Telegram Web Link
ኢትዮጵያ ብድሯን በዩዋን ለመክፈል ለቻይና ይፋዊ ጥያቄ አቅርባለች።

ኢትዮጵያ ከቻይና ከተበደረችው 5.38 ቢሊየን ዶላር ቢያንስ ከፊሉን ብድር በዩዋን ለመክፈል ከቻይና ጋር መነጋገር ጀምራለች።

ይህንን ጥያቄ ኢትዮጵያ በይፋ ማቅረቧንም የብሔራዊ ባንክ ገዢ አቶ እዮብ ተካልኝ የዓለም የገንዘብ ድርጅት (IMF) ጉባኤ ላይ በነበራቸው ቃለመጠይቅ ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ እዳዋን በዩዋን ለመክፈል ከቻይና ጋር ስምምነት ላይ የምትደርስ ከሆነ በዶላር ትከፍል ከነበረው አነስተኛ ወለድ እንድትከፍል ያግዛታል።

በተመሳሳይ ስምምነት በቅርቡ ኬኒያ እዳዋን በዩዋን ለመክፈል ከቻይና መንግስት ጋር ሥምምነት ላይ በመድረሷ ሀገሪቱ 215 ሚሊዮን ዶላር የወለድ ክፍያ ማዳን ችላለች።

የብሔራዊ ባንክ ገዢው አቶ እዮብ ተካልኝ ይፋዊ ጥያቄ መቅረቡን ይግለጹ እንጂ በእዳው ምን ያህሉን በዩዋን ለመክፈል እንደታቀደ ከመግለፅ ተቆጥበዋል።

ምንጭ: ብሉምበርግ

@TikvahethMagazine
61🤣40👎4🕊3👍1👏1
"የአገልግሎት ለውጥ ያደረጉ በሊዝ የሚተዳደሩ 2,969 ቦታዎች የአገልግሎት ለውጥ ጥያቄያቸው ተቀባይነት አግኝቷል" - የአዲስ አበባ ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ሳይፈቀድላቸው የአገልግሎት ለውጥ ያደረጉ በሊዝ የሚተዳደሩ 2,969 ቦታዎች ወደሕጋዊ ሥርዓት እንዲገቡ የአገልግሎት ለውጥ ጥያቄዎችን ተቀብሎ ፈቃድ መስጠቱን አስታውቋል።

በእስካሁኑ ተፈቅዶላቸው የአገልግሎት ለውጥ ያደረጉ ባለይዞታዎች 2,969 ሲሆኑ 2,581 (86%) የሊዝ ባለይዞታዎች የሚጠበቅባቸውን ቅድመ ክፍያ ከፍለው በማጠናቀቅ ወደ ሕጋዊ ሥርዓት እንዲገቡ ወይም የንግድ ሥራቸውን እንዲቀጥሉ ተደርጓል ነው ያለው።

በበጀት ዓመቱ ከዚህ የአገልግሎት ለውጥ 2.4 ቢሊዮን ብር ገቢ ይሰባሰባል ተብሎ እንደሚጠበቅ የአዲስ አበባ ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ገልጿል።

ሳይፈቀድላቸው የአገልግሎት ለውጥ ያደረጉና ለውጥ የተፈቀደላቸው የሊዝ ባለይዞታዎች የሚጠበቅባቸውን የሊዝ ቅድመ-ክፍያ እስከ ግንቦት 30/2018 ዓ.ም ድረስ ከፍለው ማጠናቀቅ እንደሚጠበቅባቸውም ቢሮው አሳስቧል።

@TikvahethMagazine
69🤣16😢8👍1👎1🕊1
በሰው ሰራሽ አስተውህሎት የሚደረጉ የሃቅ ማጣራቶችን ማመን እንችላለን?

የሰው ሰራሽ አስተውህሎት ቻትቦቶችን (AI chatbot) ሃቆችን ለማጣራት መጠቀም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል። እነዚህ ቻትቦቶች የሚሰጡት ምላሽ ግን ሁሌም ልናምነው የሚገባ አይደለም።

በቅርቡ ቴክራዳር በተሰኘ ተቋም የተደረገ ጥናት 27 በመቶ አሜሪካውያን የተለመዱትን እንደ ጎግል ያሉ የመፈለጊያ መንገዶች ከመጠቀም ይልቅ የሰው ሰራሽ አስተውህሎት መተግበሪያዎችን ሲጠቀሙ እነዚህ መተግበሪያዎች የሚሰጡትን መረጃ ምን ያህል ትክክል ነው የሚለው ግን ጥያቄ ነው።

ቢቢሲ ባደረገው ጥናት በራሱ በቢቢሲ የተሰሩ ዜናዎችን መሰረት አድርጎ እንደ 'CHATGPT, COPILOT,GEMINI እና PERPLEXITY' ያሉ የሰው ሰራሽ አስተውህሎት መተግበሪያዎችን ጥያቄ ሲጠይቅ 13 በመቶዎቹ በዜናዎቹ ውስጥ የተጠቀሱትን ቀይረዋል አሊያም ደግሞ ያልተጠቀሰ ነገር አካተዋል።

የሰው ሰራሽ መተግበሪያዎቹ የተሳሳተ መረጃና ምንጭ ከማቅረባቸው በተጨማሪ  በአግባቡ መመለስ የማይችሉትን ጥያቄ ሲጠየቁ እየፈጠሩ እያቀረቡ ነው።

የሰው ሰራሽ አስተውህሎት የሚሰጠንን መረጃ ከተለያየ ምንጮች የሚያሰባስብ ሲሆን መጀመሪያውንም ምንጮቹ የተዛቡና የተሳሳተ ከሆኑ መተግበሪያዎቹ ተገቢውን ምላሽ ሊሰጡን አይችሉም የሚለው ሃሳብ ለችግሩ በምክንያትነት ከሚቀርቡት ዋነኛው ነው።

በተጨማሪ እንደ Grok ያሉ የሰው ሰራሽ አስተውህሎት መተግበሪያዎች በፖለቲካ ከመቃኘታቸው አንፃር የተዛባ መረጃን ይሰጣሉ።

እንደዚሁም መተግበሪያዎቹ በሰው ሰራሽ አስተውህሎት የተሰሩ ምስሎችን እንደ እውነተኛ ምስሎች እየሰየሙ ነው።

ባለሙያዎች ቀለል ያሉ የሃቅ ማጣራቶችን በሰው ሰራሽ አስተውህሎት መተግበሪያ ማከናወን እንደሚቻል ቢመክሩም ሙሉ ለሙሉ እነሱ ላይ ጥገኛ መሆንን ግን አያበረታቱም።

ፅሁፉ የተገኘው ከDW ገፅ ነው።

@TikvahethMagazine
37👍11🙏3
2025/10/23 09:04:10
Back to Top
HTML Embed Code: