Telegram Web Link
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
የኢትዮጵያውያን ድምጽ ከማይናማር📢

" BGF ውስጥ የምንገኝ ኢትዮጵያውያን ነን።

ከዚህ ቦታ መውጣት የምንችለው በኢትዮጵያ ኤምባሲዎች አማካኝነት ብቻ ነው። ከዛ ውጭ መውጣት አንችልም።

ያለንበት ሁኔታ እጅግ በጣም ከባድ ነው። ብዙ ሰዎች በትንሽ ቦታ ተጨናንቀን ነው ያለነው።

ከቻይናዎች ፣ ከህንዶች፣ ከፓኪስታኖች ... እና የሌሎች ሀገራት ሰዎች ጋር ነው አብረን ያለነው።

ፎርም ሞልተናል፣ አስፈላጊውን ዶክመት ጨርሰናል። እነሱ ያሉን ' የኢትዮጵያ ኤምባሲ ነው የሚወስዳችሁ ' ነው ግን እስካሁን ምንም አልሰማንም ማንም ያናግረን አካል የለም። እኛም ማንን ማናገር እንዳለብን አላወቅንም።

ይህ መልዕክት በአካባቢው ወዳሉት የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች ይደረስልን። እኛ ያለንበት ቦታ ብቻ 31 ኢትዮጵያውያን አለን። ሌሎች ቦታዎች እንዲሁም ተሻግረው ታይላድ ገብተው መጠለያ ውስጥ ያሉ ብዙ ኢትዮጵያ አሉ። " - ኢትዮጵያውያን ከማይናማር

በማይናማር በተለይ ጋንጎች በሚቆጣጠሯቸው ካምፖች ላይ የማይናማር ጦር ከሰሞኑን ሰፊ ዘመቻ እያካሄደ ነው። ይህ ተከትሎ አካባቢው እንደ ከዚህ ቀደሙ የተረጋገ አይደለም። በርካቶች በማይናማር ጦር የተያዙ ሲሆን በርካቶችም ከአካባቢው ለመውጣት ጥረት ላይ ናቸው።

ቪድዮ ፦ BGF ውስጥ ኢትዮጵያውያንና የሌሎች ሀገራት ዜጎች ያሉበት ሁኔታ

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
#TikvahEthiopiaFamily

@tikvahethiopia
626😢316😭103💔42🙏35🕊22🤔9😱6🥰5👏4
TIKVAH-ETHIOPIA
ኤርትራ እና ግብፅ የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለ5 ቀን የስራ ጉብኝት ትላንት ለሊት ግብፅ መሄዳቸውን የሀገሪቱ የማስታወቂያ ሚኒስቴር አሳውቋል። ኢሳያስን " ኑ " ብለው ግብዣ ያደረጉላቸው የግብፅ ፕሬዚዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ ናቸው። በ5 ቀን ቆይታቸው በሁለትዮሽ፣ በቀጠናዊ እና ዓላም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ተብሏል። የኤርትራው ፕሬዚዳንት ከዚህ ቀደም (ከወራቶች በፊት) ወደ…
" አይዟችሁ እኔ አለሁላችሁ " ባይዋ ግብፅ !

የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በግብፁ ፕሬዜዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ ግብዣ ለ5 ቀን ግብፅ፣ ካይሮ ናቸው።

ሁለቱ ፕሬዚዳንቶች ውይይት ባደረጉበት ወቅት የግብፁ መሪ " ለሉዓላዊነታችሁ እና ለግዛታዊ አንድነታችሁ ድጋፍ ለማድረግ ቁርጠኛ ነን " ሲሉ ለኢሳያስ ነግረዋቸዋል።

ከዚህ ቀደም ጎረቤት ሀገር ሶማሊያ ከኢትዮጵያ ጋር አለመግባባት በፈጠረችበት ወቅት እኚሁ የግብፅ ፕሬዚዳንት " አይዟችሁ ፤ ለሱማሊያ ሉዓላዊነት እንዲሁም የግዛት አንድነት እኛ ድጋፍ እናደርጋለን በማንኛውም መንገድ " ሲሉ ነበር የከረሙት።

#TikvahEthiopiaFamily

@tikvahethiopia
😡1.21K583🤔99👏77🕊56😱26🙏23😭19💔11🥰8😢6
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update #EOTC

ከኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ፤ " በአንጋፋዋ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካህናት እና ምዕመናን ላይ ግድያ እና ስቃይ መፈጸሙን የሰማነው በታላቅ ድንጋጤና ሀዘን ነው " አለ።

መሰል ተግባራት በተለያዩ ወቅቶች ሲፈጸም እንደነበር አስታውሷል።

ጉባኤው የቤተክርስቲያኗን " የዛሬውን የሀዘን መግለጫ ተመልክቻለሁ " ብሏል።

" በኦሮሚያ ክልል በአርሲ ዞን ፦
- በጉና፣
- በመርቲ፣
- በሸርካ
- በሆሎንቆ ዋቢ ወረዳዎች በአንጋፋዋ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች እና ካህናት ላይ እየደረሰ ያለው ግድያ እና ስቃይ ከዕለት ዕለት እየጨመረ መምጣቱን ተረድተናል " ሲል አመልክቷል።

ይህን ግድያና እንግልት የፈጸሙት አካላት ማንነታቸው ያልታወቀ ታጣቂዎች እንደሆኑ መረዳት እንደቻለ ተናግሯል።

ጉባኤው በተፈጸመው አሰቃቂ ግድያ የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን ለቤተ ክርስቲያኒቱ አባቶች እና መሪዎች በተለይም ለተጎጂ ቤተሰቦች ገልጿል።

መንግሥት የዜጎችን በሰላም ወጥቶ የመግባት ነፃነት የማረጋገጥ ዋንኛ ኃላፊነት ያለበት በመሆኑ ችግሩ ከዚህ በላይ ተባብሶ ተጫማሪ ሀዘን እና ሰቆቃ ከመከሰቱ አስቀድሞ አስፈላጊውን የሕግ ማስከበር ሥራ እንዲሠራ ጉባኤው በአጽንኦት አሳስቧል።

ሁሉም የሃይማኖት ተቋማት እና ሕብረተሰብ ይህን እጅግ የከፋ የጭካኔ ተግባር  በአንድ ድምጽ በግልጽ ማውገዝ እና ከሕግ አካላት ጋር በመተባበር ወንጀለኞችን ለፍርድ እንዲቀርቡ የበኩሉን ሚና እንዲወጣ አደራ ብሏል።

በተያያዘ መረጃ የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በምዕመኖቿ ላይ በምስራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት የተፈጸመውን ግድያ " ኢሰብዓዊ  ድርጊት " ሲል ገልጾ በጽኑ አውግዟል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ

@tikvahethiopia
1😭1.32K559😡88🕊49💔44👏23😢13🙏10🤔7🥰6😱2
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ቀይ ባህር

" የቀይ ባህር ጉዳይ ፦
- ህጋዊ፣
- ታሪካዊ፣
- መልካምድራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥያቄ ነው ብለን እናምናለን።

ይሄ ጥያቄ አንዳንዱ ' ነገ ካልተመለሰ ' ይላል አንዳንዱ ' ነገ እኔ ስመጣ ካልጀመርኩት ' ይላል ሁለቱም አያስገልግም።

ቀይ ባህርን ኢትዮጵያ ለማጣት 30 ዓመትና ከዚያ በላይ የወሰደ ትግል ነበር ፤ በ30 ዓመት ትግል ውስጥ በብዙዎች ርብርብ ነው ኢትዮጵያ ቀይ ባህርን ያጣችው።

በተረጋጋ መንገድ፣ በሰከነ መንገድ ፣ በውይይት መሄድ አስፈላጊ ነው (ለማግኘት)። የፈለገ ብንወያይ ግን ለማጣት የፈጀብንን 30 ዓመት ለማግኘት ይፈጅብናል ብዬ ግን አላስብም። ግዜው ግን በቂ ስለሆነ በተረጋጋ መንገድ ማየት ያስፈልጋል።

የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያየው የምፈልገው ነገር ... አንዳንዱ ዛሬን ብቻ ስለሚያስብ ዳራውን ልስጥ።

በመጀመሪያ ኢትዮጵያን የቀይ ባህርን ያሳጣትን ውሳኔ ማን ወሰነው ? ካቢኔው ይሆናል ብለን የካቢኔ ዶክመንት ብናገላብጥ የለም። ካቢኔ አያውቀውም። አይ ምክር ቤት ይሆናል የወሰነው ብለን ብናስብ ምክር ቤቱም አልነበረ ምክር ቤት አያውቀውም ውሳኔውን። የለም የኢትዮጵያ ህዝብ በሪፈረንደም ወስኖ እንዳይሆን እንዳይባል ነበርን እኛም ያኔ።

የኢትዮጵያ ህዝብ ያልወሰነው ፤ ተወካዮቹ ያላዩት ፤ ቢያንስ ቢያስ ከአስፈጻሚ ካቢኔ ያላየውን ውሳኔ ማን ወሰነው ? ማጣትን የሚያክል ነገር ያጣንበት መንገድ ህጋዊነት ችግር እንዳለበት ማሳያው ተቋሞች አልገቡበትም። ካቢኔ አያውቀውም። አንድ ገጽ ወረቀት ማግኘት አልቻልንም እንዴት እንዳጣነው የሚያስረዳ።

ህዝብ ማያውቀው፣ ፓርላማ የማያውቀው ፣ ካቢኔ የማያውቀው የኢትዮጵያ የባህር በር የሚያሳጣ ውሳኔ የወሰነው ማነው የሚል ጥያቄ ማንሳት እንዴት ስህተት ሊሆን ይችላል ? ካለ ይነገረን። ከሌለ ግን ይሄ ጉዳይ ይሄን ውሃ አንስቶ እንደመድፋት አይደለም የህልውና ጉዳይ ነው። ማን ወሰነው? ይሄ ነው ጥያቄው። "  - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

#Ethiopia🇪🇹

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
14.41K😡291🙏228👏155🕊89🤔55💔42🥰34😭29😱17😢14
መብትን ያማከለ የስራ ቦታና ሁኔታ የፍትሀዊነት እና የእኩልነት መናህሪያ ነዉ፡፡

አሰሪዎች ተደራሽነትን እና ምክንያታዊ ማመቻቸትን ሲያረጋግጡ ህጎችን ማክበር ብቻ ሳይሆን የመከባበር እንዲሁም የምርታማነትን ባህል ያጎለብታሉ፡፡

ዘመናዊ አሰሪ ብዝኃነትን ፣አካታችነትን እና መድሎ አልባነትን በስራ ቦታዎች ያረጋግጣል፡፡

የኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ አካል ጉዳተኞች ማህበር ከሲቪል ራይትስ ዲፌንደርስ ባገኘዉ የገንዘብ ድጋፍ
Website: https://elda-eth.com/
Facebook: https://web.facebook.com/profile.php?id=61579398676431
Twitter: https://x.com/toelda2024
Linkdin: [https://www.linkedin.com/company/ethiopian-lawyers-with-disabilities-association/]
Tik tok : https://vm.tiktok.com/ZMSumrLhm/
219👏10😢2
መስራት ማህበር ለኢትዮጵያውያን ስራ ፈጣሪዎች ተግባራዊ ድጋፍ ለማድረግ ታስቦ የተዘጋጀ መድረክ ነው ፦
Ø  በንግድ፣ በፋይናንስ፣ በማርኬቲንግ፣ በኢንቨስትመንት፣ በገበያ ማፈላለግና በህግ ጉዳዮች ዙርያ ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች የተዘጋጁ ጽሁፎችን ማጋራት

Ø  የንግድ ስራችሁን ለማስተዳደር የምትጠቀሙበት መመሪያዎችንና ሃሳቦችን ማጋራት
Ø  በናንተ የስራ ፈጠራ መንገድ ቀድመው ካለፉና ብዙ ልምድ ማካፈል ከሚችሉ ጋር ማህበረሰብ የምትፈጥሩበትና ሃሳብ የምትለዋወጡበት መድረክ
Ø  በስራችሁ ወደፊት ለመራመድ የሚያግዙአችሁን የተለያዩ ሃሳቦች ማጋራት እንዲሁም ጠቃሚ ግንኙነቶችን የምትፈጥሩባቸው ኩነቶችን መጠቆም
የሚከተሉትን የመረጃ ምንጮች በመጠቀም የንግድ ስራችሁን አሳድጉ https://mahber.mesirat.org/wp-login.php?loggedout=true&wp_lang=en_US
118🙏3😭2🥰1
የምስራች!!
ዘኔክሰስ የሞባይል ቀፎዎች በተመጣጣኝ ዋጋ ለገበያ ቀረቡ!!

🔆 ለተጠቃሚ ምቹ የሆኑ (keypad + touchscreen) መጠቀም የሚያስችሉ
🔋 ረጅም የባትሪ ዕድሜ ያላቸው
🗂️ በ teleStorage አማካኝነት የራሳቸው የፋይል ማከማቻ ያላቸው
🤖 ወሳኝ አፕሊኬሽኖች የተጫነባቸው
🛜 ዋይፋይና ሆትስፖት ማስጠቀም የሚችሉ

ከ2 ጊ.ባ የሦስት ወራት ነጻ የዳታ ስጦታ ጋር ቀርበዋል፤ ፈጥነው የግልዎ ያድርጓቸው።

📍በአገልግሎት ማዕከሎቻችን ያገኟቸዋል!

ለተጨማሪ መረጃ: https://bit.ly/4hTWxQl

#znexus
#Ethiotelecom #telebirr #telebirrSuperApp #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
120👏7💔6😡6😭3😱2🕊1
TIKVAH-ETHIOPIA
" ያረጀ ቫልቩ ጥገና ባይከናወን የግድቡን ህልውና አደጋ ውስጥ ይከተው ነበር " - የውሃ እና ፍሳሽ ባለሥልጣን የአዲስ አበባ ከተማ ውሃ እና ፍሳሽ ባለሥልጣን የለገዳዲ ግድብ የውሃ ማስተላለፊያ ማማ የቫልቭ ቅየራ ስራ ከጥቅምት 2 ቀን 2018 ዓ/ም እስከ ጥቅምት 16 ቀን 2018 ዓም ድረስ እንደሚከናወን ማሳወቁ ይታወቃል። የቫልቭ ቅየራ ስራው እስከሚጠናቀቅም በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ፣ በቦሌ ክፍለ…
" የጥገና ስራው ግድቡ 3 ሚሊየን ሜትር ኪዩብ ተጨማሪ ውሃ መያዝ አስችሎታል " - ውሃ እና ፍሳሽ ባለሥልጣን

የአዲስ አበባ ውሃ እና ፍሳሽ ባለሥልጣን ከአለም ባንክ በተገኘ የ 11 ሚሊዩን ዩሮ የብር ድጋፍ 55 አመታት ያስቆጠረውን የለገዳዲ ግድብ የጥገና ስራ ማከናወኑን አሳውቋል።

ከጥቅምት 2 እስከ ጥቅምት 16/2018 ዓም የተከናወነው የጥገና ስራው የግድቡን ጤንነት የሚቆጣጠሩ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎን የመግጠም ስራ ያካተተ ሲሆን ለረጅም ጊዜያት ሳይቀየሩ አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩ ቫልቮችም ቅየራ ስራ መከናወኑን ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቋል።

የጥገና ስራውን ያከናወነው ዊ ብዩልድ ወይም ሳሊኒ ሲሆን በጥገና ስራው ምክንያትም ለገዳዲ ግድብ 3 ሚሊየን ሜትር ኪዩብ ተጨማሪ ውሃ መያዝ መቻሉን በውሃ እና ፍሳሽ ባለሥልጣን የግንባታ ቁጥጥር የስራ ሂደት ሃላፊ አቶ አለማየሁ ታደሰ ለቲክቫህ ተናግረዋል።

በአዲስ አበባ ውሃ እና ፍሳሽ ባለሥልጣን የውሃ አቅርቦት ፣ስርጭት ፣የውል አስተዳደር እና የግንባታ ቁጥጥር የስራ ሂደት ሃላፊ አለማየሁ ታደሰ ስለ ጥገና ስራው ለቲክቫህ በሰጡት ቃል ምን አሉ ?

" የለገዳዲ ግድብ ከተሰራ 55 ዓመት ይሆነዋል ስለዚህ የኢንቴክ ታወሮች፣ ቫልቮች እና የግድቡን ደህንነት የሚጠብቁ መቆጣጠሪያዎች ፣የደህንነት መሳሪያዎች፣ ግድቡ ውሃ ሲሞላ የሚተነፍስበት ሦስት ማስተንፈሻዎች ቅየራ እና የመግጠም ስራ ተጠናቋል።

በጥገናውም የለገዳዲ ግድብ የጥሬ ውሃ የመያዝ አቅም ከእዚህ ቀደም ከነበረው 3 ሚሊየን ኪዩቢክ ሜትር ተጨማሪ ውሃ መያዝ ያስችለዋል።

ጥገናው ግድቡ ለቀጣይ 55 ዓመታት ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ እንዲያገለግል የሚያስችል ነው።

ትልቁ ነገር ሦስት ማስተንፈሻ ቫልቮች ላይ ድንገተኛ ነገር ቢፈጠር ከእዚህ በፊት በነበረው አሰራር ግድቡ ውሃ እንደያዘ ችግሩን መፍታት አስቸጋሪ ነበር በጥገናው መሰረት ስቶፕ ሎግ የሚባል ቴክኖሎጂ የተገጠመ በመሆኑ ችግር ቢያጋጥም ውሃውን ሳንለቅ መጠገን የሚያስችለን አቅም ፈጥረናል።

በተጨማሪም ከግድቡ ውሃን ወደ ማጣሪያ ታወር የሚወስዱ አራት ቫልቮች ቅየራም ተከናውኗል።

የለገዳዲ ግድብ አጠቃላይ የጥሬ ውሃ የመያዝ አቅም 44 ሚሊየን ሜትር ኪዩብ ሲሆን የማጣራት አቅሙ ደግሞ በቀን 195 ሺ ሜትር ኪዩብ ነው በጥገናው ስራ የግድቡ የመያዝ አቅም ወደ 47 ሚሊየን ሜትር ኪዩብ ከፍ ማለት ችሏል።

የግድቡ ማስተንፈሻ ቫልቭ ወይም የደህንነት ቫልቮች ላይ የተሰራው የጥገና ስራ ባይሰራ ኖሮ አደጋ ሊፈጥር ይችል ነበር።

አጠቃላይ የግድቡን ጤንነትን የሚለኩ መሳሪያዎች ብዙ አመታት ያስቆጠሩ በመሆኑ ማየት አያስችሉም ነበር።

እነዚህ የግድቡን ጤንነት ለመከታተል የሚያስችሉ መሳርያዎች የግድቡ ጤንነት ምን ላይ ነው ያለው ከሚለው ጀምሮ የመሬት መንቀጥቀጥ ቢያጋጥም የግድቡን ሁኔታ ለመከታተል የሚያስችሉ መሳሪያዎች ከዛሬ 55 ዓመት በፊት የተገጠሙ እና የቆዩ በመሆናቸው የሚሰሩ አልነበሩም።

አሁን በጥገናው እነዚህ መሳሪያዎች የተገጠሙለት በመሆኑ የግድቡን ጤንነት መከታተል አስችሎናል።

የጥገናው አላማ የግድቡን እድሜ ማራዘም እና የተሻለ ጤንነት እንዲኖረው ማድረግ እና የመጣራት አቅሙ ውጤታማ እንዲሆን ማስቻል ነው።

በጥገና ስራው ምክንያት ግድቡ መያዝ የቻለው ተጨማሪ ውሃ በተለያየ ምክንያት ድርቅ ቢከሰት እንደ መጠባበቂያ መጠቀም ያስችላል።

ይህ ጥገና ግድቡ የነበሩበትን ችግሮች ሙሉ በሙሉ ከማስወገዱም በተጨማሪ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን እንዲገጠሙለት አድርጓል " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthipiaFamilyAA

@tikvahethiopia
598👏62🤔21🙏17😡8🕊7😢3
TIKVAH-ETHIOPIA
የስምረት ስራ አስፈጻሚ ከኃላፊነት ተነሱ። የስምረት ትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ስራ አስፈጻሚዋ በትግራይ ከነበራቸው የመንግስት የስራ ሃላፊነት ተነስተዋል። ሃላፊዋ በጊዚያዊ አስተዳደሩ ከነበራቸው የስራ ሃላፊነት የተነሱት ፓርቲያቸው ጥቅምት 14/2018 ዓ.ም ባካሄደው ጉባኤ የስራ አስፈፃሚ አድርጎ ከመረጣቸው በኋላ እንደሆነ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አረጋግጧል። ቲህቫህ ኢትዮጵያ የየኢንዳስትሪ…
" ከህወሓት አስተሳሰብ ውጪ የሆነ አቋም ማስተናገድ አለመቻል የቆየ ልማድ ነው " - ከኃላፊነታቸው የተሰናበቱት የስምረት አባል

ጥቅምት 14/2018 ዓ.ም ስምረት ባካሄደው  ጉባኤ የስራ አስፈፃሚ አድርጎ ከመረጣቸው በኋላ ጥቅምት 17/2018 ዓ.ም የስንብት ደብዳቤ ተፅፎላቸው ጥቅምት 19/2018 ዓ.ም ከኢንድስትሪ ቢሮ ኃላፊነት የተሰናበቱት ወ/ሮ አልማዝ ገ/ፃዲቅ " ተፈፅሞብኛል"  ስላሉት ኢ-ፍትሃዊ ተግባር ተናግረዋል።

የስራ አሰፈፃሚዋ ' Landa Report ' ለተባለ የዩቱብ ሚድያ ቃላቸውን ሰጥተዋል።

ወ/ሮ አልማዝ ገ/ፃዲቕ ምን አሉ ?

" በፊት የኮንስራክሽንና ከተማ ልማት ቢሮ ቀጥሎ የኢንዱስትሪ ቢሮ እየመራሁ የጊዚያዊ አስተዳደሩ የካቢኔ አባል ሆኜ ቆይቻለሁ።

የስራ ማሰናበቻ ደብዳቤው የተፃፈው ጥቅምት 17/2018 ዓ.ም ሲሆን እኔጋ የደረሰው ጥቅምት 19/2018 ዓ.ም ነው። ከስራ ለመሰናበቴ በግልፅ የተነገረኝ ምክንያት የለም።

ጥቅምት 14/2018 ዓ.ም በስምረት ፓርቲ መስራች ጉባኤ መሳተፌ ይታወቃል። ይህንን ተከትሎ ያን ቀን ምሽት ከካቢኔ የመገናኛ ፕላት ፎርም እንድወጣ ተደረገ። ይህ የተደረገው በስምረት ፓርቲ የምስረታ ጉባኤ በመሳተፌ ምክንያት እንደሆነ ግልፅ ነው።

ከአሁን በፊት የስምረት ፓርቲ አባል የሆነችው የስቪል ሰርቪስ ቢሮ ሃላፊ ሰብለ ካሕሳይ ከሃላፊነት እንድትነሳ ተደርጓል።

በጊዚያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ ብቸኛ የስምረት ፓርቲ አባል ሆኜ የቀረሁት እኔ ነበርኩ።

ጊዚያዊ አስተዳደሩ አቃፊና አሳታፊ መሆን እንዳለበት የተቋቋመበት ሰነድ ያመላክታል። የተለያዩ አስተሳሰቦችና አመለካከቶች የሚንሸራሸሩበት መሆን ነበረበት። ይሁን እንጂ የስምረት ፓርቲ አባል ተሁኖ የካቢኔ አባል ሆኖ መቀጠል በጣም ከባድ እየሆነ ነው የመጣው።

ሰብለም ትሁን እኔ ቀደም ሲል የህወሓት የማእከላይ ኮሚቴ አባላት እንደነበርን ይታወቃል። ነገር ግን የተካሄደው ጉባኤ ህገ-ወጥ ነው ብለን ተቃውመን ህወሓትን ለቀናል። ከዛ በኃላ ደግሞ በአቋማችን ፀንተን ስምረት ፓርቲን መስርተናል። ስለሆነም ከህወሓት አስተሳሰብ ውጪ የሆነ አቋም ማስተናገድ አለመቻል የቆየ ልማድ ነው።

ሰብለ በስምረት ፓርቲ ስብሰባ በመገኘትዋ ምክንያት ከስራ እንድትሰናበት ሆኗል። እኔም በኃላፊነት በቆየሁባቸው ግዚያት ተፅእኖዎች ነበሩብኝ። በሂደትም ከስራ እንደምሰናበት አውቅ  ነበር። ሰዓቱ ደረሰና በመጨረሻም ይሄው አድርገውታል።

ከኃላፊነት እንድነሳ ከህወሓት ፅህፈት ቤት በኩል የማያቋርጥ ጫና ይደረግ ነበር። ይህ ዓይነት አካሄድ ትክክል አይደለም። ለአገርና ህዝብ አይጠቅምም ፤ አይበጅም።

ትግራይ የሁላችን ናት። የተለያዩ አስተሳሰቦችና አመለካከቶች የሚንሸራሸሩባትና የሚስተናገዱባት መሆን አለባት።

የኔ አስተሳሰብና አመለካከት ብቻ ይደመጥ የሚል አቋም ረጅም ርቀት አያራምድም። ይህ ዓይነት አካሄድ እጅግ አደገኛና ትግራይን ወደፊት የማያዛልቅ በመሆኑ በጋራ ልናወግዘውና ልንታገለው ይገባል። "

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ

@tikvahethiopia
1833😡54😭23🤔18🙏12👏10🥰6😢4🕊4
 " አሁን ባለን አሃዛዊ መረጃ መሰረት አንድ የአጥንት ስፔሻሊስት ሀኪም ለ300 ሺህ ሰው ይደርሳል" - የኢትዮጵያ አጥንት ህክምና ባለሙያዎች ማህበር 

የአጥንት ህክምና አገልግሎቶችን ለማህበረሰቡ ተደራሽ ለማድረግ ከፍተኛ የሀገር እድገት፣ ገንዘብ እና  የተማረ የሰው ሃይል ይጠይቃል፣ ቀዶ ህክምናውም ከባድ ነው፣ ይህን ለማድረግ ደግሞ ባለሙያዎችን ማስተማር ብቻ በቂ አለመሆኑን የኢትዮጵያ አጥንት ህክምና ባለሙያዎች ማህበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

የማህበሩ ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ወርቁ ምን አሉ ?

" ለአጥንት ቀዶ ህክምና አገልግሎት የሚውሉ ዘመናዊ መሳሪያዎች ዋጋቸው ከፍተኛ ነው ያሉ ሲሆን የመግዛት አቅም እንኳ ቢኖረንም በብዙ ምክንያቶች ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባት አንችልም።

አሁን ላይ ደግሞ በተለይ ጦርነት ባለባቸው አካባቢዎች በየቀኑ ለህክምና ለሚመጣ ሰው አገልግሎቱን ለመስጠት እንዴት ነው Set up ማቋቋም ያለብን በሚለው ላይ በጣም ብዙ ማሰብ ይጠይቃል። " ብለዋል።

የማህበሩ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ኤፍሬም ገብረሃና በበኩላቸው ፤ " ጦርነት ባለባቸው አካባቢዎች በርካታ ተጎጅዎች እንደሚኖሩ አንስተው በዚያ አካባቢ የአጥንት ቀዶ ህክምና አገልግሎት ለመስጠት አስቸጋሪ ነው " ብለዋል።

" በባለፉት 10 አመታት ውስጥ በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወቅት የተጎዱ ሰዎችን አክመናል " ያሉ ሲሆን " ከ10 አመት በሗላ ደግሞ አሁን ባለው ጦርነት የተጎዱ ዜጎችን ማከማችን አይቀርም " ሲሉ አክለዋል።

ዶ/ር ኤፍሬም ገብረሃና በዝርዝር ምን አሉ ?

" በአሁኑ ስአት በ13 የህክምና ተቋማት የአጥንት ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስቲ ትምህርት እየተሰጠ ነው። 695 ሀከኪሞች አሉን፣ ከእነዚህ ውስጥ 295 የሚሆኑት እየተማሩ የሚያገለግሉ ናቸው። ሁሉም ኢትዮጵያዊያን ብቻም አይደሉም፣ ከደቡብ ሱዳን፣ ጅቡቲ፣ ከሶማሊያ እና ከሯንዳ ጭምር የመጡ ሀኪሞች አሉ።

ከ10 የሚበልጡ ሀኪሞች ደግሞ በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጪ ሰብ ስፔሻሊስቲ እንዲሰሩ እየተደረገ ነው፣ ያ ማለት ለየት ያለ በሀገራችን ውስጥ የሌሉ ነገሮችን ይማራሉ።

5 የአጥንት ቀዶ ህክምና ሙህራኖችን በዘንድሮው አመት በተገኘ ድጋፍ ህንድ፣ ግብጽ እና ፓኪስታን በመላክ እያስተማርን ነው።

የአጥንት ህክምና አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት ከ56 በላይ ሆነዋል። ይህ ግን ኢትዮጵያ ካላት የህዝብ ቁጥር አንጻር በጣም ትንሽ ነው። አሁን ባለን አሃዛዊ መረጃ መሰረት አንድ የአጥንት ሀኪም ለ300 ሺህ ሰው ይደርሳል።

በባህላዊ መንገድ ከሚደረጉ ህክምናዎች ጋር ተያይዞ ትልቅ ችግር አለ። በማወቅም ይሁን ባለማዎቅ በሚፈጠሩ ስህተቶች ብዙ ህጻናቶች እጅ እና እግራቸውን እያጡ ነው። በዚህ ላይ ጥናት እየተደረገ ነው፣ በቅርቡም ይፋ ይሆናል።

ባህላዊ ህክምና አያስፈልግም ማለት አይቻልም፣ ምክንያቱም ዘመናዊውም የመጣው ከባህላዊ ነው። ነገር ግን ችግሮቹን ነቅሶ በማውጣት ባህላዊ ሀኪሞችን ማስተማር እና ተቀራርቦ ለመስራት እነሱን የምናካትትበትን የጤና ፖሊሲ መፍጠር ይገባል " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ

@tikvahethiopia
919😭71😱35🙏28😢21👏13🕊10😡9🤔6🥰1
TIKVAH-ETHIOPIA
" አይዟችሁ እኔ አለሁላችሁ " ባይዋ ግብፅ ! የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በግብፁ ፕሬዜዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ ግብዣ ለ5 ቀን ግብፅ፣ ካይሮ ናቸው። ሁለቱ ፕሬዚዳንቶች ውይይት ባደረጉበት ወቅት የግብፁ መሪ " ለሉዓላዊነታችሁ እና ለግዛታዊ አንድነታችሁ ድጋፍ ለማድረግ ቁርጠኛ ነን " ሲሉ ለኢሳያስ ነግረዋቸዋል። ከዚህ ቀደም ጎረቤት ሀገር ሶማሊያ ከኢትዮጵያ ጋር አለመግባባት በፈጠረችበት…
#ETHIOPIA🇪🇹

ግብፅ ስለ ቀይ ባህር ምን እያለች ነው ?

ኢትዮጵያ የባህር በር ማግኘት የህልውናዋ ጉዳይ መሆኑን በተደጋጋሚ እየገለጸች ነው።

ይኸው የባህር በር ጉዳይ ዓለም አቀፍ አጀንዳ ሆኗል።

ኢትዮጵያ ከረጅም ዓመታት በፊት በግፍ ያጣችውን የባህር በር ዳግም ለማግኘት ጉዳዩን አጀንዳ አድርጋ ማንሳቷና በግልጽ " የባህር በር የህውልናዬ ጉዳይ ነው ፤ ማግኘቴም አይቀርም " ካለችበት ጊዜ አንስቶ የኢትዮጵያን እድገትና በጎ ነገር የማትሸው #ግብፅ ነገሩን ስታጣጥል ከርማለች።

ኢትዮጵያ በግልጽ የባህር በር ጉዳይን ማንሳቷ ግብፅን አጨርጭሯታል ፤ ይህንንም በተለያየ ጊዜ ባለስጣናቶቿ ከሚያደርጉት ንግግር የጎረቤት ሀገራትን መሪዎች እየጠሩ ከሚያደርጉት ውይይት መረዳት ይቻላል።

ድርጊታቸው " ክፋት እና ምቀኝነት " ከመባል ውጭ አንድም መግለጫ የለውም።

ይህችው ሀገር ዛሬ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ባድር አብዱላቲ በኩል " ኢትዮጵያ በቀይ ባሕር አስተዳደር ውስጥ ምንም ዓይነት ሚና የላትም ፤ የቀይ ባሕርን የማስተዳደር ጉዳይ የባሕር ዳርቻ ሀገራትን ብቻ የሚመለከት ነው " የሚል ዲስኩር ይዛ ብቅ ብላለች።

" እንደ ኢትዮጵያ ያሉ የባሕር በር የሌላቸው ሀገራት ተሳትፎ ተቀባይነት የለውም " ማለታቸውም ተሰምቷል።

" ግብፅ ከሳዑዲ አረቢያ ጋር በቀይ ባሕር አስተዳደር የወደፊት እጣ ፈንታ ዙሪያ እየመከረች ነው ይህን ወሳኝ የባሕር ላይ መተላለፊያ የማስተዳደር፣ ደህንነቱንና መረጋጋቱን የማረጋገጥ ቀዳሚ ኃላፊነት ያለባቸው ሁለቱ ሀገራት ናቸው " ሲሉ ለአል ዐረቢያ መናገራቸውን ስፑትኒክ ዘግቧል።

ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ጉዳይን፦
- ህጋዊ፣
- ታሪካዊ፣
- መልካምድራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥያቄ ነው ብላ እንደምታምን ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቀናት በፊት መናገራቸው ይታወሳል።

ቀይ ባህርን ኢትዮጵያ ለማጣት 30 ዓመትና ከዚያ በላይ የወሰደ ትግል ነበር ፤ በ30 ዓመታት በብዙዎች ርብርብ ቀይ ባህርን እንዳጣች ነው የገለጹት።

ቀይ ባህርን መልሳ ለማግኘት በተረጋጋ መንገድ፣ በሰከነ መንገድ ፣ በውይይት መሄድ አስፈላጊ ነው መሆኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ " የፈለገ ብንወያይ ግን ለማጣት የፈጀብንን 30 ዓመት ለማግኘት ይፈጅብናል ብዬ ግን አላስብም " ሲሉ ነው የተናገሩት።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
22.36K👏184😡68🕊63🙏42🤔35🥰28😭19💔16😢4
2025/11/07 05:38:02
Back to Top
HTML Embed Code: