TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ወደ መቐለ የሚያመሩ መንገዶች ዛሬም ለሁለተኛ ቀን በሁለት አቅጣጫ በትግራይ ኃይል ሰልፈኞች ተዘግተዋል። የተዘጉት መንገዶች በትግራይ ምስራቃዊ ዞን ከመቐለ በ35 ኪሎ ሜትር ርቀት በምትገኘው የኣጉላዕ ከተማ ፤ በደቡባዊ ዞን ከመቐለ 100 ኪሎ ሜትር አከባቢ በምትርቀው የመኾኒ ከተማ መሆኑ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ መረጃ ደርሶታል። በተጨማሪ በሰሜን ምዕራብ ዞን ወደ እንዳስላሰ-ሽረ…
" ያነሱትን የደመወዝ ጭማሪ ፣ የጥቅማ ጥቅምና የመሬት ጥያቄ ለመመለስ የሚያስችል መመሪያ ለማውጣት ተዘጋጅተናል " - የክልሉ ካቢኔ
ዛሬ የትግራይ ኃይል አባላት ለሶስተኛ ቀን በአራት አቅጣጫ መንገዶችን ዘግተው ነበር።
ሁለቱ መንገዶች ከምስራቃዊና ደቡባዊ ዞኖች ወደ መቐለ ከተማ የሚወስዱ ሆነው ከከተማዋ በ35 እና በ100 ኪሎ ሜትር ርቀት በኣጉላዕና በመኾኒ የተዘጉ ነበሩ።
ሶስተኛው ከእንዳባጉና ወደ እንዳስላሰ-ሽረ ከተማ የሚያስገባ ሲሆን አራተኛው ደግሞ ከዓድዋ ወደ ዓዲግራት በሚወስደው መንገድ ' ሴሮ ' የተባለው አከባቢ ነበር።
ለግል የስራ ጉዳይ ከመቐለ በተምቤን በኩል ወደ አክሱም የተጓዘው የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል በዓድዋ በኩል ወደ ዓዲግራት ከተማ ሲጓዝ ' ሴሮ ' በሚባል አከባቢ መንገድ ከተዘጋባቸው ተጓዦች አንዱ ነው።
እንደ አባላችን የአይን ምልከታ መንገዱ ከጥዋቱ 2:30 ተዘግቶ ከሰዓት በኃላ 9:40 ነው የተከፈተው።
የአከባቢው አስተዳዳሪዎች መንገዱን የዘጉትን የትግራይ ኃይል አባላት ለማነጋገር ጥረት ቢያደርጉም " ከክልሉ ፕሬዜዳንት ለተላከ አመራር ካልሆነ ለሚድያም ይሁን ለአከባቢው አስተዳዳሪዎች ቃላችን ለመስጠት ፍቃደኛ አይደለንም " በማለት ከልክለዋል።
በዚሁ ቃላቸው ፀንተው በግራና በቀኝ የተጓዙ መኪኖች በማቆም በርካታ ተጓዦች ለእንግልት ተደርገው ቆይተዋል።
ከቀኑ 9:40 መንገዱ እንዲከፈት ተደርጓል።
መንገዱ የተከፈተው በስልክ ተነጋግረው ካልሆነ በስተቀር ወደ ቦታው በአካል የመጣ የክልሉ ከፍተኛ አመራር እንደሌለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል አረጋግጧል።
ወደ መቐለና ወደ እንዳስላሰ-ሽረ ከተማ የሚያመሩ ሶስት መንገዶች ከሰዓት በፊት ሲከፈቱ ፤ አባላችን የነበረበት አቅጣጫ ከሰዓት በኃላ ነው የተከፈተው።
የክልሉ ካቢኔ በመንግስት የኮሚኒኬሽን ቢሮ በኩል ጥቅምት 5 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ፤ " የሰራዊቱ አባላት ያነሱት የደመወዝ ጭማሪ ፣ የጥቅማ ጥቅምና የመሬት ጥያቄ ለመመለስ የሚያስችል መመሪያ ለማውጣት ተዘጋጅተናል " ሲል አስታውቋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia

❤1.27K👏88🕊51🤔36😭24🙏17😢11🥰10😡10💔7😱1
እነሆ ጊዜዎን የሚያቀል አዲሱ አገልግሎታችን ! ገንዘብ ገቢ ወይም ወጪ ለማድረግ ወደ ባንካችን ቅርንጫፍ ሲሄዱ፣ ቀድመው በአቢሲንያ ሞባይል መተግበሪያ ፎርሙን በመሙላት ጊዜዎን ይቆጥቡ። ሲጨርሱ በእጅ ስልክዎ ልዩ ቁጥር ይደርስዎታል። የባንካችን ቅርንጫፍ እንደ ደረሱም፣ የተላከልዎትን ቁጥር በማሳየት የፈለጉትን የቅርንጫፍ አገልግሎት በቀላሉ ማግኘት ይችላሉ። #ወረቀትአልባየባንክአገልግሎት #Paperlessbranchmodel #BanksinEthiopia #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
❤143😡13🙏7🥰4👏4😭2🕊1
ዛሬዉኑ የM-PESAን ማህበራዊ ሚዲያ ገፆች ይቀላቀሉ።
Telegram: https://www.tg-me.com/mpesaethiopia733
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/m-pesaethiopia/
Facebook: https://www.facebook.com/61572410606905/
Instagram: www.instagram.com/mpesa.ethiopia
X (Twitter): M-PESA Ethiopia (@m_ethiopia58462) / X
TikTok: https://www.tiktok.com/@mpesa.ethiopia/
YouTube: https://youtube.com/@m-pesaethiopia?si=jldsrSE888ts2ZOe
መተግበሪያውን ለማውረድ ይህንን ይጫኑ:
https://onelink.to/ewsb22
#MPESA #MPESAEthiopia

❤81🙏5😡3
TIKVAH-ETHIOPIA
#Kenya የኬንያው ጉምቱ ፖለቲከኛ ራይላ ኦዲንጋ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ ህንድ ሀገር በህክምና ሲረዱ ቆይተው በ80 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። ራይላ ኦዲንጋ ለኬንያ ፕሬዚዳንትነት 5 ጊዜ ዕጩ ሆነው ቢቀርቡም አልተሳካላቸውም። በተጨማሪ በቅርቡ ለአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበርነት ቦታ ቢወዳደሩም ማሸነፍ ሳይችሉ ቀርተዋል። ለረጅም አመታት…
#Kenya
የኬንያ የቀድሞ ጠቅላይ ሚንስትር ራይላ ኦሞሎ ኦዲንጋ ሞት ተከትሎ በናይሮቢ ከተማ ዉጥረት ነግሶ ውሏል።
የቲክቫህ ኢትዮጵያ - ናይሮቢ
በሕንድ ሀገር በሕክም ላይ እያሉ ሕይወታቸው ያለፈዉን የቀድሞ የኬንያ ጠቅላይ ሚንስትር ራይላ ኦሞሎ ኦዲንጋ ተከትሎ በኬንያ ከተሞች የተለያዩ ሰልፎችና መሰል እንቅስቃሴዎች የተስተዋሉ መሆኑን ናይሮቢ የሚገኘው የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባል ገልጿል።
በዋና ከተማዋ ናይሮቢ ሱቁችን የመሰባበርና በአሁኑ ወቅት ሀገሪቱን እየመሩ የሚገኙት ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ስልጣን እንዲለቁ የሚጠይቁ መፎክሮችን ያነገቡ ሰልፈኞች በብዛት መስተዋላቸውን በስፍራው የሚገኘው አባላችን አመልክቷል።
በናይሮቢ ከተማ እሲሊ፣ ካሜይኮ አከባቢዎች እነዚህ እንቅስቃሴዎች የተደረጉ ሲሆን በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ሀዘናቸውን የሚገልፁ ዜጎች የተለያዩ ቅጠሎችንና የስራ መሳሪያዎችን ይዘዉ በየመንገዱ ታይተዋል።
ከዚህም በተጨማሪ በሀገሬዉ ሕዝብ በእጅጉ የሚወደዱትና በወቅቱ የኬንያ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ 'የነፃነት ታጋይ፣ የሀገር ወዳድነት ተምሳሌትና የዴሞክራሲ አባት' ተብለዉ የተገለፁት ጉምቱዉ ፖለቲከኛ ራይላ ኦሞሎ ኦዲንጋ በተወለዱበት የኬንያ ሶስተኛዋ ትልቅ ከተማ ኪሱሙ፣ ናይኩሩና ቦባሳ አከባቢዎችም ሰልፍ መሰል እንቅስቃሴ ጎልቶ ተስተዉሏል።
የራይላ ኦዲንጋ አስክሬን ወደ ሀገራቸው ገብቶ እሁድ በተወለዱበት አከባቢ ኪሱሙ ሲያያ ካዉንቲ ቦንዶ በባለ ስፍራ ግብአት መሬታቸው እንደሚከናወን ተሰምቷል።
የራይላ ኦዲንጋን ሞት ተከትሎ የፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ አስተዳደር የ7 ቀን ሀዘን አውጇል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ናይሮቢ
#TikvahEthiopiaFamily

❤534😭58🤔19🕊18🙏9😡6👏5🥰2😢1
TIKVAH-ETHIOPIA
" ያነሱትን የደመወዝ ጭማሪ ፣ የጥቅማ ጥቅምና የመሬት ጥያቄ ለመመለስ የሚያስችል መመሪያ ለማውጣት ተዘጋጅተናል " - የክልሉ ካቢኔ ዛሬ የትግራይ ኃይል አባላት ለሶስተኛ ቀን በአራት አቅጣጫ መንገዶችን ዘግተው ነበር። ሁለቱ መንገዶች ከምስራቃዊና ደቡባዊ ዞኖች ወደ መቐለ ከተማ የሚወስዱ ሆነው ከከተማዋ በ35 እና በ100 ኪሎ ሜትር ርቀት በኣጉላዕና በመኾኒ የተዘጉ ነበሩ። ሶስተኛው ከእንዳባጉና ወደ…
#Tigray
የትግራይ ኃይል አባላት ሰልፈኞች ለአራተኛ ቀን ዛሬ የመኪና መንገድ ዘግተዋል።
ዛሬ ጥቅምት 6/2018 ዓ.ም የትግራይ ምስራቃዊ ዞን ዋና ከተማ ወደ ሆነችው የዓዲግራት ከተማ የሚያስገቡና የሚያስወጡ ሶስት ዋና መንገዶች ተዘግተዋል።
ትናንት ጥቅምት 5/2018 ዓ.ም ከዓድዋ ወደ ዓዲግራት ሲጓዝ ሴሮ በተባለ ቦታ መንገድ ተዘግቶበት ከሰዓት በኃላ ተከፎቶ ወደ ከተማዋ የተጓዘው የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል እንዳረጋገጠው ፤ ከዓዲግራት ወደ መቐለ ዓድዋና ዛላአንበሳ አቅጣጫ የሚያመሩ መንገዶች ተዘግተዋል።
ከጥቅምት 3/2018 ዓ.ም ወዲህ ከክልሉ ምስራቃዊ ፣ ደቡባዊ ዞኖች ወደ መቐለ የሚወስዱ መንገዶች በኣጉላዕና ፣ በመኾኒ ወደ እንዳስላሰ-ሽረ ከተማ የሚወስድ መንገድ በእንዳባጉና ከዓድዋ ወደ ዓዲግራት የሚወስድ በሴሮ ተዘግተው በዚያው ቀን በተለያዩ ሰዓቶች መከፈታቸው ይታወሳል።
የክልሉ ካቢኔ በመንግስት የኮሙኒኬሽን ቢሮ በኩል ጥቅምት 5/2018 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ፤ የሰራዊቱ አባላት ያነሱት የደመወዝ ጭማሪ የጥቅማ ጥቅምና የመሬት ጥያቄ ለመመለስ የሚያስችል መመሪያ ማውጣቱን ትላንት አሳውቆ ነበር።
ያም ቢሆን ግን ዛሬም መንገዶች ተዘግተዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

❤464👏71🕊46😡30😭17😢14🥰7🤔7
" የወላዷን ስቃይ ሳይ ግን አልቻልኩም፣ በጣም ደከመኝ እንባዋን ሳይ እኔም ባለሁበት ቁጭ ብየ አለቀስኩ ፤ የእኔ ማልቀስ ግን ህፃኑን ማትረፍ አልቻለም፣ በዚህም በጣም አዝኛለሁ " - የአምቡላንስ ሹፌር
በጎፋ ዞን መሎ ጋዳ አካባቢ አንድ የአምቡላንስ ሹፌር አንዲት ወላድ እናትን ወደ ሆስፒታል ይዞ ሲጓዝ አምቡላንሷ በጭቃ ተውጣ እና ሹፌሩ መኪናዋን ለማውጣት የቻለውን በሙሉ አድርጎ ሲያቅተው በጭቃው ላይ ቁጭ ብሎ ሲያለቅስ የሚያሳይ ምስል በተለያዩ የማህበራዊ ገጾች ላይ ተዘዋውሮ ነበር።
ቲክቫህ ኢትዮጵያም ይህንን የአምቡላንስ ሹፌር በስልክ አግኝቶ ስለተፈጠረው ነገር አነጋግሯል።
ይህ ሹፌር ሀብታሙ ደርጉ ደረሰ ይባላል።
ሹፌር ሀብታሙ ደርጉ ደረሰ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አለ ?
" ችግሩ የተፈጠረው ከመሎ ጋዳ ወረዳ አንዲት ወላድ እናት በወሊድ ምክንያት ሪፈር ተጽፎላት ወደ ጎፋ ዞን ሆስፒታል ይዤ እየሄድኩ እያለ ልዩ ስሙ ጃውላ መንገድ ተብሎ በሚጠራው ቦታ ላይ ጥቅምት 2/2018 ዓ.ም ከሌሊቱ 8 ስአት ላይ ነው።
ከወላዷ ጋር የነበሩ ሰዎች ከእኔ ጋር በመሆን መኪናዋን ከጭቃው ለማውጣት እየታገልን እያለ ወላዷ በዚሁ ቦታ ላይ ወለደች፣ የሚያሳዝነው ግን የተወለደው ህጻን ሞቷል።
በመቀጠልም ስለተፈጠረው ነገር ለሃላፊዬ ደወልኩና ነገርኩት፣ እናትየዋ የደም ካንሰር ስላለባት በህይወት ለመቆየት ወደ ሆስፒታል መድረስ አለባት አልኩት። ከዛም ከቡልቄ ወረዳ ሌላ አምብላንስ መጥቶ እናትየዋን እንድወስዳት ተደረገ።
ይህ ነገር ከመሆኑ በፊት ግን እናትየዋን እና ህፃኑን በህይወት ለማዳን የግድ አምብላንሷን ከጭቃው ማላቀቅ ስለነበረብኝ ብዙ ስቆፍር ነበር። ነገር ግን አልሆነም፣ እኔም በዚያ ብርድ ላይ ስቆፍር አድሬ ሰኞ እለት ጠዋት 2:30 አካባቢ ላይ ወደ ጋዳ ተመልስኩ።
በሰአቱ የተሰማኝ ስሜት ከባድ ነው፣ ቆፍሬ፣ ቆፍሬ ሲደክመኝ በአካባቢው ያሉ ሰዎች እንዲረዱን አምቡላንሷን ሳስጮሀት ነበር። ግን መጀመሪያ ላይ ማንም አልመጣልንም። አብረውኝ የህክምና ባለሙያን ጨምሮ የወላዷ ባለቤት እና አማቿ ነበሩ።
በሰአቱ የወላዷን ስቃይ ሳይ አልቻልኩም፣ በጣም ደከመኝ፣ እንባዋን ሳይ እኔም ባለሁበት ቁጭ ብየ አለቀስኩ ፤ የእኔ ማልቀስ ግን ህፃኑን ማትረፍ አልቻለም፣ በዚህም በጣም አዝኛለሁ።
በህይወት የሌለ ልጅ የወለደችው እናት በስአቱ በጣም ደክሟት ነበር፣ ምክንያቱም የደም ካንሰር አለባት። ሌለኛው አምቡላንስ ወደ ሆስፒታል ወስዶ ካደረሳት በሗላ ወደ ጥቁር አንበሳ ሪፈራል ሆስፒታል ሪፈር ተጽፎላታል፣ ነገር ግን ለህክምናው የተጠየቀችው ገንዘብ ወደ 800 ሺህ ብር ስለሆነ ገና እርዳታ እያሰባሰብን ነው።
በአምቡላንስ ሹፍርና እያገለገልኩ ሁለት አመት ቆይቻለሁ፣ ብዙ ጊዜም ተመሳሳይ ችግር ይገጥመኛል፣ ሁለት እና ሶስት ቀን መንገድ ላይ የማድርባቸው አጋጣሚዎችም ነበሩ። በተደጋጋሚ የእናቶችን ከፍተኛ የሆነ ሲቃይ አይቻለሁ። በዚህኛው ግን በጣም ተስፋ ቆርጨ ከዚህ በሗላ መኪና ላለማሽከርከር አስቤ ነበር። በፌስቡክ የእኔን ምስል ብዙዎች ሲቀባበሉት ስመለከት እና ብዙዎች ለእናቶች ያላቸውን ፍቅር ሲገልፁ ሳይ ግን በጣም ደስ ብሎኛል።
ሁሌም በመንገድ ጉዳይ እንደተሰቃየን ነው፣ ችግሩ ጫፍ የወጣ ነው። የእናቶችን እና የህፃናቶችን ሞት ለማቆም ሁሉም ሰው ለመሎ ጋዳ መንገድ ትኩረት ሊሰጥ ይገባል " ሲል ተናግሯል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ

261❤5.06K😢928😭467💔295🙏227👏108🕊43😡29🥰17🤔14😱14