.ም እድሚያቸው ከ 15 እስከ 25 የሆኑ ወጣቶችን በተለይም በዝቅተኛ ኢኮኖሚያዊ ደረጃ የሚገኙ ሴቶችን ፣የአካል ጉዳተኛ ወጣቶችን፣ የሀገር ዉስጥ ተፈናቃዮችን እና የውጭ ሀገር ስደተኞች ተጠቃሚ የሚያደርግ የከፍተኛ የትምህርት እድል ተጠቃሚ እንድትሆኑ ሲጋብዝ ታላቅ ደስታ ይሰማዋል፡፡ ድጋፉ ሁሉን አቀፍ የገንዘብ፣የትምህርትና ስልጠና እንዲሁም የማህበራዊ ድጋፍን የሚያካትት ሲሆን የትምህርት ድጋፉ የሚሰጠው በቴክኒክና ሙያ የትምህርት ተቋማት ውስጥ በሚሰጡ የሳይንስ፣ቴክኖሎጂ፣ምህንድስናና ተዛማጅ የትምህርት ዘርፎች/STEM/ ደረጃ 4 እና 5 ኮርሶች ነው፡፡
ትምህርት ስልጠናና ድጋፉ የሚሰጠው በአዲስ አበባ ከተማ በጄኔራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ እና አዲስ አበባ ተግባረ እድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች፣ አዳማ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ፣ ሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክና ሀዋሳ ተግባረ እድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች እንዲሁም በባህርዳር ፖሊ ቴከኒክ ኮሌጅ በሚሰጡት የመደበኛ የትምህርትና ስልጠና መርሃግብሮች ሲሆን ሙሉ ዝርዝር መረጃ ከስር ባለው ሊንክ ይመልከቱ።
👉 https://shorturl.at/5w9EC
የማመልከቻ ቀን ከ ጥቅምት 17-21 ፤ 2018 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን ከተጠቀሰው ቀነገደብ ዉጭ የሚመጡ አመልካቾችን የማናስተናግድ መሆኑን ከወዲሁ እንገልጻለን።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥሮች
አዲስ አበባ በ 0981642541
አዳማ በ 0981643411
ባህርዳር በ 0981638351
ሀዋሳ በ 0981630651 በመደወል ወይም በድህረገጻችን www.faweethiopia.org ይጎብኙ፡፡
ምዝገባዉም ሆነ የመረጣው ሂደት ከማንኛዉም ክፍያ ነጻ መሆኑን እናሳዉቃለን!

2❤291🙏10🕊6😭5😡1
#Earthquake : ከደቂቃዎች በፊት አዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎችን ጨምሮ በሌሎችም ከተሞች ንዝረቱ የተሰማ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል።
በተለይም በህንጻዎች ላይ የሚኖሩ ነዋሪዎች ንዝረቱ እጅጉን እንደተሰማቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
ተጨማሪ መረጃ ይኖረናል።
@tikvahethiopia

3😢572❤216😭191🙏164😱50🕊45👏40🤔28💔26🥰11
TIKVAH-ETHIOPIA
#Earthquake : ከደቂቃዎች በፊት አዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎችን ጨምሮ በሌሎችም ከተሞች ንዝረቱ የተሰማ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል። በተለይም በህንጻዎች ላይ የሚኖሩ ነዋሪዎች ንዝረቱ እጅጉን እንደተሰማቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል። ተጨማሪ መረጃ ይኖረናል። @tikvahethiopia
#Earthquake
በሬክተር ስኬል 4.9 የተለካ መሬት መንቀጥቀጥ ከደብረሲና 30 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ መከሰቱን የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ ገልጿል።
የመሬት መንቀጥቀጡ ንዝረት በአፋር ከተሞች ፣ በአዳማ ፣ ደብረ ብርሃንን ጨምሮ በርካታ ከተሞች ድረስ ዘልቆ ተሰምቷል።
በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ አካባቢዎች ንዝረቱ የተሰማ ሲሆን በተለይም በህንጻዎች ላይ የሚኖሩ ነዋሪዎች ንዝረቱ አይሎ እንደተሰማቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ከሰሚህ፣ አያት ፣ ጋርመንት ፣ ገርጂ፣ ጎፋ ፣ ለቡ ፣ የካ አባዶ፣ መሪ፣ መካኒሳ ፣ጀሞ፣ ቡልቡላ ፣ ቦሌ አራብሳ፣ ጣፎ፣ ፊጋ ፣ ሚኪላንድ.. እንዲሁም ከሌሎች የከተማዋ አካባቢዎች ቃላቸውን የላኩ የቤተሰባችን አባላት ፥ የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረቱ እጅግ ጠንክሮ እንደተሰማቸው ገልጸዋል።
ንዝረቱ እቃ ጭምር ያንቀሳቀሰ እንደነበር አመልክተዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ

❤504😭154🙏63😢30🕊29💔16😱15🤔12👏8😡6🥰4
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update
" የዛሬው የመሬት መንቀጥቀጥ የተከሰተው ከፈንታሌ ዙሪያ ነው፤ በሬክተር ስኬል 4.8 የተለካ ነው " - ፕ/ር አታላይ አየለ
ዛሬ ጥቅምት 16 ቀን 2018 ዓ/ም በፈንታሌ ዙሪያ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል።
የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረቱ ከጠዋቱ 2 ሰዓት ከ25 ደቂቃ ላይ በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎችም የተሰማ ሲሆን፣ " እዚህ ይህን ያህል ከተሰማን ዋናው በተከሰተበት ቦታ ያሉት እንዴት ሆነው ይሆን ? " ሲሉ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች ሀሳባቸውን ገልጸዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያም፣ ስለጉዳዩ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ማብራሪያ ጠይቋል።
በዩኒቨርሲቲው የጂኦ ፊዚክስ ስፔስ ሳይንስና አስትሮኖሚ ኢንስቲትዩት ተመራማሪ የሆኑት ፕ/ር አታላይ አየለ፣ " የዛሬው የመሬት መንቀጥቀጥ የተከሰተው ከፈንታሌ ዙሪያ ነው፤ በሬክተር ስኬል 4.8 የተለካ ነው " ብለዋል።
የተከሰተው 2 ሰዓት ከ24 ደቂቃ መሆኑን አስረድተው፣ " በብዙ ከተሞችም ተሰምቷል " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ፈንታሌ ትንሽ ረገብ ብሎ ነበር፣ አሁንም ቀጣይነት አለው ማለት ነው ? ስንል ላቀረብነው ጥያቄ፣ " የፈንታሌው ረገብ አለ የሚባልም አይደለም። የመወጠር ነገር አለ፤ ረገብ አላለም፤ በመሳሪያ እናያለን " ብለዋል።
" ሁሌም መሬት በማያቋርጥ እንቅስቃሴ ላይ ነው ያለችውና ሁሌ #ተዘጋጅተን_መጠበቅ ነው እንጂ በዚህ ጊዜ ይጠፋል፣ በዚህ ጊዜ ይቆማል የሚባል ነገር አይደለም። ሰበር ዜና ሆኖ መደነቅ የለብንም መልመድ አለብን " ነው ያሉት።
በቅርቡም በትግራይ ክልል በተደጋጋሚ መከሰቱን ጠቅሰው፣ " ወደ ሃውዜንና ውቅሮ ምሥራቃዊ ክፍል በተደጋጋሚ ከፍተኛው 5.6 የተለካ መሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል " ብለዋል።
" የትግራዩ የመሬት መንቀሳቀጥ ከፈንታሌ ጋር የተገናኘ ሳይሆን የራሱ ነው፤ ስምጥ ሸለቆ ዙሪያ ሁል ጊዜ በማያቋርጥ እንቅስቃሴ ውስጥ ነው የሚሆነውና ያም አለው ከአፋር ቅርብ ስለሆነ፤ የፈንታሌውም የትግራዩም የስምጥ ሸለቆ ባህሪ ነው " ሲሉም አስረድተዋል።
" ስምጥ ሸለቆውን እየተከተለ አደጋው እየተደጋገመ ነው፣ በፈንታሌ፣ አፍዴራ፣ ኤርታሌ ነበር። መሬት በማያቋርጥ እንቅስቃሴ ውስጥ ነው ያለችው፤ መልመድ አለብን " ሲሉም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

❤1.35K🙏154😭111😱58🕊56🤔35💔28😢27😡21🥰10👏6
TIKVAH-ETHIOPIA
" የውሃ አገልግሎት በከፊል እና ሙሉ ለሙሉ ስለሚቋረጥ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አድርጉ " - ውሃ እና ፍሳሽ ባለሥልጣን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውሃ እና ፍሳሽ ባለሥልጣን የለገዳዲ ግድብ የጥሬ ውሃ ማስተላለፊያ ቫልቭ ቅየራ ስራ ከጥቅምት 2/2018 ዓም እስከ ጥቅምት 16/2018 ዓም ድረስ የሚከናወን መሆኑን ገልጿል። የጥገና ስራው እስከሚጠናቀቅም በአንዳንድ የከተማዋ አካባቢዎች የውሃ…
" ያረጀ ቫልቩ ጥገና ባይከናወን የግድቡን ህልውና አደጋ ውስጥ ይከተው ነበር " - የውሃ እና ፍሳሽ ባለሥልጣን
የአዲስ አበባ ከተማ ውሃ እና ፍሳሽ ባለሥልጣን የለገዳዲ ግድብ የውሃ ማስተላለፊያ ማማ የቫልቭ ቅየራ ስራ ከጥቅምት 2 ቀን 2018 ዓ/ም እስከ ጥቅምት 16 ቀን 2018 ዓም ድረስ እንደሚከናወን ማሳወቁ ይታወቃል።
የቫልቭ ቅየራ ስራው እስከሚጠናቀቅም በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ፣ በቦሌ ክፍለ ከተማ እና በቂርቆስ ክፍለ ከተማ አንዳንድ ወረዳዎች የውሃ አቅርቦት ተቋርጦ ቆይቷል።
ባለሥልጣኑ የቫልቭ ቅየራ ስራው መጠናቀቁን እና የለገዳዲ ግድብ በሙሉ አቅሙ ምርት መጀመሩን በማህበራዊ ትስስር ገጹ አሳውቋል።
ስራው ሲያከናወን የቆየው ዊ ቢውልድ /ሳሊኒ/ ሲሆን የኢትዮጵያ ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን በማማከር አገልግሎት ተሳትፏል ተብሏል።
የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢ/ር ዘሪሁን አባተ " ያረጀ ቫልቩ ጥገና ባይከናወን የግድቡን ህልውና አደጋ ውስጥ ይከተው ነበር " ያሉ ሲሆን በአጭር ጊዜ የጥገና ስራውን ላጠናቀቁ ተቋማት ምስጋና ስለማቅረባቸው ባለሥልጣኑ አሳውቋል።

❤562🙏56😡17👏15🤔8😢4🥰3🕊3
ቪድዮ ፦ ዛሬ በሰመራ ዩኒቨርሲቲ በሚገኝ አንድ የተማሪዎች ህንጻ ላይ የእሳት አደጋ ተከስቶ ነበር።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ አደጋውን በተመለከተ ከሚመለከታቸው የተቋሙ አመራሮች ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት ያደረገው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም።
አንድ የተቋሙ ተማሪ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል፥ " ቀን ወደ 11 ሰዓት አካባቢ ብሎክ 17 ነው እሳት አደጋው የደረሰው ፤ ከሶስተኛው ወለል ነው የተነሳው እሳቱ። ተማሪ ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለ ነው የሰማሁት። የአንዳንድ ተማሪዎች አልባሳት ተቃጥለዋል። ከዚህ ቀደምም እንዲህ ያለ እሳት አደጋ ተከስቶ ያውቃል " ብሏል።
Video Credit - 1337

❤415😭223😱54🙏30🕊30💔10🤔7😢7🥰4😡3👏1
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#DV2027
የ2027 የአሜሪካ ዲቪ ሎተሪ ምዝገባ ቀን ከተባለበት እና ከዚህ ቀደምም ከሚታወቅበት ቀን ቢዘገይም ፕሮግራሙ እንዳልተሰረዘ / ዲቪ እንዳልቀረ ለማወቅ ተችሏል።
ምዝገባው የሚጀመረው በዚህ ቀን ነው የሚል መረጃ ባይኖርም በቅርቡ ይፋዊ ምዝገባ መጀመሩን ሀገሪቱ ታሳውቃለች ተብሎ ይጠበቃል።
የአሜሪካ መንግሥት በይፋ የሰጠው ማብራሪያ እና ማረጋገጫ ባይኖርም ምናልባትም የዘንድሮ የዲቪ ሎተሪ ማመልከቻ ጊዜ የዘገየው ይጀመራል ከተባለው የ1 ዶላር የምዝገባ ክፍያ ሲስተም አፕዴት ጋር የተያያዘ ሊሆን እንደሚችል ተነግሯል።
የዲቪ አመልካቾች ለምዝገባው 1 ዶላር እንዲከፍሉ የሚያደርገው አሰራር ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ይጀመራል።
አሜሪካ በየአመቱ ከመላው ዓለም 55,000 ሰዎችን በዲቪ ሎተሪ ወደ ሀገሯ ታስገባለች።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
#TikvahEthiopiaFamily

❤1.27K🙏221😭83😡76👏35🕊34💔28😢26😱22🤔14🥰10
ልዩ የትምህርት ድጋፍ እድል ከፋዌ ኢትዮጵያ
ፋዌ ኢትዮጵያ እና ፋዌ አፍሪካ ከ ማስተርካርድ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር በ 2018 ዓ.ም እድሚያቸው ከ 15 እስከ 25 የሆኑ ወጣቶችን በተለይም በዝቅተኛ ኢኮኖሚያዊ ደረጃ የሚገኙ ሴቶችን ፣የአካል ጉዳተኛ ወጣቶችን፣ የሀገር ዉስጥ ተፈናቃዮችን እና የውጭ ሀገር ስደተኞች ተጠቃሚ የሚያደርግ የከፍተኛ የትምህርት እድል ተጠቃሚ እንድትሆኑ ሲጋብዝ ታላቅ ደስታ ይሰማዋል፡፡ ድጋፉ ሁሉን አቀፍ የገንዘብ፣የትምህርትና ስልጠና እንዲሁም የማህበራዊ ድጋፍን የሚያካትት ሲሆን የትምህርት ድጋፉ የሚሰጠው በቴክኒክና ሙያ የትምህርት ተቋማት ውስጥ በሚሰጡ የሳይንስ፣ቴክኖሎጂ፣ምህንድስናና ተዛማጅ የትምህርት ዘርፎች/STEM/ ደረጃ 4 እና 5 ኮርሶች ነው፡፡
ትምህርት ስልጠናና ድጋፉ የሚሰጠው በአዲስ አበባ ከተማ በጄኔራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ እና አዲስ አበባ ተግባረ እድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች፣ አዳማ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ፣ ሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክና ሀዋሳ ተግባረ እድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች እንዲሁም በባህርዳር ፖሊ ቴከኒክ ኮሌጅ በሚሰጡት የመደበኛ የትምህርትና ስልጠና መርሃግብሮች ሲሆን ሙሉ ዝርዝር መረጃ ከስር ባለው ሊንክ ይመልከቱ።
👉 https://shorturl.at/5w9EC
የማመልከቻ ቀን ከ ጥቅምት 17-21 ፤ 2018 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን ከተጠቀሰው ቀነገደብ ዉጭ የሚመጡ አመልካቾችን የማናስተናግድ መሆኑን ከወዲሁ እንገልጻለን።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥሮች
አዲስ አበባ በ 0981642541
አዳማ በ 0981643411
ባህርዳር በ 0981638351
ሀዋሳ በ 0981630651 በመደወል ወይም በድህረገጻችን www.faweethiopia.org ይጎብኙ፡፡
ምዝገባዉም ሆነ የመረጣው ሂደት ከማንኛዉም ክፍያ ነጻ መሆኑን እናሳዉቃለን!
ፋዌ ኢትዮጵያ እና ፋዌ አፍሪካ ከ ማስተርካርድ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር በ 2018 ዓ.ም እድሚያቸው ከ 15 እስከ 25 የሆኑ ወጣቶችን በተለይም በዝቅተኛ ኢኮኖሚያዊ ደረጃ የሚገኙ ሴቶችን ፣የአካል ጉዳተኛ ወጣቶችን፣ የሀገር ዉስጥ ተፈናቃዮችን እና የውጭ ሀገር ስደተኞች ተጠቃሚ የሚያደርግ የከፍተኛ የትምህርት እድል ተጠቃሚ እንድትሆኑ ሲጋብዝ ታላቅ ደስታ ይሰማዋል፡፡ ድጋፉ ሁሉን አቀፍ የገንዘብ፣የትምህርትና ስልጠና እንዲሁም የማህበራዊ ድጋፍን የሚያካትት ሲሆን የትምህርት ድጋፉ የሚሰጠው በቴክኒክና ሙያ የትምህርት ተቋማት ውስጥ በሚሰጡ የሳይንስ፣ቴክኖሎጂ፣ምህንድስናና ተዛማጅ የትምህርት ዘርፎች/STEM/ ደረጃ 4 እና 5 ኮርሶች ነው፡፡
ትምህርት ስልጠናና ድጋፉ የሚሰጠው በአዲስ አበባ ከተማ በጄኔራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ እና አዲስ አበባ ተግባረ እድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች፣ አዳማ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ፣ ሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክና ሀዋሳ ተግባረ እድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች እንዲሁም በባህርዳር ፖሊ ቴከኒክ ኮሌጅ በሚሰጡት የመደበኛ የትምህርትና ስልጠና መርሃግብሮች ሲሆን ሙሉ ዝርዝር መረጃ ከስር ባለው ሊንክ ይመልከቱ።
👉 https://shorturl.at/5w9EC
የማመልከቻ ቀን ከ ጥቅምት 17-21 ፤ 2018 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን ከተጠቀሰው ቀነገደብ ዉጭ የሚመጡ አመልካቾችን የማናስተናግድ መሆኑን ከወዲሁ እንገልጻለን።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥሮች
አዲስ አበባ በ 0981642541
አዳማ በ 0981643411
ባህርዳር በ 0981638351
ሀዋሳ በ 0981630651 በመደወል ወይም በድህረገጻችን www.faweethiopia.org ይጎብኙ፡፡
ምዝገባዉም ሆነ የመረጣው ሂደት ከማንኛዉም ክፍያ ነጻ መሆኑን እናሳዉቃለን!
❤128😱1😢1🙏1
#SafaricomEthiopia
ለእናንተ ብቻ ተብለው የተዘጋጅትን የበሽ ጥቅል በመግዛት፤ በሽ ሽልማት በየቀኑ፣ በየሳምንቱ ያግኙ! 🎉🎉🎉
✅ በቀን፣ ለ2000 አሸናፊዎች 100 ብር
✅ ሳምንታዊ፣ 100ሺህ ለ25 አሸናፊዎች
✅ ትልቁ ሳምንታዊ ሽልማት፣ 1 ሚሊየን ለ32 አሸናፊዎች!
ወደ *777*0# ይደውሉ ወይም በM-PESA የበሽጥቅል ይግዙ!
የM-PESA መተግበሪያን አሁኑኑ ያውርዱ፡https://onelink.to/ewsb22
የቴሌግራም ቦታችን: https://www.tg-me.com/official_safaricomet_bot
#MPESASafaricom
#furtheraheadtogether
#Besh100Winner

❤60😱3😡2
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ቅዱስ ሲኖዶስ የአህጉረ ስብከት ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ምደባ ውሳኔ አሳለፈ። 1. የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ብፁዕ አቡነ ቶማስ የአዊና የመተከል አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከትን ደርበው የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከትን እንዲመሩና እንዲይዙ ምልዓተ ጉባኤው ወስኗል፡፡ 2. የደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት የከሚሴ የደቡብ ወሎ ልዩ ዞን የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት…
" የመዋቅር ግንኙነቱን ወደ ቀደመ ቦታው እንዲመለስ ቅዱስ ሲኖዶስ በክልሉ ለሚገኙት አባቶች፣ ካህናትና ምእመናን ያልተቋረጠ የሰላም ጥሪውን ያስተላልፋል " - ቅዱስ ሲኖዶስ
ከጥቅምት 11 እስከ ጥቅምት 17 ቀን 2018 ዓም ሲካሄድ የቆየው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶድ ምልዓተ ጉባኤ ተጠናቋል።
የጉባኤውን መጠናቀቅ አስመልክቶ በዛሬው ዕለት መግለጫ የተሰጠ ሲሆን ቅዱስ ሲኖዶሱ በማጠቃለያ መግለጫው ከትግራይ አህጉረ ስብከት ጋር ያለው ግንኙነት ወደ መዋቅሩ እንዲመለስ ጥሪ አቅርቧል።
ቅዱስ ሲኖዶሱ :-
- ትግራይ አህጉረ ስብከት የሚገኘው ሕዝበ ክርስቲያን ሕዝባችንና ወገናችን ስለሆነ
- አብያተ ክርስቲያናቱና ገዳማቱም የቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊ ሀብቶች በመሆናቸው
- አህጉረ ስብከቱም የተደራጁት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በመሆኑ
የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሕግና ቀኖና ተጠብቆ፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ልዕልና ተከብሮ፣ የመዋቅር ግንኙነቱን ወደ ቀደመ ቦታው እንዲመለስ የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የሰላም፣ የአንድነትና የይቅርታ በር ክፍት መሆኑን ከመግለጽ ጋር ቅዱስ ሲኖዶስ በክልሉ ለሚገኙት አባቶች፣ ካህናትና ምእመናን ያልተቋረጠ የሰላም ጥሪውን ያስተላልፋል ብሏል።
አክሎም " ቀደም ሲል ለዚሁ ጉዳይ የተሠየመው ኮሚቴ ሥራውን አጠናክሮ እንዲቀጥል፣ ሊቃውንቱ፣ ካህናቱና መላው ሕዝባችንም የቤተ ክርስቲያንን አንድነት ለማጠናከር በሚደረገው ጥረት ሁሉ የበኩላችሁን እንድትወጡ " ሲል አሳስቧል።
ቅዱስ ሲኖዶስ ባካሄደው ጉባኤ ምን ውሳኔዎች ተላለፉ ?
° ብፁዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ የኢሉ አባቦራ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ የምዕራብ ወለጋ ሀገረ ስብከትን ደርበው እንዲመሩ፤
° ብፁዕ አቡነ ቶማስ የአዊና መተከል አህጉረ ስብከት ሊቀጳጳስ የምሥራቅ ጎጃምን ሀገረ ስብከት ደርበው እንዲመሩ፤
° ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ የደቡብ ወሎና ከሚሴ አህጉረ ስብከትን ደርበው እንዲመሩ፤
° ብፁዕ አቡነ ኒቆዲሞስ የምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ጳጳስ የምሥራቅ ወለጋና ሆሮ-ጉድሩ ወለጋ አህጉረ ስብከትን ደርበው እንዲመሩ፤
° የሸካ ዞን ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ተብሎ ራሱን ችሎ በሀገረ ስብከት ደረጃ እንዲቋቋም፣ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል ሀገረ ስብከቱን እንዲያደራጁና እንዲመሩ፤
° ገድለ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ በሚል ያለአግባብ በአንድ ግለሰብ ተዘጋጅቶ እየተሠራጨ ያለው መጽሐፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሰ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ የማይወክል ሆኖ በመገኘቱ ተወግዟል።
° በምዕራብና በመካከለኛው ካናዳ የሚገኙት ሁለቱ አህጉረ ስብከት ያለ ጣልቃ ገብነት በየራሳቸው እንዲተዳደሩና የኤድመንተንና አካባቢው ሀገረ ስብከት የመካከለኛው ካናዳ ኤድመንተንና አካባቢው ሀገረ ስብከት በሚል ሥያሜ እንዲስተካከል
° በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ በአረርቲ ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን በዓል ለማክበር ሄደው አዲሱን ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን በመጐብኘት ላይ እያሉ አደጋ ለደረሰባቸው ምዕመናን የተጎጂ ቤተሰቦች ለመርዳት የገንዘብ ድጋፍ እንዲደረግ
° በመላው ኢትዮጵያ በሚገኙ ገዳማት ያሉት መነኰሳትና መነኰሳይያት ለአገልግሎትና ጉዳይ ለማስፈጸም ወደ አዲስ አበባ ሲመጡ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት በኩል ማረፊያ የሚሆን ቦታ እንዲዘጋጅላቸው " የሚሉት ይገኙበታል።
(ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

❤748🕊51😡24🙏20👏18😢5🤔3🥰1
#Djibouti🇩🇯
የ77 ዓመቱ ፕሬዚዳንት ለሌላ የስልጣን ዘመን እንዲወዳደሩ የሚያስችላቸው ውሳኔ ተላለፈ።
የጅቡቲ ምክር ቤት በሀገሪቱ ሕገ-መንግሥት ለፕሬዝደንትነት የሚወዳደሩ ዕጩዎች ላይ የተጣለው የዕድሜ ገደብ እንዲነሳ የቀረበ የውሳኔ-ሐሳብ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።
ውሳኔው ፕሬዝደንት ኢስማኤል ዑመር ጉሌሕ በሚያዝያ 2018 ዓ/ም በሚካሔደው ምርጫ ለስድስተኛ የሥልጣን ዘመን በድጋሚ እንዲወዳደሩ መንገድ ከፍቷል።
የጅቡቲ ሕገ-መንግሥት ዕድሜው ከ75 ዓመት በላይ የሆነው ግለሰብ ለፕሬዝደንትነት መወዳደር እንደማይችል ይደነግጋል።
የሕገ-መንግሥቱ ገደብ በመጪው ሚያዝያ ይካሔዳል ተብሎ በሚጠበው ምርጫ የ77 ዓመቱ ጉሌሕ እንዳይወዳደሩ ያግዳቸዋል።
ይሁንና የዕድሜ ገደቡ እንዲነሳ የቀረበውን የማሻሻያ ውሳኔ 65 አባላት ያሉት የጅቡቲ ምክር ቤት በሙሉ ድምጽ እንዳጸደቀ አፈ-ጉባኤ ዲሌይታ ሞሐመድ ዲሌይታ ለፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ተናግረዋል።
ፕሬዝደንቱ በምክር ቤቱ ይኹንታ ያገኘውን ውሳኔ ማጽደቅ አሊያም ሕዝበ-ውሳኔ እንዲካሔድ መጥራት ይኖርባቸዋል።
መረጃው የዶቼ ቨለ ሬድዮ ነው።

Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🤔465❤411😡143😭48😱23💔23🕊16😢14👏12🥰4