Telegram Web Link
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#SamiTech

አዳዲስ ላፕቶፕች ከአንድ ዓመት ዋስትና ጋር!!
@samcomptech

በጥራት፣ በብራንድና በባትሪ ቆይታ አስተማማኝ የሆኑ የተለያዩ ሞዴል ላፕቶፖች በፈለጉት ስክሪን መጠን፣ ኮር አይ እና ጀነሬሽን አሉን።

ላፕቶፕ ከመገዛትዎ በፊት ማወቅ ያለባችሁን ወሳኝ ነገሮች እናስረዳለን። በላፕቶፖቻችን ጥራት ላይ አንደራደርም!

ለቢሮዎች፣ ለተማሪዎች፣ ለዲዛይን ባለሙያዎች፣ ለጌመሮች ወ.ዘ.ተ. ሁሉም አሉን።

የዕቃዎች ዋጋ፣ ዓይነት እና አድራሻ ለማግኘት 👉 @samcomptech

@sww2844

0928442662 / 0940141114

Telgram

      👇
https://www.tg-me.com/samcomptech
7💔1
የተመድ ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ባለፈው አመት ከ676 ሚሊየን በላይ ሴቶች በ50 ኪሎ ሜትር ገዳይ የግጭት ቀጣና ውስጥ እንደነበሩ አስታወቁ።

ጉተሬዝ በመላው አለም ያሉ ሴቶች በግጭቶች በእጅጉ እየተጎዱ መሆኑን አንስተው ይህንን ያህል ሴቶች በግጭት ቀጣና ውስጥ ሲሆኑ ከአስርት አመታት በኋላ ከፍተኛው ነው ብለዋል።

ዋና ፀሃፊው በሴቶች ላይ ወሲባዊ ጥቃቶች መጨመራቸውን ገልጸው በተመዘገቡ ጥቃቶች ብቻ በሴቶች ላይ የሚፈፀመው ጥቃት በ35% መጨመሩንና በአንዳንድ ቦታዎች ደግሞ ከሚፈፀሙ ጥቃቶች ውስጥ ግማሽ ያህሉ ተጠቂዎች ሴቶች ናቸው ብለዋል።

ጉተሬዝ በአፍጋኒስታን ሴቶች ከማህበራዊ ህይወት መገለላቸውን አንስተው በፍልስጤም ፣ በሱዳን፣ ሃይቲና ማይናማር ሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶች እንደጨመሩና ለሴቶች ድጋፍ የሚያደርጉ ተቋማት የአቅም ውስንነት እንደገጠማቸው ተናግረዋል።

የተመድ ዋና ፀሃፊው ጉተሬዝ አባል ሃገራት የሴቶችን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ በደንብ ሊሰሩ የሚገባበት ጊዜ ነው ብለዋል።

መረጃው የአናዶሉ ነው።

@TikvahethMagazine
30👍6🙏1
#SIT

በሸገር ከተማ እየተገነባ ያለውና ትኩረቱን የህዋ ሳይንስ፣ ኒውኪሊየር ሳይንስና ሰው ሰራሽ አስተውህሎት ላይ ያደረገው ሸገር የቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት ከዚህ ወር ጀምሮ ተማሪዎችን መቀበል ይጀምራል።

ይህ ተቋም የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ብዙ ቢሊየኖችን መድቦ እያስገነባው ያለው ሲሆን በ50 ሄክታር ላይ ያረፈው ተቋም ግንባታውም በኮዬ ፈጬ ክፍለ ከተማ እየተከናወነ ነው።

በዚህ ተቋም በልዩ ልዩ መመዘኛዎች ውስጥ ያለፉ ልዩ ችሎቻ ያላቸው ተማሪዎች ይማሩበታል ተብሏል።

የተቋሙ ፕሬዚዳንት ሃይሉ ዱፌራ( ዶ/ር) ተቋሙ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ላይ የሚደረጉ ምርምሮችን ለማድረግ መመስረቱን ተናግረው ባለፉት ሁለት አመታት አስፈላጊ የሚባሉ መሰረተ ልማቶች ግንባታ ሲከናወኑ ነበር ብለዋል።

ተቋም በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ከማስተማሩ በተጨማሪ የምርምር እና የላብራቶሪ መሰረተ ልማቶችን ላጡ ሳይንቲስቶች የምርምር ቦታ እንደሚሆንም ተገልጿል።

በኢትዮጵያ አሁን ላይ ካሉ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች ልዩ የሚያደርገው ምን እንደሆነ የተጠየቁት  ፕሬዚዳንቱ " ልዩ የሚያደርገው እኛ የምንሰጠው ትምህርት ይበልጥ በተግባር ላይ ትኩረት ያደረገ ነው" በማለት አሁን ያሉ ዩኒቨርሲቲዎች መደበኛ ትምህርት ከማስተማር ባለፈ ወደ መሬት ለማውረድ በቂ ኢንቨስትመንት አላደረጉም ብለዋል።

ተቋሙ " ኢንዱስትሪና አካዳሚውን አያይዞ ያስኬዳል" ያሉት ፕሬዚዳንቱ በሌላው ሃገር የተለመደ አሰራር ነው ብለዋል።

ሃይሉ ዱፌራ(ዶ/ር) ተቋሙ ጥቂት ተማሪዎችን ብቻ እንደሚቀበል ተናግረው ከዚህ ወር ጀምረው ተማሪዎችን መቀበል እንደሚጀምሩ ተናግረዋል።

ፕሬዚዳንቱ ተቋሙ አለም አቀፋዊ መሆኑን አንስተው ከመላው ኢትዮጵያ ተማሪዎችን እንደሚቀበሉ አንስተዋል።

መመዘኛውን የሚያሟሉ ተማሪዎች በስኮላርሺፕ እንደሚማሩ የገለፁት ፕሬዚዳንቱ ተማሪዎች ምንም አይነት ክፍያ አይከፍሉም ብለዋል።

በዚህ አመት ከ280-300 ተማሪዎችን ለመቀበል መታቀዱን ያነሱት ፕሬዚዳንቱ እስካሁን 106 ተማሪዎችን መርጠው መቀበላቸውን አንስተው ለወደፊቱም ከ300 በላይ ተማሪዎችን እንደማይቀበሉ ተናግረዋል።

በ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገብ አንዱ መስፈርት ነው ያሉት ሃይሉ ዱፌራ(ዶ/ር) ሌሎች በርካታ መመዘኛዎች አሉ ብለዋል።

በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ያመጡ በርካታ ተማሪዎችን መቀበላቸውን ሲገልፁ ምዝገባው ሐምሌ ወር መጠናቀቁንም ገልፀዋል።

የትምህርት ካሪኩለሙ አለም አቀፍ መሆኑን ያነሱት ፕሬዚዳንቱ "ከMIT እና ሃርቫርድ ጋርም ይመሳሰላል" ብለዋል።

ኢንስቲቲዩቱ ሲጠናቀቅ 130 ላብራቶሪዎች እንደሚኖሩት ያነሱት ፕሬዚዳንቱ "አንድ ላብራቶሪ ቢያንስ 5 ሚሊየን ዶላር ወጪ ይጠይቃል" ብለዋል።

ለተቋሙ ግንባታ የወጣው አጠቃላይ ወጪ ግንባታው ሙሉ ለሙሉ ሲጠናቀቅ ይታወቃል ሲሉ ይህ ሁሉ ኢንቨስትመንት ከተደረገ ልጆቻችን ራሳቸውንና ሃገራቸውን መጥቀምም ይችላሉ ብለዋል።

መረጃው የተገኘው ከቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ነው።

@TikvahethMagazine
132🤣32🤔15👍9👎1👏1🤬1🙏1
ኢትዮጵያ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ስምምነት ትግበራን ከነገ ወዲያ በይፋ ትጀምራለች።

ኢትዮጵያ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ስምምነት (AfCFTA) ድርድርን ማጠናቀቋን ተከትሎ መስከረም 29 ቀን 2018 ዓ.ም በሸቀጦች ዘርፍ የንግድ ትግበራ በይፋ ትጀምራለች ሲል የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ።

በማስጀመሪያ ንግዱ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎ ሥጋ፣ አትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም በየብስ ትራንፖርት ቡና፣ የጥራጥሬ ምርቶችና የቅባት እህሎች ወደ ኬንያ፣ ሶማሊያ እና ወደ ደቡብ አፍሪካ ይላካል ሲሉ የንግድ ትስስርና ወጪ ንግድ ፕሮሞሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ያስሚን ውሀብረቢ ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ (AfCFTA) ስምምነት ትግበራን በይፋ ስታስጀምር ቀረጥ ይከፈልባቸው የነበሩት ምርቶች በነጻ መላክ ያስችላታል።

በንግድ ማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ሴክሬታሪያት ኃላፊዎች፣ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ የተለያዩ ሀገራት ዲፕሎማቶችና አምባሳደሮች፣ እንዲሁም ላኪዎችና አምራቾች ይሳተፋሉ ተብሏል።

@TikvahethMagazine
67👍9👎1😢1🙏1
ጤና ሚኒስቴር 8 በመቶ የነበረው የሀገር ውስጥ የመድኃኒት ምርት አቅርቦት ድርሻ አሁን ላይ 41 በመቶ መድረሱን አስታወቀ። (EPA)

@TikvahethMagazine
79🤣51🤔11👍4👎1🙏1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Get your full makeup look with us @smoochcosmo 😍 with wholesale prices. ብዙ አዳዳዲስ እቃዎች አስገብተናል! All our products are from the USA. መደወል ለምትፈልጉ call/Text ☎️ 𝟎𝟗𝟕𝟑𝟏𝟓𝟕𝟕𝟕𝟕 @smoochcosmocontact ወይም በtelegram በ📱𝟎𝟗𝟐𝟏𝟔𝟐𝟑𝟕𝟑𝟕 @hilluuuu ጻፉልን!
በቅድሚያ የምናስተናግደው በጅምላ ወስደው አትርፈው ለሚሸጡ ሱቆች ነው! እናመሰግናለን!
https://www.tg-me.com/SmoochCosmo
8
ለተጎጂዎች ከተሰበሰበ ገንዘብ ላይ ከ60 ሚሊዮን ብር በላይ ሊጭበረበር ሲል ተያዘ።

በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ  ቀበሌ ሐምሌ 15/2016 ዓ/ም ተከስቶ በነበረው የመሬት መንሸራተት አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች የተሰበሰበ ከ60 ሚሊዮን ብር በላይ ከባንክ ወጪ በማድረግ ለማጭበርበር የተደረገው ሙከራ ከሽፏል ተብሏል።

ከሰሞኑ በስፋት በማኅበራዊ ሚዲያው ላይ ወጪ ትዕዛዝ የተጻፈበት ቼክ እንዲሁም ማዘዣ ደብዳቤ በርካቶች ሲያዘዋውሩት ተስተውሏል።

ይህንን አስመልክቶ በዛሬው ዕለት የዞኑ ኮሚኒኬሽን ቢሮ መግለጫ ሰጥቷል።

ዞኑ በመግለጫው ምን አለ ?

"በአደጋው ለተጎዱ ህብረተሰብ  ክፍሎች ከመጣው ገንዘብ  ላይ 60, 276,383 (ስልሳ ሚልዮን ሁለት መቶ ሰባ ስድሰት ሺ ሶስት መቶ ሰማንያ  ሶስት  ብር )ቀደም ሲል  ተሠርቶ ቮይድ በተደረገ ቼክ ቁጥር 42221123 አሰመስለው በማሳተም ገንዘቡን ለመዝረፍ ካመቻቹ በኋላ ከአዲስ አበባ ንግድ ባንክ ሸገር ቅርንጫፍ ለጎፋ ዞን አስተዳደር በተደረገ ጥቆማ ከአዲስ አበባና ክልል ፖሊስ ጋር በመተባበር ገንዘቡ ሳይወጣ  ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ውለዋል።" ሲል ገልጿል።

ዞኑ በመግለጫው የድርግቱ ፈጻሚዎችን በደፈናው "የሀገር ወስጥና የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ለተጎጅ ሕብረሰብ ክፈሎች የለገሱትን ድጋፍ ወደ ኪሳችን ገብቶ  ካልበለፀግን በሚል አሰተሳሰብ የተጠመዱ አካላት" በሚል ይጥቀስ እንጂ ስለተጠያቂነትም ይሁን ዝርዝር ጉዳዮች ያለው ነገር የለም።

@TikvahethMagazine
62😢28🤔8👏5👍2🔥1🙏1
በኤሌክትሪክ መኪና ከናይሮቢ አዲስ አበባ ... ለምን ?

ባለፈው እሁድ ከኬንያ ናይሮቢ የተነሱት የኤሌክትሪክ መኪኖች 1ሺ ስድስት መቶ ኪሎሜትሮችን አቋርጠው በመጪው አርብ አዲስ አበባ ይደርሳሉ ተብሏል።

"ጉዞ ወደ አዲስ" የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ ጉዞ ስድስት ቀናትን እንደሚፈጅ ሲጠበቅ ተጓዦቹ በአዲስ አበባ ከጥቅምት 4 - 6 በሚዘጋጀው የኤሌክትሪክ ትራንስፖርት ሳምንት (Africa E-Mobility Week) ላይ ይታደማሉ።

የቻርጀሩስ ጉዳይ ?

አዘጋጆቹ እንደገለጹት በመንገድ ላይ ጊዜያዊ የሶላር ቻርጅ ማድረጊያ ቦታዎች እንደሚዘጋጁ ገልጸዋል።

ከዚህም በተጨማሪ በመንገድ ላይ ለነዋሪዎች ስለ ኤሌክትሪክ ትራንስፖርት አገልግሎት ግንዛቤ ማስጨበጫ ዝግጅቶች ይኖሩታል ተብሎ ይጠበቃል።

@TikvahethMagazine
71🤣21👍2
አክስዮኖች ለማስመዝገብ የተቀመጠው የጊዜ ገደብ ህዳር 16 ይጠናቀቃል።

ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች (አክሲዮኖች) በሙሉ በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን መመዝገብ እንዳለባቸው መደንገጉ ይታወሳል።

በዚህም፦

📈 ከዚህ ቀደም አክሲዮኖቻቸሁን ለህዝብ የሸጡ፤

📈 የአክሲዮን ሽያጭ የጀመሩና ሽያጩ አሁንም በሂደት ላይ ያለ

አክስዮኖች ለማስመዝገብ በመመሪያው የተቀመጠው የአንድ አመት የሽግግር ድንጋጌ የጊዜ ገደብ ህዳር 16 ቀን 2018 ዓ.ም ይጠናቀቃል።

የግዜ ገደብ ከመጠናቀቁ በፊት መመሪያው የሚጠይቀውን መስፈርት በሟሟላት አክሲዮኖቻችሁን እንድታስመዘግቡ ሲል የኢትዮጵያ ካፒታል ገቢያ ባለሥልጣን አስታውቋል።

በተጨማሪም የሰነደ ሙዓለ ንዋይ ለህዝብ የማቅረብ እና ግብይት መመሪያ ከወጣ በኋላ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮችን ለሕዝብ ሽያጭ ለማቅረብ የምትፈልጉ የአክሲዮን ማህበራት ከሽያጭ በፊት  ተገቢውን መስፈርት በሟሟላት ማስመዝገብ አለባቸው ሲል ገልጿል።

@TikvahethMagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
49👍3
የዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት የሱዳን ታጣቂ መሪ የነበሩትን ሰው ጥፋተኛ ሲል በይኗል።

ከ20 ዓመት በፊት በዳርፉር በነበረው ጦርነት ወቅት በሰብዓዊነት ላይ የተቃጡ ወንጀሎችን ፈፅመዋል የተባሉት እና ጃንጃዊድ የተባለውን ታጣቂ ቡድን መርተዋል የተባሉት አሊ መሐመድ አሊ በፍርድ ቤቱ ጥፋተኛ ተብለዋል።

ታጣቂ ቡድኑ በመንግስት ድጋፍ ያገኝ ነበር ሲባል ቡድኑ ለብዙ ሺህ ሰዎች ሞት፣ መደፈር እና የመብት ጥሰት ምክንያትም ነበር።

ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ከዳርፉር ጦርነት ጋር በተያያዘ ጥፋተኛ ያለበት የመጀመሪያ ጉዳይም ነው ተብሏል።

የዳርፉር ጦርነት ጅማሬውን በ2003 ያደረገ ሲሆን በርካታ አረብ ያልሆኑ ሰዎች ላይ የዘር ማጽዳት ወንጀል የተፈፀመበትም ነው።

ዳርፉር አሁንም ቢሆን ከጦርነት ያልተላቀቀች ሲሆን የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉና የሱዳን ጦር ዋነኛ መፋለሚያ ስፍራ ሆና ቀጥላለች።

ፍርድ ቤቱ አሊ መሐመድ አንድም አረብ ያልሆነ ዘር በአካባቢው እንዳይቀር ለታጣቂዎቹ ትዕዛዝ መስጠታቸውንና ሴቶችን ለወሲብ ባርነት መዳረጉን ገልጿል።

በአጠቃላይ የታጣቂው ቡድን መሪ በ2003 እና 2004 በዳርፉር በነበረው ጦርነት በነበረው ሚና በ27 ክሶች ጥፋተኛ ሆኗል።

በዳርፉር ጦርነት በነበራቸው ተሳትፎ አሊ መሐመድ በቀጣይ የፍርድ ውሳኔ ይሰጥባቸዋል ተብሏል።

አለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት በ2019 በመፈንቅለ መንግስት ስልጣን ያጡትን ኦማር አልበሽርን ጨምሮ ሌሎች የቀድሞ ከፍተኛ ባለስልጣናት ላይ ከዳርፉር ጦርነት ጋር በተያያዘ የእስር መያዣ ማውጣቱ ይታወሳል።

አሁን ውሳኔ ይሰጥባቸዋል ከተባሉት የታጣቂ ቡድን መሪ ውጪ ሌሎቹ ያልተያዙ ሲሆን ኦማር አልበሽር በሰሜናዊ ሱዳን በሚገኝ ወታደራዊ እስር ቤት እንደሚገኙ መዘገቡ ይታወሳል።

ዘገባው የቢቢሲ ነው።

@Tikvahethmagazine
64👎10👍2👏1🙏1
🔥በመሀል ፒያሳ ከአራዳ ፓርክ ትይዩ ከወዳጅነት ፓርክ እንዲሁም አብርሆት ቤተ መፅሀፍት በቅርብ ርቀት ላይ

🌟ለ15 ቤቶች ብቻ በማስታወቅያ ዋጋ ቅንጡ አፓርትመንቶች ቀረበልዎት

🏡ከባለ አንድ እስከ ባለ ሶስት መኝታ በ 10% ቅድመ ክፍያ ብቻ
ቀሪውን ዘና ብለው የሚከፍሉት

💎 ባለ 1 መኝታ በ 441,000 ብር
💎ባለ 2 መኝታ በ 855,000 ሺ ብር
💎ባለ 3 መኝታ በ 1,170,000 ሺ ብር ቅድመ ክፍያ

ለ 15 ቤቶች ብቻ❗️

- ባሉት ውስን ቀናቶች ለሚመጡ ደንበኞች እስከ 30% የሚደርስ ታላቅ ቅናሽ አቅርበን እየጠበቅኖት ነው

ይደውሉልን
የዘመናዊ መንደራችን አካል ይሁኑ!

☎️0900025097

#telegram (@SamuelMERITRealtor)
#whatsapp
17👏1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#SamiTech

አዳዲስ ላፕቶፕች ከአንድ ዓመት ዋስትና ጋር!!
@samcomptech

በጥራት፣ በብራንድና በባትሪ ቆይታ አስተማማኝ የሆኑ የተለያዩ ሞዴል ላፕቶፖች በፈለጉት ስክሪን መጠን፣ ኮር አይ እና ጀነሬሽን አሉን።

ላፕቶፕ ከመገዛትዎ በፊት ማወቅ ያለባችሁን ወሳኝ ነገሮች እናስረዳለን። በላፕቶፖቻችን ጥራት ላይ አንደራደርም!

ለቢሮዎች፣ ለተማሪዎች፣ ለዲዛይን ባለሙያዎች፣ ለጌመሮች ወ.ዘ.ተ. ሁሉም አሉን።

የዕቃዎች ዋጋ፣ ዓይነት እና አድራሻ ለማግኘት 👉 @samcomptech

@sww2844

0928442662 / 0940141114

Telgram

      👇
https://www.tg-me.com/samcomptech
8
ሶማሊያ የስዋሂሊ ቋንቋን በትምህርት ስርዓቷ ለማካተት ማቀዷ ተነገረ።

ሶማሊያ ከምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ አባል ሃገራት ጋር ያላትን ትስስር ለማሳደግ የስዋሂሊ ቋንቋን በትምህርት ስርዓቷ በማካተት ለማስተማር አቅዳለች።

ሶማሊያ በ2024 ኬንያ፣ ታንዛኒያ ፣ ኡጋንዳ፣ ሩዋንዳ፣ ቡሩንዲ፣ ደቡብ ሱዳንና ዲሞክራቲክ ኮንጎ ያሉበትን ይህንን ጥምረት መቀላቀሏ ይታወቃል።

የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሃሰን ሼህ መሐሙድ የሃገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች ቋንቋውን በማስተማር እና በመጠቀም ረገድ መሪ እንዲሆኑ ጠይቀዋል።

ይህ የተባለው በሞቃዲሾ በተዘጋጀ  የምስራቅ አፍሪካ የትብብር እና የኢኮኖሚ ጉባኤ ሲሆን የሶማሊያው የትምህርት ሚኒስቴር ፋራህ ሼህ አብዱልቃዶር ስዋሂሊ በቀጣይ ጉባኤያቸው እንግሊዝኛን ሊተካ እንደሚችልም አንስተዋል።

ሶማሊያ የስዋሂሊ ቋንቋን በትምህርት ስርዓቷ ከማካተቷ በተጨማሪ ከሶማሊኛ፣ አረብኛ እና እንግሊዝኛ እኩል የስራ ቋንቋ የማድረግ እቅድም እንዳላት ተገልጿል።

መረጃው የTRT ነው።

@TikvahethMagazine
60👏6🤷‍♂2🙏1
ወጋገን ባንክ በጀት ዓመቱ በታሪኩ ከፍተኛውን ገቢ ማስመዝገቡን ገለጸ።

ባንኩ በ2017 በጀት ዓመት 13.5 ቢሊዮን ገቢ ያስመዘገበ ሲሆን የአንድ አክሲዮን ትርፉንም ወደ 46.10 በመቶ ማሳደጉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መግለጫ ገልጿል።

ባንኩ በመግለጫው ምነ አለ ?

በገቢ ደረጃ ካለፈው በጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ38 በመቶ እድገት አሳይቷል።

- ከታክስ በፊት በታሪኩ ከፍተኛውን የ 3.85 ቢሊዮን ትርፍ አግኝቷል። ይህም ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ73 በመቶ ብልጫ አለው።

- የባለአክሲዮኖች ብዛትን ወደ 14,871 አሳድጓል።

- የባንኩ የተከፈለ ካፒታል የ37 በመቶ ዓመታዊ እድገት በማሳየት በበጀት ዓመቱ መጨረሻ ብር 7 ቢሊዮን ደርሷል። ይህም ብሔራዊ ባንክ ካስቀመጠው የባንኮች ዝቅተኛ የተከፈለ ካፒታል መስፈርት በላይ ነው።

- የባንኩ ጠቅላላ ካፒታል በ39 በመቶ በማደግ 12.8 ቢሊዮን ብር ደርሷል።

- የባንኩ ጠቅላላ ሀብት ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ29 በመቶ ብልጫ በማሳየት በበጀት ዓመቱ መጨረሻ ወደ ብር 84.7 ቢሊዮን ማደግ ችሏል።

- በበጀት ዓመቱ የባንኩ ተቀማጭ ገንዘብ የ28 በመቶ እድገት በማስመዝገብ ብር 66.5 ቢሊዮን ደርሷል።

- የሰጠው ብድር መጠን 53.5 ቢሊዮን ብር ደርሷል። ይህም ከባለፈው በጀት ዓመት አንፃር የ18 በመቶ ጭማሪ አለው።

@TikvahethMagazine
53👏7🔥2😢2👎1🙏1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከአሜሪካ የመጡ ኦርጅናል የፉርማሲ ብራንድ የMakeUp እቃዋችን ለምትፈልጉ @smoochcosmo page አይታችሁታል??
በጅምላ ወስዳችሁ አትርፉችሁ ለምትሸጡ ሱቆች በሚገርም የwholesale ዋጋዋች አቅርበንላችሗል! ግለሰቦችንም ከmarket በደንብ ባነሰ ዋጋ እናስተናግዳለን!
መደወል እና ማዘዝ ለምትፈልጉ call/Text ☎️ 𝟎𝟗𝟕𝟑𝟏𝟓𝟕𝟕𝟕𝟕 @smoochcosmocontact ወይም በtelegram በ📱𝟎𝟗𝟐𝟏𝟔𝟐𝟑𝟕𝟑𝟕 @hilluuuu ጻፉልን! እናመሰግናለን!
https://www.tg-me.com/SmoochCosmo
18👍2
2025/10/24 17:11:07
Back to Top
HTML Embed Code: