Telegram Web Link
TIKVAH-ETHIOPIA
" ዛሬም በትክክል ሦስት ሰዎች ተገድለዋል "  - የአርሲ ዞን ሀገረ ስብከት ተደጋጋሚ ግድያ እንደሚፈጸም በሚነገርበት በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ዛሬም (ህዳር 1 ቀን 2018 ዓ/ም) በግብርና ስራ በተሰማሩበት ዲያቆንን ጨምሮ ምዕመናን በታጣቂዎች መገደላቸውን በኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የአርሲ ዞን ሀገረ ስብከት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል። አንድ የሀገረ ስብከቱ አመራር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ…
ሁለት ወረዳ ቤተ ክህነቶች የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ያወጣውን የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት ውድቅ አደረጉ።

ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፥ " የቀረበው መግለጫ ተንሻፎ የቀረበ ነው፤ የአካባቢው ህዝብም በዚህ አዝኗል " ብለዋል።

የኢትዮጵያ የሃማኖት ተቋማት ጉባኤ አጣሪ ኮሚቴ በአርሲ ዞን ፦
- ጉና፣
- ሽርካ፣
- ሆንኩሎ አቤ፣
- መርቲ ወረዳዎች በቅርቡ የተፈጸሙ ግድያዎችን፣ እገታዎችንና ዝርፊያዎችን በተመለከተ ያካሄደውን የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት ይፋ ማድረጉ ይታወቃል።

አጣሪ ኮሚቴው በመጀመሪያ ደረጃ የምርመራ ሪፖርቱ የሰሞኑን ግድያ " አንድን ሃይማኖት እና ብሄር ትኩረት ያደረገ አይደለም " ብሏል።

ከሌሎች ወረዳዎች ተለይተው ስማቸው ቢነሳ ተፅእኖ እንደሚደርስባቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የገለጹ ሁለት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የወረዳ ቤተክህነቶች የጉባኤው አጣሪ ኮሚቴ ያወጣውን ሪፖርት ውድቅ አድርገዋል።

ሪፖርት የቀረበበት የአንዱ ወረዳ ቤተክህነት አመራር ምን አሉ ?

" ጮኸታችንን ሰምቶ ወደሚመለከተው አካል ያቀርባል ተብሎ የታሰበ አንድ ትልቅ የሃይማኖት ተቋም 'ግድያው የአንድን ሃይማኖትና ብሄር ያተኮረ አይደለም ' ሚል በግልፅ የወጣውን ነገር አንሻፎ አቅርቧል።

ሰዎቹ በትክክል ' ከቤት ውጡ፣ አገሩን ልቀቁ አይመለከታችሁም፣ ቤቱ ንብረቱ የእናንተ አይደለም ' መባላቸውን ከሞት የተረፉት በሕይወት ያሉት ጭምር እየተናገሩ ብሄር ተኮር አይደለም ተብሎ ሲቀርብ እተገደልን፤ ' ጨክኑ፤ በርቱ ' እንደማለት ነው።

የቀረበው መግለጫ የውሸት ነው፤ እንዲህ እየተገደሉ እየታየ እንኳ ተንሻፎ የቀረበው መግለጫ አካባቢው ላይ ያለውን ህዝብ እጅግ በጣም አሳዝኖታል።

ከዚህ በኋላ ወደ ሃይማኖትም ተቋማትም ወደ መንግስትም አንሄድም ወደ ሰማይ አምላክ ብቻ እንጮኻለን የሰማይ አምላክ ፍርዱን ይስጥ እያልን ህዝቡን እያጽናናን ነው ያለነው።

በአንድ ወረዳ ብቻ በዚህ ዓመት ከ17 ያላነሱ ተገድለዋል (ታግተው ገንዘብ ከሰጡትና ከጠፉት ውጭ) 17ቱም ኦርቶዶክሳውያን ናቸው። ማነው ገዳዩ ለሚለው እሱን አናውቅም። የሞተውን፣ የሚገደለውን ግን እናውቃለን። ይሄ እየታዬ ግድያው አንድ ሃይማኖትና ብሄር ተኮር አይደለም ከተባለ እሺ ምን እንበለው ታዲያ ? " ብለዋል።


የሌላኛው ወረዳ ቤተ ክህነት አካል ምን አሉ ?

" ሪፖርቱን አይተነዋል፤ ውሸት ነው። ከሆነው ነገር በላይ (ከግድያው) የሚሰማው ያማል።

ልዑካኑ ከቀኑ 10 ሰዓት ነው የመጡት፤ ከአካባቢው የተውጣጡ የሀገር ሽማግሌዎች ውይይት ነበረን ከጠዋት እስከ 10 ሰዓት።
በዚህም ግድያው ይቁም፣ በሃይማኖት መካከል የሚነሳው ነገር ከፍተኛ ውድመት ያመጣል የሚለው ሲነገር ተውሎ ማጠቃለያው ላይ የጉባዔው ልዑካን መጡ።

በስብሰባው የተባለው ነገር ነው የተነገራቸው። ለየብቻ ሀሳብ ለማንሳት ሞክረን ነበር፤ ግን እነርሱ (ልዑካኑ) የመዘገቡትን ጥያቄ ለመጠየቅ እንጂ እኛ የምንሰጣቸውን ነገር ለመቀበል ፈቃደኛ አይደሉም። አሁን የተነሳውን ጫጫታ ለመሸፈን የታሰበበት አመጣጥ ነው።

በዚች በጥቅምት ወር የተደረገችውን እንጂ ሌላውን ለማየት አልሞከሩም። 10 ሰዓት መጡ 11 ሰዓት ተመለሱ። ከማንም ጋር አልተገናኙም። ስለዚህ የአካባቢው ችግር በ1 ሰዓት ውስጥ የሚፈታ አይደለም። ማጣራት ከተፈለገ በየክፍሉ ማጣራት ነበር የሚያስፈልገው፤ ማጣራት አልተደረገም።

ደርሶ እንደመመለስ አይነት ነገር ነው የተደረገው። በአመጣጣቸውም፣ በጥያቄያቸም (በልዑካኑ) ቅሬታ አለ። የወጣው መግለጫ ደግሞ እንደተባለው ከሆነ ለምን ዝርዝር አይቀርብም ? እኛ ዝርዝር ልንሰጣቸው ፈቃደኞች ነበርን የሞቱትን። በሪፓርቱ 'ሁሉም ተጎድቷል' የሚል ነገር ነው ያየነው ሁሉም ከተጎዳ ለምን ከሌላኛው እምነት አይጠቀስም ? ሃይማኖት ተኮር ካልሆነ።

በእኛ በኩል ከመስከረም 2 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ጥቅምት 18 ቀን 2018 ዓ/ም ድረስ በወረዳው ብቻ የተገደሉ 120 ምዕመናን ዝርዝር አለን። ግን ዝርዝሩን ለመውሰድ ፈቃደኞች አይደሉም። ግድያው ሃይማኖት ተኩር ለመሆኑ ማረጋገጫው ይሄ ነው።

በእርግጥ በወረዳ ላይ የወረዳ አስተዳደር፣ ፖሊስ፣ የቀበሌ ሊቀመንበር የሆኑ የሌላ ሃይማኖት አባላት ተገድለዋል ግን እነዚህ ባለስልጣናት ናቸው ሲቪል ነዋሪዎች አይደሉም።

በሌላ በኩል ፋኖ ነው ግድያ የፈጸመው ተብሏል፤ ፋኖ በየት መስመር ነው እዚህ አካባቢ ሊመጣ የቻለው? ፋኖ ያለው አማራ ክልል ድርጊቱ የተፈጸመው አርሲ ነው " ብለዋል።


(ሌሎች በጉባዔው ሪፓርት የቀረበባቸው ቀሪ ወረዳዎችን ሀሳብ ለማካተት ያደረግነው መከራ አልተሳካም። ጥረቱ ይቀጥላል)

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ በወረዳ ቤተክህነት በኩል  ለተነሱት ቅሬታዎች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የበላይ አካላት እና የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤን በማነጋገር ምላሽ ይዞ ለመቅረብ ጥረት ያደርጋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
11.3K😢215😭109👏58😡48🙏47💔18🤔16🕊14🥰3😱2
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ሐዋሳ ከተማ አዲስ ከንቲባ ተሾመላት።

የሐዋሳ ከተማ ም/ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ አቶ ጥራቱ በየነን የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ አድርጎ ሾሟል።

‎አቶ ጥራቱ በየነ ከዚህ ቀደም ከነሐሴ 24 ቀን 2011 ዓ.ም እስከ 2013 ዓ/ም የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ሆነው ሲመሩ የቆዩ ሲሆን ላለፉት ሶስት ዓመታት ደግሞ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የከተማው ከፍተኛ አመራር ሆነው አገልግለዋል።

በአዲስ አበባ አመራርነት ጊዜያቸውም በአመራር ብቃታቸው ስማቸው ጎልቶ ሲነሳ ቆይቷል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
525👏81🤔32😭20🕊8💔6🙏4😱2😢2🥰1
#Tigray

የኢትዮጵያ ገነት ቸርች ሪሊፍ ኤንድ ደቨሎፕመንት የተባለው አገር በቀል የምግባረ ሰናይ ተቋም ከኮምፓሽን ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ በትግራይ ለከፋ ሁኔት ለተጋለጡ ተፈናቃዮች 61 ሚሊየን ብር ዋጋ የሚያወጣ የምግብ ድጋፍ በእንዳስላሰ ሽር ከተማ አድርጓል።

የምግባረ ሰናይ ተቋሙ ስራ አስኪያጅ ሊበን ፀጋዬ ፥ " ያደረግነው የእህልና ዘይት ድጋፍ ነው ፤ የስራ አጋራችን ከሆነው ኮምፓሽን ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ በተገኘ የ61 ሚሊዮን ብር ነው ድጋፍ የተደረገው " ሲሉ ገልጸዋል።

በተገኘው የገንዘብ ድጋፍ የተገዛው ድጋፍ ከ17 ሺህ 400 በላይ ለሆነ ተፈናቃዮችና የተቸገሩ ወገኖች የዋለ እንደሆነ አመልክተዋል።

የምግባረ ሰናይ ተቋሙ ከዚህ ቀደም በመቐለና ዓድዋ ከተሞች ተመሳሳይ እርዳታ መስጠቱን መሰል የሰብአዊ ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተቋማቸው ጥረቱን እንደሚቀጥል ቃል ገብተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ

@tikvahethiopia
837🙏96👏65🤔32🕊15😡13😱7😭6🥰2😢2💔2
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Hawassa

ዳግም የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ ሆነው የተሾሙት አቶ ጥራቱ በየነ ፤ የኑሮ ውድነትን እና የስራ አጥነት ችግሮችን ለመፍታ እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል።

ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ ፤ " የከተማዋን የወደፊት ልማት አጠናክረን በማስቀጠል ለነዋሪዎችና ለእንግዶች ምቹ ለማድረግ መላውን ሕብረተሰብ በማሳተፍ እንሰራለን " ብለዋል።

የሐዋሳን ሰላም በማፅናት የቱሪዝምና የኮንፍረንስ ማዕከል ለማድረግ እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

የልማት፣ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ የኑሮ ውድነትንና የስራ አጥነት ችግሮችን ለመፍታ እንደሚሰሩም ቃል ገብተዋል።

#ENA

@tikvahethiopia
696🙏72🤔47👏26🥰23😡17🕊14😱9💔5😢4😭2
#ETHIOPIA🇪🇹

" በኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት ላይ እምነት ስለተጣለ እናመሰግናለን " - አምባሳደር ልዑልሰገድ ታደሰ

ኢትዮጵያ ከ50 ሺህ በላይ ተሳታፊዎች የሚታደሙበትን ጉባኤ እንድታስተናግድ ተመርጣለች።

ኢትዮጵያ ከሁለት ዓመት በኋላ የሚካሄደውን የዓለማችን ዋነኛውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአየር ፀባይ ለውጥ ጉባኤን እንድታስተናግድ ብራዚል ውስጥ እየተካሄደ ባለው የዘንድሮ ስብሰባ ላይ ተመረጠች።

ኮፕ በመባል የሚታወቀውን እና በየዓመቱ ከሚካሄደውን የአየር ፀባይ ለውጥ ጉባኤ በአውሮፓውያኑ 2027 የሚደረገውን "ኮፕ32" ኢትዮጵያ እንድታስተናግድ የተመረጠችው ናይጄሪያን በመብለጥ ነው።

ኢትዮጵያ በአውሮፓውያኑ 2027 የሚካሄደውን ጉባኤ በአዲስ አበባ እንድታስተናግድ የአፍሪካ አገራትን ድጋፍ አግኝታለች።

ኮፕ የሚለው ስያሜ 'ኮንፈረንስ ኦፍ ፓርቲስ' የሚሉት ቃላት ምህጻረ ቃል ሲሆን በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአየር ፀባይ ለውጥ ስምምነት ማዕቀፍ ስር የሚካሄድ የዓላማችን ዋነኛው የአካባቢ ጥበቃ ጉባኤ ነው።

በጉባኤው ከአሜሪካ በስተቀር (አሜሪካ በትራምፕ አስተዳደር ራሷን አግልላለች) መላው የዓለም አገራት እና ሌሎችም በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ተሳታፊዎች የሚታደሙ ሲሆን፣ ወሳኝ ድርድሮች እና ስምምነቶች የሚደረሱበት ነው።

ኢትዮጵያ ይህንን ጉባኤ ለማዘጋጀት መመረጧ በጉባኤው አጀንዳ ላይ እና በማብቂያው ላይ በሚተላለፉ ውሳኔዎች ላይ ከፍተኛ ሚና እንዲኖራት ያደርጋል።

በብራዚል የኢትዮጵያ አምባሳደር ሉልሰገድ ታደሰ ኢትዮጵያ ጉባኤውን እንድታስተናግድ መመረጧን አስመልክቶ ባሰሙት ንግግር " በኢትዮጵያ ሕዝብ እና መንግሥት ላይ እምነት ስለተጣለ እናመሰግናለን " ብለዋል።

ሰላሳኛው የኮፕ ጉባኤ በብራዚሏ ቤሌም ከተማ ውስጥ እየተካሄደ ሲሆን፣ የቀጣዩን ዓመት ጉባኤ አውስትራሊያ እና ቱርክ ለማስተናገድ እየተፎካከሩ ነው። 31ኛውን የኮፕ ጉባኤ አስተናጋጅ በቀጣዮቹ ቀናት ይታወቃል ተብሎ ይጠበቃል።

አሁን ብራዚል ውስጥ እየተካሄደ በሚገኘው ኮፕ 30 ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ከዓለም ዙሪያ 50 ሺህ በላይ ሰዎች ለመሳተፍ ተመዝግበዋል።

በጉባኤው ላይ፦
- ጋዜጠኞች፣
- የአየር ፀባይ ሳይንቲስቶች፣
- የቀደምት ማኅበረሰብ መሪዎች እና የ195 አገራት ተወካዮችን ጨምሮ ሌሎች በአካባቢ ጥበቃ ላይ ተሳትፎ ያላቸው አካላት ይገኛሉ።

የ2027ቱን ጉባኤ እንድታስተናግድ የተመረጠችው ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የዛፍ ችግኞችን እየተከለች እና ግዙፍ ታዳሽ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫዎችን እየገነባች ነው። በዚህም በአካባቢ ጥበቃ በኩል ስሟ ግሎቶ ይጠቀሳል።

ይህን መረጃ ሮይተርስን ዋቢ በማድረግ ያስነበበው ቢቢሲ ነው።

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
1.63K😡176👏97🙏59🕊25😭25🤔24😢11💔11🥰8😱2
#SafaricomEthiopia

እንኳን ደስ አላችሁ! 🎉💵

ሰኞ ህዳር 1/2018 የ11ኛው ዙር ዕድለኞች ዕጣ አወጣጥ በቲክቶክ እና ፌስቡክ ገፃችን ላይ በቀጥታ ስናስተላልፍ በነበረዉ መሰረት የ100,000 ብር ዕድለኞች ከመቀሌ ሆኑዋል።

ማን ያውቃል ቀጣይ እርስዎ ሊሆኑ ይችላሉ! የበሽ ጥቅል እየገዛን እንንበሽበሽ! 🥳🎉🎉

📲 የM-PESA መተግበሪያን አሁኑኑ ያውርዱ፡ https://onelink.to/ewsb22

የቴሌግራም ቦታችን👉🏽 https://www.tg-me.com/official_safaricomet_bot

ወደ *777*0# ይደውሉ ወይም በM-PESA የበሽ ጥቅል ይግዙ!

#MPESASafaricom
#furtheraheadtogether
#besh
77😡5🙏3😢2😭1
TIKVAH-ETHIOPIA
#ችሎት በእስር ላይ የሚገኙ የቀድሞ ሰላም ሚንስትር ዴኤታ አቶ ታዬ ደንዳአ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረቡ። አቶ ታዬ " ህገወጥ የጦር መሣሪያ መያዝ፤ ጠላትን ማገዝ እና በጉልበት ህገመንግስት ለመናድ ከሚሰሩ ቡድን ጋር መተባበር " በሚሉት ወንጀሎች ነው ተጠርጥረው የታሰሩት ሲሉ የህግ ጥበቃቸው አቶ አበራ ንጉስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል። አቶ ታዬ ዳንዳአ ተጠርጥረው በተከሰሱበት ወንጀል በዋስ መብት ከተለቀቁ…
#ችሎት

የቀድሞው የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ እና የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት አባል አቶ ታዬ ደንደአ በዐቃቤ ሕግ ከቀረቡባቸው ሦስት ክሶች ፍርድ ቤት በሁለቱ በነጻ ሲያሰናብታቸው በአንዱ ግን ጥፋተኛ ተብለዋል።

ዛሬ ማክሰኞ ኅዳር 3/2018 ዓ. ም. የአቶ ታዬን ጉዳይ የተመለከተው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የሕገ መንግሥት እና በሕገ መንግሥት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች ችሎት ከቀረቡለት ሦስት ክሶች የጦር መሣሪያ ሕግን በመተላለፍ በቀረበባቸው ክስ ጥፋተኛ ሆነው እንዳገኛቸው ወስኗል።

አቶ ታዬ ነጻ የተባሉባቸው ክሶች " ከጠላት ጋር ማበር " አና የአገር መከላከያ ሠራዊትን ለመምታት " ዝግጅት አድርገዋል " የሚሉት ሁለት ከባድ ክሶች ናቸው።

የመጀመሪያው ነጻ የተባሉበት ክስ፤ "የወንጀል ሕግ 251 ንዑስ ሐ በመተላለፍ ከጠላት ጋር (ከሸኔ እና ከፋኖ ጋር) ተባብረዋል" የሚል እንደሆነ ጠበቃቸው አበራ ንጉስ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ይህ ክስ ከ20 ዓመት እስከ ዕድሜ ልክ ወይም ሞት የሚያስቀጣ እንደሆነ ጠቅሰዋል።

ሁለተኛው ነጻ የተባሉበት ክስ፤ የወንጀል ሕን 257 ንዑስ ሠ በመተላለፍ " መንግሥትን ለመጣል የፕሮፖጋንዳ እና ሌሎች ድጋፎችን ለጠላቶች በማድረግ ግዙፋዊ መሰናዶ አድርገዋል " የሚለው ከ10 ዓመት በማይበልጥ ጽኑ እስራት የሚያስቀጣ እንደሆነ ገልጸዋል።

ጥፋተኛ ሆነው በተገኙበት ሕገ ወጥ መሣሪያ ይዞ በመገኘት ክስ የግራ ቀኝ የቅጣት አስተያየት ለመስማት ለኅዳር 15/2018 ዓ. ም. ቀጠሮ እንደተሰጠ ጠበቃው ተናግረዋል። #ቢቢሲ

@tikvahethiopia
352🤔62😡25🙏22😢17👏15😭14🕊3
ጂንካ ከተማ የተፈጠረው ምንድነው?

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አሪ ዞን ጂንካ ከተማ ከሰሞኑን ምንነቱ ባልታወቀ ህመም የአምስት ሰዎች ህይወት ማለፉን ተሰምቷል።

ጉዳዩ በጂንካ ከተማ በነዋሪዎች ዘንድ መረበሽ መፍጠሩን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ካነጋገራቸው ነዋሪዎች ተረድቷል።

ቃላቸውን ለቲክቫህ የሰጡ የከተማዋ ነዋሪ "ሰው ተጨንቆ ነው ያለው ሃዘን እንኳን ለመሄድ ፈርቶ የሚቀርም፣በድፍረት የሚሄድም አለ የመረበሽ ስሜት ውስጥ ነው ያለነው"ሲሉ ሁኔታውን ገልጸዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ባሰባሰበው መረጃ ምንነቱ ባልታወቀ ህመም ወደ ጂንካ ሆስፒታል ገብተው የነበሩ ሦስት ሰዎች ውስጥ አንዱ በሆስፒታሉ ህይወቱ ያለፈ ሲሆን ሁለቱ በሪፈር ወደ ሃዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል ሲወሰዱ አንደኛው ታማሚ በመንገድ ላይ ፣አንደኛው ታማሚ ደግሞ ሃዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል ከደረሰ በኋላ ህይወቱ ማለፉን ስሜ አይጠቀስ ካሉ እና በጂንካ ሆስፒታል ከሚሰሩ ሃኪም አረጋግጧል።

በጂንካ ሆስፒታል ተኝተው ይታከሙ ከነበሩ እና ሪፈር ከተደረጉት ታማሚዎች ጋር ግንኙነት የነበራቸው ሃኪም እና ነርስም ህይወታቸው ማለፉን ተገልጿል።

ለጊዜው ምንነቱ ባልታወቀው ህመም በአጠቃላይ የአምስት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ጉዳዩ በጂንካ ከተማ ከፍተኛ ጭንቀት መፍጠሩን ቲክቫህ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ገልጸዋል።

ቲክቫህ ያነጋገራቸው በጂንካ ሆስፒታል የሚሰሩ ሃኪም ምን አሉ?

ታመው የመጡት እና የሞቱት በአንድ ቤተክርስቲያን የሚያገለግሉ እና አብረው ይንቀሳቀሱ የነበሩ ሦስት ሰዎች ናቸው።

በአስር ቀናት ልዩነት ትላንት ከትላንት ወዲያ እና ዛሬን ጨምሮ በአጠቃላይ አምስት ሰዎች ሞተዋል።

ህይወታቸው ካለፈው ውስጥ ሁለቱ ከታማሚዎቹ ጋር ንክኪ የነበራቸው በጂንካ ሆስፒታል ይሰሩ የነበሩ ሃኪም እና ነርስ ናቸው።

ሐኪሙና ነርሱ ካለው የስራ ባህሪ አንፃር ቀጥተኛ ንኪኪ ከሰዎች ጋር ቢኖራቸውም የሕመማቸው ምክንያት ከንኪኪያቸው የተነሳ ነው ብሎ ለማለት ትንሽ የጠለቀ ማጣራት ይጠይቃል።

ለጊዜው ምልክቶቻቸው ተመሳሳይ መሆኑ ብቻ አዲስ ወረርሺኝ ነው ለማለት አያስደፍርም።

ታማሚዎቹ ሲመጡ ያሳዩት የነበረው ምልክት የወባ አይነት ምልክት ነበር ፣አንዳንዶቹ ደም በአፍንጫቸው መምጣት እና ማስቀመጥ ምልክቶች ያሳዩ ነበር።

አንደኛው ጂንካ ሆስፒታል ነው ያረፈው፣ አንደኛው መንገድ ላይ አረፈ አንደኛው ደግሞ ሃዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል እየተረዳ እያለ አርፏል።

የዛሬ ሁለት ሳምንት አካባቢ አንድ ታካሚ ተመሳሳይ ምልክቶችን አሳይቶ አርፎ ነበር ተረስቶ ከቆየ ከአንድ ሳምንት በኋላ ከአረፈው ሰው ጋር ንክኪ የነበራቸው እነዚህ ሰዎች ምልክቱን ማሳየት ጀመሩ።

ሪፈር የተደረጉት ባለፈው ሳምንት አርብ የነበረ ሲሆን አንደኛው ታማሚ በሆስፒታሉ እያለ ሲያርፍ ሁለቱ ሰኞ እና ዛሬ እሮብ ጠዋት ህይወታቸው አልፏል።

የዞኑ ጤና መምሪያ ለጊዜው ምንም ያወጣው ነገር የለም።

ጂንካ ሆስፒታል ውስጥ እንቅስቃሴዎች አሉ ጉዳዩን ለማጣራት ከክልል ከመጡ ሰዎች ጋር እየሰሩ ነው"ብለዋል።

የአሪ ዞን ጤና መምሪያ ምን ምላሽ ሰጠ?

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የአሪ ዞን ጤና መምሪያን በጉዳዩ ላይ አነጋግሮ  " ጉዳዩ በፌደራል ደረጃ ጭምር መግለጫ የሚሰጥበት ስለሆነ ለጊዜው ምንም መረጃ መስጠት አንችልም" የሚል ምላሽ አግኝቷል።

ዞን ጤና መምሪያው "የላብራቶሪ የናሙና ምርመራው ገና አላለቀም ምርመራ ላይ ስለሆነ ሲረጋገጥ በፌደራል ወይም በክልሉ ደረጃ መግለጫ የሚሰጥ ይሆናል" ብሏል።

ጤና መመሪያው ሁሉም መረጃ ሲጠናቀቅ በፌደራል ወይም በክልሉ በኩል ይፋ የደረጋል ከማለት በዘለለ የምርመራ ውጤቱ መቼ እንደሚገለጽ እና ሌሎች በዝርዝር ጉዳዮች ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል።

ቲክቫህ የአሪ ዞን አስተዳዳሪ የሆኑትን አቶ አብርሃም አታን በጉዳዩ ዙሪያ ለማነጋገር ተደጋጋሚ የስልክ ሙከራ ቢያደርግም ስልክ ለማንሳት ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ

@tikvahethiopia
1566😭262🙏33💔27😢23🤔19😱18🕊9😡7🥰5
TIKVAH-ETHIOPIA
ጂንካ ከተማ የተፈጠረው ምንድነው? በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አሪ ዞን ጂንካ ከተማ ከሰሞኑን ምንነቱ ባልታወቀ ህመም የአምስት ሰዎች ህይወት ማለፉን ተሰምቷል። ጉዳዩ በጂንካ ከተማ በነዋሪዎች ዘንድ መረበሽ መፍጠሩን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ካነጋገራቸው ነዋሪዎች ተረድቷል። ቃላቸውን ለቲክቫህ የሰጡ የከተማዋ ነዋሪ "ሰው ተጨንቆ ነው ያለው ሃዘን እንኳን ለመሄድ ፈርቶ የሚቀርም፣በድፍረት የሚሄድም አለ የመረበሽ…
" እስከአሁን ድረስ ስምንት ሰዎች (08) በበሽታው የተጠረጠሩ መሆኑ ታውቋል " - ጤና ሚኒስቴር

የጤና ሚኒስቴር በደቡበ ኢትዮጵያ ክልል በጅንካ ከተማ ምንነቱ በመረጋገጥ ላይ ያለ የሄሞራጂክ ፊቨር (Hemorrhagic Fever) በሽታ መከሰቱን በቅኝት መረጋገጡን ባወጣው መግለጫ ገለጸ።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የተከሰተውን የሄሞራጂክ ፊቨር (Hemorrhagic Fever) በሚመለከት የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ አውጥተዋል።

መግለጫው የተከሰተውን በሽታ " ምንነቱ በመረጋገጥ ላይ ያለ የሄሞራጂክ ፊቨር " ሲል የጠራው ሲሆን እስከአሁን ድረስም ስምንት ሰዎች (08) በበሽታው የተጠረጠሩ መሆኑ አሳውቋል።

ስለ ሞቱ ሰዎች በመግለጫው ያለው ነገር የለም።

የጤና ሚኒሰቴር ከኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና ከክልሉ ጤና ቢሮ ጋር በመሆን በደቡብ ኢትዮጵያ ከልል የተመዘገበውን ይህንን የበሽታ መንስኤ ለማወቅ እና ተጨማሪ ስርጭትን ለመግታት እንዲሁም ለመቆጣጠር ፈጣን ምላሽ ሰጪ ቡድን ወደቦታው በመላክ ፦
° የመስከ ግምገማዎች እና የላብራቶሪ ምርመራዎችን
° የማህበረሰብ ቅኝት
° የንከኪ ልየታ
° የቤት ለቤት ልየታ እንዲሁም የህከምና አገልግሎት አሰጣጥን እያጠናከረ እንደሚገኝ አሳውቋል።

በሚመለከታቸዉ የባለድርሻ አካላትና ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሌላ ተጨማሪ መግለጫ እስከሚሰጥ ድረስ ህብረተሰቡ ህመሙን ለመከላከል የተላለፉ ምክረ ሃሳቦችን እና ጥንቃቄዎችን ተግባራዊ እንዲያደርግ አሳስቧል።

ሚኒስቴሩ ያስተላለፋቸው ምከረ-ሃሳቦች እና ጥንቃቄዎች:-

- በአፍ፣ አፍንጫ እና ሌሎች የሰውነት ክፍሎች የመድማት፣ ትኩሳት፣ ማስቀመጥ እና ማስመለስ ምልከት ሲኖር ወደ ህክምና ተቋማት መሄድና በወቅቱ የላቦራቶሪ ምርመራ ማድረግ፣

- ምልክት ከታየበት ማንኛዉም ሰዉ ጋር ንክኪ በሚኖርበት ጊዜ ራስን የመከላከያ ዘዴዎችን መጠቀም፣

- ሁልጊዜ እጅን በሳኒታይዘር ወይም በውሃና በሳሙና በመታጠብ ማጽዳት፣

ማንኛውም ጤና ተቋም በታካሚዎች ልየታ አካባቢ ልዩ ትኩረት በመስጠት የቫይራል ሄሞሬጅከ ፊቨር (Viral Hemmoragic Fever) መሰል በሸታ መለየት፣ መመርመር፣ ማከም እና ሪፖርት ማድረግ እንደሚያስፈልግ በመግለጫው ጠቅሷል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ

@tikvahethiopia
980😭348🙏127🕊47💔42🤔32😱30😢23😡11🥰10👏4
2025/11/13 02:14:16
Back to Top
HTML Embed Code: