Telegram Web Link
TIKVAH-ETHIOPIA
#DV2027 የ2027 የአሜሪካ ዲቪ ሎተሪ ምዝገባ ቀን ከተባለበት እና ከዚህ ቀደምም ከሚታወቅበት ቀን ቢዘገይም ፕሮግራሙ እንዳልተሰረዘ / ዲቪ እንዳልቀረ ለማወቅ ተችሏል። ምዝገባው የሚጀመረው በዚህ ቀን ነው የሚል መረጃ ባይኖርም በቅርቡ ይፋዊ ምዝገባ መጀመሩን ሀገሪቱ ታሳውቃለች ተብሎ ይጠበቃል። የአሜሪካ መንግሥት በይፋ የሰጠው ማብራሪያ እና ማረጋገጫ ባይኖርም ምናልባትም የዘንድሮ የዲቪ ሎተሪ ማመልከቻ…
#USA 🇺🇸

የ2027 የአሜሪካ ዳይቫርሲቲ ቪዛ (DV) ምዝገባ እስካሁን ክፍት አለመደረጉን ስቴት ዲፓርትመንት አሳውቋል።

" ምዝገባ ተጀምሯል " የሚሉ የማጭበርበሪያ መልዕክቶች እየተዘዋወሩ እንደሚገኙ እንዲሁም አንዳንድ ግለሰቦችና አገልግሎት ሰጪዎች " የምትመረጡበትን ዕድል ከፍ እናደርግላችኋለን ክፈሉ " በማለት የማጭበርበር ተግባር ውስጥ እንደተሰማሩ ገልጿል።

ምዝገባው ገና ይፋ እንዳልተደረገ የገለጸው የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመትን " የምዝገባ ቀኑ እና ለውጥ ስለሚደርግበት የዘንድሮው ፕሮሰስ ዝርዝር መረጃ ዝግጅ ሲሆን ይፋ ይደረጋል " ብሏል።

አሜሪካ በዚህ ዓመት ለዳይቨርሲቲ ቪዛ ምዝገባ 1 ዶላር ማስከፍል እንደምትጀምር ማሳወቋ አይዘነጋም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
#TikvahEthiopiaFamily

@tikvahethiopia
11.27K🙏191😭97👏55💔33😡28🤔26🕊24😢16
🌟📱 ዘኔክሰስን ይያዙ፤ ከዓለም ጋር ይጓዙ!

በእጅግ ተመጣጣኝ ዋጋ የላቀ ፍጥነት 4ጂ ኔትወርክ የሚያስጠቅሙ ዘመናዊ የሞባይል ስልኮችን ማቅረባችንን በደስታ እንገልጻለን!

🔆 ለተጠቃሚ ምቹ የሆኑ (keypad + touchscreen)
🔋 ረጅም የባትሪ ዕድሜ ያላቸው
🗂 በ teleStorage አማካኝነት የራሳቸው የፋይል ማከማቻ ያላቸው
🤖 ቴሌብርን ጨምሮ ወሳኝ አፕሊኬሽኖች የተጫኑባቸው
🛜 ዋይፋይና ሆትስፖት ማስጠቀም የሚችሉ

ከ2 ጊ.ባ የሦስት ወራት ነጻ የዳታ ስጦታ ጋር ቀርበዋል፤ ፈጥነው የግልዎ ያድርጓቸው።

📍በአዲስ አበባ የአገልግሎት ማዕከሎቻችን እና ዘመን ገበያ ላይ ያገኟቸዋል፤ በቅርቡ ያሉበት ድረስ እንመጣለን!

ለተጨማሪ መረጃ: https://bit.ly/4hTWxQl

#znexus
#Ethiotelecom #telebirr #telebirrSuperApp #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
140😡10😭5😢2😱1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ቀኑ ሊያበቃ ነው!
የ2017 አመታዊ የግብር መክፊያ ጊዜ ሊጠናቀቅ ጥቂት ቀን ብቻ ነው የቀረው።
ግብሮን ከጥቅምት 30 ቀን 2018 ዓ.ም በፊት ይክፈሉ እራስዎን ካላስፈላጊ ቅጣት እና ውጣ ውረድ ይጠብቁ
ግብር ለሀገር ክብር
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ
76😡59🙏9🥰1
" ሰዎች ሰርተው ገንዘብ ከማግኘት ይልቅ በአቋራጭ ገንዘብ ማግኘት መፈለጋቸው ለአጭበርባሪዎች ምቹ ሆኗል " - የፌደራል ፖሊስ

በኦንላይን የማጭበርበር መንገዶች በርካቶችን ሲያጭበረብሩ የከረሙ አራት ድርጅቶች ተይዘው ክስ እንደተመሰረተባቸው የፌደራል ፖሊስ አስታውቋል።

የተለያዩ የማማለያ ስልቶችን በመጠቀም በርካታ ሰዎችን ያጭበረበሩት MMG፣ RTF፣ HCZ እና ሺን የተባሉ የኦላይን የማጭበርበሪያ ስልቶች ላይ ተሳትፎ አላቸው የተባሉ ተጠርጣሪዎች ተይዘው ክስ እንደተመሰረተባቸው የፌደራል ፖሊስ ገልጿል።

ድርጅቶቹ የተለያዩ ስያሜዎችን በመያዝ እና የተለያዩ እድሎች እንዳሉ በመግለፅ ሰዎች በቀላሉ በትርፍ ሰዓታቸው ተጨማሪ ስራ ሰርተው ገንዘብ ማግኘት እንደሚችሉ በመንገር በሚሊየኖች የሚቆጠር ገንዘብ አጭበርብረዋል።

ድርጅቶቹ "ኦንላይን ማርኬት" የሚል ሽፋን በመጠቀም ሲያጭበረብሩ ቆይተዋል።

አጭበርባሪዎቹ "ብር ኢንቨስት ካደረጋችሁ እጥፍ አድርገን እንመልሳለን" ብለው ሰዎች ብር በቀነ ገደብ እንዲያስገቡ ካደረጉ በኋላ ሰዎች ገንዘቡን ለማውጣት ሲሞክሩ የሲስተም ችግር በማለት ገፆቻቸውን ያጠፉ ነበሩ።

እነዚህን ድርጅቶች ሲመሩ እና ሲያንቀሳቅሱ ነበሩ የተባሉ #24_ሰዎችም በቁጥጥር ስር ሲውሉ አራቱ የውጪ ሀገር ዜጎች ናቸው ተብሏል።

አብዛኞቹ አጭበርባሪዎች መነሻቸው ከውጪ ሀገር ሆኖ አንዳንዶቹ ድርጅቶች ቢሮ ተከራይተው ኢትዮጵያውያንን ቀጥረው ሲያሰሩም ተይዘዋል።

ድርጅቶቹ በህጋዊ የንግድ ፈቃድ ስምም ሲይቀሳቀሱ የነበረ ሲሆን በባንካቸው ከፍተኛ ገንዘብ ሲንቀሳቀስ መቆየቱ ተገልጿል።

ለማሳያነትም MNG በተባለው ድርጅት የንግድ ባንክ አካውንት በዓንድ አመት ጊዜ ውስጥ ብቻ ከ1.2 ቢሊየን ብር በላይ መንቀሳቀሱን ፖሊስ አስታውቋል።

በ24 ቀን ጊዜ ውስጥም ወደ አንድ የባንክ አካውንት 400 ሚሊየን ብር ገብቷል ያለው ፖሊስ ይህም ምን ያህል ሰው ገብቶበት እንደነበር ያሳያል ብሏል።

ሰዎች ሰው ባስገባችሁ ቁጥር ደረጃችሁ እና የምታገኙት ገንዘብ ያድጋል ስለሚባሉ በርካታ ሰዎችን ያስገባሉ ያለው ፖሊስ በአንድ ተጠርጣሪ ስር ከ20,000 - 30,000 ሰው እንዳለ በምርመራ ማረጋገጡን ገልጿል።

ፖሊስ በዚህ የማጭበርበር ተግባር የተማረ ያልተማረ ሳይለይ የዩኒቨርሲቲ መምህራን፣ ተማሪዎችና የባንክ ሰራተኞች ጭምር ተጠቂ መሆናቸውን ገልፆ  በርካቶች ቤት ንበረታቸውን አጥተውበታል ብሏል።

ፖሊስ በተጠርጣሪዎች ላይ ምርመራውን ማጠናቀቁን ገልፆ ክስ መመስረቱን አስታውቋል።

ከዲጂታል አለሙ ማደግ ጋር ተያይዞ የኦንላይን የማጭበርበር ተግባራት የተስፋፉ ሲሆን ሰዎች ሰርተው ገንዘብ ከማግኘት ይልቅ በአቋራጭ ገንዘብ ማግኘት መፈለጋቸው ለአጭበርባሪዎች ምቹ ሆኗል።

በተደጋጋሚ ሰዎች ራሳቸውን ተገቢ ካልሆኑ የኢንቨስትመንት እና የኦንላይን ስራዎች እንዲጠብቁ በተለያዩ አካላት ቢጠየቅም ዛሬም በየቀኑ በርካቶች በተመሳሳይ መንገድ ገንዘባቸውን እያጡ ነው።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሸገር ኤፍኤም ሬድዮ ጣቢያ ነው።

Via @TikvahethMagazine
613🙏75😭30👏23😱12💔9🤔7🕊5😡4🥰2
TIKVAH-ETHIOPIA
#NewsAlert #Tigray #Afar " ኃላቀሩ ቡድን የፌደራል መንግስትን ወደ ግጭት ለማስገባት በዓፋር በኩል ትንኮሳዎች ፈፅሟል ይህንንም የአዛዡና ጌታውን ሻዕብያ አጀንዳ ለማስፈፀም የተደረገ ነው " - አቶ ጌታቸው ረዳ ጥቂት የትግራይ ኃይል አመራሮች በሻዕብያ ትእዛዝ ሰጪነት በፌደራል መንግስት ላይ ትንኮሳ እንደጀመሩና ይህን ትንኮሳ እንዲያቆሙ አቶ ጌታቸው ረዳ አሳሰቡ። የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚንስትር…
" የእናቶች ለቅሶ እስካሁን ሊቆም አልቻለም። ያለቅሳሉ እናቶች። ያለው ቁስል አልተሻረም " - አቶ ገብሩ አስራት

➡️ " በጦርነት የሚነግዱ አሉ። በትግራይ ጦርነት በልፅገው የወጡ ፣ በጣም ሃብታሞች ሆነው የወጡ ሰዎች አሉ! "

የቀድሞው የህወሓት ታጋይ እንዲሁን የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት የነበሩት ጉምቱው ፖለቲከኛ አቶ ገብሩ አስራት በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ ምን አሉ (ለኤንቢሲ ቴሌቪዥን) ?

" ከጦርነት የሚገኝ ትርፍ የለም።

እልቂት ፣ ጉዳት፣ ውድመት እንጂ ምንም አይነት ትርፍ ከጦርነት አይገኝም።

ማወቅ ያለብን ግን በጦርነት የሚያተርፉ አሉ። ስልጣናቸውን ማስጠበቅ የሚፈልጉ፣ ስልጣናቸውን ከፍ ማድረግ የሚፈልጉ አሉ።

በጦርነት የሚነግዱ አሉ። ይሄ  በግልጽ ታይቷል በትግራይ ጦርነት ወቅት። በትግራይ ጦርነት በልፅገው የወጡ ፣ በጣም ሃብታሞች ሆነው የወጡ ሰዎች አሉ። ሌላው ግን የነበረውን ሃብት ነው የጨረሰው፤ የነበረው ሃብት ተንኮታኮተ ፤ በመቶ ሚሊዮኖች የነበራቸው ኢንቬስተሮች፣ ነጋዴዎች ከስረዋል በዚህ ጦርነት ፤ ፋብሪካቸው ተቃጥሏል ፤ የነበራቸው ሃብት ተሽጦም ለእዳ አይበቃም ተበድረው ስለነበር። ይሄን ያየ ባለሃብት እና ነጋዴ እንደገና ጦርነት ሊል አይፈልግም።

ከዚህ በተጨማሪ በጣም የሚያሳዝነኝ የእናቶች ለቅሶ እስካሁን ሊቆም አልቻለም። ያለቅሳሉ እናቶች። ከእያንዳንዱ ቤተሰብ አንድ ሰው ፣ ከዛም በላይ የሞተበት ነው የትግራይ አካባቢ ሁኔታ። ይሄን መድገም (ጦርነት መፍጠር) ማለት ሀዘኑን፣ ምሬቱን ፣ አሰቃቂ ገጠመኙን መቀጠል ነው የሚሆነው ያለው ቁስል ሳይሽር።

ስለዚህ ይሄን መገንዘብ አለብን። በምንም መንገድ ወጣቱ ፣ ገበሬው ፣ ኤሊቱም ጭምር የሚገርመኝ ኤሊቱ ነው እያዩ ዝም የሚሉት፣ የሃይማኖት አባቶችም እንዲያውም በቅርቡ ኣክሱም ላይ የምግበይን ንግግር ቁጭ ብለው ሲያዳምጡ ነበር ' አንፈልግም ይሄን ጦርነት ' አላሉም የሃይማኖት አባቶች ጳጳሳት ተብለው ' ሰላም ነው የምንፈልገው ' አላሉም ፤ አንዳንዶቹ እንደውም ይሄን የሚመርቁ አሉ ፤ ይሄ እንዲሆን የሚሰሩ አሉ ይሄ ነገር መቆም አለበት።

የትግራይ ኤሊቶች ከቁጥር በላይ ኃይል ያለው  አቅም ያለው ነው፤ ኮኔክሽንም አለው ስለዚህ ይሄን ጦርነት ማስቆም ዋናው ስራ መሆን አለበት።

ይሄን እያልኩ ያለሁት በህወሓት ፣ በሻዕብያ / ፅምዶም የሚድረገውን ብቻ አይደለም በመንግሥትም በኩል መንግሥት ወደ ሰላም እንዲመጣ የመግፋት ጫና ማድረግ ያስፈልጋል። ጉዳቱ የሁላችንም ነው።

እኔ ትግራይ ስለምንቀሳቀስ ስለ ትግራይ አወራው እንጂ የጦርነት ጉዳት በሌላውም በኩል የሚሞተውን እገነዘባለሁ። የሚገድል ሁል ጊዜም ይሞታል ፤ የሚተኩስ ይሞታል፤ የሚያሸንፍውም ሟች ነው። ስለዚህ በሌላም በኩል የሚሰለፈውም ወጣት ነው።

የኤርትራዎቹ ወጣቶች እንደ ምርኮ የተያዘ ሰራዊት ነው። በዛም ቢሆን ያሳስበኛል። በቃ ዘላለም በጦርነት ውስጥ የተከተቱ። የሚያመልጠው አምልጦ የቀረውን ሰብስበው ወደ ጦርነት ነው የሚማግዱት። ይሄ ነገር ማብቃት አለበት ፤ ምንም ጥቅም የለውም። ከሻዕቢያ አመራሮች ውጭ የሚጠቀም ኤርትራዊ የለም።

እነዚህ (ከላይ የተጠቀሱ) ኃይሎች ሁሉ ጦርነት እንዳያደርጉ ጫና የመፍጠር ጉዳይ የዜጋው የኤሊቱ ፣ የነጋዴውም የባለሃብቱም የሁሉም መሆን አለበት። ድምጻቸውን የሚያሰሙበት ጊዜ አሁን ነው። "

#Tigray #Peace

@tikvahethiopia
1.14K🕊181😢68💔30🙏27👏21😡19😭10😱2
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Tigray
#Afar

ህወሓት ዛሬ ከሰዓት በኃላ ባወጣው መግለጫ ፤ የዓፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የኮሙኒኬሽን ቢሮ " የትግራይ ሰራዊት የዓፋር ክልል ዘልቀው ገብቷል " ሲል ጥቅምት 27/2018 ዓ.ም የሰጠውን መግለጫ ውድቅ አድርጎታል።

ህወሓት የዓፋር መንግስት "ሓራ መሬት " በሚል ስም በአከባቢው እየተንቀሳቐሱ " ትግራይ ያውካሉ " ያላቸውን ታጣቂዎች ቦታ መስጠቱ በፅኑ ተቃውሟል።

" የኢፌዲሪ መንግስት በዓፋር ክልል ሓራ መሬት ያሉ ታጣቂዎችን በመጠቀም ሌላ ዙር ጦርነት እየጋበዝ ነው " ሲል ከሷል። 

" ትላንት ለሊት የድሮን ድብደባ ተፈጽሟል ፤ በድሮን ድብደባው የትግራይ ሰራዊትና የአከባቢው ነዋሪዎች ተጎድተዋል " ብሏል።

ህወሓት የጉዳቱ መጠኑን በቁጥር አላስቀመጠም።

" የድሮን ድብደባው የፕሪቶሪያ ስምምነት ሙሉ በሙሉ የሚጥስና የከፋ አደጋ የሚያስከትል ተግባር ነው " ሲልም አክሏል።

" የአህጉራዊ አደራዳሪ አገራት ዝምታን ተከትሎ የኢፌዲሪ መንግስት የፕሪቶሪያ ስምምነት እንዳይፈፀም እንቅፋት ሆኖ ቆይቷል " ያለው ህወሓት "  አሁን የድሮን ድብደባ በማካሄድ ስምምነቱን በግልፅ ጥሶታል ሲል " ስሞታ አቅርቧል።

" የኢትዮጵያ መንግስት አሁንም ያሉ ልዩነቶች በሰላማዊ ፖለቲካዊ  ውይይት እንዲፈታ " ሲል ጥሪ አቅርቧል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
346🕊86😡46😭20😱7👏6🙏5🤔4😢2🥰1
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray #Afar ህወሓት ዛሬ ከሰዓት በኃላ ባወጣው መግለጫ ፤ የዓፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የኮሙኒኬሽን ቢሮ " የትግራይ ሰራዊት የዓፋር ክልል ዘልቀው ገብቷል " ሲል ጥቅምት 27/2018 ዓ.ም የሰጠውን መግለጫ ውድቅ አድርጎታል። ህወሓት የዓፋር መንግስት "ሓራ መሬት " በሚል ስም በአከባቢው እየተንቀሳቐሱ " ትግራይ ያውካሉ " ያላቸውን ታጣቂዎች ቦታ መስጠቱ በፅኑ ተቃውሟል። " የኢፌዲሪ…
" ኃላቀሩ ቡድን የወሰደው እርምጃ የትግራይና የዓፋር ህዝቦች የጀመሩት መልካም ዝምድና የሚያበላሽ የአጥፍቶ ጠፊ ውሳኔ ነው " - ስምረት

ዲምክራሲያዊ ስምረት ትግራይ ፓርቲ (ስምረት)  " ተስፋ አልባ ኋላቀር ቡድን " ሲል የገለፀው ኃይል " የእርስ በርስ ጦርነት ጥዶ ወደ እልቂት ከማስገባቱ በፊት የለውጥ ኃይሎች ተደራጅተን መመከት አለብን " አለ።

ስምረት ፓርቲ  ባወጣው መግለጫ " ኋላቀር ቡድን " ሲል የገለፀው አካል የፓለቲካ ፓርቲዎች ፣ የሃይማኖት መሪዎች ፣ የአገር ሽማግሌዎችና የዓለም አቀፍ ማሕበረሰብ ተማፅኖ ችላ በማለት ጥቅምት 26/2018 ዓ.ም የሻዕብያ ተልእኮ ለመፈፀም ዓፋር ክልል ዘልቆ በመግባት 6 መንደሮቾ ተቆጣጥሮ ይገኛል ብሏል።

" ድርጊቱና እርምጃው የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ከማፍረስ በዘለለ የትግራይና የዓፋር ህዝቦች የጀመሩት መልካም ዝምድና የሚያበላሽ የአጥፍቶ ጠፊ ውሳኔ ነው " ሲል ስምረት ፓርቲ ኮንኗል።

ድርጊቱና የትግራይ ህዝብ ፍላጎትና ዓላማ ሳይሆን የሻዕብያ ትእዛዝ ለመፈፀም የተቃጣ መሆኑ ያብራራው ስምረት ፓርቲ ድርጊቱን አውግዞ ጦርነቱ ለማስቀረት በሰላማዊ መንገድ ትግሉ እንደሚቀጥል አሳውቋል።

" እምቢ በሻዕብያ ወታደራዊ ኮማንድ በሚመራ ስር ሆነን አንዋጋም በሉ " ሲል ስምረት ፓርቲ ለትግራይ ሰራዊት አባላት ጥሪውን አቅርበዋል።

ፓርቲው ለትግራይ ዳያስፓራ ማህበረሰብ ባስተላለፈው መልእክት ደግሞ " ከነዚህ ዕድሜ ልክ ደማችንን መጠው የማይጠግቡ መዥገሮች ለመላቀቅ እጅ ለእጅ ተያይዘን ትግላችን ከፍ እናድርገው " ብሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
477😡121🕊54👏18🤔17😭11🥰4😱4💔4😢2
" የፕሮጀክቱ ቁልፍ ስራ ከሆነው የወንዝ ቅልበሳ ስራ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል " - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአማራ ክልል ጎንደር እና ባሕር ዳር የስራ ጉብኝት አድርገዋል።

በጎንደር በነበራቸው የስራ ጉብኝት የመገጭ የመስኖ ልማት ፕሮጀክት የስራ ሁኔታ መገምገሙን ገልጸዋል።

870 ሄክታር ላይ እንዳረፈ የገለጹት ይኸው ፕሮጀክት 17,000 ሄክታር መሬት በመስኖ አቅርቦት ይሸፍናል ተብሎ እንደሚጠበቅ አመልክተዋል።

" የፕሮጀክቱ ቁልፍ ስራ ከሆነው የወንዝ ቅልበሳ ስራ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል " ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ " የተቀሩት ስራዎችም በተያዘላቸው የጊዜ ሰሌዳ እየተካሄዱ ይገኛሉ " ብለዋል።

በሌላ በኩል ፥ ከቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸውና ከከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን የታደሰውን የፋሲል ጊቢ መርቀዋል።

አጠቃላይ የእድሳት ሥራው ከአንድ አመት በታች የፈጀ እንደሆነ ተገልጿል።

" በእድሳቱ ፦
- በቅርስ ስፍራው ነባሩን ታሪክ በመጠበቅ ውበቱን እና ተደራሽነቱን የማስፋት ስራ ተሰርቷል።
-  የቤተመንግሥቱ የግንባታ መዋቅር ተጠግኗል።
- የእግር መንገዶችን ማሻሻል ስራ ተሰርቷል።
- ቁልፍ የሆኑ ሕንፃዎችን ከዝግባ እና ዋንዛ ባሕላዊ ቁሳቁሶችን በመጠቀም በማደስ የስፍራውን ግለ ወጥ መልክ እና ባሕርይ የመጠበቅ ስራ ተሰርቷል።
- ለጎብኝዎች ምቾት የተሰናዱ አገልግሎት መስጫዎች ተሻሽለዋል።
- አዲስ የቱሪስት ማዕከል ተከፍቷል።
- ዘመናዊ መጸዳጃ ቤቶች፣ የተሻሻሉ የመብራት እና የደኅንነት ሥርዓቶችም ተሰናድተዋል።
- እንደ አፄ ፋሲል፣ አፄ ቀዳማዊ ዮሃንስ እና አፄ ቀዳማዊ ኢያሱ አቢያተ መንግሥት ብሎም ድልድዮች፣ መታጠቢያ ሥፍራዎች፣ ታሪካዊ በሮች ወዘተ ታድሰዋል።
- ከ40,000 ስኴር ሜትር በላይ የአካባቢው ምድር የማስዋብ ሥራ ተሰርቷል " ተብሏል።

ከዚህ በተጨማሪ ጣናነሽ የተሰኘችው ጀልባ ሥራ መጀመራ ተገልጿል።

" ጣናነሽ በጣና ውሃ ላይ እየቀዘፈች ባሕር ዳር ከተማን ከጎርጎራ ኤኮ ሎጅ ማገናኘት ጀምራለች " ሲሉ ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ገልጸዋል።

ጀልባዋ ከ180 ተጓዦች በላይ የማጓጓዝ አቅም እንዳላት አመልክተዋል።

" ለጉብኝት፣  ለመዝናናት እና አስደማሚውን የጣና ሀይቅ የተፈጥሮ ከባቢ ለመጎብኘት ወደ ጎርጎራ ኤኮ ሎጅ የሚደረገውን ጉዞ የበለጠ ምቹ አድርጋዋለች " ሲሉ አክለዋል።

#PMOEthiopia

@tikvahethiopia
1.2K😡280👏71🕊32😭25🥰23🙏23🤔14😢7
TIKVAH-ETHIOPIA
" ኃላቀሩ ቡድን የወሰደው እርምጃ የትግራይና የዓፋር ህዝቦች የጀመሩት መልካም ዝምድና የሚያበላሽ የአጥፍቶ ጠፊ ውሳኔ ነው " - ስምረት ዲምክራሲያዊ ስምረት ትግራይ ፓርቲ (ስምረት)  " ተስፋ አልባ ኋላቀር ቡድን " ሲል የገለፀው ኃይል " የእርስ በርስ ጦርነት ጥዶ ወደ እልቂት ከማስገባቱ በፊት የለውጥ ኃይሎች ተደራጅተን መመከት አለብን " አለ። ስምረት ፓርቲ  ባወጣው መግለጫ " ኋላቀር ቡድን "…
" ሕዝቡ ' እምቢ ለጦርነት ' ማለት አለበት " - የትግራይ ሙሁራን እና ባለሙያዎች ማሕበር

🚨" ህወሓት እና አንዳንድ የጦር ጀነራሎች የፕሪቶሪያ የተኩስ አቁም ስምምነትን መሰረት በማድረግ ነገሮችን በሰላማዊ መንገድ ከመፍታት ይልቅ ትግራይን ወደ ሌላ ዙር ጦርነት ለማስገባት እየፎከሩና የጦርነት ዝግጅት እያደረጉ ነው ! "

የትግራይ ሙሁራን እና ባለሙያዎች ማሕበር (GSTS) በትግራይ ያንዣበበው የጦርነት ዳመና በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ጥሪ አቀረበ።

ማሕበሩ ባወጣው አስቸኳይ መግለጫ " የትግራይ ሕዝብ ዋናው ፍላጎት ሰላምና ሰላም ብቻ ነው " ብሏል።

ከጫፍ እስከጫፍ ያለው የትግራይ ህዝብ ጦርነትና የጦርነት ወሬ መስማት አይፈልግም ያለው ማሕበሩ " ህወሓት እና አንዳንድ የጦር ጀነራሎች የፕሪቶሪያ የተኩስ አቁም ስምምነትን መሰረት በማድረግ ነገሮችን በሰላማዊ መንገድ ከመፍታት ይልቅ ትግራይን ወደ ሌላ ዙር ጦርነት ለማስገባት እየፎከሩና የጦርነት ዝግጅት እያደረጉ ነው " ብሏል።

" ሕዝብን የሚመራ አካል ጦርነት ለማስቀረት ይጥራል እንጂ ወደ ጦርነት የሚያመሩ ንግግሮችና ተግባራትን መፈጸም የለበትም " በማለትም የክልሉን ጊዚያዊ አስተዳደርም ወቅሷል።

አሁን በአካባቢው እያንዣበበ ያለውን የጦርነት ድባብን ለማስቀረት ሕዝቡ፣ በትግራይ ሐይሎችና በዓፋር ያሉ የታጠቁ ሐይሎች እንዲሁም የዳያስፖራው ማሕበረሰብ ለሰላም መቆም እንዳለባቸው አሳስቧል።

የማሕበሩ የአመራር አባል የሆኑት ዶ/ር ገብረኪዳን ገ/ስላሴ ለዶቼ ቨለ ሬድዮ በሰጡት ማብራሪያ ምን አሉ ?

" የትግራይ ሕዝብ ፍላጎት ሰላም ነው።

ሁለተኛ ጦርነት እንዳይመጣ እንጸልያለን።

ሆኖም ግን እንደዛ አይነት ጥሪ (የጦርነት ጥሪ) የሚያደርጉ በሁሉም ወገን ካሉ ወጣቱ የዚህ ሰለባ እንዳይሆን፤ ሕዝባችንም በሰራዊት ያሉም አንዱ ሀራ መሬት የሚባል አለ፤ ሌላው ቲዲኤፍ ትግራይ ውስጥ ያለው በመካከላቸው ምንም ወደ ግጭት የሚወስዳቸው ነገር ስለሌለ ወደዛ እንዳይሄዱ፤ እና ወጣቱ የጦርነት ሰለባ እንዳይሆን ጥሪ አድርገናል።

ሕዝቡ ' እምቢ ለጦርነት ' ማለት አለበት።

ያለው ልዩነት የፖለቲካ ልዩነት ነው። በፖለቲካ ውይይት እንዲፈቱት ነው የምንጠይቀው። ከዚህ በተጨማሪ ግን ህብረተሰቡ እራሱ ሕብረተሰቡ ፖለቲከኞች በሚፈጥሩት ግጭት ወደ ጦርነት እንዳይገባ የራሱን ተፅዕኖ ማድረግ አለበት። ለጦርነት ' እምቢ ' ማለት አለበት። " ብለዋል።

#Tigray #Peace

@tikvahethiopia
404🕊98😡31😭14👏7🤔6🙏6💔4🥰1
2025/11/08 01:05:43
Back to Top
HTML Embed Code: