Telegram Web Link
" በስልጠና ማጠናቀቂያ ወቅት ያገኙት ሰርተፍኬት በዩኒቨርሲቲው ለመማር በሚወዳደሩበት ወቅት 10 በመቶ ውጤት እንዲኖረው እናደርጋለን "- የአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በ2017 ዓ/ም የክረምት መርሃ ግብር በሳይበር ደህንነትና ተያያዥ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 629 ታዳጊ ወጣቶችን በዛሬው ዕለት አስመረቋል።

ታዳጊዎቹ በክረምት መርሃ ግብር የሰለጠኑት ፦
- በሳይበር ደህንነት፣
- በቴክኖሎጂ ልማት፣
- በኢምቤድድ ሲስተም፣ እና በኤሮስፔስ ዘርፎች ነው።

ላለፉት ሦስት አመታት አዲስ አበባ ላይ ብቻ ሲካሄድ የቆየው የስልጠና መርሃ ግብር፤ በ2017 ዓ/ም ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ለመጀመሪያ ጊዜ 76 ልጆች ሰልጥነው መመረቅ መቻላቸው ተገልጿል።

ስልጠናውን የተከታተሉት ታዳጊዎች ከኢለመንተሪ፣ ሃይስኩል እና ዩኒቨርሲቲ የተወጣጡ ናቸው ።

ታዳጊዎቹ ስልጠናቸውን ከኢንሳ በተጨማሪ  በአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (AASTU) ሲከታተሉ የቆዩ ሲሆን በማጠናቀቂያው ወቅት የተሰጣቸው ሰርተፍኬት በዩኒቨርሲቲው ትምህርት ለመከታተል በሚወዳደሩበት ወቅት የመቁረጫው ነጥብ ዝቅ እንደሚያደረግላቸው የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር ደረጀ እንግዳ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ደረጀ እንግዳ በዝርዝር ምን አሉ ?

" ግቢ ውስጥ በቆዩበት ጊዜ በተለያዩ ዘርፎች ስልጠናቸውን ሲከታተሉ ቆይተዋል ስልጠናውን ኮርስ በመስጠት ብቻ ሳይሆን ችግሮቻችንን በመንገር ችግሮችን መፍታት ከመቻላቸውም በላይ ፕሮዳክቶችን ይዘው መጥተዋል።

የራሳቸው የሆነ የተለያዩ ችግሮችን መፍታት እና መሸጥ የሚችሉ ፕሮዳክቶችን ይዘው ወጥተዋል።

እኛ ፈተና ፈትነን ተማሪዎችን የምንቀበል መሆኑ ይታወቃል ፈተና ፈትነን ስንቀበል የ 12 ውጤት እና የመግቢያ ፈተና ውጤት ነው የምናየው።

በእዚህ ስልጠና ከመላው የኢትዮጵያ አካባቢዎች መጥተው በግቢያችን ስልጠና ሲከታተሉ የቆዩ ተማሪዎች የወሰዱት ሰርተፍኬት በግቢያችን ለመማር በሚያመለክቱበት ወቅት ቫልዩ ይኖረዋል።

ከእዚህ ቀደም ስናወዳድር 50 በመቶ 12 ክፍል ውጤት 50 በመቶ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ውጤት እንመለከት ነበር አሁን 10 በመቶ በስልጠና ማጠናቀቂያው ወቅት ያገኙትን ሰርተፍኬት እንዲይዝ  እናደርጋለን።

አንድ ላይ ተደምሮ ከመቶ ሲያዝ የመቁረጫ ነጥብ ላይ ባመጡት ቁጥር ዝቅ ያደረግላቸዋል ፣ ልዩ ኮታ ይሰጣቸዋል ማለት ነው ።

ይህንን እድል አምናም ሰጥተናል ዘንድሮ ከገቡ መካከልም ይህንን እድል ያገኙ አሉ በሚቀጥለው አመትም ይህ ይቀጥላል።

ሁለተኛ እዚህ ስልጠናቸውን የተከታተሉ ተማሪዎች የተለያዩ ፕሮዳክቶችን አውጥተዋል እኛ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የኢንዱስትሪያል ኢኖቬሽን እና ኢንኩቤሽን ሃብ ሰርተናል ይህ ሃብ ወደ 189 ስታርታፖችን መቀበል ይችላል።

እነዚህ ስታርታፖች ከተለያዩ ቦታ እና ዩንቨርሲቲዎች የተወጣጡ ሊሆኑ ይችላሉ ነገር ግን ሜድ ኢን ኢትዮጵያ ምርቶች ያላቸው እና መሸጫ ቦታ ያጡ ሰዎችን የምናሰባስብበት ቦታ ነው።

ይህንን ስፔስ (ቦታ) ስልጠናውን ለተከታተሉ ሰዎች ለሰሯቸው ምርቶች (ፕሮዳክቶች) እናቀርባለን።

የምናቀርበው በሁለት አይነት መንገድ ነው አቅሙ ኖሯቸው በራሳችን እንቀጥል ካሉ የተወሰነ ኪራይ እናስከፍላለን ፣ምንም አቅም የለንም የሚሉ ካሉ ከተለያዩ ባለሃብቶች እና ከዩኒቨርሲቲውም አንድ ላይ አድርገን ድጋፍ በማድረግ ምርታቸው ወደ ገበያ እንዲወጣ እና ስራ ፈጣሪ እንዲሆን ድጋፍ እናደርጋለን " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
505😡26🙏11🤔8🕊3🥰1👏1😱1
የስንዴ ምርት አቀነባባሪ አምራቾች ለረጅም ጊዜ ሲያቀርቡት የነበረው ቅሬታ መፈታቱ ተገለጸ።

ለብዙ ጊዜ በገቢዎች ሚኒስቴር እና በስንዴ አቀነባባሪዎች አጨቃጫቂ የነበረው የታክስ ጉዳይ መፍትሄ አግኝቷል።

የገቢዎች ሚኒስቴር ጥቅምት 4 ቀን 2018 ባሰራጨው ሰርኩላር የስንዴ ምርት አቀነባባሪ አምራቾች ለስንዴ ግዢ የሚፈጸም ክፍያ ላይ የነበራቸው ተደጋጋሚ ቅሬታ ላይ የገንዘብ ሚኒስቴር ውሳኔ መሰጠቱን ገልጿል።

ከገንዘብ ሚኒስቴር በዶ/ር እዮብ ተካልኝ (የቀድሞ ሚኒስትር ዴኤታ) የተፈረመውና ለገቢዎች ሚኒስቴር የተላከው ደብዳቤ ጉዳዩ ለብዙ ጊዜ ለአምራቹ ኢንዱስትሪ እና ለሻጭ ጫና እየፈጠረ መሆኑንን በመጥቀስ ብዙ ጥያቄዎች ይቀርቡበት እንደነበር አንስቷል።

በገንዘብ ሚኒስቴር የተጻፈው ደብዳቤ ምን ውሳኔዎችን አሳለፈ ?

- ደብዳቤው፥ ለስንዴ ግዥ የሚፈፀም ክፍያ ላይ የቅድመ ግብር ክፍያ ሥርዓት (Witholding tax) ተፈጻሚ እንዳይሆን መወሰኑን ይገልጻል።

- የታክስ ውሳኔ ማስታወቂያ ደርሷቸው፤ በታክስ ውሳኔ ቅሬታ አጣሪ ጽ/ቤት በሂደት ላይ ያሉ እና በቀጣይ የታክሱን ትክክለኛነት ለማጣራት በሚደረጉ የኦዲት ሥራዎችም ላይ ውሳኔው ተፈጻሚ እንዲሆን ያዛል።

- የግብይት ሥርዓቱ ወደ ዘመናዊነት ተቀይሮ ትክክለኛ የግዥ ደረሰኝ ማግኘት እስኪቻል ድረስ የስንዴ ግዢ በግዥ ማረጋገጫ (Purchase vouchern የተፈጸመ ግብይት ከሆነ የገንዘብ መጠን ሳይገድበው የተፈጸመው ክፍያ ለስንዴ ሻጩ በባንክ የተላለፈ መሆኑ፣ የስንዴ ዱቄቱ በስታንዳርዱ መሠረት ስለመመረቱ እየተረጋገጠ ገቢውን ለማመንጨት የወጣው ወጪ ተቀባይነት እንዲኖረው የሚያስችል ሥርዓት በታክስ ባለስልጣኑ በኩል እንዲዘረጋ መወሰኑን ይጠቅሳል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የደብዳቤውን ትክክለኛነት ከገቢዎች ሚኒስቴር ማረጋገጥ ችሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ

@tikvahethiopia
706🙏54🕊20😢17🤔12😭9🥰8😱6
ልዩ የትምህርት ድጋፍ እድል ከፋዌ ኢትዮጵያ

ፋዌ ኢትዮጵያ እና ፋዌ አፍሪካ ከ ማስተርካርድ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር በ 2018 ዓ.ም እድሚያቸው ከ 15 እስከ 25 የሆኑ ወጣቶችን በተለይም በዝቅተኛ ኢኮኖሚያዊ ደረጃ የሚገኙ ሴቶችን ፣የአካል ጉዳተኛ ወጣቶችን፣ የሀገር ዉስጥ ተፈናቃዮችን እና የውጭ ሀገር ስደተኞች ተጠቃሚ የሚያደርግ የከፍተኛ የትምህርት እድል ተጠቃሚ እንድትሆኑ ሲጋብዝ ታላቅ ደስታ ይሰማዋል፡፡ ድጋፉ ሁሉን አቀፍ የገንዘብ፣የትምህርትና ስልጠና እንዲሁም የማህበራዊ ድጋፍን የሚያካትት ሲሆን የትምህርት ድጋፉ የሚሰጠው በቴክኒክና ሙያ የትምህርት ተቋማት ውስጥ በሚሰጡ የሳይንስ፣ቴክኖሎጂ፣ምህንድስናና ተዛማጅ የትምህርት ዘርፎች/STEM/ ደረጃ 4 እና 5 ኮርሶች ነው፡፡

ትምህርት ስልጠናና ድጋፉ የሚሰጠው በአዲስ አበባ  ከተማ  በጄኔራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ እና አዲስ አበባ ተግባረ እድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች፣ አዳማ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ፣  ሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክና ሀዋሳ ተግባረ እድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች እንዲሁም በባህርዳር ፖሊ ቴከኒክ ኮሌጅ በሚሰጡት የመደበኛ የትምህርትና ስልጠና መርሃግብሮች ሲሆን ሙሉ ዝርዝር መረጃ ከስር ባለው ሊንክ ይመልከቱ።
👉 https://shorturl.at/5w9EC

የማመልከቻ ቀን ከ ጥቅምት 17-21 ፤ 2018 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን ከተጠቀሰው ቀነገደብ ዉጭ የሚመጡ አመልካቾችን የማናስተናግድ መሆኑን ከወዲሁ እንገልጻለን።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥሮች
አዲስ አበባ በ 0981642541
አዳማ  በ 0981643411
ባህርዳር በ 0981638351
ሀዋሳ በ 0981630651 በመደወል ወይም በድህረገጻችን www.faweethiopia.org ይጎብኙ፡፡
ምዝገባዉም ሆነ የመረጣው ሂደት ከማንኛዉም ክፍያ ነጻ መሆኑን እናሳዉቃለን!
2247🙏10🕊5😭4😡1
#Earthquake : ከደቂቃዎች በፊት አዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎችን ጨምሮ በሌሎችም ከተሞች ንዝረቱ የተሰማ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል።

በተለይም በህንጻዎች ላይ የሚኖሩ ነዋሪዎች ንዝረቱ እጅጉን እንደተሰማቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

ተጨማሪ መረጃ ይኖረናል።

@tikvahethiopia
3😢559206😭189🙏159😱48🕊44👏40🤔28💔25🥰11
TIKVAH-ETHIOPIA
#Earthquake : ከደቂቃዎች በፊት አዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎችን ጨምሮ በሌሎችም ከተሞች ንዝረቱ የተሰማ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል። በተለይም በህንጻዎች ላይ የሚኖሩ ነዋሪዎች ንዝረቱ እጅጉን እንደተሰማቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል። ተጨማሪ መረጃ ይኖረናል። @tikvahethiopia
#Earthquake

በሬክተር ስኬል 4.9 የተለካ መሬት መንቀጥቀጥ ከደብረሲና 30 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ መከሰቱን የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ ገልጿል።

የመሬት መንቀጥቀጡ ንዝረት በአፋር ከተሞች ፣ በአዳማ ፣ ደብረ ብርሃንን ጨምሮ በርካታ ከተሞች ድረስ ዘልቆ ተሰምቷል።

በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ አካባቢዎች ንዝረቱ የተሰማ ሲሆን በተለይም በህንጻዎች ላይ የሚኖሩ ነዋሪዎች ንዝረቱ አይሎ እንደተሰማቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ከሰሚህ፣ አያት ፣ ጋርመንት ፣ ገርጂ፣ ጎፋ ፣ ለቡ ፣ የካ አባዶ፣ መሪ፣ መካኒሳ ፣ጀሞ፣ ቡልቡላ ፣ ቦሌ አራብሳ፣ ጣፎ፣ ፊጋ ፣ ሚኪላንድ.. እንዲሁም ከሌሎች የከተማዋ አካባቢዎች ቃላቸውን የላኩ የቤተሰባችን አባላት ፥ የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረቱ እጅግ ጠንክሮ እንደተሰማቸው ገልጸዋል።

ንዝረቱ እቃ ጭምር ያንቀሳቀሰ እንደነበር አመልክተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ

@tikvahethiopia
459😭146🙏61😢29🕊28💔15😱14🤔12👏8😡6🥰4
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

" የዛሬው የመሬት መንቀጥቀጥ የተከሰተው ከፈንታሌ ዙሪያ ነው፤ በሬክተር ስኬል 4.8 የተለካ ነው " - ፕ/ር አታላይ አየለ

ዛሬ ጥቅምት 16 ቀን 2018 ዓ/ም በፈንታሌ ዙሪያ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል።

የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረቱ ከጠዋቱ 2 ሰዓት ከ25 ደቂቃ ላይ በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎችም የተሰማ ሲሆን፣ " እዚህ ይህን ያህል ከተሰማን ዋናው በተከሰተበት ቦታ ያሉት እንዴት ሆነው ይሆን ? " ሲሉ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች ሀሳባቸውን ገልጸዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም፣ ስለጉዳዩ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ማብራሪያ ጠይቋል። 

በዩኒቨርሲቲው የጂኦ ፊዚክስ ስፔስ ሳይንስና አስትሮኖሚ ኢንስቲትዩት ተመራማሪ የሆኑት ፕ/ር አታላይ አየለ፣ " የዛሬው የመሬት መንቀጥቀጥ የተከሰተው ከፈንታሌ ዙሪያ ነው፤ በሬክተር ስኬል 4.8 የተለካ ነው " ብለዋል።

የተከሰተው 2 ሰዓት ከ24 ደቂቃ መሆኑን አስረድተው፣ " በብዙ ከተሞችም ተሰምቷል " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ፈንታሌ ትንሽ ረገብ ብሎ ነበር፣ አሁንም ቀጣይነት አለው ማለት ነው ? ስንል ላቀረብነው ጥያቄ፣ " የፈንታሌው ረገብ አለ የሚባልም አይደለም። የመወጠር ነገር አለ፤ ረገብ አላለም፤ በመሳሪያ እናያለን " ብለዋል።

" ሁሌም መሬት በማያቋርጥ እንቅስቃሴ ላይ ነው ያለችውና ሁሌ
#ተዘጋጅተን_መጠበቅ ነው እንጂ በዚህ ጊዜ ይጠፋል፣ በዚህ ጊዜ ይቆማል የሚባል ነገር አይደለም። ሰበር ዜና ሆኖ መደነቅ የለብንም መልመድ አለብን " ነው ያሉት።

በቅርቡም በትግራይ ክልል በተደጋጋሚ መከሰቱን ጠቅሰው፣ " ወደ ሃውዜንና ውቅሮ ምሥራቃዊ ክፍል በተደጋጋሚ ከፍተኛው 5.6 የተለካ መሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል " ብለዋል።

" የትግራዩ የመሬት መንቀሳቀጥ ከፈንታሌ ጋር የተገናኘ ሳይሆን የራሱ ነው፤ ስምጥ ሸለቆ ዙሪያ ሁል ጊዜ በማያቋርጥ እንቅስቃሴ ውስጥ ነው የሚሆነውና ያም አለው ከአፋር ቅርብ ስለሆነ፤ የፈንታሌውም የትግራዩም የስምጥ ሸለቆ ባህሪ ነው " ሲሉም አስረድተዋል።

" ስምጥ ሸለቆውን እየተከተለ አደጋው እየተደጋገመ ነው፣ በፈንታሌ፣ አፍዴራ፣ ኤርታሌ ነበር። መሬት በማያቋርጥ እንቅስቃሴ ውስጥ ነው ያለችው፤ መልመድ አለብን " ሲሉም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ 
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
1.25K🙏148😭108😱56🕊52🤔31💔24😢23😡21🥰9👏5
TIKVAH-ETHIOPIA
" የውሃ አገልግሎት በከፊል እና ሙሉ ለሙሉ ስለሚቋረጥ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አድርጉ " - ውሃ እና ፍሳሽ ባለሥልጣን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውሃ እና ፍሳሽ ባለሥልጣን የለገዳዲ ግድብ የጥሬ ውሃ ማስተላለፊያ ቫልቭ ቅየራ ስራ ከጥቅምት 2/2018 ዓም እስከ ጥቅምት 16/2018 ዓም ድረስ የሚከናወን መሆኑን ገልጿል። የጥገና ስራው እስከሚጠናቀቅም በአንዳንድ የከተማዋ አካባቢዎች የውሃ…
" ያረጀ ቫልቩ ጥገና ባይከናወን የግድቡን ህልውና አደጋ ውስጥ ይከተው ነበር " - የውሃ እና ፍሳሽ ባለሥልጣን

የአዲስ አበባ ከተማ ውሃ እና ፍሳሽ ባለሥልጣን የለገዳዲ ግድብ የውሃ ማስተላለፊያ ማማ የቫልቭ ቅየራ ስራ ከጥቅምት 2 ቀን 2018 ዓ/ም እስከ ጥቅምት 16 ቀን 2018 ዓም ድረስ እንደሚከናወን ማሳወቁ ይታወቃል።

የቫልቭ ቅየራ ስራው እስከሚጠናቀቅም በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ፣ በቦሌ ክፍለ ከተማ እና በቂርቆስ ክፍለ ከተማ አንዳንድ ወረዳዎች የውሃ አቅርቦት ተቋርጦ ቆይቷል።

ባለሥልጣኑ የቫልቭ ቅየራ ስራው መጠናቀቁን እና የለገዳዲ ግድብ በሙሉ አቅሙ ምርት መጀመሩን በማህበራዊ ትስስር ገጹ አሳውቋል።

ስራው ሲያከናወን የቆየው ዊ ቢውልድ /ሳሊኒ/ ሲሆን የኢትዮጵያ ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን በማማከር አገልግሎት ተሳትፏል ተብሏል።

የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢ/ር ዘሪሁን አባተ " ያረጀ ቫልቩ ጥገና ባይከናወን የግድቡን ህልውና አደጋ ውስጥ ይከተው ነበር " ያሉ ሲሆን በአጭር ጊዜ የጥገና ስራውን ላጠናቀቁ ተቋማት ምስጋና ስለማቅረባቸው ባለሥልጣኑ አሳውቋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ

@tikvahethiopia
164😡8🙏5🤔4👏1
ቪድዮ ፦ ዛሬ በሰመራ ዩኒቨርሲቲ በሚገኝ አንድ የተማሪዎች ህንጻ ላይ የእሳት አደጋ ተከስቶ ነበር።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ አደጋውን በተመለከተ ከሚመለከታቸው የተቋሙ አመራሮች ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት ያደረገው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም።

አንድ የተቋሙ ተማሪ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል፥ " ቀን ወደ 11 ሰዓት አካባቢ ብሎክ 17 ነው እሳት አደጋው የደረሰው ፤ ከሶስተኛው ወለል ነው የተነሳው እሳቱ። ተማሪ ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለ ነው የሰማሁት። የአንዳንድ ተማሪዎች አልባሳት ተቃጥለዋል። ከዚህ ቀደምም እንዲህ ያለ እሳት አደጋ ተከስቶ ያውቃል " ብሏል።

Video Credit - 1337

@tikvahethiopia
151😭109😱39🕊19🙏14🤔2🥰1
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#DV2027

የ2027 የአሜሪካ ዲቪ ሎተሪ ምዝገባ ቀን ከተባለበት እና ከዚህ ቀደምም ከሚታወቅበት ቀን ቢዘገይም ፕሮግራሙ እንዳልተሰረዘ / ዲቪ እንዳልቀረ ለማወቅ ተችሏል።

ምዝገባው የሚጀመረው በዚህ ቀን ነው የሚል መረጃ ባይኖርም በቅርቡ ይፋዊ ምዝገባ መጀመሩን ሀገሪቱ ታሳውቃለች ተብሎ ይጠበቃል።

የአሜሪካ መንግሥት በይፋ የሰጠው ማብራሪያ እና ማረጋገጫ ባይኖርም ምናልባትም የዘንድሮ የዲቪ ሎተሪ ማመልከቻ ጊዜ የዘገየው ይጀመራል ከተባለው የ1 ዶላር የምዝገባ ክፍያ ሲስተም አፕዴት ጋር የተያያዘ ሊሆን እንደሚችል ተነግሯል።

የዲቪ አመልካቾች ለምዝገባው 1 ዶላር እንዲከፍሉ የሚያደርገው አሰራር ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ይጀመራል።

አሜሪካ በየአመቱ ከመላው ዓለም 55,000 ሰዎችን በዲቪ ሎተሪ ወደ ሀገሯ ታስገባለች።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
#TikvahEthiopiaFamily

@tikvahethiopia
361🙏64😭30😡23👏13🕊9😢4😱3💔3
2025/10/27 02:17:28
Back to Top
HTML Embed Code: