TIKVAH-ETHIOPIA
#መቐለ “ ማስክ የለበሱ ታጣቂዎች ገብተው የጽሕፈት ቤታችንን ታፔላ ነቅለውታል ” - ስምረት ፓርቲ “ ማስክ የለበሱ ” ያላቸው ታጣቂዎች ትላንት ምሽት 4:00 የመቐለ ጽሕፈት ቤቱን ለመዝረፍ ሙከራ እንዳደረጉና “ ታፔላውን ነቅለው እንደሄዱ ” በነአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው አዲሱ ስምረት ፓርቲ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል፡፡ በጽሕፈት ቤታችሁ በኩል የተዘረፈ ንብረትና የደረሰ ውድመት አለ ? ስንል የጠየቅናቸው…
#ስምረት
ዴሞክራስያዊ ስምረት ትግራይ ፓርቲ (ስምረት) መስራች ጉባኤውን ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ እያካሄደ ይገኛል።
ፓርቲው መስራች ጉባኤውን ከትግራይ ውጭ እያካሄደ መሆኑ ከመስራቾች አንዱ የሆኑት ነጋ አሰፋ መኮነን ገልጸዋል።
ጉባኤው ከመላው ትግራይ ወደ አዲስ አበባ የገቡ አባላት በተሟሉበት እየተካሄደ ነው ተብሏል።
የገዢውን ጨምሮ የሌሎች የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች በእንግድትነት ተገኝተውበታል።
ፓርቲው ባለፈው ዓመት በወርሃ ነሀሴ 2017 ዓ.ም እንዲሁም ባለፈው ወርሃ መስከረም 2018 ዓ.ም በመቐለ መስራች ጉባኤውን ለማካሄድ ለጊዚያዊ አስተዳደሩ ያቀረበው ጥያቄ አልተሳካም ሲሉ አቶ ነጋ አሰፋ ተናግረዋል።
የህወሓት ምክትል ሊቀ-መንበር በነበሩት ጌታቸው ረዳ የሚገኙባቸው ገምቱ ወጣትና ነባር አመራሮች ተቋቁሞ ባለፈው ዓመት ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ቅድመ እውቅና ያገኘው ስምረት ፓርቲ በመቐለ የከፈተው ዋና ፅህፈት ቤት ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች መሰበሩ ይታወሳል።
ምንም እንኳን ፓርቲው መስራች ጉባኤውን በትግራይ ለማድረግ ቢያቅድም አስቻይ ሁኔታዎች ባለመፈጠራቸው በአዲስ አበባ እያካሄደ ነው።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
ፎቶ፦ ከማኅበራዊ ሚዲያ
@tikvahethiopia

❤480😡93🕊37🤔17🙏12😭11🥰3👏3💔1
" ሾፌሩ ምንም ጉዳት ሳይደርስበት ከተገለበጠው ተሽከርካሪ ውስጥ ወጥቷል ! "
ዛሬ ጥቅምት 14/2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ አረዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ሶር አምባ ሆቴል ፊት ለፊት ከቀኑ 6:45 ሠዓት ላይ የትራፊክ አደጋ የአጋጠመ ሲሆን በአደጋው በንብረት ላይ መጠነኛ ጉዳት ከመድረሱ በስተቀር በሠው ላይ የደረሰ ጉዳት የለም።
አደጋው በደረሰበት ሰዓት መኪናውን እያሽከረከረ የነበረዉ ሾፌር ምንም ጉዳት ሳይደርስበት ከተገለበጠው ተሽከርካሪ ውስጥ መውጣት ችሏል።
የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች በአደጋው ምክንያት የተገለበጠውን ተሽከርካሪ በማንሳት መንገዱ ለትራፊክ እንቅስቃሴ ክፍት እንዲሆን አድርገዋል።
#FDRMC

🙏558❤328😭33👏20🕊19😱10🥰6🤔5😢3
🌟 የአሜሪካ ደርሶ መልስ ትኬት መግዣን ጨምሮ የተለያዩ አጓጊ ሸልማቶችን ከ11% የገንዘብ ስጦታ ጋር ይሸለሙ!!
እስከ ጥቅምት 21 ቀን 2018 ዓ.ም ከአሜሪካ በቴሌብር ሬሚት እና በአጋሮቻችን በኩል የተላከልዎን ዓለም አቀፍ ሐዋላ በቴሌብር ሲቀበሉ 11% የገንዘብ ስጦታ ያገኛሉ።
በተጨማሪ 300 ዶላር እና ከዚያ በላይ ሲቀበሉ
✈️ 💰 300ሺህ ብር አሜሪካ ደርሶ መልስ ነጻ የበረራ ትኬት
💻 ላፕቶፕ ኮምፒተሮች
📲 የስልክ ቀፎዎች
🌐 የብሮድባንድ ኢንተርኔት የ6 ወር ክፍያዎች
📶 ከ10,000 በላይ 1GB የሞባይል ዳታ ስጦታዎችን ለሚያሸልመው የዕድል ጨዋታ ብቁ ይሆናሉ!
ዕጣዎቹ ቴሌብር ሱፐርአፕ https://bit.ly/telebirr_SuperApp ላይ ከጥቅምት 22 እስከ ጥቅምት 28/2018 ዓ.ም ክፍት ይሆናሉ!
#Ethiotelecom #telebirr #telebirrSuperApp #DigitalEthiopia #DigitalAfrica #RealizingDigitalEthiopia

❤94😡9🙏4😭4🤔3
" በየቀኑ ለጥበቃ 500 ብር እንከፍላለን፣ ከቆምን 17ኛ ቀናችን ነው " - ሹፌሮች
➡️ " የሚመለከታቸው አካላት መጥተው ጥራቱን አይተው አረጋግጠው ይሁኝታን ሲሰጡን ብቻ ነው መኪኖቹ እንዲያራግፉ የሚደረገው፣ እኛ ባቅማችን የምንፈታው ችግር የለም " - ወንደራ ዩኔየን (Union )
ከጅቡቲ ወደ ደብረ ብርሃን ከተማ ወደሚገኘው ወደራ ዩኔየን (Union) የአፈር ማዳበሪያ ጭነው የመጡ አሽከርካሪዎች " ማዳበሪያው የተበላሸ ስለሆነ ማውረድ አትችሉም " ተብለው በደብረ ብርሃን ከተማ 17 ቀን እንዲቆሙ በመደረጋቸው ችግር ላይ መውደቀቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታ አቅርበዋል።
አሽከርካሪዎቹ " ከክልሉ መጥተው ማዳበሪያውን ያዩት ባለሙያዎች የተላከላቸው ፎቶ እና የመጣው ማዳበሪያ እንደሚለያይ ነግረውናል፣ ሲያዩትም ተደናግጠው ነበር። ያልምንም መፍትሔ እንድንቆም በመደረጋችን እየተቸገርን ነው፣ በቃል ደረጃ ወደ አዲስ አበባ ጭነቱን ይዛችሁ ትመለሳላችሁ ብለውናል። ይሁን እንጂ በዚህ ቀን ትመለሳላችሁም አላሉንም፣ እኛ ከፍተኛ ችግር ላይ ነው ያለነው መፍትሔ ይሰጠን " ብለዋል።
ሹፌሮች በዝርዝር ምን አሉ ?
" በማህበር ደረጃ ነው ከጅቡቲ ጭነን የመጣነው፣ የተመደብነውም ከጅቡቲ ወደራ ዩኔየን ደብረብርሃን እንድናደርስ ነው።
ማዳበሪውን ወደ ኢትዮጵያ ጭነን ስንመጣ ችግር አለበት እያሉ ነበር መጀመሪያም። እኛ የምናወቀው ነገር የለም፣ ስለጥራትም የሚመለከተን ጉዳይ አይደለም፣ የታዘዝነውን መጫን እና ወደተባልነው ቦታ ማድረስ ነው። እሱንም አድርገናል።
ደብረብርሃን ከተማ ስንደርስ ግን ' ማዳበሪያው ችግር አለበት አንቀበልም ' አሉን፣ እኛም ለማህበራችን አሳውቀናል፣ እነሱም ' ለበላይ አካል አሳውቀናል ' ብለውናል፣ ሁሌም ' እየተነጋገርን ነው ' ይሉናል። ነገር ግን ከቆምን 17 ቀን ሆኖናል።
እኛ ገንዘብ የምናገኘው መኪኖችን ስናንቀሳቅስ ነው፣ ጎማ ካልተንቀሳቀሰ ምንም አናገኝም። እኛ ሹፌሮች ደግሞ ቤተሰብ አስተዳዳሪዎች ነን።
በጣም ችግር ላይ ነው ያለነው፣ እኛን የሚጠይቀን የለም፣ ከክልል የመጡ የግብርና ባለሙያዎች ናቸው ተብለው አይተውልን ነበር ማዳበሪያውን፣ ግን ' እኛ ይህን አንረከብም ይዛችሁ ሒዱልን ' ነው ያሉን፣ ደውለን ስንጠይቃቸው ደግሞ እየተነጋገርንበት ነው ይላሉ፣ በመሐል እየተጎዳን ያለነው እኛ 35 ሹፌሮች እና 35 ረዳቶች ነን።
ከክልሉ ግብርና ቢሮ የመጡት ባለሙያዎች 5 የሚሆኑ መኪኖች የጫኑትን ማዳበሪያ ፈተው አይተው አነጋግረውናል። በስአቱ ' እኛ ይህንን አንቀበልም ውሰዱ 'ሲሉን ወደት እንውሰደው ስንል ' አይመለከተንም ' ነው ያሉን። ' አንቀበልም ' የምትሉበትን ደብዳቤ ስጡን እና ለማህበሮቻችን እናስገባ ስንል አንሰጥም ብለውናል ነው ያሉት።
' ከመጋዘኑ ጊቢ ውጡ፣ የማትወጡ ከሆነ ደግሞ በፖሊስ እናሶጣቹሀለን ' ብለውናል። ይህን ያሉት የከተማ አስተዳደሩ እና የወደራ ዩኔን ሃላፊዎች ናቸው።
የዩኔኑ ጊቢ ሁሉንም መኪና ማቆም ስለማይችል ጊቢው ውስጥ 9 መኪና መጀመሪያ ገብቶ ነበር፣ ከዛም 3ቱን አስወጥተው 6 ብቻ ቀርተዋል፣ አሁን ደግሞ ሁሉንም ውጡ እያሉ ነው። ሌላው መንገድ ዳር ነው የቆሙት። የመኪና ማቆሚያ እና መጠበቂያ በየቀኑ እየከፈልን ነው።
መኪኖችን የሚጠብቁት ልጆች ራሱ አናውቃቸውም፣ በማህበር እንደተደራጁ ነው የነገሩን። ተስፋ የሚሰጠን አካል እንኳ የለም።
ሌሎች አሽከርካሪዎች ደግሞ እኛ ከመጣን 17ኛ ቀናችን ነው፣ ከእኛ ቀድመው የገቡ መኪኖች አራግፈው ነበር፣ ነገር ግን መልሳችሁ ጫኑ ተብለው ጭነዋል። የጫኝ የከፈሉት ደግሞ ሹፌሮቹ ናቸው።
ማዳበሪያው እንደተበላሸ ወደብ ላይ ስንጭን እየተናገርን ነበር፣ አሁን ደግሞ ቁሙ ከማለት ውጭ ስለሁኔታውም የሚያስረዳን አካል የለም። እኛ ስንቀሳቀስ ነው ብር የምናገኘው፣ ልጆች እናስተምራለን፣ ቤተሰብ እናስተዳድራለን፣ መኪኖቹ የባንክ እዳ አለባቸው፣ ብዙ መስራት የሚችል ንብረት ያለ ስራ ቁሟል፣ የቆምንበት ቦታም አስቸጋሪ ነው።
17 ቀን ያለምንም ስራ ስንቆም ያለንን ገንዘብ ጨርሰናል። ኪሳችን ባዶ ሆኗል። አሁን ላይ እንኳን ቤተሰብ ልንረዳ እኛም እየተቸገርን ነው።
መንገድ ላይ መኪኖችን ስላቆምን የቀን ለእያንዳንዱ መኪና 200 ብር፣ ለአዳር ደግሞ 300 ብር እየከፈልን ነው ለጥበቃዎች። አጠቃላይ በየቀኑ ሁሉም አሽከርካሪ 500 ብር ይከፍላል " ብለዋል።
ስለጉዳዩ የጠየቅናቸው አንድ የወንደራ ዩኔን የስራ ሃላፊ " ይህን ግብአት መጀመሪያ ከጅቡቲ ሲገዛ የነበሩ የሚመለከታቸው አካላት መጥተው ጥራቱን አይተው አረጋግጠው ይሁኝታን ሲሰጡን ብቻ ነው መኪኖቹ እንዲያራግፉ የሚደረገው። ይመለሳል ካሉም እንዲመለስ የምናደርገው በዚህ መልኩ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።
አክለው " እኛ ባቅማችን የምንፈታው ችግር የለም፣ ያመጡት ማዳበሪያ እስካሁን ከሚመጡት የተለየ ነው። ወደ ዱቄትነት የተቀየረ ነው፣ ይህንን ማዳበሪያ ለአርሶአደሩ ማከፋፈል ደግሞ ሌላ ችግር መፍጠር ነው " ሲሉ ተናግረዋል።
" ጥራቱን ማረጋገጥ አንችልም፣ ከጥራት ደረጃው በታች ነው ማለትም አንችልም፣ ይህንን ማረጋገጥ የሚችሉት የፌደራል እና የክልሉ ግብርና ቢሮ ናቸው ሲሉ አጭር ምላሽ ሰጥተዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamily

❤447😡61😭14🙏12😢10🕊10😱4🥰2🤔1
#NBE
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከግል እና የሶስተኛ ወገን የባንክ ሒሳብ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ ጥብቅ መመሪያ አስተላለፈ።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አደረኩት ባለው ምርመራ " ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ የባንክ ደንበኞች በዋናነት የንግድ ድርጅቶችና ግለሰብ ነጋዴዎች ለንግድ ሥራቸው ተብሎ ከተከፈተው እና በሚመለከተው የግብር ሰብሳቢ ተቋም ካስመዘገቡት የባንክ ሒሳቦች ውጭ የግል የባንክ ሂሳባቸው ወይም የሶስተኛ ወገን የባንክ ሒሳብ ተጠቅመው የተለያዩ የንግድ ግብይቶች እና የገንዘብ እንቅስቃሴዎች እየፈጸሙ መሆናቸውን አረጋግጫለሁ " ብሏል።
" ይህ አሰራር ከግብር ሰብሳቢ ባለስልጣናት ቁጥጥርና ክትትል ለመሸሽ የሚደረግ ተግባር ከመሆኑ በተጨማሪ በዚህ አግባብ የሚፈጸሙ የፋይናንስ ግብይቶች እና የገንዘብ እንቅስቃሴዎች የወንጀል ፍሬ ወይም ሽብርተኝነትን በገንዘብ ከመርዳት ጋር የተያያዙ ወይም የተገናኙ ሊሆኑ ይችላሉ " ሲል ገልጿል።
" እነዚህን መሰል ተግባራትንም ለመግታት አስፈላጊው የተቀናጀ እርምጃ እንዲወሰድ ተወስኗል " ሲል አሳውቋል።
የፋይናንስ ሥርዓቱን ጤናማነትና ታማኝነት እንዲሁም በአጠቃላይ የኢኮኖሚ ደህንነት ለመጠበቅ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለሁሉም ባንኮች የግል ባንክ ሂሳቦችን ለንግድ እና ለሕገ-ወጥ ድርጊት የሚጠቀሙ ደንበኞችን አስመልክቶ አስፈላጊ መረጃዎችን በማደራጀት እንዲልኩ መመሪያ አስተላልፏል፡፡
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

1❤711😡505😭50🤔28🙏19🕊15👏12🥰9😱7💔5😢4
TIKVAH-ETHIOPIA
“የ9 ጤና ባለሙያዎች ሕይወት አልፏል። 7ቱ ከአርሲ፣ ሁለቱ ከባሌ ናቸው” - የኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ ➡️ “የተጎዱት ወደ 8 ይደርሳሉ፤ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው አራት ናቸው። በአጠቃላይ 28 ባለሙያዎች ተሳፍረው ነበር” - ዞን ጤና ቢሮ ከኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ተውጣጥተው ለትምህርት ወደ ሐረማያ ዩኒቨርስቲ ሲጓዙ በነበሩ ጤና ባለሙያዎች በመኪና አደጋ ሞትና የአካል ጉዳት መድረሱን የክልሉና የዞኑ…
" አሽከርካሪዎች በተለይ ኦላንጪቲ ከተማን ለጉዞ በሚያቋርጡበት ወቅት ጥንቃቄ አድርጉ " - ዋና ኢንስፔክተር ስለሽ ባይ
ከትላንት በስቲያ ለሊት በምስራቅ ሸዋ ዞን ቦሳት ወረዳ ልዩ ስሙ " ጋር " የተባለ ስፍራ በደረሰው የትራፊክ አደጋ 7 የጤና ባለሙያዎችን ጨምሮ 9 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል።
አደጋው ከአዳማ ወደ መታሃራ ሲጓዝ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ከአይሱዙ መኪና ጋር በመጋጨቱ ነበር የደረሰው።
ከዚሁ አደጋ ጋር በተያያዘ የቦሰት ወረዳ የትራፊክ ደህንነት አስተባባሪ ዋና ኢንስፔክተር ስለሽ ባይ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል የአደጋው መንስኤ አሽከርካሪው ከተገቢው በላይ በፍጥነት ማሽከርከር በተለይም በምሽት መጓዝ ነው።
" መንገዱን በውል ለማያውቁት ከፍተኛ የትራክፊክ ፍሰት ስለሚያስተናግድ ጥንቃቄ ማድረግ ግዴታ ነው " ሲሉ አሳስበዋል።
በአደጋው ከሞቱት 9 ሰዎች መካከል ሰባቱ የህክምና ባለሙያዎች ሲሆኑ በአርሲ ዞን አግልግሎት ላይ የነበሩ እና ለሞያ አቅም ግንባታ እና ለፈተና ወደ ሀሮማያ ዩኒቨርስቲ ስጓዙ የነበሩ እንደሆኑ ይታወሳል።
ሶስት ከባድ የአካል ጉዳት እና አምስት ቀላል የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ስዎች በአዳማ እና ቦሳት ሆስፒታል በህክምና ላይ ይገኛሉ።
ኢንስፔክተር ስለሽ ባይ አደጋው የደረሰበት አካባቢ የከባድ ተሽከርካሪዎች መተላለፊያ መሆኑን በመጠቆም የህዝብ ማመላለሻ አሽከርካሪዎች በተለይ ኦላንጪቲ ከተማን ለጉዞ በሚያቋርጡበት ወቅት ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስበዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ነቀምቴ

❤145😢131😭36🙏10💔9🕊4
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update
የስምረት ፓርቲ መስራች ጉባኤ አቶ ጌታቸው ረዳ የፓርቲው ፕሬዝደንት አድርጎ መረጠ።
አቶ ነጋ አሰፋ ደግሞ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት አድርጎ መርጧል።
አቶ ሃፍቱ ኪሮስ ምክትል ፕሬዚዳንት እንዲሁም ሰብለ አሰፋ የፓርቲው ፅህፈት ቤት ኃላፊ ሆነዋል።
ለማእከላዊ ኮሚቴ ከመረጣቸው 31 አባላት ውስጥ ፦
1. አቶ ጌታቸው ረዳ
2. ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ሂወት
3. ወ/ሮ ኣልማዝ ገ/ፃድቕ
4. አቶ ብርሃነ ገ/የሱስ
5. አቶ ሃፍቱ ኪሮስ
6. ወ/ሮ ሰብለ ካሕሳይ
7. አቶ ነጋ ኣሰፋ
የፓርቲው ስራ አስፈፃሚ አድርጓቸዋል።
- አቶ ሙላት ገ/ስላሴ
- አቶ ጠዓመ ዓረዶም
- ዶ/ር ሺሻይ ኣማረ
- ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም
- አቶ ፀጋይ ገ/ተኽለ
- ዶ/ር ርእየ ኢሳያስ
- አቶ ገ/ሚካኤል እኑን
- አቶ ዮናስ ሃይለ
- አቶ ተስፋኣለም ይሕደጎ
- አቶ ኤርሚያስ ኣባቡ
- አቶ ስላስ ሃፍቱ
- አቶ ፀጋይ ፃዲቕ
- አቶ የማነ ንጉስ
- አቶ ሃፍቱ ወ/ንስአ
- አቶ ደስታ ግርማይ
- አቶ ወ/ሰንበት ተ/ኪሮስ
- አቶ መብራት ስዩም
- ዶ/ር ዮናስ ገ/ሄር
- ዶ/ር ከላሊ ኣድሀና
- ቀሺ በሪሁ ሓዱሽ
- አቶ ተዘራ ጌታሁን
- አቶ ፍፁም ለገሰ
- ወ/ሮ ኣስኳል ገብረ
- አቶ ፀጋይ ገ/ጂወርጊስ
ደግሞ የፓርቲው የማእከላይ ኮሚቴ አድርጎ በመምረጥ የአንድ ቀን ጉባኤውን ማምሻውን አጠናቋል።

❤477😡92🤔39😭28🕊15🙏8💔5😢4
TIKVAH-ETHIOPIA
" ሾፌሩ ምንም ጉዳት ሳይደርስበት ከተገለበጠው ተሽከርካሪ ውስጥ ወጥቷል ! " ዛሬ ጥቅምት 14/2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ አረዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ሶር አምባ ሆቴል ፊት ለፊት ከቀኑ 6:45 ሠዓት ላይ የትራፊክ አደጋ የአጋጠመ ሲሆን በአደጋው በንብረት ላይ መጠነኛ ጉዳት ከመድረሱ በስተቀር በሠው ላይ የደረሰ ጉዳት የለም። አደጋው በደረሰበት ሰዓት መኪናውን እያሽከረከረ የነበረዉ ሾፌር ምንም…
" ተአምር ነው ! "
ተሽከርካሪው 150 ሜትር ርዝማኔ ያለው ገደል ገብቶ አርሶ አደር ግቢ ውስጥ ቢያርፍም ከቀላል ጉዳት ውጪ ያጋጠመ ከባድ ጉዳትና ሞት የለም።
በትግራይ ክልል የሚገኘው የጥንታዊው አቡነ አረጋዊ ገዳም ዝክር በየዓመቱ የአገር ውስጥና ከውጭ የሚመጡ ምእመናን በተገኙነት ጥቅምት 14 ነው የሚከበረው።
ታዲያ " ቶዮታ ሪቮልዩሽን " በሚባለው ተሽከርካሪ ባለቤቱ እራሱን ጨምሮ 5 ሰዎች ጭኖ ዓመታዊው የአቡነ አረጋዊ ገዳም ለመሳለም በመጓዝ ላይ እያለ ተሽከርካሪው መንገድ ስቶ ተንሸራቶ ገደል ይገባል።
ተሽከርካሪው የገባበት ገደል ርዝማኔው 150 ሜትር ነው ብለዋል የአይን እማኞች።
ተሽከርካሪው መንገድ ስቶ ወደ ገደል ከተወረወረ በኃላ በፎቶው እንደሚታየው ወደ አንድ አርሶ አደር ቤት ግቢ ገብቶ ተዘቅዝቆ አርፏል።
ከአስፈሪ ገደል ተወርውሮ በሚታየው መልኩ ያረፈው ተሽከርካሪ በአርሶ አደር ቅጥር ግቢ ከነበሩት ሰዎችና እንስሳት ላይ አንድ ቀላል ጉዳት ከማድረሱ ውጪ የተከሰተ ከባድ ጉዳትና ሞት የለም።
ክስቱቱን ለሰሙት " ተአምር " ያስባለ እንደሆነ የቲክቫህ ኢትዮጵያ መቐለ ቤተሰብ አባል ገልጾልናል።
አሽከርካሪዎች ለማሽከርከር በሚያዳግቱና ተዳፋት በሆኑ መንገዶች ላይ ሲያሽከረክሩ እርጋታና ማስተዋል ሊለያቸው አይገባም።

❤605🙏279😱23🤔19👏13🕊8💔6😡4🥰2😭2