Telegram Web Link
“ ለተጨዋቾቹ አስፈሪ ቡድኖች አሉ ብዬ ነግሬያለሁ " ጋርዲዮላ

የማንችስተር ሲቲው ዋና አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ አል ሂላል በክለቦች አለም ዋንጫ ከአስፈሪ ቡድኖች አንዱ መሆኑን ተናገረዋል።

“ በዚህ ውድድር ትልቅ አቅም ያላቸው አስፈሪ ቡድኖች አሉ ብዬ ለተጨዋቾቹ ነግሬያለሁ " ያሉት ጋርዲዮላ አል ሂላል ከእነሱ ውስጥ አንዱ ነው ብለዋል።

“ አል ሂላል ተጋጣሚውን የመጉዳት አቅም አለው በፊት አድርገውታል አሁንም ያደርጉታል “ ጋርዲዮላ

ስለ ሳውዲ አረቢያ ሊግ እድገት ያነሱት ፔፕ ጋርዲዮላ " ሊጉ በግልጽ በሚታይ መልኩ እያደገ ነው " ብለዋል።

ማንችስተር ሲቲ ዛሬ ሌሊት 10:00 ሰዓት ከአል ሂላል ጋር ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
153😁35👍8👎4🤔2
TIKVAH-SPORT
“ የክለቦች አለም ዋንጫ የደከመ ሀሳብ ነው “ ክሎፕ ጀርመናዊው አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ አዲሱን የክለቦች አለም ዋንጫ ውድድር መጀመር ሀሳብ “ የማይረባ ሀሳብ “ ሲሉ ተችተዋል። “ የክለቦች አለም ዋንጫን የመጀመር ሀሳብ በእግርኳስ ከተተገበሩ ጥሩ ያልሆኑ ውሳኔዎች መካከል የከፋው ነው “ ሲሉ የርገን ክሎፕ ተናግረዋል። ውድድሩ በሚቀጥለው የውድድር አመት “ ተጨዋቾች ገጥሟቸው የማያውቀው ጉዳት…
ጋርዲዮላ የየርገን ክሎፕን ትችት ተጋርተዋል !

የማንችስተር ሲቲው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ የርገን ክሎፕ የክለቦች አለም ዋንጫ ላይ የሰነዘሩትን ትችት እንደሚጋሩ ገልጸዋል።

የርገን ክሎፕ የውድድሩን የመጀመር ሀሳብ “ በእግርኳስ ካየናቸው ጥሩ ያልሆኑ ውሳኔዎች መካከል የከፋው ነው “ ሲሉ ገልፀውት ነበር።

አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ በበኩላቸው “ በየርገን ክሎፕ ሀሳብ እስማማለሁ አስተያየቱ አላስገረመኝም እረዳዋለሁ “ ብለዋል።

ፔፕ ጋርዲዮላ አክለውም " ውድድሩ ተጨዋቾቻችንን እና ቀጣይ የውድድር አመታችንን ሊጎዳው ይችላል " ብለዋል።

የሰማያዊዎቹ አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ በተመሳሳይ ከቀናት በፊት ውድድሩን “ ቀልድ ነው “ ሲሉ ገልፀው ሲጀመር አሜሪካን ለእግርኳስ ትክክለኛ ቦታ አይደለችም ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
👏26582👍28😁22🥰2
TIKVAH-SPORT
ጋቶች ፓኖም በግብ አግቢነቱ ቀጥሏል ! የዋልያዎቹ የመሐል ሜዳ ተጫዋች ጋቶች ፓኖም በ ኢራቅ ሊግ ተከታታተይ ጨዋታዎች ግብ ማስቆጠሩን ቀጥሏል። ሁሉንም ጨዋታዎች ተሰልፎ እየተጫወተ የሚገኘው ጋቶች አራተኛ የሊግ ጎሉን ለኒው ሮዝ ስፖርት ክለብ አስቆጥሯል። ጋቶች ፓኖም ትላንት ምሽት ቡድኑን መሪ ያደረገች ግብ ሲያስቆጥር የጨዋታው ኮከብ በመባልም ተመርጧል። ኒውሮዝ ክለብ ትላንት ምሽት ተጋጣሚውን…
“ ተከታታይ ጎል በማስቆጠሬ ደስ ብሎኛል “ ጋቶች ፓኖም

በኢራቅ ሊግ ለክለቡ ኒው ሮዝ ስፖርት ክለብ በተከታታይ ጨዋታዎች ጎሎችን ያስቆጠረው ጋቶች ፓኖም በቆይታው ደስተኛ መሆኑን ተናግሯል።

ጋቶች ባለፉት ሁለት የሊግ ጨዋታዎች ለቡድኑ ብቸኛ የማሸነፊያ ግብን ጨምሮ ሁለት ግቦችን አስቆጥሯል።

“ ተከታታይ ጎል በማስቆጠሬ በግሌ ደስ ብሎኛል ፈጣሪንም አመሰግናለሁ “ ሲል ጋቶች ለዝግጅት ክፍላችን ሀሳቡን ሰጥቷል።

በተከታታይ ጎል ማግባት “ የሚጨምረው በራስ መተማመን አለ " የሚለው ጋቶች " እንደ ተጨዋች ጎል ባስቆጠርክ ቁጥር በራስ መተማመንህም ይጨምራል " ብሏል።

ከኢትዮጵያ ወደ ኢራቅ ካመራ ጀምሮ አሰልጣኙ እና የቡድኑ አባላት በእሱ ላይ ትልቅ እምነት እንዳጣሉ እና ቀጥታ በቋሚነት እንዳሰለፉት ጋቶች ተናግሯል።

“ አሰልጣኙ እኔ ላይ እምነት በመጣሉ ደስ ብሎኛል ማሳመን ደግሞ የእኔ ስራ ነበር እድሉን በአግባቡ ተጠቅሜ ከመጣሁ ጀምሮ እስካሁን በቋሚነት እየተጫወትኩ ነው።" ጋቶች ፓኖም

ስለ ቀጣይ ቆይታው ያነሳው ተጨዋቹ “ በቀጣይ እግዜር ነው የሚያውቀው የተሻለ ነገር ለማግኘት ፈጣሪ እንዲያሳካልኝ እመኛለሁ “ ብሏል።

ጋቶች ፓኖም በጥር ወር የተጨዋቾች ዝውውር መስኮት ነበር ኢትዮጵያ መድንን በመልቀቅ ወደ ኢራቅ ሊግ ያቀናው።

“ ኢትዮጵያ መድን ሻምፒዮን በመሆናችሁ እንኳን ደስ አላችሁ “ ያለው ጋቶች በትንሹ ለቡድኑ የአቅሜን ሰጥቻለሁ ለክለቡ አዲስ ታሪክ በመፃፋቸው ደስ ብሎኛል ብሏል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
266👏56🔥10😁9👍2
TIKVAH-SPORT
ጆን ኢቫንስ በዩናይትድ ሊቀጥል ነው ! ሰሜን አየርላንዳዊው የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ጆን ኢቫንስ በማንችስተር ዩናይትድ በአዲስ ሚና እንደሚቀጥል ተገልጿል። የ 37ዓመቱ ጆን ኢቫንስ ውሉ መጠናቀቁን ተከትሎ ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር መለያየቱ ተገልጾ ነበር። ተጫዋቹ አሁን ላይ በክለቡ አካዳሚ በሌላ ሚና ታዳጊ ተጨዋቾች ላይ እንዲሰራ ሀላፊነት እንደተሰጠው ተገልጿል። ጆን ኢቫንስ በቀጣይ የታዳጊ…
ጆን ኢቫንስ በሀላፊነት ተሾመ !

ሰሜን አየርላንዳዊው የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ጆን ኢቫንስ በማንችስተር ዩናይትድ በሀላፊነት ተሾሟል።

የ 37ዓመቱ ጆን ኢቫንስ በማንችስተር ዩናይትድ ያለው ውል መጠናቀቁን ተከትሎ ጫማውን መስቀሉን በይፋ አስታውቋል።

ተጫዋቹ አሁን ላይ በማንችስተር ዩናይትድ የተጨዋቾችን ውሰት ውል እንዲከታተል በሀላፊነት መሾሙ ይፋ ተደርጓል።

ጆን ኢቫንስ በቀጣይ የውሰት ውሎችን እንደሚቆጣጠር  የታዳጊ ተጨዋቾችን እድገት እንዲቆጣጠር እና ድጋፍ እንዲያደርግ ሀላፊነት እንደተሰጠው ተገልጿል።

ከክለቡ ጋር ሶስት የፕርሚየር ሊግ እና አንድ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ ያሳካው ጆን ኢቫንስ ያለው የእግርኳስ ልምድ በክለቡ እንዲቀጥል እንዳስቻለው ተነግሯል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
199😁40👍28
አርሰናል ተጨዋች ለማስፈረም ንግግር ጀመረ !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል የክሪስታል ፓላሱን የፊት መስመር ተጨዋች ኢዜ ለማስፈረም ንግግር መጀመሩ ተገልጿል።

መድፈኞቹ የተጫዋቹን ወኪሎች ማነጋገራቸው ሲገለፅ ተጫዋቹን ለማስፈረም ምን እንደሚያስፈልግ ማወቃቸው ተገልጿል።

ቶተንሀም በበኩሉ የተጨዋቹ ፈላጊ ክለብ መሆኑን የዝውውር ጉዳዮችን የሚከታተለው ጋዜጠኛ ፋብሪዝዮ ሮማኖ ተናግሯል።

ኢዜ ከዚህ በፊት " ህልሜ ለአርሰናል መጫወት ነው “ በሚለው ንግግሩ ይታወቃል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
324😁85👍23🔥16👎5
TIKVAH-SPORT
አስቶን ቪላ የሴት ቡድኑን ለመሸጥ አስቧል ! የፕርሚየር ሊጉ ክለብ አስቶን ቪላ የገጠመውን የፋይናንሻል ፌር ፕሌይ ችግር ለማስተካከል እንዲረዳው የሴት ቡድኑን ለመሸጥ ማሰቡ ተገልጿል። አስቶን ቪላ ባለፉት ሁለት አመታት የገጠማቸው የ 195 ሚልዮን ፓውንድ ኪሳራ ክለቡን የፋይናንሻል ፌር ፕሌይ ችግር ውስጥ ከቶታል። ይህንንም ተከትሎ ክለቡ የሴቶች ቡድኑን በመሸጥ ችግሩን ለማስተካከል ገዢ እያፈላለገ…
አስቶን ቪላ የሴት ቡድኑን ለመሸጥ ተስማማ !

የአስቶን ቪላ የገጠመውን የፋይናንሻል ፌር ፕሌይ ችግር ለማስተካከል እንዲረዳው የሴት ቡድኑን ለመሸጥ ከስምምነት መድረሱ ተገልጿል።

አስቶን ቪላ ባለፉት ሁለት አመታት የገጠማቸው የ 195 ሚልዮን ፓውንድ ኪሳራ ክለቡን የፋይናንሻል ፌር ፕሌይ ችግር ውስጥ ከቶታል።

ይህንንም ተከትሎ አስቶን ቪላ የሴቶች ቡድኑን መቀመጫውን አሜሪካ ላደረገ ለእህት ተቋም ለመሸጥ መስማማቱ ተነግሯል።

ቼልሲ ከዚህ በፊት የሴት ቡድኑን ለክለቡ እህት ተቋም በ 200 ሚልዮን ፓውንድ ሸጦ ያገኘው ገቢ የፋይናንስ ችግሩን ለመቅረፍ እንደረዳው ይታወሳል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
83😁36🥰8🤬2
እስቴቫኦ እንዴት ቼልሲን ሊገጥም ይችላል ?

ቼልሲ ባለፈው ጥር ወር ከብራዚሉ ክለብ ፓልሜራስ ወጣቱን የፊት መስመር ተጨዋች እስቴቫኦ ማስፈረማቸው ይታወሳል።

ሰማያዊዎቹ 34 ሚልዮን ዩሮ በማውጣት ያስፈረሙትን እስቴቫኦ እስከ አሁኑ ክረምት በፓልሜራስ እንዲቆይ አድርገው ነበር።

የ 18ዓመቱ ተጨዋች እስቴቫኦ ትንሽ በማይባሉ ብራዚላዊያን ከኔይማር በኋላ ለአለም ያበረከትነው ባለተሰጥኦ ነው ተብሎ ታምኖበታል።

ወጣቱ ተጨዋች በክለቦች አለም ዋንጫ ውድድር ሩብ ፍፃሜ የወደፊት ክለቡን ቼልሲ በተቃራኒው የሚገጥም ይሆናል።

ተጨዋቹ እንዴት ቼልሲን ሊገጥም ይችላል ?

ቼልሲ ተጨዋቹን ሲያስፈርም 18ዓመት ያልሞላው በመሆኑ ህጋዊ ዝውውሩን ማጠናቀቅ የሚችለው በዚህ ክረምት እንደነበር ተገልጿል።

ሁለቱም ክለቦች በክለቦች አለም ዋንጫ ውድድር መሳተፋቸው ነገሩን እንዳወሳሰበው ተገልጿል።

ሁለቱ ክለቦች ተጨዋቹ ፓልሜራስ ከውድድሩ እስከሚሰናበት ድርስ እዛው እንዲጫወት ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል።

ተጫዋቹ ከክለቦች አለም ዋንጫው በኋላ ወደ ቼልሲ የሚያደርገውን ዝውውር እንደሚያጠናቅቅ ተዘግቧል።

ተጨዋቹ ለፓልሜራስ ተሰልፎ ቼልሲን ከመግጠም የሚያስቆመው የፊፋ ህግ እንደሌለ ሲነገር ፊፋ የፓልሜራስ ተጨዋች እንደሆነ እንደሚያውቅ ተነግሯል።

ተጨዋቹ ቼልሲን እንዳይገጥም የሚያስቆመው የሁለቱ ክለቦች ስምምነት ብቻ እንደሚሆን እና ጥር ላይ በተደረሰው ውል ውስጥ የተቀመጠ አንቀጽ አለመኖሩ ተገልጿል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
203😁26👍11👏2🤔2
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#WanawSportswear✔️

ሙሉ የስፖርት ትጥቅዎትን በ1ደቂቃ በዋናው ሜዳ ቦት አፕሊኬሽን!
የእግር ኳስ ትጥቅዎትን ከቤትዎት አሊያም ከሰፈርዎት ሳይርቁ ይዘዙ!

🏃‍♂️ለተለያዩ ስፖርታዊ እንቅስቃኤዎች የሚሆኑ አልባሳቶች
ልኬት,የተጫዋች ስም እና አርማ | ይህ ሁሉ በሜዳ ቦት.
📱 ዛሬውኑ ይሞክሩት https://www.tg-me.com/WanawSportsBot

🛍 ከምሽት 2፡00 ሠዓት ጀምሮ ደግሞ በሁሉም ግብይቶች ላይ 2️⃣5️⃣🛍 ቅናሽ
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
19👍3
ዳኒ ካርቫል ወደ ሜዳ ይመለሳል !

ስፔናዊው የሪያል ማድሪድ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ዳኒ ካርቫል ወደ ሜዳ ለመመለስ ዝግጁ መሆኑን አስታውቋል።

በጉዳት ለረጅም ጊዜ ከሜዳ ርቆ የቆየው ዳኒ ካርቫል ከዘጠኝ ወራት በኋላ ለጨዋታ ብቁ መሆኑን አረጋግጧል።

“ከረጅም  ወራት በኋላ አሁን ለመጫወት ዝግጁ ነኝ “ ሲል ዳኒ ካርቫል አስተያየቱን ሰጥቷል።

ሪያል ማድሪድ ነገ ምሽት 4:00 ሰዓት ከጁቬንቱስ ጋር የጥሎ ማለፍ ጨዋታውን ያደርጋል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
101👍31👎8🥰4😁1
ዩናይትድ ዋትኪንስን ማስፈረም ይፈልጋል !

ማንችስተር ዩናይትድ የአስቶን ቪላውን የፊት መስመር ተጨዋች ኦሊ ዋትኪንስ ማስፈረም እንደሚፈልጉ ተገልጿል።

ቀያዮቹ ሴጣኖች ራስሙስ ሆይሉንድ ቡድኑን የሚለቅ ከሆነ ኦሊ ዋትኪንስን በተተኪነት ለማስፈረም በዝርዝራቸው መያዛቸው ተነግሯል።

የማንችስተር ዩናይትድ ሀላፊዎች በዝውውሩ ጉዳይ የአስቶን ቪላ አቻዎቻቸውን ማነጋገራቸው ተዘግቧል።

ማንችስተር ዩናይትድ እና አስቶን ቪላ ራሽፎርድን በዝውውሩ ለማካተት ንግግር ቢያደርጉም ራሽፎርድ ባርሴሎናን በመምረጡ እንዳልተሳካ ተገልጿል።

ዩናይትድ በቀጣይ በዝውውሩ ምን ላይ ይሰራሉ ?

ማንችስተር ዩናይትዶች አሁን ላይ ሙሉ ትኩረታቸው ብሪያን ምቤን ከብሬንትፎርድ ማስፈረም ላይ መሆኑ ተነግሯል።

ዩናይትድ ዝውውሩን ካጠናቀቁ በኋላ ተጨዋቾች በመሸጥ ለአዲስ ተጨዋቾች ክፍተት ለማግኘት እና ገንዘብ ለማሰባሰብ እንደሚሰሩ ተነግሯል።

ማንችስተር ዩናይትድ ተጨዋቾች የማይሸጥ ከሆነ ኦሊ ዋትኪንስን ማስፈረሙ ማስተማመኛ እንደሌለው ተነግሯል።

አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ቪክቶር ዮከሬሽን ለማስፈረም ከፍተኛ ፍላጎት ቢኖራቸውም አሁን ባለው ሁኔታ የተጨዋቹ ምርጫ አርሰናል መሆኑ ተጠቁሟል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
238😁89👎26👍23🤔6🔥3😢1
TIKVAH-SPORT
ሊዮኔል ሜሲ ውሉን ሊያራዝም ነው ! አርጀንቲናዊው የፊት መስመር ተጨዋች ሊዮኔል ሜሲ በኢንተር ሚያሚ ቤት ያለውን ኮንትራት እንደሚያራዝም ይፋ ሆኗል። የአለም ሻምፒዮኑ ሊዮኔል ሜሲ በኢንተር ሚያሚ ቤት እስከ 2026 ለመቆየት አዲስ ኮንትራት እንደሚፈረም ዘ አትሌቲክ አረጋግጧል። በክለቡ ያለው ኮንትራት በአመቱ መጨረሻ የሚጠናቀቀው ሊዮኔል ሜሲ በቅርቡ በይፋ አዲስ ውል ይፈርማል። @tikvahethsport    …
ሊዮኔል ሜሲ ኢንተር ሚያሚን ይለቅ ይሆን ?

ከኢንተር ሚያሚ ጋር ያለው ውል በ 2025 መጨረሻ የሚያበቃው ሊዮኔል ሜሲ ውሉን ለማራዘም ንግግር ላይ ይገኛል።

ሊዮኔል ሜሲ ውሉን እስከ 2026 ሊያራዝም መሆኑን ከዚህ በፊት ታማኝ የመረጃ ምንጮች መዘገባቸውም አይዘነጋም።

አሁን ላይ ሊዮኔል ሜሲ ውሉ ሲጠናቀቅ ተፎካካሪ ወደሆነ ሊግ ስለማቅናት ሊያስብ እንደሚችል ተዘግቧል።

ሊዮኔል ሜሲ ከ 2026 አለም ዋንጫ በፊት ያለውን ስድስት ወራት ተፎካካሪ በሆነ ሊግ በመጫወት ለውድድሩ ለመዘጋጀት ማሰቡ ተገልጿል።

ተጨዋቹ አሁን ላይ ከኢንተር ሚያሚ ጋር ውሉን ለማራዘም የሚያደርገው ንግግር ብዙም ለውጥ አለማሳየቱ ተነግሯል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የ 38ዓመቱ ሊዮኔል ሜሲ በቀጣዩ አለም ዋንጫ ውድድር ስለመሳተፉ በይፋ አላሳወቀም።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
274😁49👍34🔥9👎5🥰3
አሮን ራምሴይ ወደ ሜክሲኮ ሊያመራ ነው !

የቀድሞ የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል እና ጁቬንቱስ አማካይ አሮን ራምሴ የሜክሲኮውን ክለብ ፑማስ ለመቀላቀል ከስምምነት መድረሱ ተገልጿል።

ክለቡን ለመቀላቀል የህክምና ምርመራውን ያደረገው አሮን ራምሴይ ቀጣዩን የውድድር አመት በቡድኑ የሚያቆየውን ውል ለመፈረም ወደ ሜክሲኮ ለማምራት መዘጋጀቱ ተነግሯል።

ተጨዋቹ ከሳውዲ አረቢያ እና ዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ የቀረበለትን ጥያቄ ውድቅ በማድረግ ፑማስን ለመቀላቀል መምረጡ ተዘግቧል።

የ 34ዓመቱ አሮን ራምሴይ በውድድር አመቱ መጨረሻ በሶስት ጨዋታዎች ካርዲፍ ሲቲን በጊዜያዊነት አሰልጣኝነት መርቶ ነበር።

አሮን ራምሴይ ባለፈው አመት ለካርዲፍ ሲቲ አስር ጨዋታዎችን ማድረግ ችሏል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
127👍29😢12👏2
የኢንተር ሚላን ጨዋታ ሊቋረጥ ይችላል ?

በክለቦች አለም ዋንጫ ጥሎ ማለፍ ኢንተር ሚላን ከፍሉሚኔንስ ጋር ከደቂቃዎች በኋላ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

ጨዋታው ቼልሲ ከቤኔፊካ ጋር በተጫወቱበት ቻርሎቴ በሚገኘው የአሜሪካ ባንክ ስታዲየም ይካሄዳል።

የቼልሲ እና ቤኔፊካ ጨዋታ በአስቸጋሪ ዝናባማ የአየር ሁኔታ ምክንያት ለሁለት ሰዓታት እንዲቋረጥ ሆኖ ነበር።

ዛሬም በተመሳሳይ ጨዋታው በሚካሄድበት በአሜሪካ ቻርሎቴ አካባቢ አስቸጋሪ የአየር ንብረት ሁኔታ እንደሚጠበቅ ተነግሯል።

በአካባቢው ከባድ አውሎ ንፋስ ሊነሳ እንደሚችል ተተንብይዋል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
108😁26🥰6👍5👎1
“ ጋርዲዮላ የሁሉም አሰልጣኞች አርኣያ ነው “ ኢንዛጊ

የአል ሂላሉ ዋና አሰልጣኝ ሲሞን ኢንዛጊ ለማንችስተር ሲቲው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ትልቅ አድናቆት እንዳላቸው ገልጸዋል።

“ ለጋርዲዮላ የተለየ ፍቅር አለኝ “ የሚሉት ሲሞን ኢንዛጊ እሱ ለሁሉም አሰልጣኞች አርኣያ ነው በማለት ተናግረዋል።

አክለውም እግርኳስ ከፔፕ ጋርዲዮላ በፊት እና ከጋርዲዮላ በኋላ የተለየ ሆኗል ብለዋል።

“ አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ካሸነፋቸው ክብሮች በተጨማሪም የአሰልጣኝነት ፍልስፍና ያለው አሰልጣኝ ነው።" ሲሞን ኢንዛጊ

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
👍19491😁13🙏10🤩6🥰3👏2
ኢንተር ሚላን ከውድድሩ ተሰናበተ !

በክለቦች አለም ዋንጫ ውድድር ኢንተር ሚላን በብራዚሉ ክለብ ፍሉሚኔንስ ተሸንፎ ከውድድሩ ውጪ ሆኗል።

ፍሉሚኔንስ አርጀንቲናዊው ጀርማን ካኖ እና ሄርኩለስ ባስቆጠሯቸው ግቦች 2ለ0 ማሸነፍ ችሏል።

በአስቸጋሪ የአየር ንብረት ምክንያት የመቋረጥ ስጋት የነበረበት ጨዋታው ያለምንም እክል ሊጠናቀቅ ችሏል።

በጨዋታው የፍሉሚኔንሱ ተከላካይ ሬኔ የማስጠንቀቂያ ካርድ መመልከቱን ተከትሎ ቀጣይ ጨዋታ በቅጣት የሚያመልጠው ይሆናል።

ፍሉሚኔንስ ፓልሜራስን በመከተል ሩብ ፍፃሜውን የተቀላቀለ ሁለተኛው የብራዚል ክለብ መሆን ችሏል።

ኢንተር ሚላን ሩብ ፍፃሜውን ባለመቀላቀሉ ያገኝ የነበረውን 12.2 ሚልዮን ዩሮ ክፍያ አጥተዋል።

የብራዚሉ ክለብ ፍሉሚኔንስ በሩብ ፍፃሜው የማንችስተር ሲቲ እና አል ሂላልን አሸናፊ የሚገጥሙ ይሆናል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
230😁65👍15😢12👏1
ክረምትን በምን ሊያሳል አስበዋል?

Can PlayStation 🎮 መፍትሄ ይዞ ብቅ ብሏል🫴

-Sony
PlayStation 2
PlayStation 3
PlayStation 4
PlayStation 5

-Microsoft
Xbox 360
Xbox one
Xbox one s
Xbox Series

ምርቶችን አዘጋጅቶ እናንተን በመጠበቅ ላይ ነን! እንግዲያውስ እርሶ በተመችዎት ሰዓት ብቅ በማለት ሱቃችን መጎብኘት ይችላሉ።

እቃዎቻችን 6 ወር ዋስትና ስላለው ያለ ሀሳብ ይዝናኑ።

ለልጅም ሆነ ለአዋቂ የሚሆኑ PlayStation Cidi Game ስላሉን ይደውሉልን።

Tv በተለያየ Brand እና Size እኛ ዘንድ ያገኛሉ።

ባሎት ማንኛውም እቃ መቀያየር ይቻላል።

ለክፍለ ሀገር እናቀርባለን ይደውሉ።

🤝Thanks for choice!

አድራሻ፡፦
ቁጥር 1፦  መገናኛ
ቁጥር  2፦  ቦሌ

ስልክ፦ 0904658609 ወይም                  0910529770
0977349492  ይደውሉ

ለአዳዲስ መረጃ Telegram channel join ይበሉ ፦
https://www.tg-me.com/CanPlaystation

                       👍Update Your Life

    Can PlayStation እና Tv Market
23
ኦዶች ዛሬም ከፍ ብለዋል!
ታዲያ ምን ይጠብቃሉ? ለማሸነፍ በተመቻቹ ኦዶች ይወራረዱ!
አሁኑኑ Betika.et ላይ ብቻ!
ቤቲካ የአሸናፊዎች ቤት!
11👍1
" የተፈጠረው ነገር ጤናማ አይደለም “ ጋርዲዮላ

ማንችስተር ሲቲ ከአል ሂላል ጋር ያደረገውን የጥሎ ማለፍ ጨዋታ 4ለ3 ተሸንፎ ከውድድሩ ውጪ ሆነዋል።

በጉዳት ምክንያት ወሳኝ ተጨዋቾቹን አጥቶ ወደ ሜዳ የገባው አል ሂላል ታሪካዊ ድል ማስመዝገብ ችሏል።

ከጨዋታው በኋላ አስተያየታቸውን የሰጡት ፔፕ ጋርዲዮላ “ የተፈጠረው ነገር ጤናማ አይደለም አል ሂላል ጥሩ ነበሩ ትልቅ ችግር ፈጥረውብናል ብለዋል።

አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ በክለቦች አለም ዋንጫ ውድድር ታሪክ የገጠማቸው የመጀመሪያ ሽንፈት ሆኖ ተመዝግቧል።

ፔፕ ጋርዲዮላ በውድድሩ ታሪክ ሶስት ክለቦችን ሲመሩ አጠቃላይ 11 ጨዋታዎች አድርገው የተቆጠረባቸው አራት ጎል ነው።

በተጋጣሚያቸው ላይ 38 ጎል ያስቆጠሩት ፔፕ ጋርዲዮላ አሁን ላይ በአል ሂላል በአንድ ጨዋታ አራት ግቦችን አስተናግደዋል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
254😁138👍32😢8👏7👎6🤩4
2025/07/12 15:57:14
Back to Top
HTML Embed Code: