TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray የትግራይ ኃይል አባላት ሰልፈኞች ለአራተኛ ቀን ዛሬ የመኪና መንገድ ዘግተዋል። ዛሬ ጥቅምት 6/2018 ዓ.ም የትግራይ ምስራቃዊ ዞን ዋና ከተማ ወደ ሆነችው የዓዲግራት ከተማ የሚያስገቡና የሚያስወጡ ሶስት ዋና መንገዶች ተዘግተዋል። ትናንት ጥቅምት 5/2018 ዓ.ም ከዓድዋ ወደ ዓዲግራት ሲጓዝ ሴሮ በተባለ ቦታ መንገድ ተዘግቶበት ከሰዓት በኃላ ተከፎቶ ወደ ከተማዋ የተጓዘው የቲክቫህ ኢትዮጵያ…
#Tigray
የትግራይ ኃይል አባላት ሰልፈኞች ዛሬም ለአምስተኛ ቀን የመኪና መንገድ ዘግተው ውለዋል።
ትናንት ጥቅምት 6/2018 ዓ.ም ወደ ዓዳግራት ከተማ የሚያስገቡና የሚያስወጡ በሶስት አቅጣጫ የተዘጉ መንገዶ ከምሽቱ 12:00 ሰዓት ተከፍተዋል።
ዛሬ ከእንዳስላሰ-ሽረ ፣ አክሱም ፣ ዓድዋ ፣ ተምቤንና ሌሎች አከባቢዎች ወደ መቐለ የሚያስገቡ ዋና የመኪና መንገድ በትግራይ ደቡባዊ ምስራቅ ዞን ሃገረ ሰላም ከተማ ነው የተዘጋው።
ከጥዋቱ 1:00 መንገዱ የዘጉ የትግራይ ኃይል አባላት ፦
- " የተሰውት ቤተሰብ አባላት ይደገፉ ! "
- " የቆሰሉት ይታከሙ ! "
- " የሰራዊት ድምፅ ይሰማ ! "
- " የሰራዊር መብት የማያከብር መሪ ይውረድ ! "
- " መሪ ፍረድ ወይ ውረድ ! "
- " የደመወዝ ጥያቄያችን ይመለስ ! "
- " የቤት መስሪያ መሬት ይሰጠን ! "
የሚሉና ሌሎች መፈክሮች አሰምተዋል።
እሁድ ጥቅምት 3/2018 ዓ.ም የጀመረው የትግራይ ኃይል አባላት ሰልፍና ተቃውሞ ያዳመጠው የክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር የሰራዊቱ ጥያቄ ለመመለስ ያስችላል ያለው መመሪያ አውጥቻሎህ ማለቱ ይታወሳል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia

❤613🕊56👏28😭17🤔13🙏11😡9💔6😢5😱4🥰3
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray የትግራይ ኃይል አባላት ሰልፈኞች ዛሬም ለአምስተኛ ቀን የመኪና መንገድ ዘግተው ውለዋል። ትናንት ጥቅምት 6/2018 ዓ.ም ወደ ዓዳግራት ከተማ የሚያስገቡና የሚያስወጡ በሶስት አቅጣጫ የተዘጉ መንገዶ ከምሽቱ 12:00 ሰዓት ተከፍተዋል። ዛሬ ከእንዳስላሰ-ሽረ ፣ አክሱም ፣ ዓድዋ ፣ ተምቤንና ሌሎች አከባቢዎች ወደ መቐለ የሚያስገቡ ዋና የመኪና መንገድ በትግራይ ደቡባዊ ምስራቅ ዞን ሃገረ ሰላም…
#Tigray
የትግራይ ኃይል አባላት ለአምስተኛ ቀን ያካሄዱት የመኪና መንገድ መዝጋት ያካተተ ሰልፍ ተከትሎ የክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር የሰራዊት አባላት ተጠቃሚ የሚያረጋግጥ ደንብ ማጸደቁ አስታውቋል።
እሁድ ጥቅምት 3/2018 ዓ.ም የጀመረው የትግራይ ኃይል ሰልፍና ተቃውሞ ዛሬ ቀጥሎ ከእንዳስላሰ-ሽረ ፣ አክሱም ፣ ዓድዋና ተምቤንና ሌሎች አከባቢዎች ወደ መቐለ የሚያስገባ መንገድ ተዘግቶ ውሏል።
ይህንን ተከትሎ ዛሬ ጥቅምት 7/2018 ዓ.ም ከሰዓት በኃላ የፅሁፍ መግለጫ ያወጣው የጊዚያዊ እስተዳደሩ ፕሬዜዳንት ፅህፈት ቤት ካቢኔ ጥቅምት 5/2018 ዓ.ም ያወጣው የትግራይ የፀጥታ ሃይሎች ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ረቂቅ ደንብ ዛሬ ማፅደቁን አመልክተዋል።
ካቢኔው በዛሬው አስቸኳይ ስብሰባው የትግራይ የፀጥታ ሃይሎች ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ደንብ በዝርዝር ተወያይቶ ተግባራዊ እንዲሆን በሙሉ ድምፅ አፅድቆታል።
የፀደቀው ደንብ ፦
- መሰረታዊ ፍላጎቶች
- የህክምና አገልግሎት
- የቤት መስሪያ መሬት
- በመንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት የሚሰጥ የክብር አገልግሎት
- ትምህርት ስልጠናና ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞች ያካተተ ነው ብሏል ከፕሬዜዳንት ፅህፈት ቤት የተሰጠው የፅሁፍ መግለጫ።
" የፀደቀው የትግራይ ፀጥታ ኃይሎች ተጠቃሚነት ደንብ ለረጅም ጊዜ ጥናት የተደረገበት ከፀጥታ አመራሮች ውይይት ሲካሄድበት የቆየ ነው " ሲል ገልጿል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

❤1.65K👏194🕊102😡80🤔41😭40🙏32💔17🥰16😱15😢15
" ወጣቶቹ ያለ ፍርድቤት ትዕዛዝ ታስረዋል፤ ቤተሰብ እንዳይጠይቃቸውም ተደርጓል " - ቤተሰቦችና ነዋሪዎች
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጌዴኦ ዞን ኮቾሬ ወረዳ ፍሰሃ ገነት ተብሎ የሚጠራዉ አከባቢ ነዋሪዎች እና " ልጆቻችን ያለ አግባብ ታስረዋል " የሚሉት ወላጆች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታቸውን አሰምተዋል።
በአከባቢዉ ማህበረሰብ በተደጋጋሚ ሲጠየቅ የቆየዉን የፍሰሃ ገነት የወረዳ መዋቅርነት ጥያቄ " በማህበራዊ ሚዲያዎች አሰራጭታችኋል " በሚል ወጣቶችን እያሰሱ እያሰሩ ነው ሲሉ ነው ቃላቸውን የሰጡት።
" ስድስት ወጣቶች ያለ ፍ/ቤት ትዕዛዝ ታስረዋል " የሚሉት ነዋሪዎቹ የፍሰሃ ገነት ወረዳ በቀደመዉ ጊዜ የወረዳ መዋቅር የነበረዉ መሆኑንና የመዋቅር ጥያቄዉ የሕብረተሰቡ በመሆኑ እነዚህም ወጣቶች ይህንኑ ሃሳባቸዉን በማህበራዊ ሚዲያ በማሰራጨታቸው ብቻ ከስራና የትምህርት ገበታቸው እየታሰሱ መታሰራቸውንና ቤተሰብ እንዳይጠይቃቸዉ መደረጉን ገልጸዋል።
" ፖሊስ ልጆቻችንን እንዳናገኝ ከማድረጉም በላይ ' በተባባሪነት አስራችኋለዉ ' እያለ እያስፈራራን ነዉ " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የተናገሩት የአከባቢው ወጣቶች " እኛም እየተፈለግን በመሆኑ አከባቢያችንን ለቀን ሸሽተናል " ሲሉ ተናግረዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከጌዴኦ ዞንና የኮቾሬ ወረዳ ፖሊስ በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ያደረገው የዞኑ ፖሊስ አዛዥ ፈቃደኛ ባለመሆናቸዉ የኮቾሬ ወረዳ አዛዥ ደግሞ ስልካቸዉ ባለመስራቱ ለጊዜው አልተሳካም።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

2❤610😡82😭49🕊18🥰10🙏9🤔6👏5😢4
" የኑሮ ሁኔታ በጣም ከባድ ነው የሚከፈለን ብር 760 ነው፡፡ ... እኛ ሴቶች እንጨት ለቅመን ነው የምንማረው ወንዶችም እንጨት እየለቀሙ እየጋገሩ ይማራሉ " - የመምህራን ማሰልጠኛ ተማሪዎች
ከ40 አመት በላይ መምህራንን በማሰልጠን የሚታወቀዉ የደሴ መምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጅ በመምህርነት በዲግሪና ዲፕሎማ የሚሰለጥኑ ተማሪዎች በወር ለምግብ የሚሰጣቸዉ 760 ብር ለመኖር ስላላስቻላቸዉ ሰዉ ቤት ተቀጥረዉ በቤት ሰራተኝነት ከጫካ ጭራሮ እየለቀሙ የራሳቸውን ምግብ ለማብሰል መገደዳቸውን ገልጸዋል።
ከእነዚህ ተማሪዎች አንዱ በእንጨት ለቀማ ወቅት ሕይወቱ እንዳለፈም ሰልጣኞቹ ተናግረዋል።
በወር የሚከፈላቸው 760 ብር ነው ፤ አንድ እንጀራ ለመግዛት የዋጋውን ውድነት አልቻሉትም ከዚህ ኑሮ ውድነት በመነሳት ወንዶች ኩሽና ተፈቅዶላቸው እንጀራ እየጋገሩ እየኖሩ ናቸው።
ነገ ተማሪዎችን ለማስተማር የሚሰለጥኑ መምህራን የሚማሩትን ሳይሆን የሚበሉትን በማሰብ የማገዶ እንጨት በመልቀም፣ የቀን የጉልበት ሠራተኛ በመሆን፣ እንዲሁም ሊጥ አብኩተው ለምግባቸው የሚሆን እንጀራ በመጋገር ጊዜያቸውን ያሳልፋሉ ነው የተባለው።
ሰልጣኝ መምህራኑ ለዶቼ ቨለ ሬድዮ ምን አሉ ?
በ760 ብር የምግብ ወርሃዊ ክፍያ የመኖሪያ ቤት ተሰጥቷቸው በኮሌጅ የሚማሩ ተማሪዎች ከትምህርት በኋላ የሚመገቡትን ምግብ ለማብሰል በደሴ ወደሚገኙት የጦሳ፣ አዘዋና ሌሎች እንጨት ለመልቀም ወደሚያስችላቸው ጫካዎች ሲያመሩ ከሞት ጋርም ተጋፍጠዋል፡፡
ለመማር በጣም አስቸጋሪ ስለሆነ በጦሳ ተራራ እንደዚሁም በአዘዋ ተራራ ካለቀምን በስተቀር እንጨት አይገኝም ብለዋል።
በዚህም አንድ ሳሙኤል የተባለ የእንግሊዝኛ ክፍል የዲግሪ ተማሪ በጦሳ ተራራ እንጨት ሊለቅም ሄዶ ህዳር 28 ቀን ህይወቱ አልፏል፡፡
ችግሩ በተለይ ሴቶች ላይ የጎላ ነው የምትለው ሠልጣኝ ተማሪ የግማሽ ቀን የቤት ሰራተኝነትና በሌሎች ስራዎች እራሳችን እየደጎምን ነው ትምህርት የምንማረው ብላለች፡፡
" የኑሮ ሁኔታ በጣም ከባድ ነው የሚከፈለን ብር 760 ነው፡፡ ባለን አቅም እየሰራንም ነው የምንማረው በትምህርታችን ላይ ውጭ ውለን ስንገባ እየደከመን ማጥናት እንቸገራለን እንጨት ለቅመን ነው የምንማረው ወንዶችም እንጨት እየለቀሙ እየጋገሩ ይማራሉ " ስትል ተናግራለች።
" አሁን አሁንማ ሥራም ጠፍቷል ፤
አሁን የቀን ስራ ሰርተን ለመማር የማንችልበት ጊዜ ላይ እንገኛለን " የሚለው ተማሪ " ወቅታዊ ሁኔታው ተጨማሪ ስራ ሰርተን ለመማር አላስቻለንም " ብሏል።
" ሴቶች የግማሽ ቀን ስራ ካገኙ ይሰራሉ ወንዶች ቅዳሜና እሁድ ይሰራሉ። ዘንድሮ ግን የለም፤ መስራት አትችልም የተግባር ልምምድ ስለምንሄድ ትንሽ ከበድ ይላል። ባለፈው አመት ይሻላል ውጭ ላይም ትንሽ አስፈሪ ነው ሰዓቱ " ሲል ገልጿል።
በትምህርቱ ላይ ተፅዕኖ እየፈጠረ ነው መባሉን
የደሴ መምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጅ መምህር የሆኑት መምህር አበበ ደሴ እንደሚገልፁት ተማሪዎች የዕለት ኑሯቸውን በማሰብ ስለሚጠመዱ ትምህርት የመቀበል አቅማቸው ውስን ሆኗል ብለዋል፡፡
" ግማሾች የቀን ስራ ሰርተው ነው የሚኖሩት። ሴቶችም ቢሆኑ በእንጀራ ጋጋሪና ካፍቴሪያ ውስጥ ተቀጥረው እየሰሩ ነው። ክፍል ውስጥም ገብተው ስታይ በአብዛኛዉ ከሚማሩበት የሚያንቀላፉበት ነው የሚበልጠው። ወጥተው የሚመገቡት የለም " ሲሉ አስረድተዋል።
የደሴ መምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ሀሰን ወርቁ በበኩላቸው ተማሪዎቹ ያሉበት ችግር ለመማር ማስተማር ሂደቱ ላይ እንቅፋት ፈጥሯል ብለዋል።
ወርሃዊ የምግብ ክፍያቸውም ከ760 ብር ከፍ እንዲል ለክልሉ ትምህርት ቢሮ/ጥያቄ መቅረቡን አመልክተዋል።
" በአብዛኛው ከመማር ማስተማሩ ይልቅ ስለ እሚበሉት ፣የሚጠጡት ነው የሚያስቡት በትምህርት ላይ ተፅዕኖ አለው። ይህንን ታሳቢ አድርገን ክልል ላይም ጥያቄ እያቀረብን ነው፡፡ " ብለዋል።
Credit - ዶቼ ቨለ ሬድዮ

❤1.69K😢885😭242💔228😡52🤔40🕊34🙏32👏19😱17🥰14
ሚዛን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት !
የ1⃣ 0⃣ ኛ ዙር የቴክኖሎጂና የቋንቋ ኮርሶች ምዝገባችንን በማጠናቀቅ ላይ እንገኛለን።
የመክፈል አቅም ለሌላቸው በክሬዲት (ከወለድ ነፃ በሆነ ብድር/ዱቤ) መማር የሚችሉበት እድል ከማመቻቸት ባሻገር፤
✔️ ተመርቀው ሥራ ላጡ ሁሉ 25% ቅናሽ (መስፈርት: ከቀበሌ ደብዳቤ ማፃፍ)፣
✔️ ለዩኒቨርስቲና ኮሌጅ ተማሪዎች 12% ቅናሽ (መስፈርት: የታደሰ የትምህርት ቤት መታወቂያ ማሳየት)፣
✔️ ለመምህራንና ለጤና ባለሙያዎች 12% ቅናሽ (መስፈርት: ሙያዊ ማስረጃንና ተመጣጣኝ ህጋዊ ማስረጃ ማሳየት)፣
✔️ 12ኛ ክፍል ማለፊያ ውጤት ላላመጡ 20% ቅናሽ (መስፈርት: ስም እና አድሚሽን ቁጥር ማሳየት)፣
እነዚህን እድሎች አመቻችተናል።
ለመመዝገብ፦ http://www.mizantechinstitute.com
📱 በቴሌግራም @MizanInstituteOfTechnologyEthio አግኙን።
🗺 በአካል: ቤተል አፕል ፕላዛ 7ኛ ፎቅ፣ 0987143030
በማህበራዊ ሚዲያ ገፆቻችን አገኙን፦
🌐 👍🌐📱 ✅▶️🌐📧 🗺
የ
የመክፈል አቅም ለሌላቸው በክሬዲት (ከወለድ ነፃ በሆነ ብድር/ዱቤ) መማር የሚችሉበት እድል ከማመቻቸት ባሻገር፤
እነዚህን እድሎች አመቻችተናል።
ለመመዝገብ፦ http://www.mizantechinstitute.com
በማህበራዊ ሚዲያ ገፆቻችን አገኙን፦
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤281😱5🕊5😭4🥰3
TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE " ውጤት በቅርቡ ይፋ ይደረጋል " - ትምህርት ሚኒስቴር በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሲሰጥ የነበረው የ2018 የድህረ ምረቃ ትምህርት መግቢያ ፈተና መጠናቀቁን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል። ፈተናው ለመውሰድ ከተመዘገቡ 29 ሺ491 አመልካቾች መካከል 96 በመቶ ፈተናውን እንደወሰዱ አመልክቷል። በ2017 ዓ.ም. መጨረሻ ላይ ይሰጥ የነበረው የድህረ ምረቃ መግቢያ ፈተና በተለያዩ ምክንያቶች ተራዝሞ…
#NGAT
የድኅረ ምረቃ ፕሮግራም የመግቢያ ፈተና (NGAT) ውጤት ተለቋል።
የ2018 ዓ.ም የመጀመሪያ ዙር የድኅረ ምረቃ ፕሮግራም የመግቢያ ፈተና (NGAT) ውጤት ዛሬ ከሰዓት መለቀቁን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከትምህርት ሚኒስቴር አረጋግጧል።
ውጤት ለማየት 👇
https://result.ethernet.edu.et/
ከ28 ሺህ በላይ ተፈታኞች ጥቅምት 03/2018 ዓ.ም በ53 የፈተና ማዕከላት የተሰጠውን ፈተና መውሰዳቸው ይታወሳል።
ሁለተኛው ዙር የ NGAT መግቢያ ፈተና በጥር 2018 ዓ.ም ይሰጣል።
Via @tikvahuniversity

❤201😢13🙏12😭5🥰2😱2
" ተገቢዉን ፍትሕ አለማግኘቷ ያንገበግበኛል " - ወላጅ አባት
አርሶ አደር ዳንሳሞ አሌ በሲዳማ ክልል ምስራቃዊ ሲዳማ ዞን ዳኤ'ላ ወረዳ ቃዳዶ ቀበሌ ዳዱርቾ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ነዋሪ ናቸው።
ከዛሬ ሶስት ዓመታት በፊት ደጌ ዳንሳሞ አሌ የተበለች የ15 አመቷ ታዳጊ ልጃቸውን 'አበበ ክፍሌ' የተባለ ወጣት ግብራበሮቹን በማሰባሰብ ለቅሶ ቤት ተልካ ከምትመለስበት አፍነው ወደ ጫካ በመውሰድ ጭካኔ በተሞላበት መልኩ ጓደኞቹ አፍነዉ ይዘዋት በግድ ይደፍራታል።
ታዳጊዋ ደጌ በደም ተለውሳ፣ ትንፋሽ አጥሯት ከወደቀችበት አንስተው ቦታ በመቀየር ይህን እንስሳዊ ድርጊት ሲፈፅሙባት የተመለከች አንዲት ሴት ጩኸት ታሰማለች፤ እነሱም ተሸክመዋት ለማምለጥ ይሞክራሉ።
አባቷን ጨምሮ ከለቅሶ ቤት ሲመለሱ የነበሩ የአከባቢዉ ነዋሪዎች ጩኸቱን ወደ ሰሙበት ለእርዳታ ሲሯሯጡ በመጨረሻም ክፍሌና ጓደኞቹ ደጉን ጥለዋት ይሸሻሉ።
ሰው ለማገዝ ከሌሎች ሰዎች ጋር አብሮ ሮጦ የደረሰዉ አባቷ አቶ ዳንሳሞ አሌ የሚያየውን ማመን ያቅተዋል፤ የገዛ ልጁ በደም ተለውሳ በእርቃኗ ተዝለፍልፋ ወድቃ ሲያያት የሚይዘዉ የሚጨብጠውን ያጣል።
ከዚህ በኃላ ምን ተፈጠረ ?
አርሶ አደር ዳንሳሞ አሌ ስለሁኔታው ለቲክቪህ ኢትዮጵያ እስረድተዋል።
" ሰው ለመርዳት በሮጥኩበት ልጄ ተደፍራ በወደቀችበት ነበር የደረስኩት እርቃኗን ሆና ሳይ እራሴን መቆጣጠር አቃተኝ፣ የምይዘዉ የምጨብጠዉን አጣሁ፤ የለበስኩትን ጃኬት ነበር አውልቄ ሸፈንኳት፤ ጮሆኩ ሰዎች ሊያረጋጉኝ ሞከሩ፤ በጣም አሳዛኝ ልብ ሰባሪ ድርጊት ነበር " ብለዋል።
" አበበ ክፍሌና ጓደኞቹ ከአከባቢው ተሰወሩ ደጉ በዛኑ ምሽት ብዙ ደም ፈሷት ስለነበር ወደ ዳኤላ ሆስፒታል ተወሰደች ከዚያም ለተሻለ ሕክምና ወደ ሐዋሳ እንድትጓዝ ተደረገ " ሲሉ ገልጸዋል።
ደጌ ከአካላዊ መደፈር በዘለለ ከፍተኛ ስነልቦናዊ ጉዳት ስለደረሰባት እዚያዉ ሀዋሳ በአንድ ድርጅት ውስጥ እንድትቆይ ተደረገች።
ፖሊስ ዋናው ተጠርጣሪ ግለሰብ አበበ ክፍሌና ቀንደኛ ተባባሪ ጓደኛዉ ኢያሱ ግዴሳ ማምለጣቸዉንና ሶስቱን ግብራበሮች ግን መያዙን ገልፆ ክስ መሰረተባቸዉ።
ፍርድ ቤቱ በነዚህ ሶስት ግብራበሮቹ ላይ የ6 አመት ፅኑ እስር ፈርዶባቸው የነበር ቢሆንም ከ2 አመት እስር በኋላ በአመክርዎ ይለቀቃሉ።
ዋናው ወንጀለኛ እና በታዳጊዋ ላይ ጥቃት ያደረሰው " አበበ ክፍሌ" የተባለው ሰው ግን እስከ ዛሬ ድረስ አልተያዘም ለፍርድም አልቀረበምም።
የደጉ አባት ይህን ጉዳይ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሲያስረዱ " ከተፈፀመባት ነውረኛ ተግባር በላይ ተገቢዉን ፍትሕ አለማግኘቷ ያንገበግበኛል " ሲሉ ነው የገለፁት።
በዚህ መሃል አርሶ አደር ዳንሳሞ ሌላ አሳዛኝ ጉዳይ አጋጠመኝ ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል። ይህም የአከባቢው ሽማግሌዎች " ነገሩን በሽምግልና ካልፈታን " ማለት መጀመራቸው ነው።
" ፖሊስ ' ማግኘት አልቻልኩም ተሰውሮብኛል ' ያለውን ግለሰብ ሽማግሌዎቹ ከየት አመጡት " በማለት ሽምግልናውን እምቢ ማለታቸውን ገልጸዋል።
ሽማግሌዎችም " እንዴት አምቢ ትላለህ ? ሌላስ ልጅህ ላይ መሰል ነገር ቢደርስ ሽማግሌ አይደል የሚፈታው ? " እያሉ ያስጨንቋቸው እንደጀመረ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ደጌ አሁንም ፍትሕ እንደተጠማች ሀዋሳ እንደርሷ ጥቃት የደረሳቸውን ታዳጊዎች ሰብስቦ በሚያኖር ድርጅት ውስጥ ናት።
" የደጌ ታናሽ ግን ገና 12 አመቷ ነው ሽማግሌዎችን እምቢ አልክ ብለው በሷ እንዳይበቀሉኝ እፈራለሁ " ሲሉ አባት ተናግረዋል።
" ስለ ጉዳዩ ከወረዳው እስከ ክልሉ ባለድርሻ አካላት መስሪያ ቤት ደጅ ብጠናም ' የተዘጋ ፋይል ነው ፤ የነሱ ፋይል ጠፍቶብናል ስናገኝ እናሳውቃለን ' በማለት ብዙ አንገላቱኝ " ሲሉ ስለ ፍትህ ድምጻቸውን አሰምተዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በጉዳዩ ዙሪያ የዳ'ኤላ ወረዳ እና ምስራቃዊ ሲዳማ ዞን ፖሊስና ፍትሕ (ዐቃቤ ሕግ) አካለትን ለማነጋገር ቢሞክርም " በአካል ካልተገኛችሁ መረጃ መስጠት አንችልም " በማለታቸው በዚህ መረጃ ምላሻቸዉን ማካተት አልተቻለም ፤ መረጃዉ እንደደረሰን የምናቀርብ ይሆናል።

😭2.24K❤1.01K😡267💔136😢37🙏32🤔20🥰10😱9🕊9👏3