TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia በቤንዚን እና በናፍጣ የሚሰሩ ከባድ ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር እንዳይገቡ ተከልክሏል። በተፈጥሮ ጋዝ የሚሰሩ የጭነትና የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ከጉምሩክ ቀረጥ ነፃ እንዲገቡ መመሪያ ወጥቷል። ይህ መመሪያ ከወጣበት ቀን በፊት በትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር እና በሌሎች ተቋማት ወደ ሀገር እንዲገቡ ከተፈቀደላቸውና በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ ወደ ሀገር ከሚገቡት በስተቀር በቤንዚን…
የቤንዚን ወይም የናፍጣ መኪናን ወደ ጋዝ መቀየር ምን ያህል ያዋጣል ?
የገንዘብ ሚኒስቴር በተፈጥሮ ጋዝ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ከቀረጥ ነጻ ወደ ሀገር እንዲገቡ መፍቀዱ ይታወሳል።
ይህም በሶማሌ ክልል ካሉብ በዓመት 111 ሚሊዮን ሊትር ማምረት የሚችለውን የኦጋዴን ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ ፕሮጀክት የመጀመሪያ ዙር መመረቁ ከተገለፀ ከቀናት በኃላ ነበር።
ለመሆኑ በቤንዚን ወይም ናፍጣ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን የተፈጥሮ ጋዝን ወደሚጠቀሙ መቀየር ይቻላል ?
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያነጋገራቸው ባለሞያዎች “አዎን” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
ሦስተኛ ዲግሪያቸውን በታዳሽና አማራጭ ኃይል የሰሩት ዶ/ር ኃይሉ አበበ ከ20 ዓመት በላይ በአቶሞቲቭ ሥራና ስልጠና ላይ ቆይተዋል።
እንደሳቸው ገለፃ ማንኛውም ተሽከርካሪ የሞተሩ “ጤንነት” ታይቶ ሊቀየር ይችላል ሲሉ ገልፀዋል። ሆኖም ግን ቤንዚን የሚጠቀሙ ተሽከርካሪዎችን ወደ ጋዝ ማሸጋገር ከናፍጣ ይልቅ ቀላል እንደሆነ ያስረዳሉ።
“ከዋጋውም ከምቹነትም አኳያ የቤንዚን መኪናንን መቀየር ነው ብዙ ጊዜ የሚመከረው።” ብለው፤ የናፍጣ ተሽከርካሪን መቀየር ግን በጣም ውስብስብና ከፍ ያለ ዋጋ እንደሚጠይቅ አክለዋል።
የሳሚ አቶሞቲቭ ባለቤት እና የአውቶሞቲቭ ቴክኖሎጂ ባለሙያው ሳሙኤል ደጀኔንም በዚህ ኃሳብ ይስማማሉ።
ሳሙኤል በተፈጥሮ ጋዝ (CNG) የሚሰሩ መኪኖች ከቤንዚንና ከናፍጣ የበለጠ ርካሽ በመሆኑ የነዳጅ ወጪን በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚቆጥቡም ተናግረዋል።
መደበኛ ተሽከርካሪዎችን ወደ ጋዝ መቀየር ምን ያህል ያዋጣል ? ምን ያህል ገንዘብስ ያስፈልጋል ?
መደበኛ ተሽከርካሪዎች የተፈጥሮ ጋዝን መጠቀም እንዲችሉ ሲቀየሩ፤ የነዳጅ ማከማቻው (ስልባቲዮ/ Tanker)፣ የግፊት መቆጣጠሪያና የነዳጅ መርጫ (injector) ይቀየራል። ይህም ተሽከርካሪው ወደ ቤንዝን የሚቀየርበትን ዋጋ ይወስናል።
የአውቶሞቲቪው ባለሙያዊ ሳሙኤል የማስቀየሪያ ወጪ ከፍተኛ መሆን እንደ አንድ ችግር ይቆጥሩታል።
በተጨማሪም ጋዝ በመጠቀሙ ብቻ የመኪናው ጉልበት እሰከ 15 በመቶ ይቀንሳል ይላሉ።
ዶ/ር ኃይሉ የተፈጥሮ ጋዝ ከቤንዝል አንጻር ከ40 እስከ 60 በመቶ ያነሰ ዋጋ እንዳለው ይጠቅሳሉ። ሆኖም ሞተርን ለማንቀሳቀስ ከፍ ያለ ፍጆታ አለው ብለዋል።
“ለምሳሌ አንድ መኪና በአንድ ሊትር ቤንዝን ሁለት ኪሎ ሜትር ይኼዳል ብንል፤ በተፈጥሮ ጋዝ ግን ሁለቱን ኪሎ ሜትር ለመሄድ 1.5 ሊትር ይፈጃል” ሲሉ ገልፀዋል።
ቀጣዩ ጥያቄ የመቀየር ሂደቱ ኪስን ምን ያህል ይፈትሻል? የሚል ነው።
ጋዝ የተለየ ባህሪ ስላለው ከፍ ያለ እና ባለሁለት ሽፋን (layers) ነደጅ መያዣ እንደሚፈልግ ያነሱት ዶ/ር ኃይሉ “ለመቀየር የቤንዚን ከሆነ ከ500 እስከ 1500 የአሜሪካ ዶላር ያስፈልጋል። የናፍጣ ከሆነ ከ3000 ዶላር ይበልጣል” ብለዋል።
ሳሙኤል ደግሞ፣ “ከፍተኛ የመቀየሪያ ወጪ አውጥቶ ጋዝ እንደልብ ማግኘት ካልተቻለ ለተራ ተጠቃሚ አዋጭ አይሆንም። ጠቃሚ የሚሆነው በየቀኑ ብዙ ርቀት ለሚጓዙ እና የጋዝ አቅርቦት በቀላሉ ለሚያገኙ ብቻ ነው” ብለዋል።
በተፈጥሮ ጋዝ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ከተጠቃሚው አንጻር ምን ጉዳት ወይም ጥቅም አላቸው?
የተፈጥሮ ጋዝን የሚጠቀሙ ተሽከርካሪዎች አነስተኛ ተፅዕኖ እንዳላቸው ባለሙያዎቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልፀዋል።
ዋጋው ከቤንዚን እና ነፍጣ ዝቅ ማለቱ ሌላኛው ጥቅሙ ነው።
“ሆኖም፣ በብዙ ቦታዎች የጋዝ መሙያ ጣቢያዎች ውስን መሆን ትልቅ ተግዳሮት ነው። በተጨማሪም ወደ ጋዝ ለመቀየር የሚወጣው ወጪ ከፍተኛ መሆኑ እና በጋዝ በሚሰሩበት ጊዜ የጉልበት መቀነስ መኖሩ ዋና ዋናዎቹ ጉዳቶች ናቸው” ሲሉ ሳሙኤል ይናገራሉ።
ጉልበት የሚቀንስበትን ምክንያት ሲያስረዱ “ጋዙ ራሱ ያለው የኃይል ይዘት (energy density) ዝቅተኛ መሆኑ ነው። በዚህ ምክንያት በተፈጥሮ ጋዝ የሚሰሩ መኪኖች ተመሳሳይ መጠን ካላቸው የቤንዚን ሞተሮች ያነሰ ኃይል አላቸው” ይላሉ።
ዶ/ር ኃይሉ ተሽከርካሪዎች ወደ ጋዝ በሚቀየሩበት ወቅት ከባድና መጠኑ ከፍ ያለ ነዳጅ መያዣ (ሲሊንደር) እንደሚገጠምለት ጠቅሰዋል።
“ታንከሩ፣ ከፍተኛ ግፊት መቋቋም የሚችል ስለሆነ ከፍ ያለ ነው። ስለዚህ ቦታ ይይዝብናል። መኪናችን ላይ እቃ የምናስቀምጥበትን ቦታ ሊወስደው ይቻላል። በተጨማሪም የመኪናውን ክብደት ይጨምርብናል” ሲሉ አስረድተዋል።
ሌላው በጋዝ የሚሠራ መኪና ከመደበኞቹ በተቃራኒ ሞተራቸው ለመነሳት ይዘገያል።
“ የ cold start [በፍጥነት የመነሳት] ችግር ስላለ አንዳንድ ጊዜ በቤንዚን እንዲነሱ ተደርጎ በጋዝ run እንዲያደርጉ (ስራቸውን እንዲቀጥሉ) የሚደረግበት ሁኔታ አለ” ሲሉ ዶ/ር ኃይሉ ገልፀዋል።
ቀድመው የተዘረጉ የነዳጅ ማሰያዎች የተፈጥሮ ጋዝ ሊቀርብባቸው ይችላል?
ባለሙያዎች ለዚህ ጥያቄ ምላሻቸው “አይሆንም” የሚል ነው።
ሳሙኤል “የተፈጥሮ ጋዝ መሙያ ጣቢያዎች የራሳቸው የሆነ ልዩ መሠረተ ልማት ያስፈልጋቸዋል” ብለዋል።
ሆኖም ሥራ ላይ ያሉ ማደያዎች ላይ ከፍተኛ ለውጥ በማድረግ የተፈጥሮ ጋዝን እንዲይዙና እንዲከፋፈልባቸው ማድረግ እንደሚቻል ጠቅሰዋል።
ዶ/ር ኃይሉ፥ የተፈጥሮ ጋዝ ከፍ ያለ ግፊት ስላለው ከፍተኛ የደህንነት ስጋት እንደሚጋርጥ ይናገራሉ። ስለዚህ የተለየ ስርዓት (System) እንደሚፈልጉ አንስተዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia

❤1.89K👏137😡85🙏42😭42🤔31🥰14😱12🕊11
#AmazonFashion
ኳሊቲ አዳዲስ ሙሉ ልብሶች አስገብተናል። ከ10ሺ እስከ 16ሺ የተለያዩ ሱፎች ገብተዋል።ዛሬዉኑ መተዉ የእርሶን ድርሻ ይዉሰዱ።ሱፍ መግዣ ጊዜዉ አሁን ነዉ።ሳይመረጥበት እና ሳያልቅቦት ይምጡ።
ቴሌግራም ቻናላችን ላይ ፎቶዋቸው ተለቀዋል። follow ያድርጉ ከፎቶቹ ላይ ይምረጡ።
በተጨማሪም 100% cotton ሸሚዝ high quality ፤በጅንስም በሱፍም የሚለበስ በ2900 ብር ብቻ፤በ1 ሺ 500ም ኳሊቲ ሸሚዞች አለን፤ አሪፍ ኮቶችንም አስመጥተናል፤ በርካታ አማራጭ ስላለን ለብዛት ፈላጊዎች በብዙ አማራጭ አለን።
👉በተጨማሪም የሙሉ ልብስ ኪራይም በሌላኛው ብራንቻችን አለን።
አድራሻ ፒያሳ downtown ህንፃ ምድር ላይ
☎️0911072936 /0919339250
https://www.tg-me.com/joinchat-AAAAAEc8iQJX1Zjgepjq1w

❤159😡5🙏3😢1😭1
ፓስፖርት !
ሙሀባው የሱፍ የተባሉ ወንድማችን ትላንት ምሽት ቦሌ ኤርፖርት ፓስፖርትዎት ወድቆ ተገኝቷል።
እራሶ መሆንዎን የሚያረጋግጥ ማስረጃ በመላክ ፓስፖርቶን ካገኘው ሰው መውሰድ ይችላሉ።
ካታች ባለው የመልዕክት መቀበያ መልዕክት ያስቀምጡ።
የምታውቋቸው ካላችሁም መልዕክቱን ላኩላቸው።
* አንደኛ ወንድማችን ፓስፖርቱን ተቀብሏል (8:40)
(ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት አዲስ አበባ)

❤332🙏84👏47😡8🤔4😢4😭1
TIKVAH-ETHIOPIA
ቀይ ባህር " የቀይ ባህር ጉዳይ ፦ - ህጋዊ፣ - ታሪካዊ፣ - መልካምድራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥያቄ ነው ብለን እናምናለን። ይሄ ጥያቄ አንዳንዱ ' ነገ ካልተመለሰ ' ይላል አንዳንዱ ' ነገ እኔ ስመጣ ካልጀመርኩት ' ይላል ሁለቱም አያስገልግም። ቀይ ባህርን ኢትዮጵያ ለማጣት 30 ዓመትና ከዚያ በላይ የወሰደ ትግል ነበር ፤ በ30 ዓመት ትግል ውስጥ በብዙዎች ርብርብ ነው ኢትዮጵያ ቀይ ባህርን ያጣችው።…
" ኢትዮጵያ 🇪🇹 የባህር በር ማግኘቷ አይቀርም ! "
ጄነራል ዓለምሸት ደግፌ ፦
" የባህር በር የማግኘት ጉዳይ ጥያቄው ቀርቧል ፤ ተነስቷል። ብዙዎቹ ሀገሮችም አምነውበታል።
አፈጻጸሙ ላይ ችግር ሊኖረው ይችላል ፤ ሊያንገታግተን ይችላል ፤ ጊዜ ሊወስድ ይችላል ግን ኢትዮጵያ የባህር በር የማግኘቷ ጉዳይ የግድ ነው ፤ ማግኘቷም አይቀርም።
ይሄ ትልቅ ህዝብ ፣ ይሄ ትልቅ ሀገር በፍጹም ታፍኖ ሊኖር አይችልም። የባህር በር እናገኛለን ይሄን የምናገኝበት መንገድ በዋናነት በሰላማዊ መንገድ ነው ብለን ነው የምናስበው።
ይሄ ከተረጋገጠ ደግሞ እኛም ባህር ኃይላችንን እዛ ላይ አጠናክረን እናዘጋጃለን። ስለዚህ የባህር ኃይል መደራጀቱ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበር ነው።
የባህር በር ካገኘን በኃላ ' ቀስ ብለን እንደርስበታለን ' የሚባል ጉዳይ አይደለም። እያዘጋጀን እንቆያለን፣ እናሰለጥናለን ፣ ትጥቆቻችንን እናዘጋጃለን የባህር በሩ በተገኘ ሰዓት ኃይላችንን እናሰፍራለን። የራሳችንን ብሔራዊ ጥቅም እናስከብራለን። "

Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤927😡163👏89🤔41🕊25🙏19😭18🥰7😢4
TIKVAH-ETHIOPIA
ሞት ተደርዶባቸዋል ! በምያንማር የወንጀል ካምፕ የሚመራ ቤተሰብ አባላት የሆኑ 11 ሰዎች ሞት ተፈረደባቸው። ' ሚንግ ' የተባለው ቤተሰብ በርካታ አባላት ጥፋተኛ ሆነው ተገኝተዋል። አብዛኞቹም የዓመታት እስራት ተፈርዶባቸዋል። ' ሚንግ ፋሚሊ ' የተባለው ቤተሰብ በምያንማር ራስ ገዝ አስተዳደር ሥር የምትገኘውን ላውካይንግ ከተማ ከሚያስተዳድሩ አራት ጎሳዎች መካከል ይገኝበታል። በቻይና ድንበር ላይ…
#China
የቻይና ፍርድ ቤት ምያንማር ውስጥ የኦንላይን ማጭበርበር ተግባር ላይ ተሰማርተው በነበሩ 5 ዋና የውንብድና ቡድን አባላት ላይ የሞት ፍርድ አስተላለፈ።
ባይ የተባለው ቤተሰብ አባላት እና አጋሮች የሆኑ 21 ሰዎች ፦
- በማጭበርባር፣
- በነፍስ ማጥፋት፣
- በሰዎች ላይ ጉዳት በማድረስ እና በሌሎች ወንጀሎች የጥፋተኝት ውሳኔ ተላልፎባቸዋል።
ይህ ቤተሰብ በእኤአ 2000ዎቹ ላይ ኃይሉ እየጎለበት የመጣ ነው።
በድህነት እና ኋላ ቀርነት ትታወቅ የነበረችውን የምያንማሯን ላውካኢንግ ዞንን ዋነኛ የቁማር እና የወሲብ ንግድ መናኸርያ አድርጓታል።
ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ደግሞ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በሕገ ወጥ መንገድ ከተዘዋወሩ በኋላ በኦንላይን የማጭበርበር ተግባር ላይ እንዲሰማሩ ተገድደዋል።
ቤተሰቡ በዚህ የማጭበርበር ስራ በቢሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር ያገኝ ነበር።
የፍርድ ውሳኔ ከተላለፈባቸው 5 ዋነኛ ሰዎች መካከል የውንብድና ቡድኑ አለቃ ባይ ሱቸንግ እና ልጁ ባይ ዩንግካንግ ይገኙበታል።
ያንግ ሊ ቺያን፣ ሁ ሲያውጃንግ እና ቼን ግዋንዩ ቀሪዎቹ ፍርደኞች ናቸው።
የባይ ቤተሰብ ፦
- የራሱ ታጣቂ ሚሊሻ ያለው።
- ለሳይበር ማጭበርበር ተግባር እና ለቁማር የሚውሉ 41 ካምፖችን ያለው።
- የወንጀሉ እንቅስቃሴ 4.1 ቢሊዮን ዶላር የሚዘዋወርበት እንደሆነም ተገልጿል።
ባለፈው መስከረም ላይ በተመሳሳይ የቻይና ፍርድ ቤት ላውካኢንግ ዞን በዚሁ ተግባር ላይ በተሰማራ ' ሚንግ ' የተባለ ቤተሰብ አባላት ላይ የሞት ፍርድ አስተላልፏል።
መረጃው የቢቢሲ ነው።

❤1.49K👏351🙏72😭56😱36🕊24🥰17😢8😡4
#SafaricomEthiopia
እንኳን ደስ አላችሁ! 🎉💵
ሰኞ ጥቅምት 24/2018 የአስረኛው ዙር ዕድለኞች ዕጣ አወጣጥ በቲክቶክ እና ፌስቡክ ገፃችን ላይ በቀጥታ ስናስተላልፍ በነበረዉ መሰረት የ100,000 ብር ዕድለኛ ከደቡብ ጎንደር ሆኑዋል።
ማን ያውቃል ቀጣይ እርስዎ ሊሆኑ ይችላሉ! የበሽ ጥቅል እየገዛን እንንበሽበሽ! 🥳🎉🎉
📲 የM-PESA መተግበሪያን አሁኑኑ ያውርዱ፡ https://onelink.to/ewsb22
የቴሌግራም ቦታችን👉🏽 https://www.tg-me.com/official_safaricomet_bot
ወደ *777*0# ይደውሉ ወይም በM-PESA የበሽ ጥቅል ይግዙ!
#MPESASafaricom
#furtheraheadtogether
#Besh100Winner

❤61😡4😢3
#WolaitaSodo
የሶስት ዓመት ታዳጊ ላይ የግብረ ስጋ ድፍረት ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ በ17 ዓመት ፅኑ እስራት እንደተቀጠ ተሰምቷል።
በወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ አስተዳደር ድል በጌሬራ ቀበሌ ቆንቶ መንደር አቶ ቴዎድሮስ ያዕቆብ የተባለ ግለሰብ መስከረም 2018 ዓ/ም የ3 ዓመት ህፃን እናቷ ገበያ በሄደችበት የግብረ ስጋ ድፍረት ወንጀል መፈፀሙን የሶዶ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ሀብታሙ አሰፋ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተነግረዋል።
በወቅቱ መረጃው የደረሰው ፖሊስ መረጃ በማሰባሰብ በአጭር ጊዜ ዉስጥ ምርመራ በማጠናቀቅ መዝገቡን ለዐቃቤ ሕግ ማቅረቡን ገልፀዋል።
ዐቃቤ ሕግ አስፈላጊዉን ሂደት በማሟላት ለሶዶ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ማቅረቡንና ፍርድ ቤቱም ራሷን መከላከል በማትችል እና ልዩ ጥበቃና እንክብካቤ በሚያስፈልጋት ህፃን ላይ ይህ አስነዋሪ ድርጊት መፈፀሙን በሰዉና በሕክምና ማስረጃ በማረጋገጥ የጥፋተኝነት ዉሳኔ አስተላልፎበታል።
ፍርድ ቤቱም ዛሬ በ26/02/2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት ግለሰቡ በፖሊስ እጁ ከተያዘበት ቀን ጀምሮ በሚታሰብ በ17 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ዉሳኔ ማስተላለፉንም ኮማንደር ሀብታሙ አሰፋ አስረድተዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

😡737😭180❤140💔62😱18🤔11🥰2😢2🕊1
" ያለኝ ሕይወት የኔ አይደለም። የእግዚአብሔር ነው። የምኖረው እሱ የሰጠኝን ነው !! " - ሌሊሴ ዱጋ
🙏 " የካንሰር አራተኛ ደረጃ ላይ ነው ያለሁት። የሚጎዳኝ ነገር ቢሆንም በፈጣሪ አምናለሁ። ፈጣሪን አስቀድማለሁ። እፀልያለሁ !! "
የኦሮሚያ የቱሪዝም ኮሚሽን ኮሚሽነር ሌሊሴ ዱጋ የካንሰር ሕክምና እየተከታተሉ መሆናቸውን በመግለጽ ፎቷቸውን ጭምር አያይዘው በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ከቀናት በፊት አጋርተው ነበር።
ሌሊሴ ፀጉራቸውን አጥተው ከሚሠሩበት ላፕቶፕ ፊት ለፊት በፈገግታ የተሞላ ፎቶ ግራፋቸውን " እየሠራሁ፣ እየታገልኩ፣ እያሳካሁ " ከሚል የእንግሊዝኛ ጽሑፍ ጋር አጋርተዋል።
ኮሚሽነሯ ይህንን ፎቶ እና መልዕክት ካስተላለፉ በኋላ በርካታ ሰዎች እንዲፈወሱ መልካም ምኞታቸውን በመግለጽ ፎቷቸውን እያጋሩት ነው።
እንዲህ ያለውን የጤና ሁኔታ ለሕዝብ ማጋራት ባልተለመደበት ማኅበረሰብ ውስጥ ኮሚሽነር ሌሊሴ ይህንን ማድረጋቸው በብዙዎች ዘንድ መነጋጋሪያ ከመሆኑ በላይ አድናቆት እንዲቸራቸው አድርጓል።
ሌሊሴ ሕክምና እየተከታተሉ የሚገኙበት በመካከለኛው ምሥራቋ ዮርዳኖስ ውስጥ ነው።
ስላሉበት ሁኔታ ለቢቢሲ አማርኛ ቃላቸውን ሰጥተዋል።
ሌሊሴ ዱጋ ምን አሉ ?
" ሊምፎሚያ በተባለው የካንሰር ዓይነት መያዜን ያወቁት ከአራት ወራት በፊት ለሌላ ምርመራ ወደ ጤና ተቋም በሄድኩበት ወቅት ነው።
ይህ የካንሰር ዓይነት ነጭ የደም ሕዋስን የሚያጠቃ ነው።
የጋስትሮኢንተስታይን ችግር / ሰውነት ምግብ የሚያብላላበት ሆድ ዕቃ ሕመም / መስሎኝ ወደ ሆስፒታል ሄድኩ። ካንሰር እንደሆነ ተነገረኝ።
ቀላል አይደለም። የካንሰር አራተኛ ደረጃ ላይ ነው ያለሁት። የሚጎዳኝ ነገር ቢሆንም በፈጣሪ አምናለሁ። ፈጣሪን አስቀድማለሁ። እፀልያለሁ።
ባለቤቴ፣ ልጆቼ፣ ቤተሰቦቼ እና ጓደኞቼ ከጎኔ ናቸው። ይፀልዩልኛል። ያበረታቱኛል። ሕልም ስላለኝ ብታመምም መኖር፣ መታገል እና ታትሮ መሥራት አላቋርጥም።
አሁን ላይ የኬሞቴራፒ ሕክምና እያገኘው ነው። ብዙ የጎንዮሽ ጉዳት አልደረሰብኝም።
ፀጉሬን አጥቻለሁ። ቆንጆ ፀጉር ነበረኝ። ፀጉር ማጣት ለሴት ልጅ ከባድ ነው። ፀጉርን ማጣት የተለየ ዝግጅት ይጠይቃል።
ፈጣሪ ረድቶኝ ወደ አገሬ ከተመለስኩ ለሕክምና ገንዘብ የሌላቸውን የካንሰር ሕሙማን የሚደግፍ ማዕከል ማቋቋም እፈልጋለሁ።
በባለቤቴ በኩል የተባበሩት መንግሥታት የጤና መድኅን አለኝ፤ መንግሥትም እያሳከመኝ ነው። የገንዘብ ችግር ስለሌለብኝ ነው እየታከምኩ ያለሁት። እርዳታ የሚያሻቸው ብዙ ሰዎች አሉ። ሲሻለኝ እነዚህ ሰዎች ለመርዳት ማዕከል አቋቁማለሁ።
አሁን ላይ ብርታት የሰጠኝ የሕይወት ፍልስፍናዬ ነው።
የሕይወት ፍልስፍናዬ ቀላል ነው። በየቀኑ የምችለውን ማድረግ፣ ዋጋ ያለው ነገር ማድረግ እና ጥሩ መሆን። ፈጣሪ ያስተማረን ይሄንን ነው። ምድር ላይ እስካለን ድረስ ጥሩ ነገር ብናደርግ መልካም ነው።
ያለኝ ሕይወት የኔ አይደለም። የእግዚአብሔር ነው። የምኖረው እሱ የሰጠኝን ነው። ያለ ፀፀት መኖር ነው የምሻው። ለመኖር የሚያበረታኝ እና ወደፊት የምቀጥለው በዚህ ነው።
በየዕለቱ ጥሩ እንዳደረኩ ለራሴ እየነገርኩት ከፈጣሪ ምሕረትን ጠይቄ ነው የምተኛው።
ሕክምናውን ለመጨረስ ከአራት እስከ አምስት ወራት ይወስዳል " ብለዋል።
ሌሊሴ ዱጋ አሁን ላይ ካሉበት ዮርዳኖስ ሆነው ስራቸውን ቀጥለዋል።
ከሚከታተሉት ሕክምናቸው ጎን ለጎን ሥራቸውን የሚያከናውኑበት ቢሮ አላቸው። አንድም ቀን " ታምሜያለሁ " ብለው እያሰቡ እንደማያድሩ ተናግረዋል።
የኦሮሚያ የቱሪዝም ኮሚሽን የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድን እያወጡ ሲሆን በቀጣይ አምስት ዓመታት ምን መሠራት አለበት የሚለውን እየሰሩበት እንዳለ ገልጸዋል።
ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት ነው።
🙏 ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለብርቱዋ ሴት ሌሊሴ ዱጋ ህክምናቸው እንዲሳካ ፤ ሙሉ ጤንነታቸውም እንዲመለስ ዘንድ ይመኛል። ሙሉ ጤንነትን ከረጅም እድሜ ጋር እንመኝላቸዋለን። የሚያምኑት ፈጣሪ ከዚህ በሽታ ይፈውሳቸው ዘንድም እንማጸናለን።

❤3.19K🙏588😢99👏74😭73🥰44🕊30💔17😡14🤔2😱2
#NewsAlert
" ህወሓት የፕሪቶሪያውን ስምምነት በግልጽ አፍርሷል " - የአፋር ክልል መንግስት
" የህወሓት ቡድን በዛሬው ዕለት በአፋር ክልል ወሰን ውስጥ በማግባት 6 መንደሮችን በጉልበት በመቆጣጠር ንጹሃንን በሞርታርና በዙ-23 ደብድቧል " ሲል የአፋር ክልል መንግሥት አስታወቀ።
ክልሉ " ቡድኑ የተለመደውን የሽብር ተግባሩን በግልጽ ጀምሯል " ሲል ከሷል።
" በዛሬው ዕለት ማለትም በቀን 26/02/2018 ዓ/ም የአዛውንቶች የህወሓት ጉጅሌ /ቡድን/ በአፋር ክልል በዞን ሁለት በመጋሌ ወረዳ ቶንሳ ቀበሌ ዋራዓ እና ሚልኪ በሚባሉ ልዩ አካባቢዎች ወሰን ተሻግሮ በመግባት ከምሽቱ አንድ ሰአት አካባቢ በንጹሐን የአፋር አርብቶ-አደሮች ላይ የከባድ መሳሪያ ተኩስ በመክፈት የፕሪቶሪያ ስምምነትን በግጭት አዋጅ በግልጽ አፍርሷል " ሲል አሳውቋል።
" ይህ የህወሓት ጣብ-ጫሪ ቡድን በቶንሳ ቀበሌ ላይ ተኩስ በሚከፈትበት ወቅት ሰላም ወዳድ የአፋር ሽማግሌዎች እንድመለሱ ቢማፀኗቸውም የህወሓት ቡድን ግን አሻፈረኝ በማለት ግጭቱን አስከትሏል " ብሏል።
" ይህ ከትናንት ጥፋቱ የማይማረው ተስፋ ቢሱ የህወሓት ቡድን ከድርጊቱ በአስቸኳይ ካልተቆጠበ የዜጎች ደህንነትና የወሰናችንን ክብር የማስጠበቅ፣ እንዲሁም ራሳችንን ከማንኛውም ውጫዊ ጥቃት የመከላከል ኃላፊነታችን እንደምንወጣ እንገልፃለን " ሲል የአፋር ክልል መንግሥት አስጠንቅቋል።
#Afar #Tigray

😭448❤196🕊62😡37👏32🤔18😢17🙏10🥰5
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#NewsAlert
#Tigray #Afar
" ኃላቀሩ ቡድን የፌደራል መንግስትን ወደ ግጭት ለማስገባት በዓፋር በኩል ትንኮሳዎች ፈፅሟል ይህንንም የአዛዡና ጌታውን ሻዕብያ አጀንዳ ለማስፈፀም የተደረገ ነው " - አቶ ጌታቸው ረዳ
ጥቂት የትግራይ ኃይል አመራሮች በሻዕብያ ትእዛዝ ሰጪነት በፌደራል መንግስት ላይ ትንኮሳ እንደጀመሩና ይህን ትንኮሳ እንዲያቆሙ አቶ ጌታቸው ረዳ አሳሰቡ።
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚንስትር የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚንስትር አቶ ጌታቸው ረዳ ፤ " ፍስሃ ማንጁስና ዮሃንስ መዲድ የተባለችሁ የትግራይ ሰራዊት አመራሮች የጀመራችሁትን የግጭት ቀስቃስ እንቅስቃሴ አቁሙ " ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
ሚንስትሩ " ኃላቀር ቡድን " ሲሉ የጠቀሱት የህወሓት አመራር የፕሪቶሪያ ስምምነት ለመቅደድ ሁሉም ዓይነት ትንኮሳ ቢፈፅምም የፌደራል መንግስት የአፀፋ ምላሽ ከመስጠት ተቆጥቧል ብለዋል።
" ኃላቀር " ያሉት የህወሓት አመራር ቡድን የፌደራል መንግስትን ወደ ግጭት ለማስገባት " በዓፋር በኩል ትንኮሳዎች ፈፅሟል ይህንንም የአዛዡና ጌታውን ሻዕብያ አጀንዳ ለማስፈፀም የተደረገ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።
በዓፋር ክልል በኩል በፌደራል መንግስት ላይ የተደረገው ትንኮሳ " ጀነራል ፍስሃ ማንጁስና ጀነራል ዮሃንስ መዲድ ናቸው የመሩት ማቆም ያለባቸው እነሱ ናቸው " ሲሉ አሳስበዋል።
" ጦር አውርድ በሚል ፀሎት በራስ ህዝብ ላይ መከራና ጭፍጨፋ መጋበዝ ክህደት ነው " ያሉት ሚንስተር ጌታቸው " በትግራይና በዓፋር በኩል ያላችሁት የትግራይ ሰራዊት (TDF ) እና የትግራይ የሰላም ሃይል (TPF) የሻዕብያን ፍላጎት ለማሳካት ወደ እርስ በርስ ግጭት መግባት የለባችሁም " ብለዋል።
" ለትግራይ የሚያስብና እርባና ያለው ሰው ሦስተኛ ዓመቱ ያስቆጠረውን የፕሪቶሪያ ውል ከወዴት ደረሰ ? ብሎ መጠየቅ ብቻ ነው የሚያዋጣው " ሲሉ አቶ ጌታቸው ረዳ ገልጸዋል።
ትላንት ማክሰኞ ጥቅምት 25 /2018 ዓ.ም ከሰዓት በኃላ በትግራይ ኃይሎች እና በትግራይና ዓፋር ክልል አዋሳኝ በሚገኙት ራሳቸውን " የትግራይ የሰላም ኃይል ታጣቂዎች (TPF) " ብለው በሚጠሩት መካካል ግጭት መቀስቀሱ በማህበራዊ የትስስር ገፆች በስፋት ተነግሯል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

3😭299❤268🕊69🤔25😡24👏12😢9🙏5😱3