Telegram Web Link
ከዛሬ ጀምሮ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በደርሶ መልስ ጉዞ ለጎብኚዎች ክፍት ይሆናል ተባለ፡፡         

የህዳሴ ግድብ ለመጎብኘት ምዝገባ ከዛሬ ጀምሮ በኢትዮጵያ አየር መንገድ በኩል እንደሚካሄድ ሲገለጽ፤ ለጉብኝት መሄድ የሚቻለውም ከ50 ሰው ጀምሮ ነው ተብሏል።

የቱሪዝም ሚኒስትሯ ሰላማዊት ካሳ ጉዞ ማድረግ የሚቻለው ደርሶ ለመመለስ መሆኑን ገልጸዋል።

የታላቁ የህዳሴ ግድብ መጎብኘት የሚፈልጉ  ከዛሬ ጀምሮ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ትኬት ቢሮዎች መመዝገብ እንደሚቻልም አንስተዋል።

ሚኒስትሯ አክለውም፥ ከግለሰቦች በተጨማሪም ተቋማት፣ የተለያዩ ጥናት አድራጊዎች፣ ተመራማሪዎች ጉብኝት ማድረግ እንደሚችሉ አስረድተዋል፡፡

አሁን ላይ የህዳሴ ግድቡን መጎብኘት የሚቻለው በኢትዮጵያ አየር መንገድ በኩል ብቻ እንደሆነም ሲነገር ለዚሁ ሲባል በሳምንት ሁለት ቀን በረራ ተዘጋጅቷልም ተብሏል።

መረጃው የሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ነው።
ፎቶ : ቲክቫህ ኢትዮጵያ

@TikvahethMagazine
100👎14🕊4👏3🤔2
"ጊፋታ በቀጣዩ ጉባዔ በዓለም አቀፍ ቅርስነት እንዲመዘገብ እየተጠበቀ ይገኛል" - የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን

የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ጊፋታ በዓለም ዓቀፍ ቅርስነት እንዲመዘገብ የሚያስችለውን አስገዳጅ ሰነዶችን በማዘጋጀት ለዩኔስኮ መላኩን ገልጿል።

በዚህም "ሰነዱ በህንድ ኒው-ዴሊ ከህዳር 29- ታህሳስ 4 ቀን 2018 ዓ.ም በሚካሄደው የ20 ኛው የዩኔስኮ የማይዳሰስ ባህላዊ ቅርስ ጥበቃ አጠቃላይ ጉባኤ ላይ ውሳኔ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል" ሲል ገልጿል።

ባለስልጣኑ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በጉባዔው በመገኘት የምዝገባ ሂደቱን ለመከታታል ብሎም ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ለመስጠት በአሁኑ ወቅት ዝግጅት እያደረኩም ነው ብሏል።

ከዚህን በፊት የመስቀል፣ የጥምቀት፣ የፊቼ ጫምባላላ፣ የገዳ ሥርዓት፣ ሸዋል ዒድ እና ሄር-ኢሴ(የሶማሌ ኢሳ ማኅበረሰብ ያልተፃፈ ባህላዊ የዳኝነት ሥርዓት) በዓለም ቅርስነት የተባበሩት መንግሥታት የሣይንስ፣ ትምህርት እና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) መመዝገባቸውን አስታውሷል።

#ጊፋታ

@TikvahethMagazine
97🤣16🤯7👎6🤬3👍1
TIKVAH-MAGAZINE
የፈረንሳዩ ተቋም ካናል+  የደቡብ አፍሪካውን መልቲቾይዝ ግሩፕ በ3 ቢሊየን ዶላር ገዝቶታል። ካናል+ መጀመሪያውንም ቢሆን የመልቲቾይዝ 45 በመቶ ባለድርሻ የነበረ ሲሆን አሁን ሙሉ ለሙሉ ድርሻውን ገዝቶታል። መልቲቾይዝ ለ40 አመታት የቆየ ስም የገነባ መሆኑ ሲገለፅ በአፍሪካ ከ50 ሚሊየን በላይ ደንበኞች እንዳሉት ይገለፃል። መልቲቾይዝ በክፍያ ከሚሰሩ የቴሌቪዥን ገበያዎች ውስጥ አንዱ ሲሆን በዲ ኤስ…
ካናል ፕላስ የመልቲቾይዝን ግዢ ሙሉ ለሙሉ መፈፀሙን ይፋ አደረገ።

የፈረንሳዩ ተቋም ካናል ፕላስ ባለድርሻ የነበረበትን መልቲቾይዝን ሙሉ ድርሻ ለመግዛት ከወራት በፊት ተስማምቶ የነበረ ሲሆን ግዢው መጠናቀቁ ይፋ ሆኗል።

በወቅቱ አጠቃላይ ግዢው 35 ቢሊየን የደቡብ አፍሪካ ራንድ ወይም ከ2 ቢሊየን ዶላር በላይ እንደሆነ ተገልፆ ነበር።

መልቲቾይዝ በአፍሪካ ካሉ ግዙፍ የክፍያ ቴሌቪዥን አንዱ የሆነውን ዲኤስቲቪን በባለቤትነት የሚያስተዳድር ሲሆን የካናል ፕላስ ሙሉ ለሙሉ መግዛት ትልቅ እርምጃ ተደርጎ ተወስዷል።

የካናል ፕላስ ዋና ስራ አስፈፃሚ ማክሲም ሳዳ ሁነቱ ለካናል ፕላስ ትልቅ መሆኑን አንስተው የተቀላቀለው ተቋማቸው በ70 ሃገራት 40 ሚሊየን ደንበኞችን እንደሚያስተናግድ ገልፀዋል።

ከ17 ሺህ በላይ ሰራተኞች አሉን ያሉት ስራ አስፈፃሚው ተቋማቸው ትክክለኛ የመዝናኛ ቦታ መሆኑንም ተናግረዋል።

ካናል ፕላስ መልቲቾይዝን ሙሉ ለሙሉ መያዙን ተከትሎ አዳዲስ የቦርድ አመራሮቹንም አሳውቋል።

በዚህም መሰረተ የካናል ፕላስ ዋና ስራ አስፈፃሚ ማክሲም ሳዳ የቦርድ ሊቀመንበር ሲሆኑ ከዚህ ቀደም የመልቲቾይዝ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ የነበሩት ካልቮ ማዌላ የካናል ፕላስ አፍሪካን እንዲመሩ ተመርጠዋል።

ዘገባው የሮይተርስ እና የቫራይቲ ነው።

@TikvahethMagazine
99👎17👍11🤔1
🖥 🖥   🖥 🖥 🖥 🖥 🖥 🖥 🖥
BK  C  O  M  P  U  T  E  R S

  ማንኛውንም አይነት  አዳዲስ ላፕቶፖች ዱባይ ዩዝድ ላፕቶፖች ዴስክ ቶፖችን ጨምሮ ከብዛት እና ከታላቅ ቅናሽ ጋር ያዘንላቹ መተናል

ለ ቢሮዎች ፣ ለተማሪዎች፣ለግሪፊክስ ዲዛይን ባለሙያዎች ፣ ለጌመሮች እንዲሁም ለጨረታ የሚሆኑ በጥራት እና በ ብዛት  ከ አንድ አመት ዋስትና ጋር እኛ ያገኛሉ

ለተጨማሪ  መረጃ እና የላፕቶፕ አማራጮችን ለማየት የቴሌግራም ፔጃችንን Join ያድርጉ።
Tg. https://www.tg-me.com/BKComputers
Inbox @bkcomputer27

አድራሻ አዲስ አበባ መገናኛ ሲቲ ሞል ከ መሰረት ደፋር ህንፃ አጠገብ 1 ፎቅ ላይ እንገኛለን
           ☎️ 0911448148. 0955413433
           we make IT easy!
23😢2
ላለፉት ሁለት አመታት ከ 3000ሺ በላይ የሚጠጉ ሰዎችን የቤት ባለቤት ለማድረግ መንገዱን አስጀምረናል

አሁን ላይ ደግሞ በአይነቱ ለየት ያለ ሰፋፊ የሆኑ  የfamily penthouse design ያላቸው ቤቶችን አማራጮች በውቢቱዋ ለቡ መብራት ሀይል ዳግም ይዘን መተናል
-10% ቅድመ ክፍያ
-ከ 59 -295 ካሬ አማራጭ
-40% በ3አመት ከፍለው
- ቀሪውን 60%ቱን ረዘም ባለ ጊዜ የባንክ የሚከፍሉበት እና
-እንደሚከፍሉት ቅድመ ክፍያ እስከ 30% የሚደርስ ቅናሽ ያገኛሉ

ታዲያ የዘህ የቅንጡ ኑሮ አካል ለመሆን ካሰቡ
ከስር ባለው ስልክ ይደውሉልኝ

+251977225688
25🤣9👎1
ማሊ፣ ቡርኪናፋሶና ኒጀር ከአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት መውጣታቻውን ገለፁ።

በወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ስልጣን በያዙ መሪዎች በሚመሩት ሶስቱ የምዕራብ አፍሪካ ሃገራት መቀመጫውን በሄግ ካደረገው የአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት(ICC) መውጣታቸውን አስታውቀዋል።

ሶስቱ ሃገራት ፍርድ ቤቱ የቅኝ ግዛት ጭቆና ማስፈፀሚያ ነው ብለው ከሰዋል።

ሶስቱ ሃገራት በቀጣናው ስምንት ያህል መፈንቅለ መንግስቶች ከተፈፀመ በኋላ የሚመሯቸው መሪዎች ከዚህ ቀደም ሃገራቸውን ከቀጣናዊው ተቋም ኢኮዋስ ማስወጣታቸው እንደዚሁም ከቀድሞ ቅኝ ገዢያቸው ፈረንሳይ እና ምዕራባውያን ጋር ያላቸውን ትስስር አቁመው ወደ ሩሲያ ማዞራቸው ይታወሳል።

ሶስቱ ሃገራት የሄጉ ፍርድ ቤት የጦር ወንጀለኞችን ለፍትህ የማቅረብ እንደዚሁም በሰብዓዊነት ላይ የሚቃጡ ወንጀሎችና የዘር ጭፍጨፋን የመከላከልና ፍትህ የመስጠት አቅም የለውም ብለዋል።

ኒጀር፣ ማሊና ቡርኪናፋሶ ፍርድ ቤቱ የተመረጠ ፍትህን ይሰጣል ብለው ሲከሱ ሰላምና ፍትህን ለማምጣት ሃገር በቀል የሆነ ዘዴ እንደሚፈጥሩ ገልፀዋል።

የአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በ2002 ምስረታውን ቢያደርግም ሃያላኑን አሜሪካ፣ ሩሲያና ቻይናን ጨምሮ እስራኤል የፍርድ ቤቱ አባል አይደለችም።

የመረጃው ምንጭ ሮይተርስና ዶቼ ቬሌ ነው።

@TikvahethMagzine
👏8743👍5👎5🙏1
የኤአይና ሮቦቲክስ ፕሮግራሞችን በመጀመሪያ ዲግሪ ለማስጀመር የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ።

የኢፌዴሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስና ሮቦቲክስ ፕሮግራሞች በደረጃ 6 (በመጀመሪያ ዲግሪ) ስልጠና ለማስጀመር የሚያስችል ስምምነት ተፈራርሟል።

የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ከድር ስርዓተ ስልጠና ተዘጋጅቶ መጠናቀቁንና ስልጠናውም በዚህ ዓመት እንደሚጀመር ገልጸዋል። በዝግጅቱ ላይም አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ሲሳተፍ መቆየቱን አንስተዋል።

የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ኢንጂነር ወርቁ ጋቸና በበኩላቸው፤ ይህ የመጀመሪያ የሆነውን ፕሮግራም በመጀመሪያ ዲግሪ ደረጃ በኢንስቲትዩቱ እንዲሰጥ መቻሉ በዘርፉ ልዩ ያደርገዋል ሲሉ ገልጸዋል።

@TikvahethMagazine
96🔥34👍9👎9👏5🙏1
ፎቶ፦ የ2018 ዓ/ም የመስቀል ደመራ በዓል በአከባበር በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ።

#TikvahEthiopia

@TikvahethMagazine
148🙏11🔥5🤣4👎3👍1
2025/10/25 08:47:53
Back to Top
HTML Embed Code: