Telegram Web Link
የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ፓትርያርክ  መታሰቢያ ሐውልት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ጥቅምት 9 ቀን  2018 ዓ.ም ይመረቃል።

ምንጭ : EOTC

@TikvahethMagazine
184🤣13😢5👍4
በጠለፋና በአስገድዶ መድፈር የተከሰሰው ግለሰብ በ15 አመት ጽኑ እስራት ተቀጣ።

በካፋ ዞን በቢጣ ወረዳ ኦጊ ዳኪቲ ቀበሌ የካቲት 16 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 7:00 ሰዓት ላይ ገበያ ለመገበያየት እየሄደች ያለች የግል ተበዳይን ጠልፎ በመድፈር ወንጀል ተከሶ በ15 ዓመት እስራት መቀጣቱን ወረዳው አስታውቋል።

ተከሳሽ ለጊዜው እጃቸውን ለፖሊስ ካልሰጡ ግብራበሮቹ ጋር በመሆንና ስለታማ ቁስ በእጁ ይዞ በማስፈራራት የጠለፋ ወንጀል በመፈፀም ወደ ጌሻ ወረዳ ሀነቶ ቀበሌ አስገድዶ ስለመውሰዱ ነው ፖሊስ ያስረዳው።

በዚሁ መሠረት የቢጣ ወረዳ ፍርድ ቤት  ጥቅምት 3 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው የወንጀል ችሎት ተከሳሹ ኤልያስ ቆጭቶ በሁለት ወንጀሎች ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ በ15 አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል።

@TikvahethMagazine
👎4424😢17👏7🤬1
#Oromia: በኦሮሚያ ክልል በአዲስ መልክ ለተደራጁ የቀበሌ መዋቅሮች 6 ሺህ 800 የሞተር ብስክሌቶች ተከፋፍሏል።

የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ሽመልስ አብዲሳ የሞተር ብስክሌቶቹ በቀበሌ መዋቅር የመንግሥት አገልግሎት ፈጣን፣ ቀልጣፋና ውጤታማ ለማድረግ የሚሰራውን ሥራ የሚያግዙ በመሆኑ በአግባቡ ለተፈለገው ዓላማ እንዲውሉ አስገንዝበዋል። [OBN]

@TikvahethMagazine
👍66👎6218🤔11
#እንድታውቁት

ከዚህ ቀደም የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ሳይኖራችሁ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላችሁ ግብር ከፋዮች ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥራችሁን ከፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ጋር በአካል መሔድ ሳይጠበቅባችሁ https://mor-migration.fayda.et  በመጠቀም ማያያዝ የሚቻል መሆኑን የብሔራዊ መታወቂያ አስታውቋል።

እስካሁን በኢትዮጵያ ከ25 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን በፋይዳ አገልግሎት መመዝገብ ተችሏል ሲባል ከ91 በላይ ተቋማት ጋርም ትስስር ተፈጥሯል።

@TikvahethMagazine
24👎11👍3😢1
ባለ 15 ወለል የሲኒማ ኮምፕሌክስ በመዲናዋ በዛሬው ዕለት ሥራ መጀመሩን ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታወቁ።

በ24,000 ካ.ሜ ላይ ያረፈው "አዲስ ሲኒማ ኮምፕሌክስ" ባለ አራት ወለል የመኪና ማቆሚያ 592 ህፃናትንና 887 አዋቂዎችን የመያዝ አቅም ያላቸው ሁለት የሲኒማ አዳራሾችን ከሙሉ መገልገያዎች ጋር የያዘ ነው ተብሏል።

ከተማ አስተዳደሩ በቅርብ ጊዜ የህፃናትና ወጣቶች ቴአትርና ሲኒማ ኮምፕሌክስን አስመርቆ እንደነበር ይታወሳል።

@TikvahethMagazine
113👍26👎14🤔14😢3
🤙 ኑሮዎን ፒያሳ ላይ ያድርጉ

➣ ውብ አፓርትመንቶቻችን ለኑሮ ምቹ በሆነችው አዲሲቷ ፒያሳ ላይ እርሰዎን ይጠብቃል

   
     66 ካሬ ባለ 1 መኝታ
                 
➣  40% ሲከፍሉ 20% ቅናሽ  6,072,000 ብር ጠቅላላ ዋጋ

100% ለከፈለ 30% ቅናሽ 5,313,000 ብር ጠቅላላ ዋጋ
      
              2 መኝታ 75 ካሬ
  
➣ 40% ሲከፍሉ 20% ቅናሽ
6,900,000 ብር ጠቅላላ ዋጋ

100% ለከፈለ 30% ቅናሽ 6,037,500 ብር ጠቅላላ ዋጋ

          3 መኝታ 106 ካሬ

➣ 40% ሲከፍሉ 20% ቅናሽ 9,752,000 ብር ጠቅላላ ዋጋ

➣100% ለከፈለ  30% ቅናሽ 8,533,000 ብር ጠቅላላ ዋጋ

❗️ልብ ይበሉ ከላይ የተፃፉት አነስተኛ ካሬዎች ለ ምሳሌ ሲሆኑ ከፍ ያለ ካሬ ማግኜት ትችላላችሁ

ለበለጠ መረጃ
         👇
☎️
+251986687513

WhatsApp:- +251986687513
Email:-
[email protected]
18👍1
ፓኪስታንን በአዲስ አበባ

ከ 100 በላይ የፓኪስታን ካምፓኒዎችን በአንድ ቦታ ሊያገኟቸው ነው!
5ኛው የፓኪስታን-አፍሪካ የንግድ ልማት ጉባኤ እና ኤግዚቢሽን ከጥቅምት 6-8 በሚሊኒየም አዳራሽ ይካሄዳል::
የመድኃኒት ምርቶች እና የህክምና መሣሪያዎች፣ የውበት እና የቆዳ እንክብካቤ ውጤቶች፣ ጨርቃ ጨርቅ፣ የምግብ እና የግብርና ምርቶች (ሩዝ, ቅመማ ቅመሞች) ፣ የአውቶሞቲቭ መለዋወጫዎች፣ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣ የቤት እቃዎች
እና ሌሎችንም ን ምርቶች የሚያስመጡ ወይም የሚያከፋፍሉ ከሆነ ይህ እድል በፍፁም እንዳያመልጥዎት!!
ቀኑን ያስታውሱ ከጥቅምት 6-8 በሚሊኒየም አዳራሽ!!
ለበለጠ መረጃ www.pakafricaconnect.com ድህረገፃችንን ይጎብኙ
15
በአዲስ አበባ ከተማ የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አገልግሎት ምዝገባ ማካሄድ ጀምሯል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አገልግሎት የ2018 ዓ.ም ምዝገባ ከጥቅምት 1 እስከ ህዳር 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በሁሉም ጤና ጣቢያዎች የሚካሄድ መሆኑ ተገልጿል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ከ2 ሚሊዮን 500 ሺህ ለሚሆኑ የከተማዋ ነዋሪዎችን የማኅበረሰብ አቀፍ ጤና መድኅን አባል በማድረግ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማስቻሉን ገልጿል።

የዘንድሮው የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድኅን የአባልነት ምዝገባ የገቢ መጠንን መሰረት ያደረገ የአከፋፈል ሥርዓት እንደሚከተል ተነስቷል።

የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን በዓመት አንድ ጊዜ በሚዋጣ ገቢን መሰረት ያደረገ መዋጮ ራስን እና  ቤተሰብን ከድንገተኛ እና ካልታሰብ ወጪ በመታደግ መታከም የሚቻልበት ሥርዓት ነው።

ነዋሪዎች በተተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ በሚቀርባቸው  ጤና ጣቢያ ከጥቅምት 1 እስከ ህዳር 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ  በመመዝገብ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑም ጥሪ ቀርቧል።

በ2017 ዓ.ም ከ2.8 ሚሊዮን በላይ አባላትና ቤተሰቦቻቸው በተመላላሽ እና በተኝቶ ህክምና ከጤና ጣቢያ ጀምሮ ባሉ የመንግስት ጤና ተቋማት ተጠቃሚ መሆናቸው ተነግሯል፡፡

በዚህም ማህበረሰብ ከሚሰበሰበው መዋጮ በተጨማሪ የከተማ አስተዳደሩ በ2017 ዓ.ም ብቻ ለአገልግሎቱ 1.3 ቢሊዮን ብር ድጎማ አድርጓል ተብሏል፡፡

ምንጭ : ጤና ቢሮ ፤ ሸገር ኤፍ ኤም

@TikvahethMagazine
42👍10🙏3🤯1
2025/10/20 02:10:12
Back to Top
HTML Embed Code: