Telegram Web Link
ሊድስ ዩናይትድ ሎንግስታፍን ሊያስፈርም ነው !

አዲስ አዳጊው ክለብ ሊድስ ዩናይትድ ሎንግስታፍን ከኒውካስል ዩናይትድ ለማስፈረም በጥረት ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

ሊድስ ዩናይትድ ለ 27ዓመቱ አማካይ 10 ሚልዮን ፓውንድ እና ተጨማሪ ሁለት ሚልዮን ክፍያ ማቅረባቸው ተነግሯል።

ኒውካስል ዩናይትድ እስካሁን ለዝውውር ጥያቄው ምላሽ አለመስጠታቸው ተነግሯል።

ሊድስ ከኒውካስል ዩናይትድ ጋር ከስምምነት መድረስ ካልቻሉ ወደ ሌላ አማራጭ እንደሚሄዱ ተጠቁሟል።

የኒውካስል አካዳሚ ውጤት ሎንግስታፍ በሚቀጥለው አመት በነፃ ከሚለቅ በዚህ አመት ክለቡ ተጠቃሚ እንዲሆን እንደሚፈልግ ተዘግቧል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
45👍7
ዩናይትድ ግብ ጠባቂ ለማስፈረም ተመልክቷል !

ማንችስተር ዩናይትድ ሌላ ግብ ጠባቂ ማስፈረምን ከእቅዳቸው አለማውጣታቸው እና ሊያስፈርሙ እንደሚችሉ ተነግሯል።

ቀያዮቹ ሴጣኖች ግብ ጠባቂ ለማስፈረም ከወሰኑ የ 29ዓመቱን የቦታፎጎ ግብ ጠባቂ ጆን ለማስፈረም ኢላማ ማድረጋቸው ተገልጿል።

የቡድኑ ቁጥር አንድ ግብ ጠባቂ አንድሬ ኦናና በዚህ አመት በክለቡ ይቀጥላል የሚል እምነት እንዳለ መዘገቡ አይዘነጋም።

አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም በተጨማሪም የመሐል ሜዳውን ማጠናከር እንደሚፈልጉ ተገልጿል።

ይህንንም ተከትሎ ማንችስተር ዩናይትድ የቫሌንሽያውን ዣቪ ጉዌራ ለማስፈረም ፍላጎት ማሳየታቸው ተዘግቧል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
😁10266👍14👎3
ዩናይትድ ሞይስ ኪንን ማስፈረም ይፈልጋል !

ማንችስተር ዩናይትድ በቡድኑ ውስጥ ክፍተት የሚያገኝ ከሆነ ተጨማሪ የፊት መስመር አጥቂ ለማስፈረም ማሰባቸው ተገልጿል።

ቀያዮቹ ሴጣኖች ለማስፈረም ከተመለከቷቸው አጥቂዎች መካከል የፊዮሬንቲናው ሞይስ ኪን ቀዳሚው መሆኑ ተነግሯል።

ተጨዋቹ በኮንትራቱ ውስጥ በቀጣይ አንድ ሳምንት ውስጥ ሊሰራ የሚችል 52 ሚልዮን ዩሮ የውል ማፍረሻ እንዳለው ተዘግቧል።

ዩናይትድ ተጫዋቹን አጥብቆ የፈለገ የፕርሚየር ሊግ ክለብ መሆኑ ሲገለፅ ከሳውዲ አረቢያ ሊግም ተጨዋቹን ማስፈረም እንደሚፈልጉ ተጠቁሟል።

ሞይስ ኪን ፊዮሬንቲናን ከተቀላቀለ ወዲህ እውነተኛ የፍፁም ቅጣት ምት ክልል አጥቂ ሆኖ መጎልበቱ ተገልጿል።

ባለፈው አመት 19 የሊግ ጎል ያገባ ሞይስ ኪን በአማካይ ከሚነካቸው 100 ኳሶች ስድስት ኢላማውን የጠበቀ ሙከራ ሲያደርግ በሴርያው ትልቁ ቁጥር መሆኑ ተዘግቧል።

በተጨማሪም ማንችስተር ዩናይትድ ከኮንትራት ነፃ የሆኑት አጥቂዎች ጄሚ ቫርዲ ፣ ካሉም ዊልሰን እና ካልቨርት ሌዊን ቀርበውለታል።

ማንችስተር ዩናይትድ አጥቂ ሳያስፈርም አመቱ ከተጠናቀቀ ከኮንትራት ነፃ ተጨዋቾችን ይመለከታል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተዘግቧል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
124😁68👍20👎9
የሮድሪጎ የአርሰናል ዝውውር ?

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል በቀጣይ የግራ ክንፍ ተጨዋች በማስፈረም ቦታውን ለማጠናከር ማሰቡ ይታወሳል።

አርሰናሎች በሮድሪጎ ዝውውር ዙሪያ ከመጋረጃ ጀርባ ትልቅ የሚባል ስራ መስራታቸው ተገልጿል።

መድፈኞቹ ተጫዋቹን በሚያስፈርሙበት ሁኔታ ላይ የመጀመሪያ ንግግር ማድረጋቸው ተዘግቧል።

አርሰናል በተጨማሪም እንደ ኢዜ አይነት ፈጣሪ የሚባል የመሐል ሜዳ ተጨዋች ለማስፈረም መመልከቱ ተነግሯል።

አርሰናል ዝውውሮቹን የሚፈፅመው ከቪክቶር ዮከሬሽ ዝውውር የሚቀረውን በጀት በመመልከት መሆኑ ተገልጿል።

መድፈኞቹ የሮድሪጎ እና ኢዜን ዝውውር የሚያደርጉት በሚለቁ ተጨዋቾች ላይ ተመርኩዘው ሊሆንም እንደሚችል ተዘግቧል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
288😁51👍18👎2
ቼልሲ ንዋኔሪን ለማስፈረም እየተመለከተ ነው !

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ የአርሰናሉን የፊት የመስመር ተጨዋች ኢታን ንዋኔሪ ለማስፈረም የኮንትራት ሁኔታውን በቅርበት እየተከታተሉ መሆኑ ተገልጿል።

ቼልሲ ተጨዋቹ ከዚህ በፊት በአርሰናል ውሉን ከማራዘሙ በፊት ሊያስፈርሙት ከፍተኛ ጥረት አድርገው እንደነበር ይታወሳል።

አሁን ላይ ኢታን ንዋኔሪ በአርሰናል ቤት ያለው ኮንትራት አንድ አመት የሚቀረው ሲሆን ውሉን ለማራዘም ንግግር ላይ ነው።

አርሰናል የተጫዋቹን ውል ለማራዘም እስካሁን ከስምምነት ባይደርሩም በቅርቡ አዲስ ውል እንደሚፈርም እርግጠኞች ናቸው።

ቼልሲ በተጨማሪም እንግሊዛዊውን የአስቶን ቪላ ተጨዋች ሞርጋን ሮጀርስ እንደሚያደንቁ ተገልጿል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
😁10377👎15😢5👍2🔥2🤬2
TIKVAH-SPORT
አርኔ ስሎት ቡድኑን መርዳት ላይ ያተኩራሉ ! አሰልጣኝ አርኔ ስሎት ባለፈው ሳምንት ሶስቱን አዳዲስ ፈራሚዎች ከቡድናቸው ጋር የማዋሀድ ስራ ቀዳሚው ተግባራቸው አድርገው አንደነበር ተገልጿል። ከቡድኑ ተጨዋች ዲያጎ ጆታ ድንገተኛ ህልፈት በኋላ አሁን ላይ የአሰልጣኙ ቀዳሚ እቅድ አስፈላጊ ነገር ተደርጎ አይታይም። አሰልጣኝ አርኔ ስሎት በቀጣይ ቀዳሚው ፈታኝ ተግባራቸው በቡድን አጋራቸው አሳዛኝ ህልፈት…
ሊቨርፑል የዝግጅት ጊዜውን ጀመረ !

በድንገተኛ የመኪና አደጋ ተጫዋቹ ዲያጎ ጆታን ያጣው ሊቨርፑል ዛሬ በልምምድ ማዕከሉ በመገኘት ዝግጅቱን ይጀመራል።

በሊቨርፑሉ " AXA " ልምምድ ማዕከል በር ላይ ዲያጎ ጆታን የሚገልጹ በርካታ መልዕክቶች እና አበባዎች ተቀምጠው ታይተዋል።

መሐመድ ሳላህ በልምምድ ማዕከሉ ሲገኝ አዲሱ ፈራሚ ፍሪምፖንግ እንዲሁም ሌሎች ተጨዋቾች ቀድመው በማዕከሉ ተገኝተዋል።

ሊቨርፑል ከአምስት ቀናት በኋላ ከፕሪስተን ጋር የመጀመሪያ የወዳጅነት ጨዋታ ሲያደርግ ጨዋታው የቀጥታ ስርጭት ሽፋን ያገኛል ተብሏል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
141👏14👎9👍1
TIKVAH-SPORT
ዳርዊን ኑኔዝ ናፖሊን ለመቀላቀል ተስማማ ! ዩራጓዊው የፊት መስመር አጥቂ ዳርዊን ኑኔዝ በዚህ ክረምት ሊቨርፑልን ይለቃሉ ተብለው ከሚጠበቁ ተጨዋቾች መካከል ይጠቀሳል። አሁን ላይ ዳርዊን ኑኔዝ የጣሊያን ሴርያውን ክለብ ናፖሊ ለመቀላቀል መስማማቱ ተገልጿል። ይሁን እንጂ ለዝውውሩ እውን መሆን ናፖሊ በተጨዋቹ ዝውውር ሒሳብ ዙሪያ ከሊቨርፑል ጋር ከስምምነት መድረስ ይጠበቅባቸዋል። ኬቨን ዴብሮይንን…
ሊቨርፑል የናፖሊን ጥያቄ ውድቅ አደረገ !

ናፖሊ ዩራጓዊውን የፊት መስመር አጥቂ ዳርዊን ኑኔዝ ለማስፈረም ለሊቨርፑል ያቀረበው 50 ሚልዮን ዩሮ ውድቅ እንደተደረገበት ተገልጿል።

ናፖሊ በቀጣይ አዲስ የዝውውር ሒሳብ ያቀርባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተነግሯል።

ዳርዊን ኑኔዝ የጣሊያን ሴርያውን ክለብ ናፖሊ ለመቀላቀል ቀደም ብሎ መስማማቱ አይዘነጋም።

ኬቨን ዴብሮይንን በነፃ ዝውውር ያስፈረሙት አሰልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴ በቀጣይ ቡድናቸውን ለማጠናከር ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛሉ።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
90😁23👍8🙏2
ፒኤስጂ ተከላካዩ ሁለት ጨዋታ ይቀጣል !

ፊፋ የፒኤስጂውን የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ዊሊያን ፓቾ ሁለት ጨዋታዎች ለመቅጣት መወሰኑ ተገልጿል።

ተጨዋቹ ፒኤስጂ ባየር ሙኒክን ባሸነፈበት የሩብ ፍፃሜ ጨዋታ ቀይ ካርድ መመልከቱ አይዘነጋም።

ዊሊያን ፓቾ የሪያል ማድሪድን ጨዋታ ጨምሮ ፒኤስጂ ለፍፃሜ ከደረሰ የፍፃሜ ጨዋታው እንደሚያልፈው ተገልጿል።

በተጨማሪም ሌላኛው ተጨዋች ሉካስ ሄርናንዴዝ በተመሳሳይ ሁለት ጨዋታዎች እንደሚቀጣ ይፋ ተደርጓል።

የሪያል ማድሪዱ የመሐል ተከላካይ ዲን ሁይሰን በበኩሉ የአንድ ጨዋታ ቅጣት ተጥሎበታል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
74👍14😱11🔥2
የኒኮ ጎንዛሌዝ የማንችስተር ሲቲ ቆይታ ?

የማንችስተር ሲቲው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ኒኮ ጎንዛሌዝ በቀጣይ ክለቡን ሊለቅ ይችላል መባሉ ሀሰተኛ መሆኑ ተገልጿል።

ተጨዋቹ በማንችስተር ሲቲ የሚቀጥለው የውድድር አመት እቅድ ውስጥ መሆኑን ለክለቡ ቅርብ የሆኑ ምንጮች አስነብበዋል።

ስፔናዊው አማካይ ኒኮ ጎንዛሌዝ ከአምስት ወራት በፊት ጥር ወር ላይ ከፖርቶ ማንችስተር ሲቲን መቀላቀሉ አይዘነጋም።

ተጨዋቹ ለማንችስተር ሲቲ 17 ጨዋታዎችን አድርጎ ሁለት ጎሎችን አስቆጥሯል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
66😁10👍2🔥1
2025/07/08 12:50:52
Back to Top
HTML Embed Code: