Telegram Web Link
‎" ከ6 ዓመታት በፊት የተጀመረዉ መንገድ አለመጠናቀቁ ለዘርፈ ብዙ ችግሮች ዳርጎናል " - የሸካ ዞን ነዋሪዎች

‎በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ ዞን ነዋሪዎች ፥ የሸካ ዞንን ከተለያዩ ከተሞች የሚያገናኘው መንገድ ተጀምሮ ለረጅም ዘመናት አለመጠናቀቅ ለዘርፈ ብዙ ችግሮች እየዳረገን ነዉ ሲሉ ቅሬታቸዉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሰምተዋል።

‎ስማቸዉ እንዲገለፅ ያልፈለጉ ሁለት የሸካ ዞን ቴፒ ከተማ  ነዋሪዎች " ዞኑን ከጎሬ ቴፒ ማሻ፣ ከጪዳ ታርጫ፣ ዋቻ ጀሙ፣ ሚዛን ቴፒ  የሚያገናኘው መንገድ ከ6 እና 7 ዓመታት በፊት የተጀመረ ቢሆንም እስካሁን አልተጠናቀቀም " ብለዋል።

" በዚህም ምክንያት በንግድ እንቅስቃሴ፣ በሕዝብ ትራንስፖርትና በከተማዋ ሁለንተናዊ ዕድገት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ አሳርፏል " ሲሉ ተናግረዋል።

‎የአከባቢዉ ነዋሪዎች በተለይም የዞኑ አርሶአደሮች ዞኑ ካሽ ክሮፕ ከመሆኑም በላይ የቡና፣ የሻይ ቅጠል፣ የኮረሪማ፣ ዝንጅብል፣ እርድና ሌሎችም የግብርና ምርቶችን ለገበያ ለማቅረብ መቸገራቸዉን ገልፀዋል።

‎ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሀሳባቸውን ያጋሩ ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ አንድ የቴፒ ከተማ አመራር የሸካ ዞን የመንገድ ጉዳይ ከዞኑ መንግስት አቅም በላይ ነዉ ያሉ ሲሆን ከሕዝቡ ጩኸት በዘለለ አመራሩ በተደጋጋሚ በተለያዩ መድረኮች የሚያነሳው ቢሆንም የዞኑ መንግስት የማስፈፀም አቅም ስለሌለው ለዘመናት እልባት ሊያስገኝ አልቻለም ብለዋል።

ሌላ ስማቸዉ እንዲገለፅ ያልፈለጉ የሸካ ዞን የቀድሞ አመራር " ከመንገድ ችግሮች ጋር በተያያዘ ጥያቄዎች ሲበረቱ ማዘናጊያ እንቅስቃሴዎች የማድረግና ' ከኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ጋር እየተነጋገርን ነዉ ' የሚሉ ዜናዎችን በዞንና ወረዳ የሕዝብ ግንኙነት ገፆች ማሰራጨት ልማድ በዞኑ ተደጋግሞ ይስተዋላል " ሲሉ ገልጸዋል።

ሰሞኑንም ይኸው ድርጊት እየተስተዋለ መሆኑን አንስተዉ ይህ ተደጋጋሚ ድርጊት አሁን ላይ ሕዝቡን አስመርሯል ሲሉ ተናግረዋል።

" ‎አሁን ላይ ለሸካ ዞን የመንገድ መሰረተ ልማት ጉዳይ የህልውና ጉዳይ ነዉ " የሚሉት ቅሬታ አቅራቢዎቹ " በየትኛውም መመዘኛ የሕዝብ የመሠረተ ልማት ጥያቄ በአግባቡ ሊመለስ እንጂ ሌላ ትርጉም ሊሰጠው አይገባም " ብለዋል።

በማህበራዊ ሚዲያዎች የአከባቢውን የመንገድ ችግር ጥያቄ ያስተጋቡ ግለሰቦችን የማስፈራራት ሁኔታዎች በመንግስት አመራሮች ሲፈጸሙ እንደሚስተዋልም ጠቁመዋል።

‎ቲክቫህ ኢትዮጵያ በጉዳዩ ዙሪያ የሸካ ዞን መንገድ ልማትና ትራንስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሀብታሙ ሀራን ለማነጋገር ያደረገዉ ሙከራ በተደጋጋሚ ቀጠሮ ምክንያት ሳይሳካ ቀርቷል። ሀሳባቸውን ማግኘት ስንችል የምናካትት ይሆናል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
1868😡100😭71🙏69💔34🕊29👏17😢13🤔11
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#SamiTech

አዳዲስ ላፕቶፕች ከአንድ ዓመት ዋስትና ጋር!!
@samcomptech

በጥራት፣ በብራንድና በባትሪ ቆይታ አስተማማኝ የሆኑ የተለያዩ ሞዴል ላፕቶፖች በፈለጉት ስክሪን መጠን፣ ኮር አይ እና ጀነሬሽን አሉን።

ለቢሮዎች፣ ለተማሪዎች፣ ለዲዛይን ባለሙያዎች፣ ለጌመሮች ወ.ዘ.ተ. ሁሉም አሉን።

የዕቃዎች ዋጋ፣ ዓይነት እና አድራሻ ለማግኘት 👉 @samcomptech

@sww2844
0928442662 / 0940141114

Telgram : https://www.tg-me.com/samcomptech
175🙏9😢2😭1
ለተስካር ሊውል የነበረውን 3.2 ሚሊዮን ብር ለተፈናቃይና ለተቸገሩ ወገኖች የለገሱት ቤተሰቦች !

ተወልደ ግደይ ገብረዋህድ ቤተሰቦቻቸው በትግራይ ሰሜን ምዕራብ ዞን የእንዳስላሰ-ሽረ ከተማ ነዋሪ ናቸው።

ቤተሰቦቹ ለነፍስሄር ወላጅ እናታቸውና ወንድማቸው ለተስካር ሊውል የተዘጋጀው 3.2 ሚሊዮን ብር በከተማዋ በከፋ ሁኔታ ኑሮዋቸው በመግፋት ላይ ለሚገኙት ተፈናቃዮችና የተቸገሩ ወገኖች ለግሰዋል።

ጥቅምት 10/2018 ዓ.ም በተከናወነው የልገሳ ስነ-ስርዓት ፦ 2 ሚሊዮን ብር በከተማዋ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ሲከፋፈል ፤ የተቀረው በስራ ለተሰማሩት የተሰው ቤተሰቦች ማጠናከሪያ ለአረጋውያን ማህበር፣ ለህፃናት ማሳደጊያ ማእከልና ለ6 ገዳማትና አብያተ ቤተክርስትያን መርጃ ተከፋፍሏል።

" ለጋሽ ቤተሰቦች ገንዘቡ ለተስካር ከማባከን በችግር ለተጎዱ ወገኖች ማዋል ምድራዊና ሰማያዊ ሀሴት ያስገኛል " በማለት መፈፀማቸውንና ሌሎችም የነሱ ዳና መከተል እንደሚገባቸው ገልፀዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia      
1👏1.84K682🙏134🤔42🥰21🕊16😡6😱5😢4
#Cameroon

የ92 ዓመቱ ፖል ቢያ የካሜሩንን ምርጫ ለስምንተኛ ጊዜ ማሸነፋቸው ተነገረ።

የ43 ዓመት የስልጣን ዘመን ቆይታቸው ተራዝሟል።

ፖል ቢያ በቅርብ በሀገራቸው የተደረገውን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ 53.66% ድምጽ በማግኘት እንዳሸነፉ ለሀገሪቱ ለሕገ-መንግሥት ጉዳዮች ም/ቤት የቀረበው ይፋዊ ውጤት አሳይቷል።

የቅርብ ተቀናቃኛቸው ኢሳ ቲቺሮማ ባካሪ በ18 በመቶ ነጥብ ርቀው 35% ድምጽ አግኝተዋል ተብሏል።

ስምንተኛ የሥልጣን ዘመናቸው የ43 ዓመት ፕሬዝዳንትነታቸውን ያራዘመ እንደሆነ ስፑትኒክ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
🤔674254😭193😡83😱44😢17🙏13🕊12👏10💔8🥰3
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስ ዓቢይ ጉባኤ በዛሬው ዕለት በጸሎት መከፈቱን ቤተክርስቲያኗ አሳውቃናለች።

@tikvahethiopia
🙏1.59K623🥰70🕊51😡31🤔15😭11😢10😱3
2025/10/27 03:14:21
Back to Top
HTML Embed Code: