TIKVAH-ETHIOPIA
" ያነሱትን የደመወዝ ጭማሪ ፣ የጥቅማ ጥቅምና የመሬት ጥያቄ ለመመለስ የሚያስችል መመሪያ ለማውጣት ተዘጋጅተናል " - የክልሉ ካቢኔ ዛሬ የትግራይ ኃይል አባላት ለሶስተኛ ቀን በአራት አቅጣጫ መንገዶችን ዘግተው ነበር። ሁለቱ መንገዶች ከምስራቃዊና ደቡባዊ ዞኖች ወደ መቐለ ከተማ የሚወስዱ ሆነው ከከተማዋ በ35 እና በ100 ኪሎ ሜትር ርቀት በኣጉላዕና በመኾኒ የተዘጉ ነበሩ። ሶስተኛው ከእንዳባጉና ወደ…
#Tigray
የትግራይ ኃይል አባላት ሰልፈኞች ለአራተኛ ቀን ዛሬ የመኪና መንገድ ዘግተዋል።
ዛሬ ጥቅምት 6/2018 ዓ.ም የትግራይ ምስራቃዊ ዞን ዋና ከተማ ወደ ሆነችው የዓዲግራት ከተማ የሚያስገቡና የሚያስወጡ ሶስት ዋና መንገዶች ተዘግተዋል።
ትናንት ጥቅምት 5/2018 ዓ.ም ከዓድዋ ወደ ዓዲግራት ሲጓዝ ሴሮ በተባለ ቦታ መንገድ ተዘግቶበት ከሰዓት በኃላ ተከፎቶ ወደ ከተማዋ የተጓዘው የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል እንዳረጋገጠው ፤ ከዓዲግራት ወደ መቐለ ዓድዋና ዛላአንበሳ አቅጣጫ የሚያመሩ መንገዶች ተዘግተዋል።
ከጥቅምት 3/2018 ዓ.ም ወዲህ ከክልሉ ምስራቃዊ ፣ ደቡባዊ ዞኖች ወደ መቐለ የሚወስዱ መንገዶች በኣጉላዕና ፣ በመኾኒ ወደ እንዳስላሰ-ሽረ ከተማ የሚወስድ መንገድ በእንዳባጉና ከዓድዋ ወደ ዓዲግራት የሚወስድ በሴሮ ተዘግተው በዚያው ቀን በተለያዩ ሰዓቶች መከፈታቸው ይታወሳል።
የክልሉ ካቢኔ በመንግስት የኮሙኒኬሽን ቢሮ በኩል ጥቅምት 5/2018 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ፤ የሰራዊቱ አባላት ያነሱት የደመወዝ ጭማሪ የጥቅማ ጥቅምና የመሬት ጥያቄ ለመመለስ የሚያስችል መመሪያ ማውጣቱን ትላንት አሳውቆ ነበር።
ያም ቢሆን ግን ዛሬም መንገዶች ተዘግተዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia

❤454👏70🕊46😡30😭17😢14🤔7🥰6
" የወላዷን ስቃይ ሳይ ግን አልቻልኩም፣ በጣም ደከመኝ እንባዋን ሳይ እኔም ባለሁበት ቁጭ ብየ አለቀስኩ ፤ የእኔ ማልቀስ ግን ህፃኑን ማትረፍ አልቻለም፣ በዚህም በጣም አዝኛለሁ " - የአምቡላንስ ሹፌር
በጎፋ ዞን መሎ ጋዳ አካባቢ አንድ የአምቡላንስ ሹፌር አንዲት ወላድ እናትን ወደ ሆስፒታል ይዞ ሲጓዝ አምቡላንሷ በጭቃ ተውጣ እና ሹፌሩ መኪናዋን ለማውጣት የቻለውን በሙሉ አድርጎ ሲያቅተው በጭቃው ላይ ቁጭ ብሎ ሲያለቅስ የሚያሳይ ምስል በተለያዩ የማህበራዊ ገጾች ላይ ተዘዋውሮ ነበር።
ቲክቫህ ኢትዮጵያም ይህንን የአምቡላንስ ሹፌር በስልክ አግኝቶ ስለተፈጠረው ነገር አነጋግሯል።
ይህ ሹፌር ሀብታሙ ደርጉ ደረሰ ይባላል።
ሹፌር ሀብታሙ ደርጉ ደረሰ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አለ ?
" ችግሩ የተፈጠረው ከመሎ ጋዳ ወረዳ አንዲት ወላድ እናት በወሊድ ምክንያት ሪፈር ተጽፎላት ወደ ጎፋ ዞን ሆስፒታል ይዤ እየሄድኩ እያለ ልዩ ስሙ ጃውላ መንገድ ተብሎ በሚጠራው ቦታ ላይ ጥቅምት 2/2018 ዓ.ም ከሌሊቱ 8 ስአት ላይ ነው።
ከወላዷ ጋር የነበሩ ሰዎች ከእኔ ጋር በመሆን መኪናዋን ከጭቃው ለማውጣት እየታገልን እያለ ወላዷ በዚሁ ቦታ ላይ ወለደች፣ የሚያሳዝነው ግን የተወለደው ህጻን ሞቷል።
በመቀጠልም ስለተፈጠረው ነገር ለሃላፊዬ ደወልኩና ነገርኩት፣ እናትየዋ የደም ካንሰር ስላለባት በህይወት ለመቆየት ወደ ሆስፒታል መድረስ አለባት አልኩት። ከዛም ከቡልቄ ወረዳ ሌላ አምብላንስ መጥቶ እናትየዋን እንድወስዳት ተደረገ።
ይህ ነገር ከመሆኑ በፊት ግን እናትየዋን እና ህፃኑን በህይወት ለማዳን የግድ አምብላንሷን ከጭቃው ማላቀቅ ስለነበረብኝ ብዙ ስቆፍር ነበር። ነገር ግን አልሆነም፣ እኔም በዚያ ብርድ ላይ ስቆፍር አድሬ ሰኞ እለት ጠዋት 2:30 አካባቢ ላይ ወደ ጋዳ ተመልስኩ።
በሰአቱ የተሰማኝ ስሜት ከባድ ነው፣ ቆፍሬ፣ ቆፍሬ ሲደክመኝ በአካባቢው ያሉ ሰዎች እንዲረዱን አምቡላንሷን ሳስጮሀት ነበር። ግን መጀመሪያ ላይ ማንም አልመጣልንም። አብረውኝ የህክምና ባለሙያን ጨምሮ የወላዷ ባለቤት እና አማቿ ነበሩ።
በሰአቱ የወላዷን ስቃይ ሳይ አልቻልኩም፣ በጣም ደከመኝ፣ እንባዋን ሳይ እኔም ባለሁበት ቁጭ ብየ አለቀስኩ ፤ የእኔ ማልቀስ ግን ህፃኑን ማትረፍ አልቻለም፣ በዚህም በጣም አዝኛለሁ።
በህይወት የሌለ ልጅ የወለደችው እናት በስአቱ በጣም ደክሟት ነበር፣ ምክንያቱም የደም ካንሰር አለባት። ሌለኛው አምቡላንስ ወደ ሆስፒታል ወስዶ ካደረሳት በሗላ ወደ ጥቁር አንበሳ ሪፈራል ሆስፒታል ሪፈር ተጽፎላታል፣ ነገር ግን ለህክምናው የተጠየቀችው ገንዘብ ወደ 800 ሺህ ብር ስለሆነ ገና እርዳታ እያሰባሰብን ነው።
በአምቡላንስ ሹፍርና እያገለገልኩ ሁለት አመት ቆይቻለሁ፣ ብዙ ጊዜም ተመሳሳይ ችግር ይገጥመኛል፣ ሁለት እና ሶስት ቀን መንገድ ላይ የማድርባቸው አጋጣሚዎችም ነበሩ። በተደጋጋሚ የእናቶችን ከፍተኛ የሆነ ሲቃይ አይቻለሁ። በዚህኛው ግን በጣም ተስፋ ቆርጨ ከዚህ በሗላ መኪና ላለማሽከርከር አስቤ ነበር። በፌስቡክ የእኔን ምስል ብዙዎች ሲቀባበሉት ስመለከት እና ብዙዎች ለእናቶች ያላቸውን ፍቅር ሲገልፁ ሳይ ግን በጣም ደስ ብሎኛል።
ሁሌም በመንገድ ጉዳይ እንደተሰቃየን ነው፣ ችግሩ ጫፍ የወጣ ነው። የእናቶችን እና የህፃናቶችን ሞት ለማቆም ሁሉም ሰው ለመሎ ጋዳ መንገድ ትኩረት ሊሰጥ ይገባል " ሲል ተናግሯል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ

261❤5K😢923😭464💔291🙏224👏107🕊43😡29🥰16🤔14😱13
#AwashBank
እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን!
===========
አዋሽ ባንክ በዓለም አቀፍ የቁጠባ እና የሪቴል ባንኪንግ ተቋም እንዲሁም የአውሮፓ የቁጠባ እና የሪቴል ባንኪንግ ቡድን በጋራ የሚያዘጋጁትን የWSBI-ESBG አዋርድ አሸናፊ ሆነ።
ይህንኑ ሽልማት በትላንትናው እለት በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ በተካሄደው የWSBI-ESBG የሽልማት መርሃ-ግብር ላይ በመገኘት የባንካችን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ፀሀይ ሽፈራው ተቀብለዋል። ባንካችንም ይህን እውቅና ሊያገኝ የቻለው የዘላቂ ልማት ግቦች ትግበራ ላይ የላቀ አፈፃፀም በማስመዝገብ እንዲሁም አርዓያነት ያለቸውን ምርጥ አሰራሮችን በተለያዩ ዘርፎች በማስመዝገቡ ነው። ከነኚህ ዘርፎችም መካከል ፡-
* በአካታች የባንክ አገልግሎት እና ማህበራዊ ተፅዕኖ፣
* በኢኮኖሚያዊ ዕድገት እና አቅም ማጎልበት፣
* በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እና የቴክኖሎጂ ፈጠራ እንዲሁም
* ደንበኛ ተኮር የአቅም ግንባታ ማከናወን ይገኙባቸዋል፡፡
ይህ የእውቅና ሽልማት የተገኘው ክቡራን ደንበኞቻችን በባንካችን ላይ ባሳደራችሁት እምነት በመሆኑ በዚሁ አጋጣሚ የላቀ ምስጋናችንን እያቀረብን ለወደፊቱም በበለጠ ልናገለግላችሁ ዝግጁ መሆናችንን በአክብሮት እንገልፃለን፡፡
አዋሽ ባንክ!
#AwashBank #WSBI_ESBGAwards

2❤649👏91🙏44😡40🤔16🥰9😱4🕊4😭3😢1
“አንድ ፖሊስ ጥይት ባርቆበት ነው ልጁ የሞተው ” - የአካባቢው ባለስልጣን
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጌዲኦ ዞን ወናጎ ከተማ አስተዳደር አንድ ወጣት “በግዴለሽ አያያዝ” ከፖሊስ በተባረቀ ጥይት ሕይወቱ ማለፉን የአካባቢው ባለስልጣን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
“በወናጎ ወረዳ” አንድ በጋራዥ ሥራ የተሳማራ ወጣት ትላንት ለሻይ በተቀመጠበት አጠገቡ የነበረ ፖሊስ ጥይት ባርቆበት እንደቆሰለና ወደ ህክምና ቢወሰድም ህይወቱን ማትረፍ እንዳልተቻለ ተሰምቷል፡፡
በቦታው የነበሩ ሰዎች፣ “ፖሊሱ መሳሪያውን አቀባብሎ ጭኑ ላይ አስቀምጦት ነበር፤ ይሁን እንጅ ጥይት ለማቀባበል የሚያደርስ በአካባቢው የተለዬ የጸጥታ ችግር አልነበረም” ብለዋል፡፡
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ስለሁነቱ አንድ የአካባቢወን ባለስልጣን ያነጋገረ ሲሆን፣ ጥቃቱ መድረሱን አረጋግጠው፣ ድርጊቱ የተፈጠረው ግን “ወናጎ ወረዳ ላይ ሳይሆን ከተማ አስተዳደሩ ላይ ነው፤ ከተማ አስተዳደሩና ወረዳው ይለያያሉ” ሲሉ ገልጸዋል፡፡
ሁነቱን ሲያስረዱም፣ “አንድ ፖሊስ ጥይት ባርቆበት ነው ልጁ ላይ የሞት ጉዳት የደረሰው፡፡ ፖሊስ ሆን ብሎ ያደረገው ነገር አይደለም” ነው ያሉት፡፡
“ከተማ አስተዳደሩ ውስጥ ባጋጣሚ የተፈጠረ እንጅ ሆን ተብሎ የተደረገ ድርጊት አይደለም” ያሉት እኝሁ አካል፣ “ፖሊሱ በሕግ ጥላ ሥር ነው ያለው” ሲሉም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል፡፡

1😭1.27K❤563😡186😢62💔62🕊31🙏21🤔17🥰9😱6
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ዲቫይዞቹ በኢትዮ ቴሌኮም ብራንድ፣ ስያሜ እና ዲዛይን የተመረቱ ናቸው " - ኢትዮ ቴሌኮም
ኢትዮ ቴሌኮም በክላውድ ላይ የተመሰረቱ "ዘኔክሰስ" ሲል የጠራቸው ስማርት ዲቫይስ እና የክላውድ ዎርክስፔስ መፍትሄዎችን ማቅረቡን ይፋ አድርጓል።
በዛሬው ዕለት ይፋ የተደረጉት ዲቫይዞች በከፍተኛ የስማርት ዲቫይሶች ዋጋ ምክንያት የተከሰተውን የአጠቃቀም ክፍተት (usage gap) ለመሙላት ያስችላሉ ተብሏል።
የአጠቃቀም ክፍተትን ለመሙላት ያስችላሉ የተባሉት እና ኢትዮ ቴሌኮም ይፋ ያደረጋቸው " ዘኔክሰስ " የተሰኙት ዲቫይዞች :-
- የሞባይል ስልኮች፣
- ታብሌቶች፣
- ዴስክቶፖች፣
- ላፕቶፖች፣
- ቲን ክላየንት (thin clients) እና የክላውድ ዎርክስፔስ መፍትሔዎችን ያካተቱ ናቸው።
ዲቫይዞችን ይፋ ያደረጉት የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ " ከ60 በመቶ በላይ የሚሆኑት ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት የሚገኙ የሞባይል ተጠቃሚዎች የኔትወርክ ሽፋን ያለበት አካባቢ የሚኖሩ ቢሆንም የስማርት ስልኮችን መግዛት ባለመቻላቸው ከዲጂታል አገልግሎቶች ተገልለው ይገኛሉ " ብለዋል።
ይህንን ማህበረሰብ ወደ ዲጂታል አገልግሎቱ ማስገባት እንዲቻል ዲቫይዞቹ ይፋ መደረጋቸውን ዋና ስራ አስፋጻሚዋ ገልጸው " ዲቫይዞቹ በኢትዮ ቴሌኮም ብራንድ፣ ስያሜ እና ዲዛይን የተመረቱ ናቸው " ብለዋል።
በእዚህ አመት 3.5 ሚሊየን ዲቫይዞችን በተለያየ ሞዴል ለማቅረብ አስበናል ያሉት ዋና ስራ አስፈጻሚዋ ዘ ኔክሰስ የኢትዮጵያ ማርኬት ለሌሎችም ገበያ እንዲሆን ታልሞ ይህንን ስያሜ መሰጠቱን ጠቅሰዋል።
በተጨማሪም ስማርት ፊቸር ፎን የተባለበት ምክንያት ተች ያለው በመሆኑ ፣ ከክላውድ ጋር የተገናኘ እና የተለያዩ አይነት አፕልኬሽኖችን ማስጠቀም የሚችል በመሆኑ ምክንያት መሆኑን አስረድተዋል።
ስቶሬጅን በሚመለከትም በሚያስፈልጋቸው ልክ እያሳደጉ የሚጠቀሙበት እድል ተፈጥሯል ብለዋል።
የሞባይል ቀፎዎቹ የቀረቡበትን ዋጋ በቀጥታ ያልገለጹ ሲሆን ተመሳሳይ ደረጃ ላይ ካሉ ስልኮች ጋር ሲነጻጸር ግን ከ60 -70 በመቶ ዋጋው እንደሚቀንስ አስረድተዋል።
ዲቫይዞቹ በሁለቱም (keypad + touchscreen) ማስጠቀም የሚያስችሉ ፣ ረጅም የባትሪ ዕድሜ ያላቸው፣ በተገጠመ የቴሌስቶሬጅ (teleStorage) አማካኝነት የፋይል ማከማቻ ገደቦችን የሚያስወግዱ እና የቴሌብር፣ የትምህርት ይዘቶች እንዲሁም ሚዲያዎች ያሉ አፕሊኬሽኖችን የተጫነባቸው እንደሆኑ ተገልጿል።
ይፋ የተደረጉት ስማርት ዲቫይሶች:-
➡️ ዘኔክሰስ 127 ላይት (znexus 127 Lite)፣
➡️ ዘኔክሰስ 131 ላይት (znexus 131 Lite) እና ➡️ ዘኔክሰስ 2028 ላይት (znexus 2028 Lite) ሞዴሎች ናቸው።
ዲቫይዞቹ ዩቲዩብ፣ ቲክቶክ፣ ፌስቡክ፣ ጌሞች፣ አጫጭር ፊልሞች እና ዜናዎች የመሳሰሉ መተግበሪያዎች በክላውድ በማቅረብ ተጠቃሚዎች በቀላሉ የስማርት ስልክ (smartphone-lite) ተሞክሮ እንዲያገኙ ያስችላሉ ተብሏል።
ዘኔክሰስ በክላውድ ላይ የተመሰረተ እና ስማርት ስልኮች የሚሰጡትን አገልግሎት መስጠት የሚያስችል የስልክ አይነት መሆኑን ይፋ በማድረጊያ ስነ ስርአቱ ወቅት ተገልጿል።
በተጨማሪም ኢትዮ ቴሌኮም "ዘኔክሰስ ክላውድ ወርክስፔስ ሶሉሽን" ይፋ ያደረገ ሲሆን የክላውድ ወርክስፔስ ሶሉሽኑ ቢዝነሶችን፣ የመንግስት እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ቨርቹዋል ዴስክቶፖችን እና አፕሊኬሽኖችን ከማንኛውም ዲቫይስ ጋር ለማገናኘት የሚያስችል መሆኑን እና የአይ.ቲ ወጪዎችን ለመቀነስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ተነግሯል።

❤755😡44👏34🙏15😭12🕊9🤔6🥰2😱2
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" በአስክሬን ሽኝቱ ፕሮግራም ላይ በተነሳ ብጥብጥ 7 ሰዎች ሞተዋል " - ነዋሪዎች
ዛሬ በናይሮቢ ካሲራኒ ለቀድሞዉ የኬንያ ጠቅላይ ሚንስትር ራይላ ኦዲንጋ የአስከሬን ሽኝት መርሃግብር ተካሂዷል።
በዚሁ ወቅት በተነሳ ብጥብጥ የሰባት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የዐይን እማኞች ናይሮቢ ለሚገኘው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ባልደረባ ተናግረዋል።
እንደ ዐይን እማኞቹ ገለፃ ሁለት ሰዎች ከፀጥታ ሃይል በተተኮሰ ጥይት የተገደሉ ሲሆን አምስት ሰዎች ተኩሱን ተከትሎ በነበረ ግርግር ሕይወታቸው ማለፉን ገልፀዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በስፍራው ተገኘቶ እንደተመለከዉ በስታዲየሙ የራይላ ኦዲንጋ አስክሬን ስንብት እየተካሄደ በነበረበት የተወሰኑ ወጣቶች ከፀጥታ አካላት ጋር በፈጠሩት አለመግባባት ጥይት የተተኮሰ ሲሆን አስለቃሽ ጭስም ተወርውሮ ሕዝቡ ከስታዲየሙ እንዲወጣ ተደርጓል።
የሀገሪቱ ሚዲያዎች የሟቾችን ቁጥር ሁለት ብለዉ የዘገቡ ሲሆን ጉዳት ስለደረሰባቸው ሰዎች እስካሁን ምንም የተባለ ነገር የለም።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ናይሮቢ
#TikvahEthiopiaFamilyNairobi

❤466😢140🤔40💔20😭19😡17🕊15🥰7👏7😱7🙏3