TIKVAH-ETHIOPIA
የእዳ ሽግሽግን በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምን አሉ ? " ኢትዮጵያ አሁን ላይ እዳዋን ለመክፈል ምንም ችግር የለባትም " ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ። " በሪፎርሙ አመካኝነት ከ4 እስከ 4 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር የሚደርስ የእዳ ሽግሽግ ተደርጓል " ያሉ ሲሆን " ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ መንግስት አንድም ዶላር የንግድ ብድር አልወሰደም። ይህ ደግሞ እዳን ለመቆጣጠር ያለንን…
" የዋጋ ንረትን ወደ አንድ አሃዝ ለማውረድ እንሰራለን " - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ስለ ዋጋ ንረት ምን አሉ ?
መንግስት የዋጋ ንረቱን ለማረጋጋት 440 ቢሊዮን ብር ድጎማ እንዳደረገ ከዚህም ውስጥ 160 ቢሊዮን ብር የሚሆነው ለደሞዝ ጭማሪ ድጎማ የተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
ለነዳጅ 140 ቢሊዮን ድጎማ መደረጉንም ገልጸዋል።
በዚህም የጥቅምት ወር የዋጋ ንረት ወደ 11 ነጥብ 7 እንደወረደ ይህም ከሪፎርሙ ዘመን ጀምሮ ትንሹ የዋጋ ንረት ሆኖ መመዝገቡን ተናግረዋል።
" በቀጣይ ይህን አሃዝ ወደ አንድ አሃዝ ለማውረድ ይሰራል " ብለዋል።
#PMOEthiopia
@tikvahethiopia

4😡1.01K❤565😭76🙏50👏40🤔37🕊8🥰5😢5
TIKVAH-ETHIOPIA
የእዳ ሽግሽግን በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምን አሉ ? " ኢትዮጵያ አሁን ላይ እዳዋን ለመክፈል ምንም ችግር የለባትም " ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ። " በሪፎርሙ አመካኝነት ከ4 እስከ 4 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር የሚደርስ የእዳ ሽግሽግ ተደርጓል " ያሉ ሲሆን " ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ መንግስት አንድም ዶላር የንግድ ብድር አልወሰደም። ይህ ደግሞ እዳን ለመቆጣጠር ያለንን…
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ ስላለባት እዳ ምን አሉ ?
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ፦
" ' ኢትዮጵያ በከፍተኛ እዳ ውስጥ ትገኛለች ' የተባለው እውነት ነው ፤ ግን በንጽጽር እና በቁጥር ማየት ተገቢ ነው።
አፍሪካ ውስጥ አንደኛ ፣ ሁለተኛ ፣ ሶስተኛ የሚባሉ ኢኮኖሚዎች ከኢትዮጵያ በብዙ እጥፍ እዳ አለባቸው። አንዱ ሀገር 300 ቢሊዮን ብር እዳ አለበት፣ ሁለተኛው 177 ቢሊዮን ብር እዳ አለበት፣ እዚሁ እኛ አካባቢ ያሉ ሀገራት እንኳን ከ78 ቢሊዮን ዶላር በላይ እዳ አለባቸው፤ የኛ እዳ ከ23 ቢሊዮን ዶላር አይበልጥም።
በንፅፅር ሲታይ ያን ያህል አስደንጋጭ ባይሆንም የኛ መጥፎ የሆነው ብድር የወሰድንበት መንገድ ነው። አብዛኛው ብድር የንግድ (ኮሜርሻል) ብድር ነው።
የንግድ (ኮሜርሻል) ብድር ማለት በአጭር ጊዜ ብዙ መክፈል የሚጠይቅ የብድር ስርዓት ስለሆነ የኛ ጥያቄ የነበረው ያንን የብድር ሁኔታ መሸጋሸግ አለበት ነው። እንደተባለው ለG20 ሀገራት ኮመን ፍሬምዎርክ የሚባለው ድርድር ሲካሄድ የቆየው ኢትዮጵያ የወሰደችው ኮሜርሻል ብድር ወደ ኮንሴሽናል ብድር (ስስ ፣ የረጅም የብድር መክፈያ ጊዜ ያለው) መቀየር አለበት የሚል ነው። በዚህ በሪፎርሙ ምክንያት ከ4 እስከ 4.5 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ የእዳ ሽግሽግ ተደርጓል ይህ ታላቅ ድል ነው የሪፎርሙ ውጤት ነው።
ኢትዮጵያ አሁን እዳ ለመክፈል ምንም አይነት ችግር የለባትም። ከሪፎርም በፊት እንቸገራለን በዚህ የሚቀጥል ከሆነ የሚል ስጋት ነበረን የተሳካ ድርድር ስላካሄድን አሁን እዳችንን ለማስተዳደር ችግር የለብንም።
ዩሮ ቦንድን በሚመለከት ሌሎች (አበዳሪዎች) የኮመን ፍሬምዎርክ ተቀብለው ሲስማሙ ዩሮ ቦንድ ያበደሩ አካላት ግን ' የኢትዮጵያ ኤክስፖርት በከፍተኛ ደረጃ እያደገ ስለሆነ ኢኮኖሚያችሁ እያደገ ስለሆነ በዛ ፍሬምዎርክ መታቀፍ አንፈልግም ' ሚል ሃሳብ ነው ያነሱት። እድገታችንን አጋነው ለማየት ' መክፈል ስለምትችሉ በነበረው መንገድ መቀጠል አለበት ' ነው ያሉት። በዚህ ላይ ድርድር እያካሄድን ነው።
የኛ ጥያቄ ሁሉም ብድሮች በኮመን ፍሬምዎርክ ማዕቀፍ ውስጥ ገብተው ሽግሽግ ይደረግላቸው ነው። ለዛም ነው ከ4 እስከ 4.5 ቢሊዮን የምለው 4 የተረጋገጠ ቢሆንም ቀሪ ድርድሮች ስላሉ ከፊሉ መረጋገጥ ይፈልጋል።
የለውጡ መንግሥት ባለፉት 7+ አመታት አንድም ዶላር በንግድ ብድር (ኮሜርሻል ብድር) አልተበደርንም። የፀና አቋም ስላለን የኢትዮጵያ እዳ መስተካከል ስላለበት የኢትዮጵያ አቅም መውጣት ስላለበትና ለእዳ ካለን ግምት አንጻር ነው አንድም ዶላር ኮሜርሻል ብድር ሳንወስድ በሜጋ ፕሮጀክቶች ስኬት ልናመጣ የቻልነው። "
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ

❤1.34K😡529😭66🙏48🤔30😱21🕊19👏14💔13😢9🥰1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለ ባህር በር ጉዳይ ምን አሉ ?
" ሚሊዮን ፐርሰት እርግጠኛ ነኝ ኢትዮጵያ🇪🇹 ተዘግታ አትኖርም አትኖርም ፤ ማንም ፈለገም አልፈለገም፤ ተዘግታ አትኖርም " - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
@tikvahethiopia
" ሚሊዮን ፐርሰት እርግጠኛ ነኝ ኢትዮጵያ
@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤2.27K🤔258👏198😡158😭99🙏75🕊33🥰22😱22💔12😢11
TIKVAH-ETHIOPIA
#HoPR🇪🇹 " ሁላችንም ካለፈው ጥፋቶቻችን ለምን አንማርም ? እንደ ሀገር ስንት ትውልድ በጦርነት እየበላን እንቀጥላለን ? " - ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) የምክር ቤት አባሉና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ተወካዩ ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) ከፀጥታ፣ ከኑሮ ውድነት ፣ ከኢኮኖሚ እንዲሁም ከባህር በር ጋር የተያያዘ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥያቄ አቅርበዋል። - " ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር እንደ ፀጥታ ኃይሎች…
ኢትዮጵያ እና አሰብ ወደብ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ፦
" በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል ሰላም ሲፈጠር መጀመሪያ እኔ ወደ አስመራ ተጉዤ በኃላ የኤርትራው ፕሬዚዳንት ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ የመጀመሪያውን መድረክ ያደረግነው ሚሊኒየም አዳራሽ ነው። ብዙ ህዝብ ባለበት በቀጥታ ስርጭት። ካልሰማችሁ አሁን ዩትዩብ ላይ ግቡና ስሙት። የመጀመሪያው ስብሰባ #አሰብ ነው የሚለው እሳቸው ባሉበት። ለህዝብ በሚገባው ልክ።
ኤርትራ ስመላለስ አስመራን ካየው በኋላ ከክቡር ፕሬዚዳንቱ ጋራ አሰብ መሄድ እፈልጋለሁ ብዬ አሰብ ሄጄ ባህሩ ጋር ቆመን ያወራነው ነገር ምንድነው ስለ ወደብ ነው። ተማሳችሁ እዩ። የት ? ኤርትራ ምድር ውስጥ።
የመደመር ትውልድ መፅሀፍ ውስጥ በግልጽ ጂዮ ፖለቲክስን አስፍሬ የአሰብ ጉዳይን አስቀምጬ ለኤርትራ ባለስልጣናት በስጦታ ልኬላቸዋለሁ ሚስጥር አይደለም። ያቁታል። ከሁሉም ሌኬላቸዋለሁ።
የዛሬ 6 አመት 5 አመት ባህር ኃይል አቋቁመናል እና እዚህ ውስጥ (የብርጭቆ ውሃ ውስጥ) ልንዋኝ ነው ባህር ኃይል ያቋቋምነው ? ለምን ሰዎች ይሄን ደምረው ማየት እንደሚቸገሩ አይገበኝም።
ኢትዮጵያ ቀይ ባህር እንደሚያስፈልጋት ከለውጡ በፊት እናምን ነበር እንናገር ነበር ያኔ መደመጥ አንችልም ከጀመርንበት ቀን አስቶ ንግግሩ አለ። ያ ንግግር ግን ሰላማዊ መሆን አለበት።
የተከበሩ (ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔን ነው) እንዳነሱት ከኤርትራ መንግሥት ጋር ተስማምተን ከዚህ ወደ አሰብ የሚወስደውን መንገድ ጠግነናል እኮ እኛ። እንከፍታለን ብለን ጠግነናል ከጠገንን በኃላ ' ችግር አለብን ፖርቱ ተዳክሟል ' አሉን። አንዳንድ ሰው ፀቡ በአንድ ምሽት የመጣ ይመስለዋል እንደዛ አይደለም ታሪኩ ስለማንናገር ነው።
ወደ አሰብ መንገድ ጠግነን ከጨረስን በኃላ ' ፖርቱ ችግር አለበት ' ሲሉ የጋራ ወዳጅ የሆነ ሀገር ለምንነን ጀነሬተር እና ክሬን በእርዳታ ወደ ኤርትራ እንዲመጣ አድርገን አሰብ ወደብ ሲደርስ የኤርትራ መንግስት ' አልፈልግም ' ብሎ መለሰ። ያኔ ነው የገባን ይሄ ነገር ተስፋ የለውም የሚለው።
መንገድ ጠገንን፣ ለምንነን ብናመጣም ፍላጎት አልነበረም። ወደ ኤርትራ ልክ እንደ ሱዳን ፣ ልክ እንደ ጅቡቲ በኛ ወጪ የኤሌክትሪክ ኃይል ቀጥለን ኃይል እንስጣችሁ ጀነሬተር አትጠቀሙ ብንልም ' ቆይ እናስብበት ' ነው የተባለው።
ኢትዮጵያ ውስጥ የቤት ችግር አለ ፤ 1.5 ቤት እንገነባለም ብለናል። አሰብ ስሄድ ቤት አለ በር አለ ሰው የለም፤ ይሄ እውነተኛ ታሪክ ነው። ይሄን ከተማ መልሰን ህይወት እንስጠው ስራ ነው ህይወት የሚያመጣለት የሚል በየጊዜው ተነጋግረናል። ሁሉም የሚሄድ ልዑክ ተነጋግሮበታል።
በኤርትራ በኩል በግልጽ ባላወቅነው መንገድ ለዚያ ጉዳይ ምላሽ ለመስጠት ብዙ ዝግጁ አልነበሩም። እሱ ቀርቶ የከፈትናቸውን ድንበሮች በሰሜን በኩል ወዲያው ወዲያው ተዘጉ። የተዘጉት አሁን አይደለም እናተ ችግር እንዳለ ሳትሰሙ ነው የተዘጉት።
እና የኤርትራ ህዝብ አሁንም ወንድም ህዝብ ነው ፤ ምስኪን ህዝብ ነው ፤ ሀገሩን ለቆ እየተሰደደ ያለ ህዝብ ነው ከዚህ ህዝብ ጋር መስራት መተባበር ፍላጎታችን ነው በፍጹም የውጊያ መሻት የለንም። በህጋዊ መንገድ እና በንግግር ሊፈታ ይችላል።
ለብዙ ሀገራት በተናጠል ተናግሪያለሁ። ምክር ቤት መስማት ከፈለገ ግን ፦
- ለአሜሪካ
- ለቻይና
- ለራሽያ
- ለአውሮፓ
- ለአፍሪካ አሁን በተከበረው ምክር ቤት ፊት መግለጽ የምፈልገው ነገር የኢትዮጵያ የቀይ ባህር ተጠቃሚነት ጉዳይ አይቀሬ ስለሆነ ቅድሚያ የምንሰጠው ሰላምና ንግግር ስለሆነ እባካችሁ ሸምግሉን እና መፍትሄ አምጡልን። ይኸው ጥያቄያችን።
' አዎ እንሸመግልላችኋለን ፣ ሰላም ያስፈልጋል ' እያሉ ማዘናጋት ከሆነ ግን ብዙ የሚሄድ አይመስለኝም ጉዳዩ። ይሄ እኔ ሰለፈለኩ እናተ ስለፈለጋችሁ አይደለም በተፈጥሮ አይሆንም ነገርየው። በአንድ ቀን እንመልሰውም በአንድ ቀን አላጣነውም። የተፈጥሮ ሂደቱን ተከትሎ ይሄዳል። "
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopia

5❤4.16K😡249🙏191👏147🤔70🕊63🥰34💔30😭28😱14😢10
በውጭ አገር ያለን ዳያስፖራዎች የቴሌብር ሬሚት መተግበሪያን ከፕሌይ ስቶር ወይም ከአፕ ስቶር በማውረድ እና በማስጀመር ያለምንም ሀሳብ በቀጥታ ለቤተሰቦቻችን ገንዘብ መላክ እንችላለን!
በቴሌብር ሬሚት ገንዘብ ስንልክ ምንም አይነት ተጨማሪ ክፍያ አንጠየቅም!
ቴሌብር ሬሚትን ያውርዱ: https://onelink.to/telebirr-remit
#ደንበኛ_ስንሆን_እንዲህ_ነን
#ስንመዘገብ_እንዲህ_ነን
#ስንጭን_እንዲህ_ነን
#ስናስጀምር_እንዲህ_ነን

❤88🙏5👏2🤔2
የትራንዥን ማኑፋክቸሪነግ ብራንድ የሆነው ታዋቂው የአሌክትሮኒክስ እቃዎች አምራች ኢንፊኒክስ ኢትዮጵያ እና ተግባረ ዕድ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በትብበር ለመስራት የሚያችላቸውን ስምምነት በዛሬው ዕለት ተፈራርመዋል። ይህ ስምምነት ተማሪዎች በፈጠራ እና በቴክኖሎጂ ዘርፍ የተግባር ልምድ እንዲያገኙ ከማድረግም አልፎ በኮሌጁ "ኢንፊኒክስ ክለብ" በማቋቋም የክለቡ አባላት በትራንዥን ማኑፋክቸሪነግ የኢንተርንሺፕ እንዲሁም የስራ እድል የሚያገኙበትንም ሁኔታ አመቻችቷል።
በዚህ ፕሮግራም ላይ የኢንፊኒክስ ኢትዮጵያ ብራንድ ማናጀር አቶ አሌክስ ማ በቲክቶክ እና በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ ገፆች ላይ የኢኒፊኒክስ ኢትዮጵያን ቻሌንጅ ላሸነፉ ተወዳሪዎች አዲሱን HOT 60 Pro+ ስልኮች እና የስማርት ዋች ሸልማቶችን አበርክተዋል።
ከፊርማው ስነስርዓት በኋላ ስድሰተኛው ወርሃዊ የኢንፊኒክስ ቀን በሙዚቃ እና በተለያዩ አዝናኝ ጨዋታዎች ታጅቦ የተከበረ ሲሆን ይህም ታዳሚዎች የኢንፊኒክስ ምርቶችን ተጠቅመው የሚሞክሩበትን አጋጣሚዎች ፈጥሯል። ኢንፊኒክስ ወጣቶች ከቴክኖሎጂ ጋር ያላቸውን ጤናማ ግንኙነት ለማሳደግ ጠንክሮ እየሰራ ሲሆን በመጪው ወር በሃገራችን ትልቁን የPUBG Mobile ጌሚንግ ውድድር ለማካሔድ ዝግጅቱን ጨርሷል። የውድድሩ አሸናፊ ቡድን ሙሉ በሙሉ ወጪው ተሸፍኖለት ወደ ታይላንድ በመሄድ PMGC 2025 የፍፃሜ ውድድርን የሚታደም ይሆናል።
#InfinixEthiopia #InfinixDay #TechEducation #YouthEmpowerment #TogetherForTomorrow

❤137👏8🤔3😢2
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ትግራይ የምንልከው በጀት በሙሉ ለወታደሮች ነው እየዋለ ያለው " - ዐብይ አህመድ (ዶ/ር)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) በትግራይ ስላለው ሁኔታ ምን አሉ ?
" ትግራይ የምንልከው በጀት በሙሉ ለወታደሮች ነው እየዋለ ያለው ይህ ትግራይን እየጎዳ ነው።
አሁን ለምሳሌ ጅግጅጋ በኮሪደር ልማት ከፍተኛ ለውጥ አለ ከሱማሌ ክልል ገቢ ባለፈው አመት የትግራይ ክልል ገቢ በከፍተኛ ደረጃ ይበልጣል።
ከጅግጅጋ ገቢ የመቐለ ገቢ ስድስት እና ሰባት እጥፍ ይበልጣል። ገቢን ሰብስቦም ከእዚህም ተመድቦ እንዴት አንድ ወይም ሁለት ኪሎ ሜትር ኮሪደር አይሰራም ?
ወደ ልማት ካልተኬደ ሁል ጊዜ ውግያ እና ግጭት ጠቃሚ አይደለም።
በተቻለ መጠን ወደ ሰላም ወደ ንግግር ገብቶ የህዝቡን ችግር መፍታት ያስፈልጋል።
በዘንድሮ ክረምት እርሻ ለማየት በድሮን በትግራይ ክልል በስፋት እንበር ነበር የሚገርም ማሳ አለ በንጽጽር ከፍተኛ እርሻ ይታያል፣ በወሰድናቸው የምስል መረጃዎች የሚያሳዩት የትሻለ ምርት እንዳለ ነው።
እኛ የምንፈልገው ያን ምርት በሰላማዊ መንገድ ተሰብስቦ ወደ ገበያ እንዲውል አርሷ አደሩ እንዲጠቀም እና ከልመና እስረኝነት እንዲገላገል ነው።
ህዝቡን የልመና እስረኛ ማድረግ ጠቃሚ ስላልሆነ ከልመና እስረኝነት ወጥቶ ወደ መሻሻል ህይወቱ እንዲገባ መስራት ነው የምንፈልገው።
ትግራይ ውስጥ የፌደራሉ መንግስት የውጊያ አላማ የለውም አንፈልግም ጥቅም የለውም።
የትግራይ ክልል ያሉ ሰዎች ይህንን ምክር ሰምተው ወደ ሰላም ቢያዘነብሉ ይሻላል ነው ምክሩ። "

❤559😡137👏42🕊28😭14🤔10🙏6🥰1
" 14 ምዕመናን ናቸው በታጣቂዎች የተገደሉት ! "
ታጣቂዎች በአርሲ ሀገረ ስብከት በኖኖ ጃዊ ቀበሌ የሚኖሩ 14 ምዕመናን መገደላቸውን ማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ዘግቧል።
ጥቃቱ ከለሊቱ 6:00 ሰዓት አካባቢ በዕለተ ረቡዕ ጥቅምት 13 ቀን 2018 ዓ.ም ለ14 አጥቢያ እንደተፈጸመ ተመላክቷል።
ታጣቂዎቹ ምእመናኑን ከተኙበት ቤታቸው አስወጥተው በከፈቱት ተኩስ በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸው ተገልጿል።
ስድስቱ ከመገደላቸው ከአንድ ቀን በፈት ቀድመው ታፍነው ተወስደው ነበር ተብሏል።
የተገደሉት ምእመናን የዕድሜ ክልላቸው ከ2 ዓመት ጀምሮ እስከ 76 ዓመት አዛውንት እንደሚገኙበት ቴሌቪዥን ጣቢያው ገልጿል።
በተጨማሪም ሁለት ሰዎች በጥቃቱ ምክንያት ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸው ለተሻለ ሕክምና ወደ አቦምሳ ከተማ ሪፈር መሄዳቸውን ተነግሯል፡፡
ከዚህ በፊት ታጣቂዎች 8 ምዕመናን በተመሳሳይ ሁኔታ ከቤታቸው አስወጥተው በአቃቂ ሁኔታ መግደላቸው ተመላክቷል።
ከተገደሉት ምእመናን 6ቱ በገገሌ በዓለወልድ ቤተ ክርስቲያን፣ አንድ ደግሞ በሞዬ ቅዱስ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን እና ቀሪ ሟቾች ባሉበት አካባቢያቸው ሥርዓተ ቀብራቸው ተፈጽሟል።
በቀበሌው ባለ ከፍተኛ ስጋት በቀጣይ የባሰ ችግር እንዳይፈጠር በሀገረ ስብከት ደረጃ ከመንግሥት ጋር በጋራ መሥራት ይገባል ተብሏል።
በአሁን ሰዓት በአካባቢው ሁኔታዎችን ለማረረጋት የሀገር መከላከያ በስፍራው እንደሚገኝ ከቴሌቪዥን ጣቢያው የተገኘው መረጃ አመልክቷል።

😭1.01K❤214😡91💔30😢26🕊15👏6😱5🙏4🥰2
የቻይና-አፍሪካ የዐቃብያነ ሕግ የትብብር ፎረም በቻይና ጓንዶንግ ግዛት ጓንጁ ከተማ ከጥቅምት 19-20 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚካሄድ የፍትሕ ሚኒስቴር ገለጸ።
በፎረሙ ላይ የፍትሕ ሚኒስትር ወ/ሮ ሐና አርዓያሥላሴ የሚመሩትና እና ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተስፋዬ ዳባ ያሉበት ልዑክ ቻይና የገባ ሲሆን በተለያዩ ስብሰባዎች ይሳተፋል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የፍትሕ ሚኒስትር ከቻይና ሉዐላዊ ሕዝብ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዪንግ ዮንግ ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል።
በውይይቱም ላይ " ኢትዮጵያና ቻይና የቀደምት ሥልጣኔ ተምሳሌት መሆናቸው እና 55 አመታት ያስቆጠረ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያላቸው ሀገራት ናቸው " ብለዋል።
በሁለቱ ሀገራት መካከል የፍርደኞች ማዘዋወር እና በወንጀል ጉዳዮች የጋራ ትብብር የተደረጉ ስምምነቶችን ለመተግበር ሁለቱም ወገን እንደሚሰራ ተገልጿል።
በቻይና ፍትሕ ሚኒስቴር እና በአ.ፌ.ዲ.ሪ. ፍትሕ ሚኒስቴር መካከል የአቅም ግንባታ ስራዎችን ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት የተፈረመ መሆኑን በማስታወስ በቀጣይ በበለጠ ትብብር ለመስራት ተስማምተዋል።
የቻይናው ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ፤ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ሕብረት መቀመጫ መሆኗን እንዲሁም በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ጠንካራ ወዳጅነት በመጠቀም ቻይና በአፍሪካ ሊኖራት ለሚገባው መልካም ግንኙነት እንደመግቢያ በር እንደምትታይ ገልጸዋል።
በቀጣይ የቻይና መንግሥት ከኢትዮጵያ ጋር የሚኖረውን ግንኙነት የበለጠ እንደሚያጠናክር ገልጸዋል።

❤205🥰8💔6🕊5👏4😭3
TIKVAH-ETHIOPIA
" ትግራይ የምንልከው በጀት በሙሉ ለወታደሮች ነው እየዋለ ያለው " - ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) በትግራይ ስላለው ሁኔታ ምን አሉ ? " ትግራይ የምንልከው በጀት በሙሉ ለወታደሮች ነው እየዋለ ያለው ይህ ትግራይን እየጎዳ ነው። አሁን ለምሳሌ ጅግጅጋ በኮሪደር ልማት ከፍተኛ ለውጥ አለ ከሱማሌ ክልል ገቢ ባለፈው አመት የትግራይ ክልል ገቢ በከፍተኛ ደረጃ ይበልጣል።…
ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ለምን ተቃቃሩ ?
" ሞራል ይሰጥኻል እንጂ አይሞትልህም። መጨረሻ የምትሞተው አንተው ነህ አያዋጣም " - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ፦
" ' ኢትዮጵያ ካደገች ካደገች ' ብሎ የሚሰጉ ሰዎች ደሞ አሉ ፤ ሀገራትም ፥ ኢትዮጵያ ኦልሬዲ ትልቅ ናት እኮ የት ነው የምታድገው ? በአፍሪካ ትልቁ ፖፕሌሽን (የህዝብ ቁጥር) ያላት ናት እኮ ፤ በዓለምም እኮ 10ኛዋ ናት ትልቅ ናት።
በነገራችን ላይ በየዓመቱ ኢትዮጵያ 3 ሚሊዮን ሰው ትጨምራለች። በየዓመቱ አንድ አንድ ኤርትራ ትጨምራለች በየዓመቱ ፤ እና ኢትዮጵያ በየዓመቱ ሀገር እየጨመረች ትልቅ የሆነች ሀገር ' ካደገች ምን ትሆናለች ? ' ከተባለ፥ ካደገች ታግዛለች ሌላ የምታደርገው ነገር የለም። አሁንም እኮ እያደረገች ነው ስንትና ስንት ስደተኛ ተሸክመን የለም እንዴ ? እዚህ ዛሬ ሳናድግ።
ይሄ ሥጋት ችግር አለበት እና የኛ ጎረቤቶች በሰላም መኖር እንደምንፈልግ ማወቅ አለባቸው።
ታዲያ ለምንድን ነው ከኤርትራ ጋር የተጀመረው ጉዳይ ፈር ለቆ የወጣው ያላችሁ ከሆነ ፕሪቶሪያ ነው።
በወደቡም ስንለምን ነበር፣ በልማቱም ስንለምን ነበር፣ ስንለማመጥ ነበር፣ በጣም ስንለምን ነበር ከዛሬ ነገ ይሆናል ብለን።
ግን ፕሪቶሪያ ስንፈራረም ' ትክክል አይደለም፣ ለምን ይቆማል TPLF ህውሓትም ተጠቅልለው ካልጠፉ ቀጠናው ሰላም አያገኝም ' አሉ። አይ እኛ እኮ ህዝባችን ናቸው ልብ ከገዙ እንዲጠፉ አንፈልግም አልንና አቆምን፣ በዚህ በኩል ማስቀጠል ሲያቅታቸው በዚያ በኩል አስጀመሩ ዋናው ጉዳይ ጭቅጭቅ ውጥ ግቡ ነው፣ ' ሳትዋጉ አትቀመጡ ' ነው።
የኛ መልዕክት ለኤርትራ መንግስት ፦
ኤርትራዊያን ወንድሞቻችን ናቸው ከእነርሱ ጋር ውጊያ አንፈልግም ለኤርትራ መንግስት ያለን መልዕክት ፦
1ኛ. ጥይት አስተላላፊ አትሁኑ። ሀገር ሁኑ። ወደ ጎረቤት ሀገር ጥይት ማስተላለፍ ጥሩ አይደለም። ዓባይም ጸባይ ገዝቷል፤ የእኛም ሽፍቶች ጸባይ ይገዛሉ። አንድ ቀን ጥይት ሳመላልስ ብለው ታሪክ ስለሚነገሩን ጥይት ማመላለሱ ቢቀርባችሁ ስለማናውቅ አይደለም እናያችኋለን።
2ኛ. ህገወጥ የሰዎች ዝውውር ቢቀር፤ ተጨናንቀናል። ከተማ ውስጥም እንደምታዩት የሚመጣ ሰው ካለ በህጋዊ መንገድ ቢመጣ።
3ኛ. ህገ-ወጥ ንግድ ቢቀር። ፎርጅድ ብር ቢቀር። አሜሪካ አስቀምጣችሁ የምታሰሯቸው ብላክ ማርኬት ቢቀር። እንደ ጎረቤት ብንተሳሰብ።
ህጋዊነትን ከተከተልን በንግዱም፣ በሚፈናቀለውም፤ ጥይት ማቀበሉን ከተዋችሁ በሰላም አብረን ለማደግ በፍቅር አብረን ለመቀጠል ከምን ጊዜውም በላይ ኢትዮጵያ ፍላጎት አላት።
እኔ ልክ እንደባለፈው አስመራ የመሄድ ፍላጎት አለኝ ችግር የለብኝም። ምን ከሆነ ? ትርፍ ካለው ነው ትርፍ ከሌለው ጊዜ ማባከን ነው እኔ ባሌ የምመላለስበትን ጊዜ ዝም ብዬ አስመራ ልመላለስበት አልችልም ጊዜ የለኝም። ሥራ አለኝ።
ጦርነት አንፈልግም የምንለው ደግሞ በምክንያት ነው። እኛ ደግሞ እንዳያችሁት የሚያጓጓ ነገር አለን። የ10 ቢሊዮን ብር [ዶላር] ኤርፖርት እንገነባለን፤ የ10 ቢሊዮን ብር ነዳጅ ማዳበሪያ እንገነባለን የምናምን ሚሊዮን ብር ቤት እንገነባለን፣ ኮሊደር እንገነባለን ይሄ ሁሉ የሚያጓጓ ስራ እያለ ሰው ጦርነት ሊያስብ አይችልም።
ጦርነት የሚያስብ ሥራ የሌለው ብቻ ነው። እኛ የሚያጓጓ የምንተጋለት፣ የምንለፋለት የልማት ሥራዎች አሉ ከማንም ጋር የመዋጋት ፍላጎት የለንም።
ውጊያው ከተነሳ ውጤቱ ግልጽ ነው። ከዛ በኋላ እዬዬ አይሰራም። አሁን ነው አለመጀመር ማለት ነው።
አሁን ውጊያ እንትና ያግዘኛል እንትና ያግዘኛል የሚባል ነገር እንዴ ሰው እንዴት ዩክሬን እያየ ፖሊስቴንን (ፍልስጤም) እያየ ስለማገዝ ያወራል ? ማንም አይሞትልህም። ሞራል ይሰጥኻል እንጂ አይሞትልህም። መጨረሻ የምትሞተው አንተው ነህ አያዋጣም።
' ከበደ አለ፣ ተሰማ አለ ' አያዋጣም። ከበደ ተሰማ 10 ጥይት ያቀብልኻል እንጂ መቶ ከይሞትልህም። አየን እኮ በቲፎዞ ውጊያ እንደማይቆም አየን።
እና እኛ አንፈልግም ልማት ነው የምንፈልገው፤ ሰላም ነው የምንፈልገው፣ ከማንም ጋር ግጭት ለማድረግ ፍላጎት የለንም ከገባን ግን ግልጽ ነው ውጤቱ። አስተማማኝ አቅም ነው ያለን ማንም አያቆመንም። ይሄ ግልጽ መሆን አለበት ማንም አያቆመንም። ወደዚያ እንዳንሄድ ሪስፖንሲብሊ (በኃላፊነት) መስራት አስፈላጊ ይመስለኛል። "
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

2❤1.87K😡199🕊110👏80🤔40🙏29😢8😭8🥰4😱4💔4
TIKVAH-ETHIOPIA
" 14 ምዕመናን ናቸው በታጣቂዎች የተገደሉት ! " ታጣቂዎች በአርሲ ሀገረ ስብከት በኖኖ ጃዊ ቀበሌ የሚኖሩ 14 ምዕመናን መገደላቸውን ማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ዘግቧል። ጥቃቱ ከለሊቱ 6:00 ሰዓት አካባቢ በዕለተ ረቡዕ ጥቅምት 13 ቀን 2018 ዓ.ም ለ14 አጥቢያ እንደተፈጸመ ተመላክቷል። ታጣቂዎቹ ምእመናኑን ከተኙበት ቤታቸው አስወጥተው በከፈቱት ተኩስ በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸው ተገልጿል። …
" መርቲ ወረዳ ከተቀበሩት ውስጥ ከአንድ ቤት አምስት ሰዎች ተገድለዋል። ሚስትና ሁለት ልጆችን ጨምሮ " - የአርሲ ዞን ሀገረ ስብከት
በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ሁለት ወረዳዎች በታጣቂዎች ከተገደሉት ምዕመናን መካከል አምስቱ የአንድ ቤተሰብ አባላት እንደሆኑና ከዚህ ቀደምም በጀጁ ወረዳ በታጣቂዎች የታገቱ ሰዎች እንዳልተመለሱ የዞኑ ሀገረ ስብከት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ዛሬ ምሽት ገልጿል።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ሀገረ ስብከት በሰጠን ቃል፣ በሰሞንኛው ጥቃት መርቲ እና ጉና ወይም አባጀማ በተሰኙት ሁለት ወረዳዎች ላይ የሟቾች ቀብር መፈጸሙን ገልጿል።
ጥቃቱ የተፈጸመው ጥቅምት 13 እኩለ ሌሊት መሆኑን ገልጾ፣ " ለምሳሌ መርቲ ወረዳ ከተቀበሩት ውስጥ ከአንድ ቤት አምስት ሰዎች ተገድለዋል። ሚስትና ሁለት ልጆችን ጨምሮ " ብሏል።
ይህን ያሉን ለደኅንነታቸው ሲባል ስማቸው እንዲነገር ያልፈለጉ የሀገረ ስብከቱ አመራር፣ ትክክለኛውን የሟቾች ቁጠር በተመለከተ በቀጣይ አጣርተው እንደሚገልጹ ጠቁመዋል። " አሁን በደረሰኝ መረጃ መሰረት ቁጥራቸው ከፍም ዝቅም ይላል " ብለዋል።
" ሟቾች የተቀበሩበት ቤተክርስቲያን ሎሜ ሰቃ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ነው " ሲሉም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ከዚህ በፊት ተመሳሳይ ጥቃት ደርሶ ያውቃል ? ተብሎ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፣ " ይህ አካባቢ እንኳን ትልልቅ ባለስልጣናትም የወጡበት ቦታ ነውና ከፍተኛ ጥበቃ የነበረበት፣ መቻቻል መፈቃቀር ያለበት ነበር " ሲሉም አስታውሰዋል።
" እንደሌሎቹ እንደነ ጀጁ፣ ሽርካ ስጋት ያለበት ቀጠና አልነበረም። ከዚያ በፊት ወደ ግን ስድስት ሰዎች ላይ ሙከራ ተደርጓል " ሲሉም አክለዋል።
" ከጀጁ ወረዳ ታግተው የተወሰዱ ምዕመናን አሉ። የታገቱት አልተለቀቁም ከእነርሱ ውጭ ነው ይሄ የሰሞንኛው ጥቃት የገለጽንላችሁ " ነው ያሉት።
ሰሞንኛውን ግድያ በፈጸሙት ታጣቂ ኃይሎች ላይ " መንግስትም የወሰደው እርምጃ አለ። በዞኑ አጸፋዊ ምላሽ ተሰጥቷል " ሲሉም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበበባ

😭750❤271😡58💔32😢24🕊18👏9🤔7🙏3
#UK
ዩናይትድ ኪንግደም ጥገኝነት ጠያቂዎችን በወታደራዊ ካምፖች ልታቆይ እንደምትችል ተገለጸ።
በስኮትላንድ እና በደቡባዊ ኢንግላንድ ባሉ ወታደራዊ ካምፖች ጥገኝነት ጠያቂዎችን ለማቆየት ውይይት እንደተጀመረ ተነግሯል።
ከዚህ ቀደም ጥገኝነት ጠያቂዎች ጉዳያቸው ውሳኔ እስከሚያገኝ #በሆቴል ይኖሩ ነበር።
ጠቅላይ ሚኒስትር ሰር ኪር ስታርመር፤ የአገር ውስጥ ጉዳይ እና የመከላከያ ሚኒስቴር አመራሮች ወታደራዊ ካምፖችን በአፋጣኝ ለጥገኝነት ጠያቂዎች ማቆያ እንዲያዘጋጁ ትዕዛዝ ማስተላለፋቸውን ተዘግቧል።
ጥገኝነት ጠያቂዎችን በሆቴል ማቆየት በቢሊዮን ፓውንድ የሚቆጠር ገንዘብ ስለሚያስወጣ አሠራሩን ለማስቀረት የዩኬ መንግሥት ወስኗል።
መረጃው የቢቢሲ ነው።

😭288❤255👏21🙏14💔11😱9🕊6🥰4😡4🤔1