Telegram Web Link
በሜሪጆይ ኢትዮጵያ በሐዋሳ ከተማ የተገነባው የኩላሊት እጥበት ማዕከል ተመረቀ።

ሜሪጆይ ኢትዮጵያ  የኩላሊት እጥበት ማዕከል ሐዋሳ ቅርንጫፍ ከ29 ሚሊዬን ብር በላይ በፈጀ ወጪ ተገንብቶ ተመርቋል።

የክልሉ መንግስት 10 ሚሊዮን ብር እና አንድ አንቡላንስ መኪና ድጋፍ ሲያደርግ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር በበኩሉ የ5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

ማዕከሉ 13 የእጥበት ማሽን ያለው ሲሆን፤ በአንድ ጊዜ 12 ህመምተኞችን ያስተናግዳል ሲባል 10ሺህ ዙር የኩላሊት እጥበት ማከናወን እንደሚችልም ተጠቁሟል።

@TikvahethMagazine
74👍10👎2
#TanaForum

በአፍሪካ ፀጥታና ደህንነት ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረገው 11ኛው ጣና ፎረም በባህር ዳር እና አዲስ አበባ ከተሞች እንደሚካሄድ ተገለጸ።

የፎረሙ የመጀመሪ ምዕራፍ በባህር ዳር ጥቅምት 14  እንደሚካድ በመግለጽ፤ በፎረሙ በአፍሪካ ቀንድን የሚከታተሉ ልዩ መልዕክተኞች እንደሚወያዩ ገልጸዋል።

የፎረሙ ሁለተኛ ምዕራፍ ጥቅምት 15 እና 16 በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ጠቁመዋል። (EPA)

@TikvahethMagazine
31🤣16👎4👍1🕊1
BYD ከ115,000 በላይ የኤሌክትሪክ መኪናዎች ላይ ማሻሻያ እንደሚያስፈልጋቸው ገለጸ።

የቻይናው ግዙፉ የኤሌትሪክ መኪኖች አምራች ቢ.ዋይ.ዲ በዲዛይንና በባትሪ ተከላ ችግር ምክንያት ከ115,000 በላይ መኪኖችን ለማሻሻያ ወደ ማምረቻ እንዲመለሱ ጥሪ አቅርቧል።

ይህ ችግር የተገኘባቸው ከ2015 እስከ 2017 የተመረቱ ከ44 ሺ በላይ የታንግ እና ከ2021 እስከ 2022 የተመረቱ ከ71ሺ በላይ የዩዋን ፕሮ ሞዴሎች ላይ መሆኑ ተገልጿል።

በዩዋን ፕሮ ሞዴሎች ላይ ያጋጠመው ችግር ባትሪውን ከውኃ እንዲሁም ሌሎች ቆሻሻዎች ለመሸፈን የተገጠመው መከላከያ (Sealing Gasket) በአግባቡ አለመጥበቁ መሆኑ ተገልጿል።

ይህም ውኃ ወይም ሌሎች ነገሮች ወደ ኤሌክትሪካል ሲስተሙ እንዲገቡ እና ተግባሩን ሊረብሹ ይችላሉ።

ተቋሙ በተደጋጋሚ በምርቶቹ ላይ የማሻሻያ ጥሪ ቢያቀርብም ይህኛው ከእስካሁኖቹ በመጠን ከፍ ያለ ነው ተብሏል።

ኩባንያው ፈጠረ ያለውን ችግሮች ከክፍያ ነፃ እንደሚያስተካክል ተናግሯል።

ተጨማሪ ማንበብ ለምትፈልጉ ምንጮች ከላይ ተያይዘዋል።

@TikvahethMagazine
62🤣45👍5🤔5🔥4😢4👎2
ስለ ቴሌግራም ዳይሬክት ሚሴጅ (DM) ያውቃሉ ?

ቴሌግራም በቅርቡ በተለይ የቻናል ተከታታዮች መልዕክታቸውን በቀጥታ ለቻናል አስተዳዳሪዎች የሚልኩበት Direct Message (DM) የተሰኘ አገልግሎት አስተዋውቋል።

የቻናል ተከታዮች መልዕክት በዚሁ በኩል ሲልኩ የላኩት መልዕክት በቀጥታ ለቻናል አስተዳዳሪዎች የሚደርስ ሲሆን ቀጥታ ንግግር በዚያው በኩል ማድረግ ያስችላል።

የቻናል አስተዳዳሪዎችም የሚመጣላቸውን መልዕክት ለማስተዳደር የሚቀላቸው ሲሆን በተለይ ከተከታዮቻቸው ጋር የሚኖር ግንኙነትን ይበልጥ ያጠናክረዋል።

ይህንን አገልግሎት ለመጠቀም በመጀመሪያ የቻናል አስተዳዳሪዎች መፍቀድ የሚጠበቅባቸው ይሆናል። ፈቃድ በተሰጣቸው ቻናሎች ላይ ዳይሬክት ሚሴጅ ለተጠቃሚው በስተግራ በግርጌ በኩል ባለ 💬 ምልክት ማግኘት ይቻላል።

@TikvahethMagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
65👍11🙏5👎1🕊1
#Oromia: የኦሮሚያ  ክልላዊ መንግስት በዛሬው ዕለት በሞጆ ከተማ በተካሄደው መርሐግብር በሴፍቲኔት ድጋፍ ስር ለቆዩ ዜጎች ከ200 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የወጣባቸውን 1945 የውኃ ፖምፕ ሞተሮች ማስረከቡን የክልሉ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ገልጿል።

@TikvahethMagazine
69👎35👍19
#ጥንቃቄ: የጥቅምትና ቀጣይ ወራት ነፍሻማና ደረቅ የአየር ንብረት ለእሳት መከሰትና መባባስ አስተዋጾው ከፍተኛ በመሆኑ ህብረተሰብ እሳትና የእሳት ምንጮችን በሚጠቀም ጊዜ ከወትሮው የተለየ ጥንቃቄ እንዲያደርግ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አሳስቧል። (AMN)

@TikvahethMagazine
👍6834🤔2
ሙሉ ኮከብ ሪልሰቴት  በሲኤምሲ የሚገኝ ከ ስኩል ኦፍ ቱሞሮ ዝቅ ብሎ የሚገኝ እጅግ ዘመናዊ ና ጥራታቸውን የጠበቁ አፓርትመንት ቤቶች ይዘንሎት ቀርበናል
👉ግንባታቸው 100% የተጠናቀቁ  ቅንጡ አፓርታማ ቤቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ከባለ 1 መኝታ እስከ ባለ 4 መኝታ የተለያዬ የካሬ አማራጭ የያዘ
👉60% የባንክ ብድር አማራጭ የተዘጋጀላቸው
👉ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቁ እና በግንባታ ላይ ያሉ።
      
     🔸2 ሊፍት
      🔸️የከርሰ ምድር ውሃ
      🔸️backup ጀነኔተር
    🔸️የ ልጆች መጫወቻ እና አረንጓዴ ስፍራ የተሟላለት 3000 ካሬ ላይ ያረፈ ቅንጡ ኮምፓውንድ አፓርትመንት በኢትዮጵያ ብር ለሽያጭ አቅረበናል።

ባለ 1 መኝታ 82 ካሬ
ባለ 2 መኝታ 96,99, እና 105ካሬ
ባለ 3 መኝታ 120,124 እና 127 ካሬ
ባለ 4 መኝታ 181 ካሬ

60%ባንክ ብድር የተመቻቸላቸው ዲጅታል የተናጥል ካርታ የተዘጋጀላቸው

📣በ መሀል CMC መኖሪያ ቤቶን ይግዙ።

ለበለጠ መረጃ
💁‍♂📞 +2519-21-85-72-39
            +2519-48-74-31-71
13
ይሸጣል ብሎ መለጠፍ ድሮ ቀረ

ያገለገለ እቃዎትን ባሉበት ፎቶ በማንሳት ይሽጡ

ልብ ይበሉ ሁላችንም ቤት አንድ የማንፈልገውና የማንጠቀምበት ያገለገለ እቃ አለ በተቃራኒው ደግሞ ያንን እቃ የሚፈልጉ ግን የት እንደሚገኝ የማያውቁ ሰዎች አሉ።

አላማችን እርሶ የማይጠቀሙበትን ያገለገለ እቃ በቀላሉ ካሉበት ሆነው ፖስት በማስደረግ እንዲሸጡ ማስቻል ሲሆን ያገለገለ እቃ መግዛት ሲፈልጉ ደግሞ በቀጥታ ከእቃው ባለቤት በጥሩ ዋጋ እንዲገዙ ማገዝ ነው።

ስለሆነም እርሶም ቤት አገልግሎት ሳይሰጥ ቦታ ይዞ የተቀመጠ ያገለገለ እቃ ካሎት ፎቶ አንስተው ይላኩልን ወይም በሌሎች ሰወች ፖስት የተደረጉ ያገለገሉ እቃዎችን ፎቶ ፣ አድራሻ ፣ ዋጋ እና የእቃውን ባለቤት ስልክ ቁጥር በ ET Creatives በቀላሉ ያገኛሉ

JOIN 👉 https://www.tg-me.com/ET_Creatives_Family

ET Creatives
48
በፓሪስ ከሚገኝ ሙዚየም በእንቁዎች ያጌጡ ቅርሶች መሰረቃቸው ተገለጸ

ትናንት ማለዳ በፓሪስ ሉቨር ሙዚየም በዋጋ የማይተመኑ የተባሉ ጌጣ ጌጦች ተሰረቁ። የፓሪስ ፖሊስ የሌቦቹን ቡድን ለመያዝ አሰሳ እያደረገ መሆኑ ገልጿል።

የፈረንሳይ አገር ውስጥ ሚኒስትር ላውረንት ኑኔዝ እሁድ ዕለት ማለዳ ሙዚየሙ ለጎብኚዎች ክፍት በሆነ በደቂቃ ውስጥ ጭምብል ያጠለቁ ተጠርጣሪዎች ዘረፋውን ለመፈጸም ደቂቃዎች ብቻ እንደፈጀባቸው ተናግረዋል።

የዘራፊዎቹ ቡድን የሙዚየሙ የመጀመሪያ ፎቅ መስኮት ላይ ለመድረስ ከመኪና ላይ የተዘረጋ መሰላል መጠቀማቸው የተገለፀ ሲሆን፣ ጌጣጌጦቹን ለዕይታ ከተቀመጡበት ሰብረው በማውጣት በአነስተኛ ሞተር ሳይክል አምልጠዋል።

በዘራፊዎቹ የተወሰዱት ጌጣጌጦች የፈረንሳይ ንጉሣውያን ቤተሰቦች ይገለገሉባቸው የነበሩ ናቸው። ባለሥልጣናት ዘጠኝ ጌጣጌጦች መወሰዳቸውን ጨምረው አስታውቀዋል።

አራት ሰዎች በዘረፋው ላይ የተሳተፉ ሲሆን ሁለቱ ወደ ሕንጻው ከገቡ በኋላ ጠባቂዎችን ሲያስፈራሯቸው መሰላል የጫነ መኪና ወደ ሕንጻው የመጀመሪያ ፎቅ መስኮት በመጠጋት መሰላሉን መዘርጋቱን ተገልጿል።

እነዚህን የከበሩ ማዕድናትና የተዋቡ ጌጣ ጌጦችን ሙሉ በሙሉ ለመሸጥ መሞከር በቀላሉ ስለሚታወቅ ሊያጋልጣቸው ስለሚችል ወንጀለኞቹ በቀላሉ በታትኖ ለመሸጥ የሚያመቻቸውን ጌጣጌጦች መርጠዋል ነው የተባለው።

@TikvahethMagazine
42🤣21👏13🔥2
በታቦተ ህጉ ላይ የተሳለቁ አምስት ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ።

በደቡብ ምዕራብ ክልል በካፋ ዞን ዋቻ ከተማ አስተዳደር መስከረም መስከረም 26 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት ተከሳሽ አብረሃም ክፍል በሚል መጠሪያ በተከፈተ የቲክቶክ አካውንት በኦርቶዶክስ እምነትና በታቦተ ህጉ ላይ በመሳለቅ ቪዲዮ በመስራት ያጋሩ 5 ተከሳሾች በህግ ቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው ነበር።

ጉዳዩን የተመለከተው የዋቻ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጥቅምት 7 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት በአምስቱ ተከሳሾች እያንዳንዳቸዉ ላይ  በአንድ ዓመት ፅኑ እስራትእንዲቀጡ ወስኖባቸዋል

መረጃው የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ነው።

@TikvahethMagazine
👍32887🤣46👏22🤬13🤔10🤝6👎4🙏2
ሙሉ ኮከብ ሪልሰቴት  በሲኤምሲ የሚገኝ ከ ስኩል ኦፍ ቱሞሮ ዝቅ ብሎ የሚገኝ እጅግ ዘመናዊ ና ጥራታቸውን የጠበቁ አፓርትመንት ቤቶች ይዘንሎት ቀርበናል
👉ግንባታቸው 100% የተጠናቀቁ  ቅንጡ አፓርታማ ቤቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ከባለ 1 መኝታ እስከ ባለ 4 መኝታ የተለያዬ የካሬ አማራጭ የያዘ
👉60% የባንክ ብድር አማራጭ የተዘጋጀላቸው
👉ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቁ እና በግንባታ ላይ ያሉ።
      
     🔸2 ሊፍት
      🔸️የከርሰ ምድር ውሃ
      🔸️backup ጀነኔተር
    🔸️የ ልጆች መጫወቻ እና አረንጓዴ ስፍራ የተሟላለት 3000 ካሬ ላይ ያረፈ ቅንጡ ኮምፓውንድ አፓርትመንት በኢትዮጵያ ብር ለሽያጭ አቅረበናል።

ባለ 1 መኝታ 82 ካሬ
ባለ 2 መኝታ 96,99, እና 105ካሬ
ባለ 3 መኝታ 120,124 እና 127 ካሬ
ባለ 4 መኝታ 181 ካሬ

60%ባንክ ብድር የተመቻቸላቸው ዲጅታል የተናጥል ካርታ የተዘጋጀላቸው

📣በ መሀል CMC መኖሪያ ቤቶን ይግዙ።

ለበለጠ መረጃ
💁‍♂📞 +2519-21-85-72-39
            +2519-48-74-31-71
3
ባሉበት ፎቶ አንስተው በመላክ ያገለገለ እቃዎትን ይሽጡ - መግዛትም ይቻላል

ልብ ይበሉ ሁላችንም ቤት አንድ የማንፈልገውና የማንጠቀምበት ያገለገለ እቃ አለ በተቃራኒው ደግሞ ያንን እቃ የሚፈልጉ ግን የት እንደሚገኝ የማያውቁ ሰዎች አሉ።

አላማችን እርሶ የማይጠቀሙበትን ያገለገለ እቃ በቀላሉ ካሉበት ሆነው ፖስት በማስደረግ እንዲሸጡ ማስቻል ሲሆን ያገለገለ እቃ መግዛት ሲፈልጉ ደግሞ በቀጥታ ከእቃው ባለቤት በጥሩ ዋጋ እንዲገዙ ማስቻል ነው።

ስለሆነም እርሶም ቤት አገልግሎት ሳይሰጥ ቦታ ይዞ የተቀመጠ ያገለገለ እቃ ካሎት ፎቶ አንስተው ይላኩልን ወይም በሌሎች ሰወች ፖስት የተደረጉ ያገለገሉ እቃዎችን ፎቶ ፣ አድራሻ ፣ ዋጋ እና የእቃውን ባለቤት ስልክ ቁጥር በ ET Creatives በቀላሉ ያገኛሉ

JOIN 👉 https://www.tg-me.com/ET_Creatives_Family

ET Creatives
5
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በዐይን ውስጥ በሚቀበር ቺፕ ዕይታን ዳግም የመለሰው የምርምር ውጤት

ሳይንቲስቶች ከእድሜ ጋር የተገናኘ የዕይታ ማጣትን ሊቀርፍ የሚችል ግኝት አስተዋውቀዋል። ይህ ግኝት በአይን ውስጥ በሚቀመጥ ማይክሮ ቺፕ እንዲሁም በመነጽርና በእጅ በሚያዝ ፕሮሰሰር እገዛ የሚከወን ነው።

ይህ ጥናት በሙከራ ደረጃ በተመረጡ 38 ሰዎች ላይ የተሞከረ ሲሆን 12 ወራትን ከፈጀ ክትል በኋላ በዚህ ቴክኖሎጂ 84 በመቶ የሚሆኑት ሰዎች ዕይታቸው ሊመለስ ችሏል።

በዐይን ውስጥ የምትቀበረው አነስተኛ ቺፕ መጠኗ 2 ሚ.ሜ በ 2 ሚ.ሜ የሚሆኖ ሲሆን ከሪቲና በታች የሚቀበር ነው። በተጨማሪ በካሜራ የታገዘው መነጽር ምስሉን ወደ እጅ ወደሚያዘው ፕሮሰሰር በመላክ ወደ ኤሌክሪካል ሲግናል በመቀየር አዕምሯችን እንዲያነበው የሚያስችል ነው ተብሎለታል።

ይህ የምርምር ውጤት በዘርፉ ትልቅ ለውጥ የሚፈጥር እንደሚሆን ታምኖበታል።

ቪዲዮ: አሰራሩን የሚገልጽ መጠነኛ ቪዲዮ

@TikvahethMagazine
24👏7🤔4👎3
በቻይና የጄኔሬቲቭ ኤአይ ተጠቃሚዎች ቁጥር ምን ይመስላል ?

የቻይና ኢንተርኔት፣ ኔትወርክ፣ ኢንፎርሜሽን ማዕከል ባወጣው መረጃ እስከ 2025 አጋማሽ ድረስ 515 ሚሊዮን የጄኔሬቲቭ ኤአይ ተጠቃሚዎች አሉ ብሏል።

ይህ ቁጥር በ2024 ከነበረው በ36.5 በመቶ ጭማሪ ያሳየ ሲሆን 74.6 በመቶ የሚሆኑት እድሜያቸው ከ40 ዓመት በታች ነው። 37.5 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ የመጀመሪያ ዲግሪና ከዛ በላይ ያላቸው ናቸው።

በተጠቃሚዎች ቁጥር ብቻ ሳይሆን ቻይና በኤአይ የተደገፉ አገልግሎቶችንም በማቅረብ ረገድም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል። በሪፖርቱ መሰረትም 1.5 ሚሊዮን ከኤ አይ ጋር የተያያዘ የአዕምሯዊ መብት ምዝገባ ጥያቄ ቀርቧል።

@TikvahethMagazine
5
ኢትዮጵያ ብድሯን በዩዋን ለመክፈል ለቻይና ይፋዊ ጥያቄ አቅርባለች።

ኢትዮጵያ ከቻይና ከተበደረችው 5.38 ቢሊየን ዶላር ቢያንስ ከፊሉን ብድር በዩዋን ለመክፈል ከቻይና ጋር መነጋገር ጀምራለች።

ይህንን ጥያቄ ኢትዮጵያ በይፋ ማቅረቧንም የብሔራዊ ባንግ ገዢ አቶ እዮብ ተካልኝ በዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (IMF) ጉባኤ ላይ በነበራቸው ቃለመጠይቅ ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ እዳዋን በዩዋን ለመክፈል ከቻይና ጋር ስምምነት ላይ የምትደርስ ከሆነ በዶላር ትከፍል ከነበረው አነስተኛ ወለድ እንድትከፍል ያግዛታል።

በተመሳሳይ ስምምነት በቅርቡ ኬኒያ እዳዋን በዩዋን ለመክፈል ከቻይና መንግስት ጋር ሥምምነት ላይ በመድረሷ ሀገሪቱ 215 ሚሊዮን ዶላር የወለድ ክፍያ ማዳን ችላለች።

የብሔራዊ ባንክ ገዢው አቶ እዮብ ተካልኝ ይፋዊ ጥያቄ መቅረቡን ይግለጹ እንጂ በእዳው ምን ያህሉን በዩዋን ለመክፈል እንደታቀደ ከመግለፅ ተቆጥበዋል።

ምንጭ: ብሉምበርግ

@TikvahethMagazine
26🤣22👎3🕊1
"የአገልግሎት ለውጥ ያደረጉ በሊዝ የሚተዳደሩ 2,969 ቦታዎች የአገልግሎት ለውጥ ጥያቄያቸው ተቀባይነት አግኝቷል" - የአዲስ አበባ ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ሳይፈቀድላቸው የአገልግሎት ለውጥ ያደረጉ በሊዝ የሚተዳደሩ 2,969 ቦታዎች ወደሕጋዊ ሥርዓት እንዲገቡ የአገልግሎት ለውጥ ጥያቄዎችን ተቀብሎ ፈቃድ መስጠቱን አስታውቋል።

በእስካሁኑ ተፈቅዶላቸው የአገልግሎት ለውጥ ያደረጉ ባለይዞታዎች 2,969 ሲሆኑ 2,581 (86%) የሊዝ ባለይዞታዎች የሚጠበቅባቸውን ቅድመ ክፍያ ከፍለው በማጠናቀቅ ወደ ሕጋዊ ሥርዓት እንዲገቡ ወይም የንግድ ሥራቸውን እንዲቀጥሉ ተደርጓል ነው ያለው።

በበጀት ዓመቱ ከዚህ የአገልግሎት ለውጥ 2.4 ቢሊዮን ብር ገቢ ይሰባሰባል ተብሎ እንደሚጠበቅ የአዲስ አበባ ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ገልጿል።

ሳይፈቀድላቸው የአገልግሎት ለውጥ ያደረጉና ለውጥ የተፈቀደላቸው የሊዝ ባለይዞታዎች የሚጠበቅባቸውን የሊዝ ቅድመ-ክፍያ እስከ ግንቦት 30/2018 ዓ.ም ድረስ ከፍለው ማጠናቀቅ እንደሚጠበቅባቸውም ቢሮው አሳስቧል።

@TikvahethMagazine
15
2025/10/21 07:33:02
Back to Top
HTML Embed Code: