በባንክ ግሩፕ ከሚቋቋሙ ውጪ ፈቃድ የተሰጠው የመጀመሪያው የኢንቨስትመንት ባንክ መቋቋሙ ይፋ ተደርጓል።
የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን በመጋቢት ወር 2017 ዓ.ም በሶስት የአገልግሎት ዘርፎች ለሚንቀሳቀሱ ተቋማት ማለትም ለሁለት የኢንቨስትመንት ባንኮች(የኢትዮጵያ ንግድ ባንክና ወጋገን ባንክ) ፣ለአንድ የሰነደ ሙዓለ ገበያ አከናዋኝ እና ለሁለት የኢንቨስትመንት አማካሪ ኩባንያዎች ፈቃድ መስጠቱን መገለጹ ይታወቃል።
ባለስልጣኑ ለመጀመሪያዎቹ ሁለት የኢንቨስትመንት ባንኮች ፈቃድ ከሰጠበት መጋቢት 12/2017 ዓም በኋላ ሦስተኛው የኢንቨስትመንት ባንክ የሆነው "ፈርስት አዲስ" ኢንቨስትመንት ባንክ ከካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ፈቃድ ተቀብሎ ሌሎች የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪዎችን መቀላቀሉን ባንኩ ይፋ አድርጓል።
ፈርስት አዲስ ኢንቨስትመንት ባንክ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ከባንክ ግሩፕ ከሚቋቋሙ ውጪ ፈቃድ የተሰጠው የመጀመሪያው ኢንዲፔንደንት የኢንቨስትመንት ባንክ መሆኑን ይፋ በማድረጊያ ስነ ስርአቱ ወቅት አሳውቋል።
በ 28 ሚሊየን ብር ካፒታል የተመሰረተው ባንኩ የመጀመሪያው ኢንዲፔንደንት ኢንቨስትመንት ባንከ በመሆን ፈቃዱን ከኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን የተቀበለው ጥቅምት 20,2018 ዓ.ም ነው።
ባንኩ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች :-
° የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ለገበያ እንደ አዲስ በሚወጡበት ወቅት ማማከር
° የተቋማትን ውሕደት እና ግዢ ማማከር
° ወደ ግል ይዞታ ማዞር
° የኢንቨስትመንት እና የኩባንያ ጥናት፣
° የኩባንያ እና የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ግመታ፣
° አዲስ ካፒታል ማፈላለግ እና ማማከር ፣
° የንግድ እና የልማት ካፒታልን በማዋሃድ በተመጣጣኝ ዋጋ ማሰባሰብ ለተገቢው ዓላማ ማዋል
° ሌሎች በመመሪያዉ መሰረት የተፈቀዱ ተመሳሳይ አገልግሎቶችን እንደሚሰጥ አሳውቋል።
በአሁኑ ሰአት በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን መመሪያ መሰረት ወደ አክሲዮን ምዝገባ ስራ መግባት ያለባቸውን የአክሲዮን ኩባንያዎችን የአክሲዮን ምዝገባ ስራ የማማከር አገልግሎት በመስጠት ላይ እንደሚገኝ ባንኩ ገልጿል።
የኢንቨስትመንት ባንኩ ከሌላ የባንኪንግ ግሩፕ ውጪ ገለልተኛ በሆነ አደረጃጀት የተቋቋመ መሆኑ ቀዳሚ ያደርገዋል ነው የተባለው።
የባንኩ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሚካኤል አዲሱ
"በቀጣይነትም ተጨማሪ መሟላት ያለባቸውን መስፈርቶችን ማሟላት በቅርቡ ወደ የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ (ESX) አገበያይ አባል (Trading Member) በመሆን ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ለማገበያየት እቅድ ይዞ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል" ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
@tikvahethiopia

