የኤም 23 ታጣቂዎች ከግንቦት ወር ጀምሮ 70 ሚሊየን ዶላር ዋጋ ያለው ወርቅ መዝረፋቸው ተነገረ።
በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎ የሚንቀሳቀሰው ታጣቂው በያዘው የማዕድን ማውጫ አካባቢ ከ500 ኪሎግራም በላይ ወርቅ ከግንቦት ወር ጀምሮ መዝረፉ ተዘግቧል።
በሩዋንዳ የሚደገፈው ታጣቂ ቡድኑ ከዲሞክራቲክ ኮንጎ መንግስት ጋር ግጭት ውስጥ ሲሆን ይህንን የወርቅ ማውጫም የያዘው በግንቦት ወር ነበር።
የወርቅ ማውጫውን ያስተዳድር የነበረው ድርጅትም 500 ኪሎግራም ወርቅ ካወጡ በኋላ መሬት ስር ባሉ ማስተላለፊያዎች ማጓጓዛቸውን አስታውቋል።
ኮንጎ ከሩዋንዳ ጋር የምትዋሰንበት የምስራቃዊ ኮንጎ ቀጣና በማዕድን የበለፀገ ቢሆንም ሩዋንዳ የምትደግፋቸው የኤም 23 ታጣቂዎች በብዛት ተቆጣጥረውታል።
ግጭቱን የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጣልቃ ገብተው አስቁመው የሰላም ስምምነት ሁለተ አገራት ቢፈራረሙም ተፈፃሚ ሊሆን አልቻለም።
መረጃው የሮይተርስ ነው።
@TikvahethMagazine

❤54💔8🤬4🤣2👎1
#የሥራ_ማስታወቂያ
ዴቫፋስ ኤሌክትሪካል ኮንሰልታንሲ ኃ.የተ.የግ.ማ ለጀማሪ ኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ ምሩቃን የሥራ እድል አቅርቧል።
ዝርዝሩን ከላይ ከተያያዘው ማስታወቂያ መመልከት ይችላሉ።
@TikvahethMagazine
ዴቫፋስ ኤሌክትሪካል ኮንሰልታንሲ ኃ.የተ.የግ.ማ ለጀማሪ ኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ ምሩቃን የሥራ እድል አቅርቧል።
ዝርዝሩን ከላይ ከተያያዘው ማስታወቂያ መመልከት ይችላሉ።
@TikvahethMagazine
❤30👎5🤯2😢2
ከሱዳን ጦርነት የምታተርፈው ግብፅ
የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ከሱዳኗ ፖርት ሱዳን ወደ ሃገሯ የሚደረጉ በረራዎችን ከከለከለች በኋላ የሱዳን የወርቅ ንግድ መዛባት ገጥሞታል።
የሱዳን ጦር ምንም እንኳን ኤምሬቶችን የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉን ትደግፋለች ብሎ ቢወነጅልም፣ የውጪ ምንዛሬውን ያገኝ የነበረው ወደዚሁ ወደሚወነጅላት ሃገር ከሚልከው ወርቅ ነበር።
የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ባለፈው ነሐሴ ከፖርት ሱዳን ወደ ሃገሯ የሚደረግን ሁሉንም የንግድ በረራዎች የከለከለች ሲሆን ወደቧንም ለሱዳን ዝግ አድርጋለች።
ይህም የሱዳንን ህጋዊ የወርቅ የወጪ ንግድ ሲጎዳው መገበያያ ገንዘቧም ቀንሶ አንድ ዶላር ይሸጥበት ከነበረው 2200 ወደ 3600 የሱዳን ፓውንድ በመግባት 40 በመቶ ዋጋውን አጥቷል።
የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች 90 በመቶ የሚሆነውን የሱዳን የወርቅ ገበያ ትይዝ የነበረ ሲሆን እስከ 2025 አጋማሽ ድረስ ብቻ 840 ሚሊየን ዶላር ዋጋ ያለው 8.8 ሚሊየን ቶን ወርቅ ከሱዳን አስገብታለች። ወደ ኤምሬቶች በህገወጥ የሚገባው ወርቅ ደግሞ ከዚህም በ4 እጥፍ ይልቃል።
የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የሱዳንን በረራ መከልከል ተከትሎ ግን ግብፅ ተጠቃሚ መሆን ጀምራለች።
የበረራ መከልከሉን ተከትሎ የሱዳን ወርቅ ወደ ግብፅ እየተላከ ሲሆን ግብፅም ከፍተኛ ጥቅም በማግኘት ወርቁን ወደ ተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ዳግም ትልካለች።
የግብፅን ያህል ባይሆንም ኳታርና ኦማንም የሱዳን ወርቅ አልፎባቸው ወደ ኤምሬቶች የሚገቡባቸው ሃገራት ሆነዋል።
ዘገባው ከሮይተርስ የተገኘ ነው።

❤80😢26🤔15👍6
ሙሉ ኮከብ ሪልሰቴት በሲኤምሲ የሚገኝ ከ ስኩል ኦፍ ቱሞሮ ዝቅ ብሎ የሚገኝ እጅግ ዘመናዊ ና ጥራታቸውን የጠበቁ አፓርትመንት ቤቶች ይዘንሎት ቀርበናል
👉ግንባታቸው 100% የተጠናቀቁ ቅንጡ አፓርታማ ቤቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ከባለ 1 መኝታ እስከ ባለ 4 መኝታ የተለያዬ የካሬ አማራጭ የያዘ
👉60% የባንክ ብድር አማራጭ የተዘጋጀላቸው
👉ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቁ እና በግንባታ ላይ ያሉ።
🔸2 ሊፍት
🔸️የከርሰ ምድር ውሃ
🔸️backup ጀነኔተር
🔸️የ ልጆች መጫወቻ እና አረንጓዴ ስፍራ የተሟላለት 3000 ካሬ ላይ ያረፈ ቅንጡ ኮምፓውንድ አፓርትመንት በኢትዮጵያ ብር ለሽያጭ አቅረበናል።
ባለ 1 መኝታ 82 ካሬ
ባለ 2 መኝታ 96,99, እና 105ካሬ
ባለ 3 መኝታ 120,124 እና 127 ካሬ
ባለ 4 መኝታ 181 ካሬ
60%ባንክ ብድር የተመቻቸላቸው ዲጅታል የተናጥል ካርታ የተዘጋጀላቸው
📣በ መሀል CMC መኖሪያ ቤቶን ይግዙ።
ለበለጠ መረጃ
💁♂📞 +2519-21-85-72-39
+2519-48-74-31-71

❤6👎1
ፕሬዚዳንት ትራምፕ ለግዙፉ የክሪፕቶከረንሲ መገበያያ ስርዓት ባይናንስ መስራች ቻንግፔንግ ዣኦ ምህረት አደረጉ።
ባይናንስ የተሰኘው ግዙፉን የክሪፕቶከረንሲ መገበያያ ተቋም የመሰረተው ዣኦ እሱ በመሰረተው ባይናንስ የገንዘብ ማጭበርበር እንዲደረግ አድርጓል በሚል ተከሶ አራት ወራትን በእስር እንዳሳለፈና ባይናንስም 4 ቢሊየን ዶላር ቅጣት እንዲከፍል ተወስኖ ነበር።
ዣኦ 50 ሚሊየን ዶላር ለመክፈል መስማማቱ የሚታወስ ሲሆን በዚሁ የተነሳም ከባይናንስ ኃላፊነቱም ለቋል።
የኋይት ሃውስ ቃለ አቀባይ ካሮሊን ሊያቪት ትራምፕ የምህረት ደብዳቤውን መፈረማቸውን አረጋግጠው " ዣኦ ምንም ጥፋት አልሰራም፤ የባይደን አስተዳደር ክሪፕቶከረንሲን ለማጥፋት የወሰነው ውሳኔ ነበር" ብለዋል።
አክለውም ውሳኔው አሜሪካ የቴክኖሎጂ እና ፈጠራ መሪ በመሆን የነበራትን ስም አጉድፏል በማለት የባይደን አስተዳደር በክሪፕቶ ላይ የነበረው ጦርነት አብቅቷልም ብለዋል።
ዣኦም ለውሳኔው ትራምፕን ሲያመሰግን የመሰረተው መገበያያ ባይናንስም ምስጋናውን አድርሷል።
የትራምፕ አስተዳደር ወደ ስልጣን ከተመለሰ በኋላ ለክሪፕቶከረንሲ ከፍተኛ ትኩረት የሰጠ ሲሆን አሜሪካንም በዘርፉ ቀዳሚ ለማድረግ እንደሚሰራ በተደጋጋሚ ተገልጿል።
መረጃው የተገኘው ከኤንቢሲ ነው።

❤53👍16🤣15👎1
በሱዳን ከ30 ሚሊየን ሰዎች በላይ አስቸኳይ የሰብዓዊ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል ተባለ።
አለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት፣ የተመድ የስደተኞች ኤጀንሲ፣ ዩኒሴፍ እና የአለም የምግብ ፕሮግራም ሱዳን በአለም ላይ ከባዱን የአስቸኳይ እርዳታ አጋጥሟታል ሲሉ 9.6 ሚሊየን የውስጥ ተፈናቃዮችን ጨምሮ 15 ሚሊየን ህፃናት ችግር ውስጥ ናቸው ብለዋል።
በሱዳን በተወሰነ መልኩ መረጋጋት ከታየ በኋላ 2.6 ሚሊየን ተፈናቃዮች ወደነበሩበት ቦታ ተመልሰዋል ሲባል በግጭቱ በርካታ ቤቶች እና አገልግሎቶች ወድመዋል ተብሏል።
በሱዳን የኮሌራና የወባ በሽታ ስርጭት አስጊ ነው ሲሉ ለትምህርት ከደረሱ 17 ሚሊየን ህፃናት መካከል 14 ሚሊየኑ ከትምህርት ገበታ ውጪ ሆነዋልም ተብሏል።
የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ በያዛት ኤልፋሸር ከ260 ሺህ በላይ ሰዎች ላለፉት 16 ወራት ከእርዳታ ተነጥለዋል ተብሏል።
መረጃው ከሚድል ኢስት ሞኒተር የተገኘ ነው።

❤29😢24🕊2🙏1
ይህ ፎቶ መነሻው ከየት ነው ?
በማኅበራዊ ሚዲያው ሰፊ መነጋገሪያ ከሆነው ፎቶ መካከል ፖሊሶች በጀሪካን ያለ አረቄን ሲያስደፉ የሚያሳዩ ፎቶዎች ናቸው።
ይህ መረጃ ትክክል ነው ?
✅ ፎተው ትክክለኛ ፎቶ ሲሆን የዚህ ፎቶ የመጀመሪያ ምንጭ በጉራጌ ዞን የቸሀ ወረዳ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ቢሮ ነው። ዞኑ ይህንን መረጃ ያጋራው ጥቅምት 8 ቀን 2018 ዓ.ም ነው።
ከዚህ ጋር ተያይዞ በተንቀሳቃሽ ምስል የቀረቡት መረጃዎችስ ?
🚫 በተንቀሳቃሽ ምስል የተመለከትናቸው ልጥፎች አብዛኞቹ ትክክለኛውን ፎቶዎች በመጠቀም በAI የተቀየሩ ናቸው።
የዞኑ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ያወጣው መረጃ ምንድን ነው ?
"የቸሀ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት፣ ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት ፣ሚሊሻ ጽ/ቤት እንዲሁም ፀጥታ ጽ/ቤት በጋራ በመተባበር በመኪና ተጭኖ ሲጓጓዝ የነበረ 540 ሊትር ከፍተኛ የአልኮል ይዘት ያለዉ አረቄ ተወርሶ በዛሬዉ እለት በአፍጥር ገበያ የማስወገድ ስራ ተሠርቷል" ሲል ነው የገለጸው።
የቸሀ ወረዳ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ክፍሌ ሀይሌ ፦
"ይህ አረቄ የብዙ ቤተሰቦች ህይወት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር በመጠቆም ህፃናት ያለአባት እንዲቀሩ ፣ወጣቶች ሱስ ሆኖባቸዉ ከስራ እንዲፈናቀሉ እና ጠባቂ ሆነዉ የአካባቢዉ ሰላም የሚያዉኩ እና ብጥብጥና ፀብ ዉስጥ እንዲገቡ ለማድረግ የሚችል ነዉ።"
የቸሀ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ የሆኑት ምክትል ኢንስፔክተር ክብሩ ሟሩ፦
"ይህ አረቄ ብዙ የማህበረሰብ ክፍሎች ለወንጀል የሚገፋፋ እና ብዙዎች ዉድ ህይወታቸዉ ከንቱ ያስቀረ [ነው] "
የቸሀ ወረዳ ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት ሀላፊ የሆኑት አቶ መሀመድ ኑርዱላ፦
"መነገድ ለሚፈልጉ ሰዎች የተለያዩ የንግድ አማራጮች እንዳሉ እያወቁ የሠዉ ልጆች የሚጎዱና ለጤና ተስማሚ ያልሆኑ ምግቦችና መጠጦች መሸጥ ፈጽሞ የተከለከለ [ነው] "
የቸሀ ወረዳ ሚሊሻ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ማረጉ ፈርሻ፦
"[ጽ/ቤቱ] በቀጣይም የተቻለዉን በማድረግ ድርጊቱ የሚፈጽሙ አካላት ላይ የማስተማር
እርምጃ የመዉሰዱ ሂደት ይቀጥላል"
ከአረቄ ጋር ተያይዞ የመጣው መረጃ መቼ ተጀመረ ?
ሸገር ኤፍ ኤም ጥቅምት 7 ቀን 2018 "በአዲስ አበባ አንድም የቢንጎ ማጫወቻም ሆነ የአረቄ መሸጫ ቤት መኖር የለበትም ተባለ" የሚል ዘገባ ይዞ ወጥቶ በማኅበራዊ ሚዲያው ላይ ትልቅ መነጋገሪያ ሆኖ ነበር።
ዘገባው የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደርን በመጥቀስ የአረቄ ቤቶቹ እንዳይኖሩ ይደረጋል የተባለበትን ምክንያት "ቤቶቹ የወንጀል ምክንያት በመሆናቸው ነው" በሚል አስቀምጧል።
አክሎም የቢሮው ሀላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ "የቢንጎ ማጫወቻ እና በየመንደሩ ያሉ አረቄ ቤቶች የከተማው ወንጀል መፈልፈያ ቦታዎች ናቸው" ማለታቸውን አንስቷል።
የሰዎች ግብረ መልስ ምንድን ነው ?
በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ በተደጋጋሚ የቀረቡት ሙግቶች ይህን ይመስላሉ ፦
- እውነት እዚች አገር ላይ ችግር እየፈጠሩ ያሉት አረቄ ቤቶች ወይስ ውስኪ እንደ ውሃ የሚራጭባቸው ምሽት ቤቶች ?
- ያው እንግዲህ እነ ጂን፣ ኡዞ፣ ቮድካም ሆነ ውሰኪ ያው አረቄ አይደሉ! ነው ወይስ ችግሩ ያለው ከሀገርኛው ካቲካላ ጋር ነው? ግን ግን ንግዱን እና አጠቃቀሙን ስርዓት ማስያዝ አይሻልም?
- ወንጀል ሲሰሩ መያዝ በቁጥጥር ስር ማዋል እንጂ ሰርተው ነግደው ህይወታቸውን የሚመሩ ግለሰቦችን ወንጀል ሊሰሩ ይችላሉ ብሎ ሰርተው የመኖር መብታቸውን መገደብ እንደሆነ እንዴት አልታያቸውም ?
- ንግድ ፈቃድ እንዲያወጡ ግብር እንዲከፍሉ ማድረግ እንጂ የተኛው ጥናት ነው አረቄ ቤት የወንጀል ምንጭ ነው የሚለው?
- መጀመሪያ የግንዛቤ ሥራ ይሠራ። በአረቄ ሽያጭ የተያያዘ የሚመራ የቤተሠብ ህይወት አለ።ከፍተኛ የኑሮ ቀውሥ ይፈጥራል።ጠንካራ ማሥጠንቀቂያ ካልተሠጠና ድንገት እርምጃ መውሠድ አግባብነት የለውም።

Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤101👎35🤔8👏5😢2🤷♀1
#እንድታውቁት
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ያወጣው 7ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ ለተጨማሪ 10 ሥራ ቀናት (እስከ ጥቅምት 28/2018) መራዘሙን የመሬት ሊዝ ጨረታ አስፈጻሚ ኮሚቴ አስታውቋል።
የጨረታ ሰነዱን ለማግኘት https://landleasedocument.aalb.gov.et/

❤8👍5👎3😢1
#ማሳሰቢያ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የገናሌ ዳዋ 3ኛ የኃይል ማመንጫ ግድብ ውሃ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱን በመግለጽ የግድቡን ደህንነት ለማስጠበቅ ሲባል ውሃውን ከጥቅምት 18 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ላልተወሰኑ ቀናት እንደሚለቀቅ አስታውቋል።
በዚህም ምክንያት በሊበን እና መዳወላቡ ወረዳዎች ኮባዲ፣ ሚኤሳ፣ መዳ፣ ኦዳ ቦጂ፣ እና ቢድሬ ቀበሌዎች እና በአካባቢያቸው ያሉ ነዋሪዎች የሚለቀቀው ደራሽ ውሃ በሰውም ሆነ በእንሰሳት ላይ ጉዳት እንዳያደርስ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስቧል።

❤27👍13🤬2👎1🙏1
ዓለም አቀፉ የህግ ተቋም ዴንቶንስ በአዲስ አበባ ቢሮውን ከፍቷል።
ተቋሙ ባለፈው አመት በኢትዮጵያ ቢሮ ለመክፈት ፍላጎት እንዳለው ካሳወቀ በኋላ ከታምራት አሰፋ ሊበን የህግ ቢሮ ጋር በመሆን ቢሮውን በአዲስ አበባ ከፍቷል።
ዴንቶንስ በአፍሪካ በ16 ሃገራት ከ280 በላይ ጠበቆች በስሩ ያሉት ሲሆን የአዲስ አበባ ቢሮውም በአፍሪካ 24ኛ ቢሮው ሆኗል።
ተቋሙ የኢትዮጵያ ቢሮውን የከፈተው በሃገሪቱ ያሉ የታዳሽ ኃይል እና የመሰረተ ልማት ኢንሼቲቮች የተነሳ ሲሆን የሰነደ መዋዕል ገበያ መጀመርም ምክንያት መሆኑን ገልጿል።
ምስረታውን እ.ኤ.አ በ2013 ያደረገውና መቀመጫውን በአሜሪካ ያደረገው የህግ ተቋሙ 5931 የህግ ሰዎችን በስሩ በማቀፍ በአሜሪካ ግዙፉ ነው።
ትኩረቱን በፋይናንስ ላይ ያደረገው ተቋሙ ድርጅቶችን ለማዋህድ እና ለማቀላቀል የህግ ድጋፍም ያደርጋል።
ተቋሙ በትራንስፖርት ፕሮጀክት፣ በኃይል፣ በማዕድን፣ በሪል ስቴት፣ በቴሌኮሚኒኬሽን እና ሚዲያ፣ በክሪፕቶከረንሲ እንደዚሁም በአየር ትራንስፖርት ዘርፎች የሚሰራም ነው።
በ2024 ከ2.7 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ ያገኘው ተቋሙ በ2025 የግሎባል 200 ሰርቬይም በገቢ ደረጃ ከዓለም ካሉ የህግ ቢሮዎች 18ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
ተቋሙ ከታምራት አሰፋ ሊበን ጋር የከፈተው ቢሮም ዴንቶንስ ታምራት የሚል ስም ሲሰጠው በቦሌ መድኃኔዓለም ሮቤሎ ፕላዛ እንደሚገኝም ጠቁሟል።
መረጃው ከAfrican Law Gropu, Law.com እና ከተቋሙ ድህረገጽ የተገኘ ነው።

❤49👍7🤔3👎1🤣1