Telegram Web Link
ኦፕንኤአይ(OpenAi) ሙዚቃ የሚሰራ መተግበሪያ እያበለፀገ መሆኑ ተዘገበ።

'ChatGpt' የተሰኘውን የሰው ሰራሽ አስተውህሎት በማልማት የሚታወቀው ኦፕንኤአይ አሁን ደግሞ በፅሁፍ እና ድምፅ ላይ ተመስርቶ ሙዚቃ የሚሰራ መተግበሪያ እየሰራ ነው ተብሏል።

ተቋሙ ባለፉት ጊዜያት በድምፅ ሞዴል ላይ እየሰራ የቆየ ሲሆን አዲሱ መተግበሪያም እንደ ሱኖ ያሉ የሰው ሰራሽ አስተውህሎት የሙዚቃ መስሪያ መተግበሪያዎችን ይፎካከራል ተብሎ ይጠበቃል።

ኦፕንኤአይ ይህንን መተግበሪያ መቼ እንደሚለቀው ያልታወቀ ሲሆን ከ'ChatGpt' ወይም ከቪዲዮ መተግበሪያው ሶራ ጋር አንድ ላይ ያካትተዋል ወይስ ለብቻው ይለቀዋል የሚለውም አልተገለፀም።

መረጃው ከዘ ኢንፎርሜሸን የተገኘ ነው።

@TikvahethMagazine
37🤔11👎6🤯3👍1
ዶናልድ ትራምፕ ካምቦዲያና ታይላንድ" ታሪካዊ" የሰላም ስምምነት መፈራረማቸውን አስታወቁ።

የሰላም ስምምነቱን የታይላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር አኑቲን ቻርኒቪራኩልና የካምቦዲያው አቻቸው ሁን ማኔት ተፈራርመዋል።

ካምቦዲያና ታይላንድ ለአመታት የድንበር ግጭት ላይ የቆዩ ሲሆን ባለፈው ሐምሌ ጦር ከተማዘዙ በኋላ በትራምፕ ማስጠንቀቂያ የሰበቁትን ጦር መልሰዋል።

ትራምፕ ስምምነቱ የሚሊየኖችን ህይወት ታድጓል ሲሉ ሰላምን ማምጣት " ልማዴ" ሆኗል ሲሉ ከተመድም እሻላለሁ ብለዋል።

በተጨማሪ ትራምፕ የሚዋጉ ሃገራትን በንግድ ስምምነቶች ጫና በማድረግ ወደ ሰላም ማምጣት እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል።

በስምምነቱ ሃገራቱ ከባድ የጦር መሳሪያዎችን ከድንበራቸው ለማንሳትና በድንበራቸው የተዘረጉ የማጭበርበሪያ ካምፖችን ለማጥፋት እንደሚሰሩ ተገልጿል።

ሁለቱም ሃገራት ከስምምነቱ በኋላ የንግድ ስምምነት ከአሜሪካ ጋር ሲፈራረሙ የካምቦዲያው ጠቅላይ ሚኒስትርም ትራምፕን ለቀጣዩ የኖቤል ሽልማት ዕጩ አድርገው ማቅረባቸውን ከወዲሁ ገልፀዋል።

መረጃው የቢቢሲ ነው።

@TikvahethMagazine
🤣9871🕊9👎6🤝4👍2🤬2🙏2🤔1
ታላቅ የምስራች ለቤት ፈላጊዎች በሙሉ!
መሀል ፒያሳ ላይ አራዳ ፓርክ ፊት ለፊት ለ 10 ደምበኞች ብቻ በወጣ ልዪ ቅናሽ የቅንጡ እና ዘመናዊ ቤት ባለቤት ይሁኑ እያልን:-

👉ባለ 1 መኝታ መሉ ክፍያ በ 3,088,000 ብር
👉ባለ 2 መኝታ ሙሉ ክፍያ በ 5,985,000 ብር
👉ባለ 3 መኝታ ሙሉ ክፍያ በ 8,190,000 ብር የግሎ ማረግ ይችላሉ !

ማሳሰብያ:- ከላይ የተጠቀሱት ዋጋ 100% ለሚከፍሉ ደምበኞች ብቻ ሲሆን በቅድመ ክፍያ መስተናገድ ለምትፈልጉ ደምበኞች በ 10% ቅድመ ክፍያ ማለትም ከ 441,000 ብር ጀምሮ መቀላቀል ይቻላል!

ለበለጠ መረጃ በ 0930627256 ይደውሉ!
5
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የመጀመሪያ መኪናችሁን ይሁን አስረኛ መኪናችሁንም ቢሆን ለመግዛት ያሰቡት፤ ያገለገሉ መኪና መሸጫ ቻናሎች የመኪና ዋጋ ማጣራት እና መግዛት ሂደቱን ያቀለዋል። ነገር ግን የመኪና መሸጫ ቻናሎች መኪና መግዛት የሚፈልጉትን ብቻ ሳይሆን የሚጠቅመው ለመኪና ባለቤቶችም መኪናቸውን ለመሸጥ ሲያስቡ ገዢ እንዲያገኙ ይጠቅማል።

ለገዢዎች የሚፈልጉትን መኪና በማቅረብ ለሻጭ ደግሞ ገዢ(ብዙ ጊዜ በዛ ያሉ ገዢዎችን) በማምጣት ደግሞ UZD Cars በ online ገቢያው ላይ ጥሩ ስም አለው።

https://www.tg-me.com/usedcarsinethiopia በመቀላቀል ለራስዎ ያረጋግጡ።

UZD Cars'ን ስለመረጡ እናመሰግናለን።
6👍5
ማሊ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ ሁሉንም ትምህርት ቤቶቿን ለሁለት ሳምንት ዘጋች።

ማሊ ትምህረት ቤቶቿን የዘጋችው በአልቃይዳ የሚደገፈው ጃማዓት ኑስራት አል ኢስላም ዋል ሙስሊምን የተሰኘው አሸባሪ ቡድን ነዳጅ እንዳይገባ በማገዱ የተነሳ በተፈጠረ የነዳጅ እጥረት ነው።

አሸባሪው ከማሊ ጎረቤቶች ነዳጅ ከባለፈው መስከረም ወር ጀምሮ እንዳይገባ መከልከሉን ተከትሎም በርካታ ነዳጅ የጫኑ መኪኖች በማሊ ድንበር ላይ ቆመዋል።

ቡድኑ የነዳጅ መተላለፊያዎችንም መያዙ ሲነገር ጥቃትም እያደረሰ ነው።

የነዳጅ እጥረቱ ታዲያ የተማሪዎችንና የመምህራንን እንቅስቃሴ በመገደቡ የተነሳ ዩኒቨርሲቲዎችን ጨምሮ ሁሉም ትምህርት ቤቶች ለሁለት ሳምንታት እንዲዘጉ መወሰኑን የሃገሪቱ የትምህርት ሚኒስትር አስታውቀዋል።

በሃገሪቱ ረጃጅም የነዳጅ ሰልፎች ሲታዩ የሸቀጦችና የትራንስፖርት ዋጋም ጨምሯል።

አሸባሪው ቡድን ነዳጅ እንዳይገባ ማድረጉን ተከትሎም መንግስት ነዳጅ ለማዳረስ እየሰራ ሲሆን በ2020 በመፈንቅለ መንግስት ስልጣን ለያዘው ወታደራዊ መንግስትም ትልቅ ጋሬጣ ሆኗል።

መረጃው የተገኘው ከፈርስት ፖስት ነው።

@TikvahethMagazine
32😢9
TIKVAH-MAGAZINE
Photo
#Update

የቴሌግራም መስራቹ እና ዋና ስራ አስፈፃሚ ፓቨል ዱሮቭ ከፈረንሳይ ሙዚየም የተሰረቁ እንቁዎችን መግዛት እንደሚፈልግ ገልጿል።

ዱሮቭ ባለፈው ሳምንት ከፓሪስ ሙዚየም የተሰረቁ 102 ሚሊየን ዶላር ዋጋ ያላቸውን እንቁዎች ነው መግዛት የፈለገው።

ፓቨል ዱሮቭ ከገዛ በኋላ ጌጦቹን ወደ ሙዚየም የሚመልስ ሲሆን፣ የሚመልሰው ግን ወደ ፓሪሱ የሉቭሬ ሙዚየም ሳይሆን አቡዳቢ ወደሚገኘው የሉቭሬ ሙዚየም መሆኑን ገልጿል። በምክንያትነት ያነሳው ደግሞ እነዚህ የተሰረቁ ቅርሶች ከፓሪስ ይልቅ በአቡዳቢ ደህንነታቸው የተጠበቀ ነው የሚል ነው።

ባለፈው ሳምንት በፓሪስ የሚገኝ ሙዚየም ውስጥ 4 ሰዎች ገብተው 102 ሚሊየን ዶላር ዋጋ ያላቸውን ቅርሶችና ጌጦች ሰርቀው መውጣታቸው ሲታወስ ዱሮቭ በነገሩ እንዳልደነገጠና በአንድ ወቅት ታላቅ የነበረች ሃገር መውደቋን ያሳየ ተግባር መሆኑን ገልጿል።

@TikvahethMagzaine
🤣9537👍13🤔5👎3
2025/10/27 14:14:03
Back to Top
HTML Embed Code: