Telegram Web Link
ልዩ የትምህርት ድጋፍ እድል ከፋዌ ኢትዮጵያ

ፋዌ ኢትዮጵያ እና ፋዌ አፍሪካ ከ ማስተርካርድ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር በ 2018 ዓ.ም እድሚያቸው ከ 15 እስከ 25 የሆኑ ወጣቶችን በተለይም በዝቅተኛ ኢኮኖሚያዊ ደረጃ የሚገኙ ሴቶችን ፣የአካል ጉዳተኛ ወጣቶችን፣ የሀገር ዉስጥ ተፈናቃዮችን እና የውጭ ሀገር ስደተኞች ተጠቃሚ የሚያደርግ የከፍተኛ የትምህርት እድል ተጠቃሚ እንድትሆኑ ሲጋብዝ ታላቅ ደስታ ይሰማዋል፡፡ ድጋፉ ሁሉን አቀፍ የገንዘብ፣የትምህርትና ስልጠና እንዲሁም የማህበራዊ ድጋፍን የሚያካትት ሲሆን የትምህርት ድጋፉ የሚሰጠው በቴክኒክና ሙያ የትምህርት ተቋማት ውስጥ በሚሰጡ የሳይንስ፣ቴክኖሎጂ፣ምህንድስናና ተዛማጅ የትምህርት ዘርፎች/STEM/ ደረጃ 4 እና 5 ኮርሶች ነው፡፡

ትምህርት ስልጠናና ድጋፉ የሚሰጠው በአዲስ አበባ  ከተማ  በጄኔራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ እና አዲስ አበባ ተግባረ እድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች፣ አዳማ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ፣  ሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክና ሀዋሳ ተግባረ እድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች እንዲሁም በባህርዳር ፖሊ ቴከኒክ ኮሌጅ በሚሰጡት የመደበኛ የትምህርትና ስልጠና መርሃግብሮች ሲሆን ሙሉ ዝርዝር መረጃ ከስር ባለው ሊንክ ይመልከቱ።
👉 https://shorturl.at/5w9EC

የማመልከቻ ቀን ከ ጥቅምት 17-21 ፤ 2018 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን ከተጠቀሰው ቀነገደብ ዉጭ የሚመጡ አመልካቾችን የማናስተናግድ መሆኑን ከወዲሁ እንገልጻለን።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥሮች
አዲስ አበባ በ 0981642541
አዳማ  በ 0981643411
ባህርዳር በ 0981638351
ሀዋሳ በ 0981630651 በመደወል ወይም በድህረገጻችን www.faweethiopia.org ይጎብኙ፡፡
ምዝገባዉም ሆነ የመረጣው ሂደት ከማንኛዉም ክፍያ ነጻ መሆኑን እናሳዉቃለን!
227😱3😢3🙏2🕊1
#SafaricomEthiopia

ለእናንተ ብቻ ተብለው የተዘጋጅትን የበሽ ጥቅል በመግዛት፤ በሽ ሽልማት በየቀኑ፣ በየሳምንቱ ያግኙ! 🎉🎉🎉

በቀን፣ ለ2000 አሸናፊዎች 100 ብር
ሳምንታዊ፣ 100ሺህ ለ25 አሸናፊዎች
ትልቁ ሳምንታዊ ሽልማት፣ 1 ሚሊየን ለ32 አሸናፊዎች!

ወደ *777*0# ይደውሉ ወይም በM-PESA የበሽጥቅል ይግዙ!

የM-PESA መተግበሪያን አሁኑኑ ያውርዱ፡https://onelink.to/ewsb22

የቴሌግራም ቦታችን: https://www.tg-me.com/official_safaricomet_bot

#MPESASafaricom
#furtheraheadtogether
#Besh100Winner
84😡5😱4
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ቅዱስ ሲኖዶስ የአህጉረ ስብከት ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ምደባ ውሳኔ አሳለፈ። 1. የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ብፁዕ አቡነ ቶማስ የአዊና የመተከል አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከትን ደርበው የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከትን እንዲመሩና እንዲይዙ ምልዓተ ጉባኤው ወስኗል፡፡ 2. የደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት የከሚሴ የደቡብ ወሎ ልዩ ዞን  የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት…
" የመዋቅር ግንኙነቱን ወደ ቀደመ ቦታው እንዲመለስ ቅዱስ ሲኖዶስ በክልሉ ለሚገኙት አባቶች፣ ካህናትና ምእመናን  ያልተቋረጠ የሰላም ጥሪውን ያስተላልፋል " - ቅዱስ ሲኖዶስ

ከጥቅምት 11 እስከ ጥቅምት 17 ቀን 2018 ዓም ሲካሄድ የቆየው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶድ ምልዓተ ጉባኤ ተጠናቋል።

የጉባኤውን መጠናቀቅ አስመልክቶ በዛሬው ዕለት መግለጫ የተሰጠ ሲሆን ቅዱስ ሲኖዶሱ በማጠቃለያ መግለጫው ከትግራይ አህጉረ ስብከት ጋር ያለው ግንኙነት ወደ መዋቅሩ እንዲመለስ ጥሪ አቅርቧል።

ቅዱስ ሲኖዶሱ :-

- ትግራይ አህጉረ ስብከት የሚገኘው ሕዝበ ክርስቲያን ሕዝባችንና ወገናችን ስለሆነ

- አብያተ ክርስቲያናቱና ገዳማቱም የቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊ ሀብቶች በመሆናቸው

- አህጉረ ስብከቱም የተደራጁት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በመሆኑ

የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሕግና ቀኖና ተጠብቆ፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ልዕልና ተከብሮ፣ የመዋቅር ግንኙነቱን ወደ ቀደመ ቦታው እንዲመለስ የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የሰላም፣ የአንድነትና የይቅርታ በር ክፍት መሆኑን ከመግለጽ ጋር ቅዱስ ሲኖዶስ በክልሉ ለሚገኙት አባቶች፣ ካህናትና ምእመናን ያልተቋረጠ የሰላም ጥሪውን ያስተላልፋል ብሏል።

አክሎም " ቀደም ሲል ለዚሁ ጉዳይ የተሠየመው ኮሚቴ ሥራውን አጠናክሮ እንዲቀጥል፣ ሊቃውንቱ፣ ካህናቱና መላው ሕዝባችንም  የቤተ ክርስቲያንን አንድነት ለማጠናከር በሚደረገው ጥረት ሁሉ  የበኩላችሁን እንድትወጡ " ሲል አሳስቧል።

ቅዱስ ሲኖዶስ ባካሄደው ጉባኤ ምን ውሳኔዎች ተላለፉ ?

° ብፁዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ የኢሉ አባቦራ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ የምዕራብ ወለጋ ሀገረ ስብከትን ደርበው እንዲመሩ፤

° ብፁዕ አቡነ ቶማስ የአዊና መተከል አህጉረ ስብከት ሊቀጳጳስ የምሥራቅ ጎጃምን ሀገረ ስብከት ደርበው እንዲመሩ፤

° ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ የደቡብ ወሎና ከሚሴ አህጉረ ስብከትን ደርበው እንዲመሩ፤

° ብፁዕ አቡነ ኒቆዲሞስ የምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ጳጳስ የምሥራቅ ወለጋና ሆሮ-ጉድሩ ወለጋ አህጉረ ስብከትን ደርበው እንዲመሩ፤

° የሸካ ዞን ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ተብሎ ራሱን ችሎ በሀገረ ስብከት ደረጃ እንዲቋቋም፣ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል ሀገረ ስብከቱን እንዲያደራጁና እንዲመሩ፤

° ገድለ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ በሚል ያለአግባብ በአንድ ግለሰብ ተዘጋጅቶ እየተሠራጨ ያለው መጽሐፍ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሰ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ የማይወክል ሆኖ በመገኘቱ ተወግዟል።

° በምዕራብና በመካከለኛው ካናዳ የሚገኙት ሁለቱ አህጉረ ስብከት ያለ ጣልቃ ገብነት በየራሳቸው እንዲተዳደሩና የኤድመንተንና አካባቢው ሀገረ ስብከት የመካከለኛው ካናዳ ኤድመንተንና አካባቢው ሀገረ ስብከት በሚል ሥያሜ እንዲስተካከል

° በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ በአረርቲ ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን በዓል ለማክበር ሄደው አዲሱን ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን በመጐብኘት ላይ እያሉ አደጋ ለደረሰባቸው ምዕመናን የተጎጂ ቤተሰቦች ለመርዳት የገንዘብ ድጋፍ እንዲደረግ

° በመላው ኢትዮጵያ በሚገኙ ገዳማት ያሉት መነኰሳትና መነኰሳይያት ለአገልግሎትና ጉዳይ ለማስፈጸም ወደ አዲስ አበባ ሲመጡ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት በኩል ማረፊያ የሚሆን ቦታ እንዲዘጋጅላቸው " የሚሉት ይገኙበታል።

(ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
1.18K🕊71🙏37😡28👏27🤔7😢7🥰2
#Djibouti🇩🇯

የ77 ዓመቱ ፕሬዚዳንት ለሌላ የስልጣን ዘመን እንዲወዳደሩ የሚያስችላቸው ውሳኔ ተላለፈ።

የጅቡቲ ምክር ቤት በሀገሪቱ ሕገ-መንግሥት ለፕሬዝደንትነት የሚወዳደሩ ዕጩዎች ላይ የተጣለው የዕድሜ ገደብ እንዲነሳ የቀረበ የውሳኔ-ሐሳብ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።

ውሳኔው ፕሬዝደንት ኢስማኤል ዑመር ጉሌሕ በሚያዝያ 2018 ዓ/ም በሚካሔደው ምርጫ ለስድስተኛ የሥልጣን ዘመን በድጋሚ እንዲወዳደሩ መንገድ ከፍቷል።

የጅቡቲ ሕገ-መንግሥት ዕድሜው ከ75 ዓመት በላይ የሆነው ግለሰብ ለፕሬዝደንትነት መወዳደር እንደማይችል ይደነግጋል።

የሕገ-መንግሥቱ ገደብ በመጪው ሚያዝያ ይካሔዳል ተብሎ በሚጠበው ምርጫ የ77 ዓመቱ ጉሌሕ እንዳይወዳደሩ ያግዳቸዋል።

ይሁንና የዕድሜ ገደቡ እንዲነሳ የቀረበውን የማሻሻያ ውሳኔ 65 አባላት ያሉት የጅቡቲ ምክር ቤት በሙሉ ድምጽ እንዳጸደቀ አፈ-ጉባኤ ዲሌይታ ሞሐመድ ዲሌይታ ለፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ተናግረዋል።

ፕሬዝደንቱ በምክር ቤቱ ይኹንታ ያገኘውን ውሳኔ ማጽደቅ አሊያም ሕዝበ-ውሳኔ እንዲካሔድ መጥራት ይኖርባቸዋል።

መረጃው የዶቼ ቨለ ሬድዮ ነው።

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🤔614610😡167😭60😱31💔24🕊23😢19👏15🥰9🙏5
TIKVAH-ETHIOPIA
Video
" የተቃጠለው ብሎክ 2ኛ ፎቅ ላይ ዶርም ተሰጥቶኝ የምኖር ነበርኩ፤ ብሎክ 17 ነው " - የዩኒቨርሲቲው ተማሪ

➡️ " በሰመራ ዩኒቨርሲቲ ይሄ ሁለተኛው ወይም ሶስተኛው የእሳት አደጋ ነው " - ዩኒቨርሲቲው

በሰመራ ዩኒቨርሲቲ ትላንት ምሽት በተማሪዎች ማደሪያ ብሎክ የተከሰተው ቃጠሎ ሰው ላይ ጉዳት እንዳላደረሰና መሰል አደጋ ግን መደጋሙን ዩኒቨርሲቲውና ተማሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

አንድ ዩኒቨርሲቲው ተማሪ፣ " አደጋው የተከሰተው ኤሌክትሪክ ኮንታክት አድርጎ ነው። ከዚያ 3ኛ ፎቅ ኮርኒሱ ችቡድ ስለሆነ በቀላሉ ተያያዘ። በተማሪዎች ላይ የደረሰ ጉዳት የለም። አልባሳት ግን ተቃጥለዋል። አደጋው የተከሰተው በተማሪዎች ዶርም ነው። እዛው የተቃጠለው ብሎክ 2ኛ ፎቅ ላይ ዶርም ተሰጥቶኝ የምኖር ነበርኩ፤ ብሎክ 17 ነው " ብሏል።

ዩኒቨርሲቲው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አለ ?

" እሳቱ 3ኛ ፍሎር ላይ ነው የተነሳው። ነበልባሉ እስከታች የደረሰ ይመስላል እንጅ 1ኛና 2ኛ ፎቅ እሳቱ ገርፎታል እንጅ አልተቀጣጠለም " ሲሉ የዩኒቨርሲቲው የህዝብ ግንኘነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ መሃመድ አህመድ ተናግረዋል።

የእሳት አደጋ ሰራተኞችና ተማሪዎች ባደረጉት ርብርብ እሳቱን ማጥፋት እንደተቻለ ገልጸው፣ " ሦስተኛው ፎቅ ተማሪዎች ስላልነበሩበት ዝግ ነው የነበረው። እሳት ገርፎት የተቃጠለ የሳፋሪኮም ገመድ አለ " ብለዋል።

" እሳቱ ከላይ ስለነበር የተነሳው ከታች ያሉት እቃዎች በመስኮት ጭምር አውጥተዋል፥ የደረሰ ጉዳት የለም፥ አንዳንድ ጫማም አንሶላም ረስቻለሁ የሚል ተማሪ ስላለ ነው ጉዳት ደረሰ የሚሉት " ነው ያሉት።

ቃጠሎ በተነሳበት ቦታ " ተማሪዎች ይኖሩ እንደነበር " እየገለጹ የተስተዋሉ አሉ፣ እርስዎ ደግሞ በዶርሙ ተማሪ አልነበረበትም አሉ፥ እንዴት ነው ነገሩ ? ስንል ጠይቀናቸው በሰጡን ምላሽም፣ " ሦስተኛ ፎቅ የተዘጋ ዶርም ነው፣ ተማሪ የለውም። አንደኛና ሁለተኛ ፎቅ ግን ተማሪዎች ነበሩ ግን በአደጋው ወቅት ወጥተዋል " ብለዋል።

የአደጋውን መንስኤ ስንጠይቃቸውም፣ " አደጋው እንዴት እንደተነሳ ገና አጣርተን ነው የሚታወቀው፤ መንስኤውን የሚያጣራ ኮሚቴ ተቋቁሟል፥ ለማጣራት ሁለት ቀናት ነው ተሰጠው፤ የምናሳወቅ ይሆናል " ሲሉ ተናግረዋል።

" በተለያዩ ጊዜያቶች የእሳት አደጋ ተፈጥሯል። በሰመራ ዩኒቨርሲቲ ይሄ ሁለተኛው ወይም ሶስተኛው የእሳት አደጋ ነው፤ ሰኔ እና ግንቦት ወራት ላይ ከሙቀቱ ጋር ተያይዞ ተማሪዎቹም ፋንም ስለሚጠቀሙ ገመዶች እየቀለጡ እሳቶች ይፈጠሩ ነበር " ሲሉም አስታውሰዋል።

ለተጨማሪ መረጃ ወደ ተማሪዎች ኀብረት ጽሕፈት ቤት ደውለን ስልክ ያልተነሳ ቢሆንም፣ የብሎኩ 2ኛ ፎቅ ነዋሪ ተማሪ እና የዩኒቨርሲቲው መምህር፣ ሦስተኛ ፎቅ ላይ ተማሪ አልነበረውም ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
842😢79🙏28🕊22😭22💔7👏6🥰4😱4🤔2😡1
በወጋገን ይሸለሙ

ወጋገን ባንክ ከጥቅምት 18 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በሚያካሂደው የጥያቄ እና መልስ ውድድር ጠቀም ያሉ ሽልማቶችን ይዞልዎት መጥቷል!

አሁኑኑ ከስር የተቀመጠውን የባንካችንን የቴሌግራም ቻናል ማስፈንጠሪያ ተጭነው በመቀላቀል እና ጥያቄዎችን ቀድመው በመመለስ ተሸላሚ ይሁኑ፡፡

👉ቴሌግራም https://www.tg-me.com/WegagenBanksc

ልብ ይበሉ! ይፋዊ የባንካችንን የቴሌግራም ቻናል በመቀላቀል እና ሌሎችም እንዲቀላቀሉ በመጋበዝ የጥያቄ እና መልስ ውድድሩን በመሳተፍ አሸናፊ ሲሆኑ ጠቀም ያሉ ሽልማቶችን ከባንካችን ያገኛሉ።

#WegagenBank #Question #Answer #Prize #Winner
116😡6😭3
" ያሰራጩት መረጃ ሀሰተኛ ነው " - ፖሊስ

የሙዚቃ ስራዎቻቸውን ለማቅረብ ወደ አዲስ አበባ የመጡት MAPARA A JAZZ የተባሉና የደቡብ አፍሪካ ዜግነት ያላቸው ሁለት ግለሰቦች" አዲስ አበባ ውስጥ አፈናና ድብደባ ተፈጽሞብናል " ብለው በፌስ ቡክ ገፃቸው ያሰራጩት መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን ማረጋገጡን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ።

የደቡብ አፍሪካ ዜግነት ያላቸው Mapara A JAZZ የተባሉት ወደ አዲስ አበባ መጥተው ነበር። ወደዚህ የመጡትም የሙዚቃ ስራቸውን ለማቅረብ ነበር።

እነዚህ ግለሰቦች ስራቸውን ጨርሰው በሠላም ወደ ሀገራቸው ከተመለሱ በኋላ " አዲስ አበባ ውስጥ አፈናና ድብደባ ተፈፅሞብናል " ብለው በፌስ ቡክ ገፃቸው ያሰራጩትን መረጃ መሰረት በማድረግ ፖሊስ ተገቢውን የማጣራት ተግባር እንዳከናወነ ገልጿል።

" ተፈፅሞብናል " ስላሉት ወንጀል ለፖሊስ መረጃ ደርሶ እንደሆነ ለማረጋገጥ በክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ እና በፖሊስ ጣቢያዎች ተጠይቆ ምንም ዓይነት የቀረበ አቤቱታ እንዳላገኘ አሳውቋል።

በፖሊስ ምርመራ የተሰባሰቡ የተንቀሳቃሽ ምስል፣ የፎቶና የድምጽ ማስረጃዎች እንዲሁም ከአዘጋጁ ቅሩንፉድ ኢንተርቴይመንት ጭምር እንደተረጋገጠው ግለሠቦቹ ይህን የሀሠት መረጃ የለቀቁት ብዙ ተከታዮችን ለማግኘት ሆን ብለው መሆኑን እንዳረጋገጠ አመልክቷል።

ግለሰቦቹ " አፈናና ድብደባ ተፈጽሞብናል " ያሉት አርብ ጥቅምት 14 ቀን 2018 ዓ/ም ቢሆንም በማግስቱ ጥቅምት 15 በተጋበዙበት መድረክ ላይ ተገኝተው የሙዚቃ ስራቸውን ፍጹም ሠላማዊ በሆነ መንገድ አቅርበው ማጠናቀቃቸው እና በሠላም ወደመጡበት ሀገር መመለሳቸውን ከኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት እንዲሁም ከአዘጋጆቹ መረጋገጡን አሳቋል።

ያሰራጩትም መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን ፖሊስ ገልጿል።

#AddisAbabPolice

@tikvahethiopia
1.12K😡287🤔89😢21😱11💔11🕊10😭10🥰6🙏6
2025/10/28 09:39:30
Back to Top
HTML Embed Code: