Telegram Web Link
" በየቀኑ ለጥበቃ 500 ብር እንከፍላለን፣ ከቆምን 17ኛ ቀናችን ነው " - ሹፌሮች

➡️ " የሚመለከታቸው አካላት መጥተው ጥራቱን አይተው አረጋግጠው ይሁኝታን ሲሰጡን ብቻ ነው መኪኖቹ እንዲያራግፉ የሚደረገው፣ እኛ ባቅማችን የምንፈታው ችግር የለም " - ወንደራ ዩኔየን (Union )

ከጅቡቲ ወደ ደብረ ብርሃን ከተማ ወደሚገኘው ወደራ ዩኔየን (Union) የአፈር ማዳበሪያ ጭነው የመጡ አሽከርካሪዎች " ማዳበሪያው የተበላሸ ስለሆነ ማውረድ አትችሉም " ተብለው በደብረ ብርሃን ከተማ 17 ቀን እንዲቆሙ በመደረጋቸው ችግር ላይ መውደቀቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታ አቅርበዋል።

አሽከርካሪዎቹ " ከክልሉ መጥተው ማዳበሪያውን ያዩት ባለሙያዎች የተላከላቸው ፎቶ እና የመጣው ማዳበሪያ እንደሚለያይ ነግረውናል፣ ሲያዩትም ተደናግጠው ነበር። ያልምንም መፍትሔ እንድንቆም በመደረጋችን እየተቸገርን ነው፣ በቃል ደረጃ ወደ አዲስ አበባ ጭነቱን ይዛችሁ ትመለሳላችሁ ብለውናል። ይሁን እንጂ በዚህ ቀን ትመለሳላችሁም አላሉንም፣ እኛ ከፍተኛ ችግር ላይ ነው ያለነው መፍትሔ ይሰጠን " ብለዋል።

ሹፌሮች በዝርዝር ምን አሉ ?

" በማህበር ደረጃ ነው ከጅቡቲ ጭነን የመጣነው፣ የተመደብነውም ከጅቡቲ ወደራ ዩኔየን ደብረብርሃን እንድናደርስ ነው።

ማዳበሪውን ወደ ኢትዮጵያ ጭነን ስንመጣ ችግር አለበት እያሉ ነበር መጀመሪያም። እኛ የምናወቀው ነገር የለም፣ ስለጥራትም የሚመለከተን ጉዳይ አይደለም፣ የታዘዝነውን መጫን እና ወደተባልነው ቦታ ማድረስ ነው። እሱንም አድርገናል።

ደብረብርሃን ከተማ ስንደርስ ግን ' ማዳበሪያው ችግር አለበት አንቀበልም ' አሉን፣ እኛም ለማህበራችን አሳውቀናል፣ እነሱም ' ለበላይ አካል አሳውቀናል ' ብለውናል፣ ሁሌም ' እየተነጋገርን ነው ' ይሉናል። ነገር ግን ከቆምን 17 ቀን ሆኖናል።

እኛ ገንዘብ የምናገኘው መኪኖችን ስናንቀሳቅስ ነው፣ ጎማ ካልተንቀሳቀሰ ምንም አናገኝም። እኛ ሹፌሮች ደግሞ ቤተሰብ አስተዳዳሪዎች ነን።

በጣም ችግር ላይ ነው ያለነው፣ እኛን የሚጠይቀን የለም፣ ከክልል የመጡ የግብርና ባለሙያዎች ናቸው ተብለው አይተውልን ነበር ማዳበሪያውን፣ ግን ' እኛ ይህን አንረከብም ይዛችሁ ሒዱልን ' ነው ያሉን፣ ደውለን ስንጠይቃቸው ደግሞ እየተነጋገርንበት ነው ይላሉ፣ በመሐል እየተጎዳን ያለነው እኛ 35 ሹፌሮች እና 35 ረዳቶች ነን።

ከክልሉ ግብርና ቢሮ የመጡት ባለሙያዎች  5 የሚሆኑ መኪኖች የጫኑትን ማዳበሪያ ፈተው አይተው አነጋግረውናል። በስአቱ ' እኛ ይህንን አንቀበልም ውሰዱ 'ሲሉን ወደት እንውሰደው ስንል ' አይመለከተንም ' ነው ያሉን። ' አንቀበልም ' የምትሉበትን ደብዳቤ ስጡን እና ለማህበሮቻችን እናስገባ ስንል አንሰጥም ብለውናል ነው ያሉት።

' ከመጋዘኑ ጊቢ ውጡ፣ የማትወጡ ከሆነ ደግሞ በፖሊስ እናሶጣቹሀለን ' ብለውናል። ይህን ያሉት የከተማ አስተዳደሩ እና የወደራ ዩኔን ሃላፊዎች ናቸው።

የዩኔኑ ጊቢ ሁሉንም መኪና ማቆም ስለማይችል ጊቢው ውስጥ 9 መኪና መጀመሪያ ገብቶ ነበር፣ ከዛም 3ቱን አስወጥተው 6 ብቻ ቀርተዋል፣ አሁን ደግሞ ሁሉንም ውጡ እያሉ ነው። ሌላው መንገድ ዳር ነው የቆሙት። የመኪና ማቆሚያ እና መጠበቂያ በየቀኑ እየከፈልን ነው።

መኪኖችን የሚጠብቁት ልጆች ራሱ አናውቃቸውም፣ በማህበር እንደተደራጁ ነው የነገሩን። ተስፋ የሚሰጠን አካል እንኳ የለም።

ሌሎች አሽከርካሪዎች ደግሞ እኛ ከመጣን 17ኛ ቀናችን ነው፣ ከእኛ ቀድመው የገቡ መኪኖች አራግፈው ነበር፣ ነገር ግን መልሳችሁ ጫኑ ተብለው ጭነዋል። የጫኝ የከፈሉት ደግሞ ሹፌሮቹ ናቸው።

ማዳበሪያው እንደተበላሸ ወደብ ላይ ስንጭን እየተናገርን ነበር፣ አሁን ደግሞ ቁሙ ከማለት ውጭ ስለሁኔታውም የሚያስረዳን አካል የለም። እኛ ስንቀሳቀስ ነው ብር የምናገኘው፣ ልጆች እናስተምራለን፣ ቤተሰብ እናስተዳድራለን፣ መኪኖቹ የባንክ እዳ አለባቸው፣ ብዙ መስራት የሚችል ንብረት ያለ ስራ ቁሟል፣ የቆምንበት ቦታም አስቸጋሪ ነው።

17 ቀን ያለምንም ስራ ስንቆም ያለንን ገንዘብ ጨርሰናል። ኪሳችን ባዶ ሆኗል። አሁን ላይ እንኳን ቤተሰብ ልንረዳ እኛም እየተቸገርን ነው።

መንገድ ላይ መኪኖችን ስላቆምን የቀን ለእያንዳንዱ መኪና 200 ብር፣ ለአዳር ደግሞ 300 ብር እየከፈልን ነው ለጥበቃዎች። አጠቃላይ በየቀኑ ሁሉም አሽከርካሪ 500 ብር ይከፍላል " ብለዋል።

ስለጉዳዩ የጠየቅናቸው አንድ የወንደራ ዩኔን የስራ ሃላፊ " ይህን ግብአት መጀመሪያ ከጅቡቲ ሲገዛ የነበሩ የሚመለከታቸው አካላት መጥተው ጥራቱን አይተው አረጋግጠው ይሁኝታን ሲሰጡን ብቻ ነው መኪኖቹ እንዲያራግፉ የሚደረገው። ይመለሳል ካሉም እንዲመለስ የምናደርገው በዚህ መልኩ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

አክለው " እኛ ባቅማችን የምንፈታው ችግር የለም፣ ያመጡት ማዳበሪያ እስካሁን ከሚመጡት የተለየ ነው። ወደ ዱቄትነት የተቀየረ ነው፣ ይህንን ማዳበሪያ ለአርሶአደሩ ማከፋፈል ደግሞ ሌላ ችግር መፍጠር ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

" ጥራቱን ማረጋገጥ አንችልም፣ ከጥራት ደረጃው በታች ነው ማለትም አንችልም፣ ይህንን ማረጋገጥ የሚችሉት የፌደራል እና የክልሉ ግብርና ቢሮ ናቸው ሲሉ አጭር ምላሽ ሰጥተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamily

@tikvahethiopia
694😡84😭31🙏17😢15🕊12😱6🤔5🥰2👏1
#NBE

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከግል እና የሶስተኛ ወገን የባንክ ሒሳብ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ ጥብቅ መመሪያ አስተላለፈ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አደረኩት ባለው ምርመራ " ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ የባንክ ደንበኞች በዋናነት የንግድ ድርጅቶችና ግለሰብ ነጋዴዎች ለንግድ ሥራቸው ተብሎ ከተከፈተው እና በሚመለከተው የግብር ሰብሳቢ ተቋም ካስመዘገቡት የባንክ ሒሳቦች ውጭ የግል የባንክ ሂሳባቸው ወይም የሶስተኛ ወገን የባንክ ሒሳብ ተጠቅመው የተለያዩ የንግድ ግብይቶች እና የገንዘብ እንቅስቃሴዎች እየፈጸሙ መሆናቸውን አረጋግጫለሁ " ብሏል።

" ይህ አሰራር ከግብር ሰብሳቢ ባለስልጣናት ቁጥጥርና ክትትል ለመሸሽ የሚደረግ ተግባር ከመሆኑ በተጨማሪ በዚህ አግባብ የሚፈጸሙ የፋይናንስ ግብይቶች እና የገንዘብ እንቅስቃሴዎች የወንጀል ፍሬ ወይም ሽብርተኝነትን በገንዘብ ከመርዳት ጋር የተያያዙ ወይም የተገናኙ ሊሆኑ ይችላሉ " ሲል ገልጿል።

" እነዚህን መሰል ተግባራትንም ለመግታት አስፈላጊው የተቀናጀ እርምጃ እንዲወሰድ ተወስኗል " ሲል አሳውቋል።

የፋይናንስ ሥርዓቱን ጤናማነትና ታማኝነት እንዲሁም በአጠቃላይ የኢኮኖሚ ደህንነት ለመጠበቅ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለሁሉም ባንኮች የግል ባንክ ሂሳቦችን ለንግድ እና ለሕገ-ወጥ ድርጊት የሚጠቀሙ ደንበኞችን አስመልክቶ አስፈላጊ መረጃዎችን በማደራጀት እንዲልኩ መመሪያ አስተላልፏል፡፡

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
1930😡576😭56🤔35🙏25👏18🕊16🥰15💔11😱10😢5
TIKVAH-ETHIOPIA
“የ9 ጤና ባለሙያዎች ሕይወት አልፏል። 7ቱ ከአርሲ፣ ሁለቱ ከባሌ ናቸው” - የኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ ➡️ “የተጎዱት ወደ 8 ይደርሳሉ፤ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው አራት ናቸው። በአጠቃላይ 28 ባለሙያዎች ተሳፍረው ነበር” - ዞን ጤና ቢሮ ከኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ተውጣጥተው ለትምህርት ወደ ሐረማያ ዩኒቨርስቲ ሲጓዙ በነበሩ ጤና ባለሙያዎች በመኪና አደጋ ሞትና የአካል ጉዳት መድረሱን የክልሉና የዞኑ…
" አሽከርካሪዎች በተለይ ኦላንጪቲ ከተማን ለጉዞ በሚያቋርጡበት ወቅት ጥንቃቄ አድርጉ " - ዋና ኢንስፔክተር ስለሽ ባይ

ከትላንት በስቲያ ለሊት በምስራቅ ሸዋ ዞን ቦሳት ወረዳ ልዩ ስሙ " ጋር " የተባለ ስፍራ በደረሰው የትራፊክ አደጋ 7 የጤና ባለሙያዎችን ጨምሮ 9 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል።

አደጋው ከአዳማ ወደ መታሃራ ሲጓዝ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ከአይሱዙ መኪና ጋር በመጋጨቱ ነበር የደረሰው።

ከዚሁ አደጋ ጋር በተያያዘ የቦሰት ወረዳ የትራፊክ ደህንነት አስተባባሪ ዋና ኢንስፔክተር ስለሽ ባይ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል የአደጋው መንስኤ አሽከርካሪው ከተገቢው በላይ በፍጥነት ማሽከርከር በተለይም በምሽት መጓዝ ነው።

" መንገዱን በውል ለማያውቁት ከፍተኛ የትራክፊክ ፍሰት ስለሚያስተናግድ ጥንቃቄ ማድረግ ግዴታ ነው " ሲሉ አሳስበዋል።

በአደጋው ከሞቱት 9 ሰዎች መካከል ሰባቱ የህክምና ባለሙያዎች ሲሆኑ በአርሲ ዞን አግልግሎት ላይ የነበሩ እና ለሞያ አቅም ግንባታ እና ለፈተና ወደ ሀሮማያ ዩኒቨርስቲ ስጓዙ የነበሩ እንደሆኑ ይታወሳል።

ሶስት ከባድ የአካል ጉዳት እና አምስት ቀላል የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ስዎች  በአዳማ እና ቦሳት ሆስፒታል በህክምና ላይ ይገኛሉ።

ኢንስፔክተር ስለሽ ባይ አደጋው የደረሰበት አካባቢ የከባድ ተሽከርካሪዎች መተላለፊያ መሆኑን በመጠቆም የህዝብ ማመላለሻ አሽከርካሪዎች በተለይ ኦላንጪቲ ከተማን ለጉዞ በሚያቋርጡበት ወቅት ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ነቀምቴ

@tikvahethiopia
550😢309😭91💔25🙏22🕊17🥰3
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

የስምረት ፓርቲ መስራች ጉባኤ አቶ ጌታቸው ረዳ የፓርቲው ፕሬዝደንት አድርጎ መረጠ።

አቶ ነጋ አሰፋ ደግሞ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት አድርጎ መርጧል።

አቶ ሃፍቱ ኪሮስ ምክትል ፕሬዚዳንት እንዲሁም ሰብለ አሰፋ የፓርቲው ፅህፈት ቤት ኃላፊ ሆነዋል።

ለማእከላዊ ኮሚቴ ከመረጣቸው 31 አባላት ውስጥ ፦

1. አቶ ጌታቸው ረዳ
2. ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ሂወት
3. ወ/ሮ ኣልማዝ ገ/ፃድቕ
4. አቶ ብርሃነ ገ/የሱስ
5. አቶ ሃፍቱ ኪሮስ
6. ወ/ሮ ሰብለ ካሕሳይ
7. አቶ ነጋ ኣሰፋ

የፓርቲው ስራ አስፈፃሚ አድርጓቸዋል።

- አቶ ሙላት ገ/ስላሴ
- አቶ ጠዓመ ዓረዶም
- ዶ/ር ሺሻይ ኣማረ 
- ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም
- አቶ ፀጋይ ገ/ተኽለ
- ዶ/ር ርእየ ኢሳያስ 
- አቶ ገ/ሚካኤል እኑን
- አቶ ዮናስ ሃይለ
- አቶ ተስፋኣለም ይሕደጎ
- አቶ ኤርሚያስ ኣባቡ
- አቶ ስላስ ሃፍቱ
- አቶ ፀጋይ ፃዲቕ
- አቶ የማነ ንጉስ
- አቶ ሃፍቱ ወ/ንስአ
- አቶ ደስታ ግርማይ 
- አቶ ወ/ሰንበት ተ/ኪሮስ
- አቶ መብራት ስዩም
- ዶ/ር ዮናስ ገ/ሄር
- ዶ/ር ከላሊ ኣድሀና
- ቀሺ በሪሁ ሓዱሽ
- አቶ ተዘራ ጌታሁን
- አቶ ፍፁም ለገሰ
- ወ/ሮ ኣስኳል ገብረ
- አቶ ፀጋይ ገ/ጂወርጊስ

ደግሞ የፓርቲው የማእከላይ ኮሚቴ አድርጎ በመምረጥ የአንድ ቀን ጉባኤውን ማምሻውን አጠናቋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
1.25K😡176🤔86😭44🕊36🙏20👏11😢11💔8🥰3
TIKVAH-ETHIOPIA
" ሾፌሩ ምንም ጉዳት ሳይደርስበት ከተገለበጠው ተሽከርካሪ ውስጥ ወጥቷል ! " ዛሬ ጥቅምት 14/2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ አረዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ሶር አምባ ሆቴል ፊት ለፊት ከቀኑ 6:45 ሠዓት ላይ የትራፊክ አደጋ የአጋጠመ ሲሆን በአደጋው በንብረት ላይ መጠነኛ ጉዳት ከመድረሱ በስተቀር በሠው ላይ የደረሰ ጉዳት የለም። አደጋው በደረሰበት ሰዓት መኪናውን እያሽከረከረ የነበረዉ ሾፌር ምንም…
" ተአምር ነው ! "

ተሽከርካሪው 150 ሜትር ርዝማኔ ያለው ገደል ገብቶ አርሶ አደር ግቢ ውስጥ ቢያርፍም ከቀላል ጉዳት ውጪ ያጋጠመ ከባድ ጉዳትና ሞት የለም።

በትግራይ ክልል የሚገኘው የጥንታዊው አቡነ አረጋዊ ገዳም ዝክር በየዓመቱ የአገር ውስጥና ከውጭ የሚመጡ ምእመናን በተገኙነት ጥቅምት 14 ነው የሚከበረው።

ታዲያ በ" ቶዮታ " ተሽከርካሪ ባለቤቱ እራሱን ጨምሮ 5 ሰዎች ጭኖ ዓመታዊው የአቡነ አረጋዊ ገዳም ለመሳለም በመጓዝ ላይ እያለ ተሽከርካሪው መንገድ ስቶ ተንሸራቶ ገደል ይገባል።

ተሽከርካሪው የገባበት ገደል ርዝማኔው 150 ሜትር ነው ብለዋል የአይን እማኞች።

ተሽከርካሪው መንገድ ስቶ ወደ ገደል ከተወረወረ በኃላ በፎቶው እንደሚታየው ወደ አንድ አርሶ አደር ቤት ግቢ ገብቶ ተዘቅዝቆ አርፏል።

ከአስፈሪ ገደል ተወርውሮ በሚታየው መልኩ ያረፈው ተሽከርካሪ በአርሶ አደር ቅጥር ግቢ ከነበሩት ሰዎችና እንስሳት ላይ አንድ ቀላል ጉዳት ከማድረሱ ውጪ የተከሰተ ከባድ ጉዳትና ሞት የለም።

ክስቱቱን ለሰሙት " ተአምር " ያስባለ እንደሆነ የቲክቫህ ኢትዮጵያ መቐለ ቤተሰብ አባል ገልጾልናል።

አሽከርካሪዎች ለማሽከርከር በሚያዳግቱና ተዳፋት በሆኑ መንገዶች ላይ ሲያሽከረክሩ እርጋታና ማስተዋል ሊለያቸው አይገባም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
4.22K🙏1.33K😱133🤔69🕊66👏47💔38😡21🥰19😭12😢6
#SafaricomEthiopia
#MPESASafaricom

እንኳን ደስ አላችሁ! 🎉💵

ባሳለፍነው ጥቅምት 10 በነበረን የስምንተኛ ዙር ዕድለኞች ዕጣ አወጣጥ መሰረት የ1,000,000 ብር እድለኛ ከሻሸመኔ እንዲሁም የ100,000 ብር እድለኛ ደግሞ ከጅጅጋ ሆነዋል!

ማን ያውቃል ቀጣይ እርስዎ ሊሆኑ ይችላሉ! የበሽ ጥቅል እየገዛን እንንበሽበሽ! 🥳🎉🎉

ሌሎች የ100ብር አሸናፊዎች #Besh100Winner በመጠቀም ኮሜንት ላይ ወይም story ላይ ሳፋሪኮም ኢትዮጽያን ታግ በማድረግ ያሳውቁን።

📲 የM-PESA መተግበሪያን አሁኑኑ ያውርዱ፡ https://onelink.to/ewsb22

የቴሌግራም ቦታችን👉🏽 https://www.tg-me.com/official_safaricomet_bot

ወደ *777*0# ይደውሉ ወይም በM-PESA የበሽ ጥቅል ይግዙ!

#furtheraheadtogether
#Besh100Winner
203😡12🙏9😱7😢7🤔4💔4😭2👏1
" ድርጊቱና አሳፋሪና ከሙያው ስነምግባር የወጣ ነው። የትኛውም ሰው ከሙያ ባህሪው የወጣ ነገር ሲሰራ በሕግ ይጠየቃል "- ስልጤ ዞን ፖሊስ

➡️ " እምቢታ ካለም ሴትዮዋን በሕግ መጠየቅ ይቻል ነበር። ይህን አለመከተሉ የፓሊስ አባሉ ችግር ነው። በቁጥጥር ስር ውሎ ታስሯል! "

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በስልጤ ዞን ምስራቅ ስልጢ ወረዳ ገርቢ በር ከተማ አንድ የፖሊስ አባል አንዲት እናት ለሽያጭ ያቀረበችውን ጎመን በእግሩ በመበታተን ከጥቅም ውጭ ማድረጉና ይህችውን እናት ማመናጨቁ በርካቶችን በብርቱ አስቆጥቷል።

የፖሊስ አባሉ ለሽያጭ የቀረበውን ጎመን በእግሩ ሲበታትነው የሚያሳይ ቪዲዮ በገሃድ የተሰራጨ ሲሆን፣ ይህንኑ አስነዋሪ ድርጊት የተመለከቱና በቦታው የነበሩ ነዋሪዎች " ከፖሊስ የማይጠበቅ፣ የእናትን እና የስራን ክብር የጣሰ ተግርባር በመሆኑ ፖሊሱ በሕግ ሊጠየቅ ይገባል " ሲሉ ድርጊቱን አውግዘዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ፥ በጉዳዩ ዙሪያ የስልጤ ዞን ፖሊስ አዛዥ ምክትል ኮማንደር ኑረዲን አብደላን አነጋግሯል።

ኮማንደር ኑረዲን ነገሩ መከሰቱን አረጋግጠዋል።

የፖሊስ አባሉ ድርጊቱን መፈጸሙን ገልጸው፣ " ድርጊቱ አሳፋሪና ከሙያው ስነምግባር የወጣ ነው። የትኛውም ሰው ከሙያ ባህሪው የወጣ ነገር ሲሰራ በሕግ የሚጠየቅበት አግባብ አለ " ነው ያሉት።

" መደረግ የሌለበት ነው፥ ለዚህ የሚያበቃም አይደለም፥ ጤናማ በሆነ መንገድ ማንሳት፣ እምቢታ ካለም ሴትዮዋን በሕግ መጠየቅ ይቻል ነበር። ይህን አለመከተሉ የፓሊስ አባሉ ችግር ነው። በቁጥጥር ስር ውሎ ታስሯል " ሲሉም አክለዋል።

" ቦታው ቁልቁለት ስለሆነ ለሰው ደህንነት ሲባል ሌላ የገበያ ቦታ ተቀይሯል። ግን እዛ ቦታ ላይ መጥተው ይቀመጣሉ (ነጋዴዎች) ወደ ተፈቀደው ቦታ እንዲሄዱ ለማድረግ ፖሊሶች በቦታው ይመደባሉ "ሲሉ አስረድተው፥ ድርጊቱ የተፈጸመው ጥቅምት 10 ቀን 2018 ዓ/ም በዚሁ በተከለከለ ቦታ ቁጭ ብላ በነበረች ሴት መሆኑን ገልጸዋል።

ለገበያ ከተፈቀደው ቦታ ሰዎቹን ያነሷቸው ሌሎች የከተማው አካላት ጭምር እንደሆኑ፥ ፖሊስም በቦታው እንደሚመደብ ኮማንደሩ አስረድተዋል።

ፖሊስ ድርጊቱ የተፈጸመባትን እናት ቀርቦ ያደረገላት ድጋፍ አለ ? ስነ ልቦነዋ እንዳይጎዳስ ምን ተደረገላት ? ለሚለው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ፥ " ፖሊስ፥ ሌሎች የማህበረሰብ አካላትም ድጋፍ ለማድረግ ጥረት እያደረጉ ነው " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
1.72K😡589😭149👏119💔81🙏57😢25🕊23🤔15😱15🥰6
የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ነገ እሁድ ልዩ በሆነ መልኩ እንዳለ ሰምተዋል?

ለፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ለመመዝገብ አስበው ጊዜ እና ሰዓት አልመቻች ብሎዎታል? ተማሪዎችስ ከትምህርት ሰዓት ውጭ ለመመዝገብ? እንግዲያው ነገ ጥቅምት 16 በልዩ ሁኔታ በሁሉም የምዝገባ ጣቢያዎች አገልግሎት ስለምንሰጥ በአቅራቢያዎ በሚገኝ የምዝገባ ጣቢያ በመሔድ ይመዝገቡ።

ለተጨማሪ መረጃ id.gov.et ይጎብኙ ወይም 9779 ይደውሉ።

#ፋይዳለኢትዮጵያ #ፋይዳለሁሉም #ፋይዳምዝገባ
253😡49🤔22🥰7🕊5😢4😭3
" በስልጠና ማጠናቀቂያ ወቅት ያገኙት ሰርተፍኬት በዩኒቨርሲቲው ለመማር በሚወዳደሩበት ወቅት 10 በመቶ ውጤት እንዲኖረው እናደርጋለን "- የአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በ2017 ዓ/ም የክረምት መርሃ ግብር በሳይበር ደህንነትና ተያያዥ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 629 ታዳጊ ወጣቶችን በዛሬው ዕለት አስመረቋል።

ታዳጊዎቹ በክረምት መርሃ ግብር የሰለጠኑት ፦
- በሳይበር ደህንነት፣
- በቴክኖሎጂ ልማት፣
- በኢምቤድድ ሲስተም፣ እና በኤሮስፔስ ዘርፎች ነው።

ላለፉት ሦስት አመታት አዲስ አበባ ላይ ብቻ ሲካሄድ የቆየው የስልጠና መርሃ ግብር፤ በ2017 ዓ/ም ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ለመጀመሪያ ጊዜ 76 ልጆች ሰልጥነው መመረቅ መቻላቸው ተገልጿል።

ስልጠናውን የተከታተሉት ታዳጊዎች ከኢለመንተሪ፣ ሃይስኩል እና ዩኒቨርሲቲ የተወጣጡ ናቸው ።

ታዳጊዎቹ ስልጠናቸውን ከኢንሳ በተጨማሪ  በአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (AASTU) ሲከታተሉ የቆዩ ሲሆን በማጠናቀቂያው ወቅት የተሰጣቸው ሰርተፍኬት በዩኒቨርሲቲው ትምህርት ለመከታተል በሚወዳደሩበት ወቅት የመቁረጫው ነጥብ ዝቅ እንደሚያደረግላቸው የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር ደረጀ እንግዳ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ደረጀ እንግዳ በዝርዝር ምን አሉ ?

" ግቢ ውስጥ በቆዩበት ጊዜ በተለያዩ ዘርፎች ስልጠናቸውን ሲከታተሉ ቆይተዋል ስልጠናውን ኮርስ በመስጠት ብቻ ሳይሆን ችግሮቻችንን በመንገር ችግሮችን መፍታት ከመቻላቸውም በላይ ፕሮዳክቶችን ይዘው መጥተዋል።

የራሳቸው የሆነ የተለያዩ ችግሮችን መፍታት እና መሸጥ የሚችሉ ፕሮዳክቶችን ይዘው ወጥተዋል።

እኛ ፈተና ፈትነን ተማሪዎችን የምንቀበል መሆኑ ይታወቃል ፈተና ፈትነን ስንቀበል የ 12 ውጤት እና የመግቢያ ፈተና ውጤት ነው የምናየው።

በእዚህ ስልጠና ከመላው የኢትዮጵያ አካባቢዎች መጥተው በግቢያችን ስልጠና ሲከታተሉ የቆዩ ተማሪዎች የወሰዱት ሰርተፍኬት በግቢያችን ለመማር በሚያመለክቱበት ወቅት ቫልዩ ይኖረዋል።

ከእዚህ ቀደም ስናወዳድር 50 በመቶ 12 ክፍል ውጤት 50 በመቶ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ውጤት እንመለከት ነበር አሁን 10 በመቶ በስልጠና ማጠናቀቂያው ወቅት ያገኙትን ሰርተፍኬት እንዲይዝ  እናደርጋለን።

አንድ ላይ ተደምሮ ከመቶ ሲያዝ የመቁረጫ ነጥብ ላይ ባመጡት ቁጥር ዝቅ ያደረግላቸዋል ፣ ልዩ ኮታ ይሰጣቸዋል ማለት ነው ።

ይህንን እድል አምናም ሰጥተናል ዘንድሮ ከገቡ መካከልም ይህንን እድል ያገኙ አሉ በሚቀጥለው አመትም ይህ ይቀጥላል።

ሁለተኛ እዚህ ስልጠናቸውን የተከታተሉ ተማሪዎች የተለያዩ ፕሮዳክቶችን አውጥተዋል እኛ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የኢንዱስትሪያል ኢኖቬሽን እና ኢንኩቤሽን ሃብ ሰርተናል ይህ ሃብ ወደ 189 ስታርታፖችን መቀበል ይችላል።

እነዚህ ስታርታፖች ከተለያዩ ቦታ እና ዩንቨርሲቲዎች የተወጣጡ ሊሆኑ ይችላሉ ነገር ግን ሜድ ኢን ኢትዮጵያ ምርቶች ያላቸው እና መሸጫ ቦታ ያጡ ሰዎችን የምናሰባስብበት ቦታ ነው።

ይህንን ስፔስ (ቦታ) ስልጠናውን ለተከታተሉ ሰዎች ለሰሯቸው ምርቶች (ፕሮዳክቶች) እናቀርባለን።

የምናቀርበው በሁለት አይነት መንገድ ነው አቅሙ ኖሯቸው በራሳችን እንቀጥል ካሉ የተወሰነ ኪራይ እናስከፍላለን ፣ምንም አቅም የለንም የሚሉ ካሉ ከተለያዩ ባለሃብቶች እና ከዩኒቨርሲቲውም አንድ ላይ አድርገን ድጋፍ በማድረግ ምርታቸው ወደ ገበያ እንዲወጣ እና ስራ ፈጣሪ እንዲሆን ድጋፍ እናደርጋለን " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
592😡29🙏14🤔9🕊4👏3😱2🥰1😢1
2025/10/31 15:11:32
Back to Top
HTML Embed Code: