Telegram Web Link
ኦዶች ዛሬም ከፍ ብለዋል!
ታዲያ ምን ይጠብቃሉ? ለማሸነፍ በተመቻቹ ኦዶች ይወራረዱ!
አሁኑኑ Betika.et ላይ ብቻ!
ቤቲካ የአሸናፊዎች ቤት!
ክረምትን በምን ሊያሳልፋ አስበዋል?

Can PlayStation 🎮 መፍትሄ ይዞ ብቅ ብሎሎታል🫴

-Sony
PlayStation 2
PlayStation 3
PlayStation 4
PlayStation 5

-Microsoft
Xbox 360
Xbox one
Xbox one s
Xbox Series

ምርቶችን አዘጋጅቶ እናንተን በመጠበቅ ላይ ነን
እንግዲያውስ እርሶ በተመቻቹ ሰአት ብቅ በማለት ሱቃችን መጎብኘት ይችላሉ

እቃዎቻችን 6 ወር ዋስትና ስላለው የለ ሀሳብ ይዝናኑ

ለልጅም ለአዋቂ የሚሆኑ PlayStation Cidi Game ስላሉን ይደውሉልን

Tv በተለያየ Brand እና Size እኛ ዘንድ ያገኛሉ

ባሎት ማንኛውም እቃ መቀያየር ይቻላል

ለክፍለ ሀገር እናቀርባለን ይደውሉ

🤝Tanks for choice

አድራሻ፡፦
ቁጥር 1፦  መገናኛ
ቁጥር  2፦  ቦሌ

ስልክ፦ 0904658609 ወይም                  0910529770
0977349492  ይደውሉ

ለአዳዲስ መረጃ Telegram channel join ይበሉ ፦
https://www.tg-me.com/CanPlaystation

                       👍Update Your Life

    Can PlayStation እና Tv Market
TIKVAH-SPORT
ዩናይትድ ተጨዋች ለማስፈረም እያነጋገሩ ነው ! ማንችስተር ዩናይትድ ወጣቱን ተጨዋች ዲያጎ ሊዮን ከፓራጓዩ ክለብ ሴሮ ፖርቴኖ ለማስፈረም ንግግር ላይ መሆናቸው ተገልጿል። ቀያዮቹ ሴጣኖች የ 17ዓመቱን ወጣት የግራ መስመር ተመላላሽ ዲያጎ ሊዮን በሚቀጥለው አመት ለማስፈረም ንግግር መጀመራቸውን ዘ አትሌቲክ ዘግቧል። ተጨዋቹ በዚህ የውድድር አመት በክለቡ በአስራ ዘጠኝ ጨዋታዎች ተሰልፎ መጫወቱ ተነግሯል።…
ዩናይትድ በይፋ ተጨዋች አስፈረመ !

ማንችስተር ዩናይትድ ወጣቱን ተጨዋች ዲያጎ ሊዮን ከፓራጓዩ ክለብ ሴሮ ፖርቴኖ ማስፈረማቸውን በይፋ አስታውቀዋል።

ቀያዮቹ ሴጣኖች የ 18ዓመቱን ወጣት የግራ መስመር ተመላላሽ ዲያጎ ሊዮን ለማስፈረም ጥር ላይ መስማማታቸው አይዘነጋም።

ማንችስተር ዩናይትድ ለተጨዋቹ ዝውውር ስድስት ሚልዮን ፓውንድ ማውጣታቸው ተነግሯል።

ተጨዋቹ በቀጣይ በቅድመ ውድድር ቡድኑን እንደሚቀላቀል ሲጠበቅ ለክለቡ ከ 21ዓመት በታች ቡድንም ይጫወታል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ካይል ዎከር በርንሌይን ለመቀላቀል ተቃርቧል ! እንግሊዛዊው የመስመር ተጨዋች ካይል ዎከር አዲስ አዳጊውን በርንሌይ ለመቀላቀል ከጫፍ መድረሱ ተገልጿል። በርንሌይ የ 35ዓመቱን ተጨዋች ካይል ዎከር በቋሚነት ለማስፈረም የጤና ምርመራውን ለማድረግ መዘጋጀታቸው ተነግሯል። ተጨዋቹ በበርንሌይ የሁለት አመት ኮንትራት ይፈርማል ተብሎ ሲጠበቅ በርንሌይ በበኩሉ ለቡድኑ የረጅም ጊዜ ልምድ ባለቤት ተጨዋች ያገኛል።…
በርንሌይ በይፋ ካይል ዎከርን አስፈረመ !

እንግሊዛዊው የመስመር ተጨዋች ካይል ዎከር ማንችስተር ሲቲን በመልቀቅ አዲስ አዳጊውን በርንሌይ መቀላቀሉ ይፋ ተደርጓል።

በርንሌይ የ 35ዓመቱን የመስመር ተጨዋች ካይል ዎከር በሁለት አመት ኮንትራት አስፈርመዋል።

ካይል ዎከር በቶተንሀም በነበረው ቆይታ ከአሁኑ የበርንሌይ አሰልጣኝ ስኮት ፓርከር ጋር ለሁለት አመታት ተጫውተዋል።

ማንችስተር ሲቲ በሚቀጥለው አመት ውሉ ከሚጠናቀቀው ካይል ዎከር ዝውውር አምስት ሚልዮን ፓውንድ መቀበላቸው ተገልጿል።

ካይል ዎከር ስድስት የፕርሚየር እና አንድ የሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ ካሳካበት ማንችስተር ሲቲ ጋር ተለያይቷል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አርሰናል ኖኒ ማዱኬን ማነጋገር ጀመሩ !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል እንግሊዛዊውን የቼልሲ የፊት መስመር ተጨዋች ኖኒ ማዱኬ ለማስፈረም ስራ መጀመራቸው ተገልጿል።

መድፈኞቹ ተጫዋቹን በግል በማነጋገር ላይ መሆናቸው ሲገለፅ በጥቅማጥቅም ዙሪያ ለስምምነት ተቃርበዋል ተብሏል።

ተጨዋቹ ቼልሲ እንዲለቀው ባይጠይቅም አርሰናል ሊያስፈርመው ከፈለገ ፍቃደኛ መሆኑ ተዘግቧል።

አርሰናል ከተጨዋቹ ጋር ለስምምነት ይቃረቡ እንጂ ገና ክለቡ ቼልሲን ማነጋገር አልጀመሩም።

ኢንዞ ማሬስካ ስለ ማዱኬ ምን አሉ ?

የቼልሲው አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ ስለ ኖኒ ማዱኬ የወደፊት ቆይታ ተጠይቀው “ እኔ የምፈልገው እዚህ ከእኛ ጋር ደስተኛ የሆነን ተጨዋች ነው " ብለዋል።

አሰልጣኙ አክለውም “ እዚህ ከእኛ ጋር ደስተኛ ያልሆነ ተጨዋች መልቀቅ ከፈለገ መልቀቅ ይችላል “ ሲሉ ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ቼልሲ ተጨዋች ለማስፈረም ተስማማ ! የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ የእንግሊዛዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ጄሚ ጊቴንስ ለማስፈረም ከዶርትመንድ ጋር ከስምምነት ደርሰዋል። ሰማያዊዎቹ ተጫዋቹን ለማስፈረም ከቦርስያ ዶርትመንድ ጋር ከስምምነት መድረሳቸው የተገለፀ ሲሆን በቀጣይ የጤና ምርመራ ያደርጋሉ ተብሏል። ቼልሲዎች ተጫዋቹን በሰባት አመት ኮንትራት ለማስፈረም ቀደም ብለው በግል ከስምምነት መድረሳቸው…
ቼልሲ ተጨዋች አስፈረመ !

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ የእንግሊዛዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ጄሚ ጊቴንስ ከዶርትመንድ አስፈሬመዋል።

ቼልሲዎች ተጫዋቹን 48.5 ሚልዮን ፓውንድ በማውጣት በሰባት አመት ኮንትራት ማስፈረማቸውን በይፋ አስታውቀዋል።

ተጨዋቹ ፊርማውን ካኖረ በኋላ “ እንደ ቼልሲ ያለ ትልቅ ክለብ መቀላቀል ስሜቱ የተለየ ነው በማለት ተናግሯል።

ከአምስት አመታት በፊት ከማንችስተር ሲቲ አካዳሚ ዶርትመንድን የተቀላቀለው ጄሚ ጊቴንስ ለዋናው ቡድን 106 ጨዋታዎች ማድረግ ችሏል።

የ 20ዓመቱ ጄሚ ጊቴንስ በተጠናቀቀው የውድድር አመት ጥሩ ጊዜ ሲያሳልፍ ለዶርትመንድ የሻምፒየንስ ሊግ አራት ግቦችን ጨምሮ 12 ጎሎች አስቆጥሯል።

በግራ የፊት መስመር መጫወት የሚቀናው ጄሚ ጊቴንስ በተጨማሪም የአጥቂ አማካይ ቦታ ተሰልፎ የመጫወት የተለየ ክህሎት እንዳለው ይነገራል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዲያጎ ጆታ በምሽቱ ጨዋታ ይታሰባል !

በምሽቱ የፒኤስጂ እና ባየር ሙኒክ የክለቦች አለም ዋንጫ ጨዋታ ዲያጎ ጆታ እና ወንድሙ እንደሚታሰቡ ተገልጿል።

በአሳዛኝ አደጋ ህይወታቸው ያለፈው ተጨዋቾቹ ትላንት በተደረጉ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎች ላይ ታስበው እንደነበር ይታወሳል።

በትላንቱ የአል ሂላል ጨዋታ ተጨዋቾቹ ሲታሰቡ ዲያጎ ጆታ የቡድን አጋሮች ሩበን ኔቬዝ እና ጇ ካንሴሎ ስሜታዊ ሆነው ነበር።

በፒኤስጂ ቡድን ውስጥ በፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን ከዲያጎ ጆታ ጋር የተጫወቱ አምስት ተጨዋቾች ይገኛሉ።

ኑኖ ሜንዴዝ ፣ ቪቲንሀ ፣ ጇ ኔቬስ ፣ ራሞስ እና ሬናቶ ሳንቼዝ በፒኤስጂ የሚገኙ የተጨዋቹ ቅርብ ተጨዋቾች ናቸው።

በሌላ በኩል በባየር ሙኒክ ውስጥ ተጨማሪ ሁለት ተጨዋቾች ራፋኤል ጉሬሮ እና ጆ ፓልሂንሀ ይገኛሉ።

@Tikvahethsport       @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
አርሰናል ኖኒ ማዱኬን ማነጋገር ጀመሩ ! የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል እንግሊዛዊውን የቼልሲ የፊት መስመር ተጨዋች ኖኒ ማዱኬ ለማስፈረም ስራ መጀመራቸው ተገልጿል። መድፈኞቹ ተጫዋቹን በግል በማነጋገር ላይ መሆናቸው ሲገለፅ በጥቅማጥቅም ዙሪያ ለስምምነት ተቃርበዋል ተብሏል። ተጨዋቹ ቼልሲ እንዲለቀው ባይጠይቅም አርሰናል ሊያስፈርመው ከፈለገ ፍቃደኛ መሆኑ ተዘግቧል። አርሰናል ከተጨዋቹ ጋር ለስምምነት…
አርሰናል ኖኒ ማዱኬን ለማስፈረም ተስማማ !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል እንግሊዛዊውን የቼልሲ የፊት መስመር ተጨዋች ኖኒ ማዱኬ ለማስፈረም በግል ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል።

መድፈኞቹ በቀጣይ ተጫዋቹን ለማስፈረም ከቼልሲ ጋር ተቀራርበው ለመነጋገር ማሰባቸው ተነግሯል።

ተጨዋቹ ለመድፈኞቹ ፍቃዱን የሰጠ ሲሆን አርሰናል ከቼልሲ ጋር ያለውን ጥሩ ግንኙነት ተጠቅሞ ዝውውሩን ያጠናቅቃል ተብሎ ይጠበቃል።

አርሰናል ተጫዋቹን የቀኝ የፊት መስመሩን ለማጠናከር እንዳጩት ሲገለፅ በተቃራኒ ቦታ መጫወት መቻሉ ለቡድኑ ተጨማሪ አቅም ይፈጥራል ተብሎ ታስቧል።

አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በዚህ ክረምት የፊት መስመራቸውን ለማጠናከር ሁለገብ ተጨዋች በማፈላለግ ላይ መሆናቸው ይታወቃል።

ኖኒ ማዱኬ በዚህ አመት ለቼልሲ 45 ጨዋታዎች ሲያደርግ 11 ግቦችን አስቆጥሮ አምስት አመቻችቶ አቀብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ኖቲንግሃም ሲጠይቀኝ ሁለቴ አላሰብኩም “

ኖቲንግሀም ፎረስት ብራዚላዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ኢጎር ጄሱስ ከቦታፎጎ ማስፈረማቸውን አሳውቀዋል።

የ 24ዓመቱ ተጨዋች ኢጎር ጄሱስ ለኖቲንግሀም ፎስት የአራት አመት ኮንትራት ፈርሟል።

ተጨዋቹ ከፊርማው በኋላ “ ኖቲንግሃም ፎረስት ሲጠይቀኝ ለመቀበል ሁለቴ አላሰብኩም “ ሲል ተደምጧል።

ክለቡ ባቀረበለት እቅድ መደነቁን የገለፀው ተጨዋቹ ወደዚህ በመምጣቴ ተተደስቻለሁ በማለት ተናግሯል።

ባለፈው አመት ከዩናይትድ አረብ ኤምሬትሱ ሻባብ አል አህሊ ቦታፎጎን የተቀላቀለው ተጨዋቹ 59 ጨዋታዎች አድርጎ 17 ጎሎችን አስቆጥሯል።

ተጨዋቹ ከዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ ሊግ ወደ ሀገሩ ከተመለሰ በኋላ ለብራዚል ብሔራዊ ቡድን ጥሪ ቀርቦለት እንደነበር ይታወሳል።

@Tikvahethsport       @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፍ !

1:00 ፒኤስጂ ከ ባየር ሙኒክ

@Tikvahethsport       @kidusyoftahe
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ልዩ የእግር ኳስ ጥቅል ለክለቦች ዋንጫ ሩብ ፍጻሜ!⚽️

አጓጊውን የፒኤስጂ እና ባየርን ሙኒክ ጨዋታ ለ3 ሰአታት በሚቆይ ልዩ 2.5ጊባ ጥቅል ከዳር እስከ ዳር በሚገኘው በሳፋሪኮም ኔትወርክ ላይ በDSTV በቀጥታ እንከታተል!

#SafaricomEthiopia  #1Wedefit
#Furtheraheadtogether
ባየር ሙኒክ ተጨዋቾቹ ለቅጣት ተቃርበዋል !

ዛሬ ምሽት ከፒኤስጂ ወሳኝ ጨዋታ ያለበት የጀርመኑ ክለብ ባየር ሙኒክ በርካታ ተጨዋቾቹ ለቅጣት ተቃርበዋል።

ባየር ሙኒክ ስድስት ተጨዋቾቹ ዛሬ የማስጠንቀቂያ ካርድ የሚመለከቱ ከሆነ ቡድኑ ለግማሽ ፍፃሜው ካለፈ አንድ ጨዋታ የሚቀጡ ይሆናል።

ሀሪ ኬን ፣ ጀማል ሙሲያላ ፣ ጆሽዋ ኪሚች ፣ ጆናታን ታህ ፣ ጎሬዝካ እና ኮንራድ ላይመር ለቅጣት የተቃረቡ ተጨዋቾች ናቸው።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
2'

ፒኤስጂ 0 - 0 ባየር ሙኒክ

@Tikvahethsport       @kidusyoftahe
14'

ፒኤስጂ 0 - 0 ባየር ሙኒክ

@Tikvahethsport       @kidusyoftahe
33 '

ፒኤስጂ 0 - 0 ባየር ሙኒክ

@Tikvahethsport       @kidusyoftahe
እረፍት

ፒኤስጂ 0 - 0 ባየር ሙኒክ

@Tikvahethsport       @kidusyoftahe
60 '

ፒኤስጂ 0 - 0 ባየር ሙኒክ

@Tikvahethsport       @kidusyoftahe
70 '

ፒኤስጂ 0 - 0 ባየር ሙኒክ

@Tikvahethsport       @kidusyoftahe
2025/07/05 22:02:41
Back to Top
HTML Embed Code: