የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የ2018 የቲክኒክና ሙያ ሰልጣኞች መግቢያ ነጥብ ይፋ አድርጓል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመለከተው የተቋሙ ደብዳቤ፣ በ2018 ዓ/ም የስልጠና ዘመን ወደ ቲክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት የሚገቡ ሰልጣኞች የመግቢያ ነጥብ በ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ውጤታቸው መሰረት ለተፈጥሮና ማህበራዊ ሳይንስ የመግቢያ ውጤት ከደረጃ 1 እስከ 5 በዝርዝር አስቀምጧል።
የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ እና ቅድመ ዝግጅት (12ኛ ክፍል) ላጠናቀቁ ደረጃ 1 እና ደረጃ 2 ሰልጣኞች መቁረጫ ነጥብ፦
-ለወንዶች አርብቶ አደር አካባቢዎችን ሳይጨምር 134 እና ከዚያ በታች፣
-ለወንዶች አርብቶ አደር አካባቢዎች 132 እና ከዚያ በታች፣
-ሴቶች አርብቶ አደር አካባቢዎችን ሳይጨምር 121 እና ከዚያ በታች፣
-ሴቶች አርብቶ አደር አካባቢዎች 120 እና ከዚያ በታች፣
-ለሁሉም ክልል አካል ጉዳተኞች 120 እና ከዚያ በታች ሆኖ ተቆርጧል።
የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ እና ቅድመ ዝግጅት (12ኛ ክፍል) ላጠናቀቁ ደረጃ 3 እና 4 ሰልጣኞች መቁረጫ የጥብ፦
-ወንዶች አርብቶ አደር አካባቢዎችን ሳይጨምር 135 እና ከዚያ በላይ፤
-ወንዶች አርብቶ አደር አካባቢዎች 133 እና ከዚያ በላይ፤
-ሴቶች አርብቶ አደር አካባቢዎችን ሳይጨምር 122 እና ከዚያ በላይ፤
-ሴቶች አርብቶ አደር አካባቢዎች 121 እና ከዚያ በላይ፤
-ለሁሉም ክልል አካል ጉዳተኞች 121 እና ከዚያ በላይ ሆኖ ተቆርጧል።
እንዲሁም፣ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ እና ቅድመ ዝግጅት (12ኛ ክፍል) ላጠናቀቁ ደረጃ 5 ሰልጣኞች መቁረጫ ነጥብ፦
-ወንዶች አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር 179 እና ከዚያ በላይ፤
-ወንዶች አርብቶ አደር አካባቢዎች 168 እና ከዚያ በላይ፤
-ሴቶች አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር 168 እና ከዚያ በላይ፤
-ሴቶች አርብቶ አደር አካባቢ 157 እና ከዚያ በላይ፤
-ለሁሉም ክልል አካል ጉዳተኞች 142 እና ከዚያ በላይ ሆኖ ተቆርጧል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia

1❤725🙏42😭42🤔21😡17👏15🕊14💔14🥰3😱1😢1
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ፦ የታላቁ አባት የተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ አስክሬን ፒያሳ በሚገኘው ኑር መስጂድ የዱዓ እና የሽኝት ሥነ-ሥርዓት ተካሄደ። የተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ አስከሬን ለ40 ዓመታት ባስተማሩበት ኑር መስጂድ ሶላተል ጀናዛ ተሰግዶበታል። ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ ሥርዓተ ቀብራቸው የሚፈፀም ይሆናል። Photo Credit - EBC & ENA @tikvahethiopia
የታላቁ የሃይማኖት አባት የቀድሞው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ሥርዓተ ቀብር ተፈጽሟል።
ከስርዓተ ቀብራቸው ቀደም ብሎ በሚሊኒየም አዳራሽ ሽኝት ተደርጓል።
ታላቁ የሃይማኖት አባት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር በታላቁ አንዋር እና በኑር (በኒ) መስጂዶች ከአራት አስትርት ዓመታት በላይ ኢስላማዊ ሃይማኖታዊ ትምህርት አስተምረዋል።
ከ50 በላይ ሃይማኖታዊ መጽሐፍትንም ጽፈዋል፡፡
ቅዱስ ቁርአንንም ተርጉመዋል፡፡ የቁርአን ትርጉም ሥራቸውን በሲዲ በማሳተም አሰራጭተዋል፡፡
ከ50 ዓመታት በላይ በዘለቀ የአዲስ አበባ ቆይታ ቅዱስ ቁርአንን ከ300 ጊዜ በላይ በትርጉም (ተፍሲር) አስተምረዋል፡፡
ተቀዳሚ ሙፍቲ በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች የተፈጠሩ ሃይማኖታዊ አለመግባባቶችን በመፍታት የሃይማኖታዊ አባትነታቸውን ሚና ተወጥተዋል።
በ1967 ዓ.ም የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ሲመሰረት የምክር ቤቱ አባልና የዑለማ ሊቀመንበር በመሆን አገልግለዋል።
ከ2010 መጋቢት እስከ ግንቦት ወር 2014 ዓ.ል ድረስ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትን በፕሬዚዳንትነት እንዲሁም የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ በመሆን አገልግለዋል፡፡
ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ባለትዳርና የአምስት ወንዶችና የአራት ሴቶች አባት እንደነበሩ ከጠቅላይ ምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

❤1.41K😭658🕊87💔76🙏46😢35🥰22🤔16😱11😡8
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ኢትዮጵያ በጣት ከሚቆጠሩ አረጋውያን፣ አፈ ማር ከሆኑ መካሪዎችዋ መካከል አንዱ የሆኑትን፣ ለመወደድ የታደሉትን የዘመናችን ጌጥ አጥታለች።
ይህንን የድካም ዓለም መገላገል ለእርሳቸው ዕረፍት ቢሆንም ለአገር ግን ታላቅ ጉዳት ከመሆኑም በላይ ዕድሜን ከጥበብ ጋር ያዋሐዱ በሁሉ ዘመን አይገኙምና ኀዘናችን ጥልቅ ነው። " - ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
ፎቶ ፦ ቅዱስነታቸው በተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ሽኝት ላይ በእምባ ተሞልተው ነበር።
Photo Credit - Ahmed Nega

2😭2.87K❤825🙏149💔91🕊63😢37😡16👏13🥰8😱7
" እርቦናል፤ ጠምቶናል ፣ የ8 ወር ደመወዝ አልተከፈለንም። ... በመጠጥ ውሃም ችግር ላይ ወድቀናል፣ እኛ ማንን እንጠይቅ፣ በየጊዜው አመራሮች ይቀያየራሉ፣ ህዝቡ ተቸግሯል " - ሰልፈኞቹ
➡️ " የሀገር ሽማግሌዎች መጥተው ' ለ3 ቀን ታገሱን ' ሲሉ ጠየቁን፣ እኛም አባቶቻችንን ማስከፋት ስላልፈለግን እሺ ብለናቸዋል "
በአፋር ክልል የገዋኔ ወረዳ ዞን 3 ነዋሪዎች ከደመወዝ ጥያቄ እና ከመጠጥ ውሃ ችግር ጋር በተገናኘ በዛሬው እለት ጥቅምት 10/2018 ዓ/ም ከጠዋቱ ሶስት ሰአት አካባቢ ህዝባዊ ተቃውሞ ሰልፍ መንገድ በመዝጋት አካሂደዋል።
ሰልፈኞቹ በሰልፉ ላይ ፦
- " ካልተከፈለን አናስተምርም "
- " እኛ የገዋኔ ነዋሪዎች እርቦናል ፤ ጠምቶናል "
- " ለወላጅ አልባ ህጻናት የ8 ወር ደመዝ ይሰጠን " የሚሉ እና ሌሎችም ደምጾችን አሰምተዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያም በሰልፉ ላይ የነበሩ የወረዳ ነዋሪዎችን ስለጉዳዩ ጠይቋል።
ነዋሪዎቹ በዝርዝር ምን አሉ ?
" የገዋኔ ወረዳ ሁሉም የመንግስት ሰራተኞች በ2017 ዓ.ም የ5 ወር ደመወዝ አልተከፈለንም፣ በ2018 ዓ.ም በጀት አመት ደግሞ የሀምሌ፣ የነሀሴ እና የመስከረም ወር አልተከፈለንም። በአጠቃላይ የ8 ወር ማለት ነው።
ይህ የሆነው በወረዳው የፋይናንስ ጽህፈት ቤት ሃለፊ ነው። ሃላፊው ወረዳው ላይ አይኖርም፣ አዲስ አበባ እና አዋሽ እንደሚኖር ነው የሰማነው። ቢሮ ስንሄድ አናገኘውም። ችግሩ የማን እንደሆነም እንኳ ማወቅ አልቻልንም።
ክልሉ እራሱ ጥያቄያችንን ሰምቷል፣ በባለፈው አመት ሲከፍሉን የመቼ፣ የመቼ ወር እንኳ እንደከፈሉ አልነገሩንም።
አልፎ አልፎ ይከፍላሉ፣ እኛን እያዘናጉን ነው፣ በዘንድሮው አመት ችግሮች ይስተካከላሉ ብለን ስንጠብቅ ይሄው መስከረም አልቆ ጥቅምት ላይ ነን፣ እስካሁን ግን የተስተካከለ ነገር የለም።
የመጠጥ ውሃ ችግር በክልሉ እንደአጠቃላይ እንዳለ እናውቃለን፣ ነገር ግን የእኛ የተለየ ነው፣ ይህን የውሃ ችግር ለመቅረፍ በ2012 ዓ.ም ከወረዳዋ 30 ኪሎሜትር እርቀት ላይ ከሚገኝ ቦታ ተቆፍሮ ተሰርቶ ነበር። ነገር ግን ብዙም ሳይቆይ ተበላሽቷል፣ ከዛም በኋላ ችግሩ ተበብሶ ቀጥሏል።
አሁን ላይ አንዱን የሮቶ ውሃው ከ250 እስከ 350 ብር እየገዛን ነው፣ ይህንን ራሱ ለመግዛት እንኳ ደመወዛችን እየተሰጠን አይደለም። የገዋኔ ነዋሪ እያየው ያለው ሰቆቃ በጣም ያሳዝናል።
የወረዳዋ ነዋሪዎች አብዛኞቹ ወላጅ አልባ ህፃናት ናቸው። እርዳታ አያገኙም፣ በጣም ችግር ላይ ናቸው፣ ደመወዝ በአግባቡ ቢሰጥ ኖሮ በቤተሰቦቻቹው የጡረታ ገንዘብ ይተዳደሩ ነበር። ይህ ግን አልሆነም።
ከሌላ አካባቢ መጥተው በወረዳዋ በመምህርነት የሚያገለግሉ መምህራኖች ስራቸውን ለቀው ወጥተዋል። በዛሬው እለትም ከትምህርት ቤት ተማሪዎች ተመልሰዋል።
መብላት እና መጠጣት ያልቻለ መምህር እንደት አድርጎ ያስተምራል ? እኛ ማንን እንጠይቅ፣ በየጊዜው አመራሮች ይቀያየራሉ፣ ህዝቡ ተቸግሯል።
ይህን ተከትሎ በዛሬው እለት የወረዳው ነዋሪ ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተን ነበር። ሰልፍ የወጡት ወጣቶች በመሃል መንገድ ላይ ደረቅ እንጨት እሳት በመለኮስ ተቃውሞ አሰምተናል። ለተወሰነ ደቂቃም የትኛውም ተሽከርካሪ እንዳይንቀሳቀስ አግደን ነበር። ሰልፍ ላይ እያለን የሀገር ሽማግሌዎች መጥተው ' ለ3 ቀን ታገሱን ' ሲሉ ጠየቁን፣ እኛም አባቶቻችንን ማስከፋት ስላልፈለግን እሺ ብለናቸዋል።
አባቶች በስአቱ ያሉን ' መንገዱን ክፈቱት መኪኖች ይሒዱ፣ ለእኛ ደግሞ የሶስት ቀን እድሜ ስጡን፣ ችግሩን ለመቅረፍ በዚህ ሶስት ቀን እኛ የወረዳውን አስተዳደር እንጠይቅ፣ መፍትሔ ከሌለው ግን ለእናንተ እናሳውቃለን ' ነው ያሉት፣ እነሱን የላካቸው የወረዳው አስተዳደር እንደሆነም ሰምተናል።
ሰልፍ የወጣንበት ዋነኛ ምክንያት ለ8 አመት በመጠጥ ውሃ ችግር ላይ በመሆናችን፣ የመንግስት ሰራተኛው ደግሞ የ8 ወር ደመወዝ ስላልተከፈለው ነው። የጡረታ ደመወዝ የሚያገኙ ህፃናት በርሃብ ውስጥ ስለሆኑ ነው።
ውሃ የምንገዛው በየወሩ ነው። ይህንንም የምናገኘው በመከራ ነው። ውሃውን የሚያመጡት የመንግስት መኪኖች ናቸው። በየጊዜው ጥያቄ ስንጠይቅ መፍትሔ እናመጣለን ነው ወረዳው ምላሹ፣ ዛሬ ደግሞ የሀገር ሽማግሌዎች ሰልፍ ላይ እያለን ለሶስት ቀን እንዲንታገስ ጠይቀውናል፣ ነገር ግን አስቡት እስኪ 8 አመት ለተጠየቀ ጥያቄ በ8 አመት መመለስ ሳይችሉ በሶስት ቀን ይመለሳል ብሎ ማሰብ ከባድ ነው " ብለዋል።
ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃላቸውን ከሰጡ መካከል በወረዳው የአመራርነት የስራ ሃላፊነት ያላቸው አንድ አካል ጉዳዩ በቀላሉ እንደማይፈታ እና የፌደራል መንግስት የማህበረሰቡን ችግር ተገንዝቦ መፍትሔ ቢሰጥ የተሻለ እንደሚሆን ተናግረዋል።

❤315😭134👏11😢8😡4🙏3💔2🥰1🕊1
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Earthquake
ዛሬ ጥቅምት 10 ቀን 2018 ዓ.ም ምሽት ላይ ከዓዲግራት ደቡባዊ ምስራቅ 43 ኪሎሜትር የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ በበርካታ አከባቢዎች ላይ ንዝረት ተሰምቷል።
ከምሽቱ 1:30 የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ በሬክተር ስኬል 4.5 የተለካ እንደሆነ የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቨይ መረጃ ያሳያል።
የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረቱ ከተሰማባቸው አካባቢዎች አንዷ የትግራይ መዲና መቐለ ስትሆን ንዝረቱ በተለይም በፎቅ/ህንፃዎች ላይ አስፈሪ ስሜት እንደነበር የቲክቫህ ኢትዮጵያ መቐለ ቤተሰብ አባል ገልጿል።
ከጥቅምት 2 ቀን 2018 ዓ.ም ወዲህ ንዝረቱ ትግራይ እና አፋር በርካታ አካባቢዎች ጎልቶ የሚሰማ የተለያየ ልኬት ያለው መሬት መንቀጥቀጥ እየተሰማ ነው።
በተለይ እሁድ ጥቅምት 2/2018 ዓ.ም የተከሰተው በሬክተር ስኬል 5.6 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ አፋር ክልል የሰው ህይወት ቀጥፎ በርካታ ቤቶችን አፍርሶ ከ40 ሺህ በላይ ሰዎች ያለመጠለያ እንዲቀሩ አድርጓል። በተመሳሳይ በትግራይ ምስራቃዊ ዞን አፅቢ ወምበርታ ወረዳ ቤቶች እንዲፈርሱ ምክንያት ሆኗል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

❤101😭72🙏15😱11💔6😢5🕊4👏3
TIKVAH-ETHIOPIA
" ኢትዮጵያ በጣት ከሚቆጠሩ አረጋውያን፣ አፈ ማር ከሆኑ መካሪዎችዋ መካከል አንዱ የሆኑትን፣ ለመወደድ የታደሉትን የዘመናችን ጌጥ አጥታለች። ይህንን የድካም ዓለም መገላገል ለእርሳቸው ዕረፍት ቢሆንም ለአገር ግን ታላቅ ጉዳት ከመሆኑም በላይ ዕድሜን ከጥበብ ጋር ያዋሐዱ በሁሉ ዘመን አይገኙምና ኀዘናችን ጥልቅ ነው። " - ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ…
" ሀገራችንን አላህ ሰላም ያድርግልን። ሀገራችንን አላህ አማን ያድርግልን።
እኛም የምንዋደድ አላህ ያድርገን። የምንከባብር አላህ ያድርገን። የምንረዳዳ አላህ ያድርገን። የምንመካከር አላህ ያድርገን።
ጥላቻን ከውስጣችን አላህ ያጥፋው።
በሃይማኖትም ሆነ በፖለቲካ መገዳደልን፣ መጋጨትን፣ መለያየትን ከሀገራችን ከውስጣችን አላህ ያንሳልን።
እንደ አባቶቻችን ከዛም በበለጠ የምንተባበር ፣ የምንከባበር፣ የምንዋደድ ፣ የምንረዳዳ አላህ ያድረገን። " - ታላቁ አባት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ

🙏378😭151❤127🕊25💔16👏11😢5