❤316👏19🙏5💔5😭2😡2😢1🕊1
  
  TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ ምን አለ ?
" በጥቅምት ወር 2018 ዓ.ም. ብቻ 25 ኦርቶዶክሳውያን ወገኖቻችን አገራችንና ምድራችን ብለው በሰላም በተኙበት በድንገት ማንነታቸው ባልታወቀ ታጣቂዎች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል " - ቋሚ ሲኖዶስ
ቋሚ ሲኖዶስ ፥ " በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በምሥራቅ አርሲ ዞን አስተዳደር ፦
- በጉና፣
- በመርቲ፤
- በሸርካ እና በሆሎንቆ ዋቢ ወረዳዎች ውስጥ በሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች ላይ ጥቅምት 14 ለ15 ቀን 2018 ዓ.ም. በጉናና መርቲ ወረዳዎች 17 ክርስቲያኖች፣ ጥቅምት 17 ለ18 ቀን 2018 ዓ.ም. በሸርካ ወረዳ 3 ክርስቲያኖች እንዲሁም ጥቅምት 18 ለ19 ቀን 2018 ዓ.ም. በሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ 5 ክርስቲያኖች በድምሩ በጥቅምት ወር 2018 ዓ.ም. ብቻ 25 ኦርቶዶክሳውያን ወገኖቻችን አገራችንና ምድራችን ብለው በሰላም በተኙበት በድንገት ማንነታቸው ባልታወቀ ታጣቂዎች በአሰቃቂ ሁኔታ እንደተገደሉና ግድያውም ከዕለት ወደ ዕለት እየተባባሰ መሆኑን የምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት የላከውን ሪፖርት ቋሚ ሲኖዶሱ የተመለከተው በከባድና ጥልቅ የኃዘን ስሜት ነው " ብሏል።
በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት እንዲህ ዓይነቱ አሰቃቂ ድርጊት ሲፈጸም የቆየው በተደጋጋሚ እንደሆነ የገለጸው ቋሚ ሲኖዶድ " እንዲህ ዓይነቱ አስነዋሪ ድርጊት በቅዱሳት መጻሕፍት ሆነ በሰው ልጅ ሰብዓዊ መብት ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው፣ በነጻነት የማምለክ ሕገ መንግሥታዊ መብትን የሚጋፋ፣ ተከባብሮና ተቻችሎ የመኖር መንፈሳዊ ዕሴቶቻችንን የሚያጠፋ፣ ክብረ ነክና ሊወገዝ የሚገባው ኢ-ስነምግባራዊ ድርጊት በመሆኑ በጽኑ እናወግዛለን " ሲል ገልጿል።
ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸው መንግሥታዊ አካላትም ይህን ኢ-ሰብዓዊ የሆነ ተግባር በጽኑ በማውገዝና በሕገ መንግሥቱ የተረጋገጠውን በሕይወት የመኖርና የእምነት ነጻነት መብትን እንዲያስከብሩ ይህን አስነዋሪ ድርጊት የፈጸሙትን ሕገ ወጥ ግለሰቦች ለሕግ በማቅረብ የሕግ የበላይነትን ከማረጋገጥ በተጨማሪም በቀጣይ እንዲህ ዓይነቱ ሕገ ወጥ ተግባር እንዳይደገም አስፈላጊውን የሕግ ከለላ በመስጠት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ቋሚ ሲኖዶስ አሳስቧል።
#EOTC

1😭2.3K❤524😡117💔88🕊70😢46👏30🤔16🙏14
  
  TIKVAH-ETHIOPIA
#ሀዋሳ  " ባልተገባ መልኩ ተይዘዋል " ያላቸውን የመንግሥት ቤቶች በማስለቀቅ ለከተማ ነዋሪዎች ማስተላለፍ ጀምራለሁ ሲል የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር አሳወቀ።  ከተማ አስተዳደሩ ይህን ያለው በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጹ ነው።  የግል ቤት ኖሯቸው በመንግሥት ቤት ውስጥ የሚኖሩትን በማስለቀቅ ለሚገባቸው የከተማው ነዋሪዎች አስረክባለሁ ብሏል።  በቅርቡ የተሾሙት አዲስ ከንቲባ አቶ ተክሌ ጆምባ " በተለያዩ…
#Hawassa
ከነበሩበት የቀበሌ ቤቶች ያለምንም ህጋዊ አሰራር እንዲወጡ የተደረጉ ግለሰቦችን ወደ ቀድሞ ቤታቸው የማስመለስ ስራ እየሰራ መሆኑን የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር አሳውቋል።
ዛሬ በሀዋሳ ከተማ ከቀበሌ መኖሪያ ቤታቸው የወጡ ግለሰቦችን የማሰሰመለሱ ስራ መጀመሩን በቅርቡ የተሾሙት የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ተክሌ ጆንባ ገልጸዋል።
ዜጎች ከቤታቸው እንዲወጡ የተደረገበት ተግባር " ህጋዊ አሰራርን ያልተከተለና የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ነው " ያሉት ከንቲባው ከቤታቸው የተፈናቀሉ ግለሰቦችን የማስመለሱን ስራ ጀምረናል ብለዋል።
ዜጎችን ከቤታቸው የማፈናቀል ተግባር በማን እና እንዴት እንደተከናወነ ለዚህም ህገወጥ ድርጊት በህግ የሚጠየቅ አካል ስለመኖሩ የተባለ ነገር የለም።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ

❤551👏137🙏24🥰14😭9🤔8🕊6😢2
  
  TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
የኢትዮጵያውያን ድምጽ ከማይናማር📢
" BGF ውስጥ የምንገኝ ኢትዮጵያውያን ነን።
ከዚህ ቦታ መውጣት የምንችለው በኢትዮጵያ ኤምባሲዎች አማካኝነት ብቻ ነው። ከዛ ውጭ መውጣት አንችልም።
ያለንበት ሁኔታ እጅግ በጣም ከባድ ነው። ብዙ ሰዎች በትንሽ ቦታ ተጨናንቀን ነው ያለነው።
ከቻይናዎች ፣ ከህንዶች፣ ከፓኪስታኖች ... እና የሌሎች ሀገራት ሰዎች ጋር ነው አብረን ያለነው።
ፎርም ሞልተናል፣ አስፈላጊውን ዶክመት ጨርሰናል። እነሱ ያሉን ' የኢትዮጵያ ኤምባሲ ነው የሚወስዳችሁ ' ነው ግን እስካሁን ምንም አልሰማንም ማንም ያናግረን አካል የለም። እኛም ማንን ማናገር እንዳለብን አላወቅንም።
ይህ መልዕክት በአካባቢው ወዳሉት የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች ይደረስልን። እኛ ያለንበት ቦታ ብቻ 31 ኢትዮጵያውያን አለን። ሌሎች ቦታዎች እንዲሁም ተሻግረው ታይላድ ገብተው መጠለያ ውስጥ ያሉ ብዙ ኢትዮጵያ አሉ። " - ኢትዮጵያውያን ከማይናማር
በማይናማር በተለይ ጋንጎች በሚቆጣጠሯቸው ካምፖች ላይ የማይናማር ጦር ከሰሞኑን ሰፊ ዘመቻ እያካሄደ ነው። ይህ ተከትሎ አካባቢው እንደ ከዚህ ቀደሙ የተረጋገ አይደለም። በርካቶች በማይናማር ጦር የተያዙ ሲሆን በርካቶችም ከአካባቢው ለመውጣት ጥረት ላይ ናቸው።
ቪድዮ ፦ BGF ውስጥ ኢትዮጵያውያንና የሌሎች ሀገራት ዜጎች ያሉበት ሁኔታ
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
#TikvahEthiopiaFamily

❤265😢169😭61💔22🙏17🕊10🤔7🥰4👏2😱2
  
  TIKVAH-ETHIOPIA
ኤርትራ እና ግብፅ  የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለ5 ቀን የስራ ጉብኝት ትላንት ለሊት ግብፅ መሄዳቸውን የሀገሪቱ የማስታወቂያ ሚኒስቴር አሳውቋል።  ኢሳያስን " ኑ " ብለው ግብዣ ያደረጉላቸው የግብፅ ፕሬዚዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ ናቸው።  በ5 ቀን ቆይታቸው በሁለትዮሽ፣ በቀጠናዊ እና ዓላም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ተብሏል።  የኤርትራው ፕሬዚዳንት ከዚህ ቀደም (ከወራቶች በፊት) ወደ…
" አይዟችሁ እኔ አለሁላችሁ " ባይዋ ግብፅ !
የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በግብፁ ፕሬዜዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ ግብዣ ለ5 ቀን ግብፅ፣ ካይሮ ናቸው።
ሁለቱ ፕሬዚዳንቶች ውይይት ባደረጉበት ወቅት የግብፁ መሪ " ለሉዓላዊነታችሁ እና ለግዛታዊ አንድነታችሁ ድጋፍ ለማድረግ ቁርጠኛ ነን " ሲሉ ለኢሳያስ ነግረዋቸዋል።
ከዚህ ቀደም ጎረቤት ሀገር ሶማሊያ ከኢትዮጵያ ጋር አለመግባባት በፈጠረችበት ወቅት እኚሁ የግብፅ ፕሬዚዳንት " አይዟችሁ ፤ ለሱማሊያ ሉዓላዊነት እንዲሁም የግዛት አንድነት እኛ ድጋፍ እናደርጋለን በማንኛውም መንገድ " ሲሉ ነበር የከረሙት።

😡489❤224🤔41👏39🕊26😱17😭11🙏8💔6😢4
  
  TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update #EOTC
ከኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ፤ " በአንጋፋዋ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካህናት እና ምዕመናን ላይ ግድያ እና ስቃይ መፈጸሙን የሰማነው በታላቅ ድንጋጤና ሀዘን ነው " አለ።
መሰል ተግባራት በተለያዩ ወቅቶች ሲፈጸም እንደነበር አስታውሷል።
ጉባኤው የቤተክርስቲያኗን " የዛሬውን የሀዘን መግለጫ ተመልክቻለሁ " ብሏል።
" በኦሮሚያ ክልል በአርሲ ዞን ፦
- በጉና፣
- በመርቲ፣
- በሸርካ
- በሆሎንቆ ዋቢ ወረዳዎች በአንጋፋዋ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች እና ካህናት ላይ እየደረሰ ያለው ግድያ እና ስቃይ ከዕለት ዕለት እየጨመረ መምጣቱን ተረድተናል " ሲል አመልክቷል።
ይህን ግድያና እንግልት የፈጸሙት አካላት ማንነታቸው ያልታወቀ ታጣቂዎች እንደሆኑ መረዳት እንደቻለ ተናግሯል።
ጉባኤው በተፈጸመው አሰቃቂ ግድያ የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን ለቤተ ክርስቲያኒቱ አባቶች እና መሪዎች በተለይም ለተጎጂ ቤተሰቦች ገልጿል።
መንግሥት የዜጎችን በሰላም ወጥቶ የመግባት ነፃነት የማረጋገጥ ዋንኛ ኃላፊነት ያለበት በመሆኑ ችግሩ ከዚህ በላይ ተባብሶ ተጫማሪ ሀዘን እና ሰቆቃ ከመከሰቱ አስቀድሞ አስፈላጊውን የሕግ ማስከበር ሥራ እንዲሠራ ጉባኤው በአጽንኦት አሳስቧል።
ሁሉም የሃይማኖት ተቋማት እና ሕብረተሰብ ይህን እጅግ የከፋ የጭካኔ ተግባር በአንድ ድምጽ በግልጽ ማውገዝ እና ከሕግ አካላት ጋር በመተባበር ወንጀለኞችን ለፍርድ እንዲቀርቡ የበኩሉን ሚና እንዲወጣ አደራ ብሏል።
በተያያዘ መረጃ የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በምዕመኖቿ ላይ በምስራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት የተፈጸመውን ግድያ " ኢሰብዓዊ ድርጊት " ሲል ገልጾ በጽኑ አውግዟል።

1😭277❤128🕊26😡21👏10💔8🥰2
  
  TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ቀይ ባህር 
" የቀይ ባህር ጉዳይ ፦
- ህጋዊ፣
- ታሪካዊ፣
- መልካምድራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥያቄ ነው ብለን እናምናለን።
ይሄ ጥያቄ አንዳንዱ ' ነገ ካልተመለሰ ' ይላል አንዳንዱ ' ነገ እኔ ስመጣ ካልጀመርኩት ' ይላል ሁለቱም አያስገልግም።
ቀይ ባህርን ኢትዮጵያ ለማጣት 30 ዓመትና ከዚያ በላይ የወሰደ ትግል ነበር ፤ በ30 ዓመት ትግል ውስጥ በብዙዎች ርብርብ ነው ኢትዮጵያ ቀይ ባህርን ያጣችው።
በተረጋጋ መንገድ፣ በሰከነ መንገድ ፣ በውይይት መሄድ አስፈላጊ ነው (ለማግኘት)። የፈለገ ብንወያይ ግን ለማጣት የፈጀብንን 30 ዓመት ለማግኘት ይፈጅብናል ብዬ ግን አላስብም። ግዜው ግን በቂ ስለሆነ በተረጋጋ መንገድ ማየት ያስፈልጋል።
የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያየው የምፈልገው ነገር ... አንዳንዱ ዛሬን ብቻ ስለሚያስብ ዳራውን ልስጥ።
በመጀመሪያ ኢትዮጵያን የቀይ ባህርን ያሳጣትን ውሳኔ ማን ወሰነው ? ካቢኔው ይሆናል ብለን የካቢኔ ዶክመንት ብናገላብጥ የለም። ካቢኔ አያውቀውም። አይ ምክር ቤት ይሆናል የወሰነው ብለን ብናስብ ምክር ቤቱም አልነበረ ምክር ቤት አያውቀውም ውሳኔውን። የለም የኢትዮጵያ ህዝብ በሪፈረንደም ወስኖ እንዳይሆን እንዳይባል ነበርን እኛም ያኔ።
የኢትዮጵያ ህዝብ ያልወሰነው ፤ ተወካዮቹ ያላዩት ፤ ቢያንስ ቢያስ ከአስፈጻሚ ካቢኔ ያላየውን ውሳኔ ማን ወሰነው ? ማጣትን የሚያክል ነገር ያጣንበት መንገድ ህጋዊነት ችግር እንዳለበት ማሳያው ተቋሞች አልገቡበትም። ካቢኔ አያውቀውም። አንድ ገጽ ወረቀት ማግኘት አልቻልንም እንዴት እንዳጣነው የሚያስረዳ።
ህዝብ ማያውቀው፣ ፓርላማ የማያውቀው ፣ ካቢኔ የማያውቀው የኢትዮጵያ የባህር በር የሚያሳጣ ውሳኔ የወሰነው ማነው የሚል ጥያቄ ማንሳት እንዴት ስህተት ሊሆን ይችላል ? ካለ ይነገረን። ከሌለ ግን ይሄ ጉዳይ ይሄን ውሃ አንስቶ እንደመድፋት አይደለም የህልውና ጉዳይ ነው። ማን ወሰነው? ይሄ ነው ጥያቄው። " - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
#Ethiopia🇪🇹 

#Ethiopia
@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
    VIEW IN TELEGRAM
  ❤583😡58🙏36🕊17🤔11🥰6👏5💔5😭5