Telegram Web Link
TIKVAH-SPORT
ቶተንሀም ጊቢስ ዋይትን ማስፈረም ይፈልጋል ! የሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሀም ሞርጋን ጊብስ ዋይትን ከኖቲንግሀም ፎረስት ማስፈረም እንደሚፈልጉ ዘ አትሌቲክ ዘግቧል። አዲሱ የቶተንሀም አለቃ ቶማስ ፍራንክ የእንግሊዛዊው አማካይ ሞርጋን ጊብስ ዋይት የረጅም ጊዜ አድናቂ መሆናቸው ተገልጿል። ቶተንሀም አሁን ላይ በሌሎች ክለቦች የሚፈለገው ሞርጋን ጊብስ ዋይት እንዲቀላቀላቸው ለማሳመን እየሰሩ መሆኑ ተነግሯል።…
ኖቲንግሀም ፎረስት ቶተንሀምን ሊከሱ ነው !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሀም ሞርጋን ጊብስ ዋይትን ለማስፈረም ተገቢ ባልሆነ መንገድ ማነጋገሩ ተገልጿል።

ኖቲንግሀም ፎረስት ቶተንሀም ካለፈቃዳቸው ተጫዋቹን ማነጋገሩን ተከትሎ ለፕርሚየር ሊጉ ቅሬታ ለማቅረብ መዘጋጀታቸው ተነግሯል።

በተጨማሪም ኖቲንግሀም ቶተንሀም ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ወደ ተጫዋቹ ቀርቧል በማለት ህጋዊ እርምጃ ለመውሰድ እየሰሩ መሆኑ ተዘግቧል።

ቶተንሀም የ 25ዓመቱን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሞርጋን ጊብስ ዋይት ለማስፈረም ከስምምነት መድረሳቸው ተዘግቦ ነበር።

የተጨዋቹ ዝውውር ሂደት አሁን ላይ መቆሙ ተዘግቧል።

ቶተንሀም የተጫዋቹን ዝውውር ለማጠናቀቅ በዛሬው ዕለት የጤና ምርመራ ለማድረግ ቀጠሮ ይዘው ነበር።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
😁15981👍4👎3🥰1
ኖኒ ማዱኬ የቼልሲን ስብስብ ለቋል !

እንግሊዛዊው የፊት መስመር ተጨዋች ኖኒ ማዱኬ አሜሪካ የሚገኘውን የቼልሲ ቡድን ስብስብ መልቀቁ ተገልጿል።

ተጨዋቹ እሁድ በሚካሄደው የክለቦች አለም ዋንጫ ውድድር ፍፃሜ ጨዋታ ላይ እንደማይሳተፍ ዘ አትሌቲክ ዘግቧል።

ኖኒ ማዱኬ በቀጣይ ወደ እንግሊዝ በመመለስ ወደ አርሰናል የሚያደርገውን ዝውውር ለማጠናቀቅ የጤና ምርመራውን እንደሚያደርግ ተነግሯል።

ቼልሲ ተጨዋቹ ወደ አርሰናል ሄዶ የጤና ምርመራውን እንዲያደርግ ፍቃድ መስጠታቸው ተገልጿል።

አርሰናል ኖኒ ማዱኬን በ 52 ሚልዮን ፓውንድ ለማስፈረም ከስምምነት መድረሳቸው አይዘነጋም።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
268😁96👎73👍6😱6😢6🤩3🙏3👏2
ቼልሲ የጎዳና ላይ ክብረበዓል ያዘጋጃል ?

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ እሁድ የክለቦች አለም ዋንጫ ፍፃሜ ጨዋታውን ከፒኤስጂ ጋር የሚያደርግ ይሆናል።

ሰማያዊዎቹ ዋንጫውን ካሸነፉ ድሉን ከደጋፊዎቻቸው ጋር በጎዳና ላይ ለማክበር አለማሰባቸው ተገልጿል።

ቼልሲዎች ከፍፃሜ ጨዋታው በኋላ ለተጨዋቾቹ የሶስት ሳምንታት እረፍት ለመስጠት ማሰባቸው ተነግሯል።

ብዙዎቹ የክለቡ ተጨዋቾች ፒኤስጂን ካሸነፉ የዋንጫ ድሉን በጎዳና ላይ የማክበር ሀሳቡን እንዳልተቀበሉት ተዘግቧል።

አብዛኞቹ የክለቡ ተጨዋቾች በበኩላቸው ከፍፃሜው በኋላ ከቤተሰቦቻቸው ጋር ወደ ካሪቢያን እና ሎስ አንጀለስ ለማምራት ማቀዳቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

ለክለቦች አለም ዋንጫ ፍፃሜ በመድረስ 87.5 ሚልዮን ፓውንድ ያገኘው ቼልሲ በቀጣይ ለተጨዋቾቹ ጉርሻ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
271😁172👍21👏6🙏6🤩3👎2
🔉 ጎልልልልልል- የኳስ መረጃዎችን በየቀኑ በስልካችን!

ከሳፋሪኮም ቁጥራችን 'A’ ብለን ወደ 30002 SMS በመላክ ወይም ወደ *799# በመደወል አሁኑኑ ቴስታ ጎል እንቀላቀል! በቀን 1 ብር ብቻ!

በቴስታ ጎል ትኩስ ስፖርታዊ መረጃዎች በሽ በሽ ነው!⚡️

#SafaricomEthiopia
#1Wedefit
#Furtheraheadtogether
21🤬4
#Wanawsportswear✔️

እናመሰግናለን!

በዚህ ታላቅ ዝግጅት ዋናው የስፖርት አልባሳት ተሳታፊ እና ስፖንሰር ስለነበር ታላቅ ደስታ እና ኩራት ይሰማዋል! ይህ አጋርነት ትጥቅ ስለማቅረብ ወይም ሽልማት ለተሳታፊ ስለማቅረብ አይደለም! ሀበሻውያኖች እሴታቸውን እና ባህላቸውን በባህር ማዶ አስጠብቆ ለማኖር የሚካሄድ እንቅስቃሴ ተሳታፊ ስለመሆን ነው!

🤝 ለESfna አዘጋጆች፣ ዝግጅቱ ላይ ለተሳተፋቹ ደጋፊዎች፣ለስፖርተኞች እና ለሁሉም ባለድርሻ አካሎች ዋናው ስፖርት ይህ ገና ጅማሮ ነው አብረን ጉዞችንን እንቀጥላለን።

ዋናው ወደፊት»»»

ለበለጠ መረጃ
8️⃣2️⃣8️⃣9️⃣

🔗 ማህበራዊ ገጾቻችን🔗
Instagram|Facebook |TikTok |X|Youtube
🔥🔥🔥🔥በኢትዮጵያ የተመረተ🔥🔥🔥🔥
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
18
ቼልሲ ተጨዋቹ ልምምድ ሰርቷል !

የሰማያዊዎቹ ወሳኝ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሞይሰስ ካይሴዶ በዛሬው የቡድኑ ልምምድ ላይ መሳተፍ ችሏል።

ተጨዋቹ በቡድኑ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ጉዳት አጋጥሞት እንደነበር የሚታወስ ነው።

ሞይሰስ ካይሴዶ በእሁዱ የፍፃሜ ጨዋታ ዝግጁ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

በሌላ በኩል ሌላኛው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሮሚዮ ላቪያ በዛሬው ልምምድ ላይ ሳይሳተፍ መቅረቱ ተገልጿል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
🔥9866😁11👏10🥰4👍1😢1🙏1
TIKVAH-SPORT
ክሪስታል ፓላስ ዩኤፋን ሊያነጋግሩ ነው ! የዩሮፓ ሊግ ተሳታፊው ክሪስታል ፓላስ በውድድሩ ተሳትፎ ዙሪያ ከአውሮፓ እግርኳስ ማህበር ጋር ለንግግር ሊቀመጡ መሆኑ ተገልጿል። በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ለአውሮፓ መድረክ የበቃው ክሪስታል ፓላስ በተመሳሳይ ክለብ ባለቤትነት ህግ ጋር በተያያዘ ተሳትፎው አደጋ ላይ ወድቋል። የዩሮፓ ሊግ ተሳታፊው ኦሎምፒክ ሊዮኑ ባለቤት ጆን ቴክስተር በክሪስታል ፓላስ ድርሻ…
ክሪስታል ፓላስ በዩሮፓ ሊግ አይሳተፍም !

ክሪስታል ፓላስ በሚቀጥለው የውድድር አመት በዩሮፓ ሊግ መሳተፍ እንደማይችል የአውሮፓ እግርኳስ ማህበር አስታውቋል።

በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ለአውሮፓ መድረክ የበቃው ክሪስታል ፓላስ በተመሳሳይ ክለብ ባለቤትነት ህግ ጋር በተያያዘ ከዩሮፓ ሊግ ወደ ኮንፈረንስ ሊግ ወርዷል።

የዩሮፓ ሊግ ተሳታፊው ኦሎምፒክ ሊዮኑ ባለቤት ጆን ቴክስተር በክሪስታል ፓላስ ድርሻ እንዳላቸው ይታወቃል።

ኦሎምፒክ ሊዮን በሊጉ የተሻለ ደረጃ ይዞ ማጠናቀቁን ተከትሎ ቅድሚያ እንደተሰጠው ተገልጿል።

ክሪስታል ፓላስ በቀጣይ በአውሮፓ ኮንፈረንስ ሊግ እንዲጫወት የወረደ ሲሆን በምትኩ ኖቲንግሀም ፎረስት ወደ ዩሮፓ ሊግ አድጓል።

አሜሪካዊው ባለቤት ጆን ቴክስተር በክሪስታል ፓላስ ያላቸውን ድርሻ ለመሸጥ በሂደት ላይ ሲሆኑ ክሪስታል ፓላስ በበኩሉ ይግባኝ ሊጠይቅ እንደሚችል ተጠቁሟል።

@Tikvahethsport       @kidusyoftahe
162😢71👍15👎7😁3🤩3🥰1
“ ይሸነፋሉ ስለተባለ ጫናው ይቀንስልናል “ ሌቪ ኮልዊል

የሰማያዊዎቹ ተጨዋች ሌቪ ኮልዊል ቡድናቸው በእሁዱ ፍፃሜ በብዙዎች የተሸናፊነት ግምት ማግኘቱ ያለ ጫና  እንዲጫወት እንደሚረዳው ተናግሯል።

“ ሰዎች ፍፃሜውን እንደምንሸነፍ እያሰቡ ነው ስለዚህ ይህ ለእኛ ብንሸነፍ የምናጣው ነገር እንደሌለ ይነግረናል “ ሲል ሌቪ ኮልዊል ተናግሯል።

ቡድናቸው አነስተኛ የማሸነፍ ግምት ማግኘቱ ጨዋታውን እንዳይፈራ በማድረግ እና ጫና በመቀነስ እንደሚረዳቸው ተጨዋቹ ተናግሯል።

“ ወደዛ ሄደን የራሳችንን እግርኳስ መጫወት አለብን በራሳችን መተማመን እና ሁሉንም ለማስደነቅ መጣር አለብን “ ሌቪ ኮልዊል

ሌቪ ኮልዊል አክሎም “ እኛ ሪያል ማድሪድ ወይም ኢንተር ሚያሚ አይደለንም " ያለ ሲሆን በተለየ መንገድ ነው የምንጫወተው ፒኤስጂን ከእነሱ በተሻለ እንፈትነዋለን ብሏል።

@Tikvahethsport       @kidusyoftahe
😁215142👏30👍11😢4🤬1🙏1
“ የተወሰነ የቆመ ኳስ አስቆጥርላችኋለሁ “ ኖርጋርድ

አዲሱ የመድፈኞቹ አማካይ ክርስቲያን ኖርጋርድ ለቡድኑ ከሚያበረክታቸው አስተዋጽኦዎች አንዱ ቡድኑን መምራት መሆኑን ገልጿል።

“ የተወሰኑ የቆሙ ኳሶችን በማስቆጠር እንደማግዝ ተስፋ አለኝ በተጨማሪም ቡድኑን በመምራት አግዛለሁ “ ሲል ክርስቲያን ኖርጋርድ ተናግሯል።

አክሎም “ እንዲሁም የቡድኑን አማካይ የእድሜ ጣሪያ ከፍ አደርገዋለሁ " ብሏል።

ተጨዋቹ ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ በአርሰናል ልምምድ ማዕከል ተገኝቷል።

@Tikvahethsport       @kidusyoftahe
👍298😁23897🔥17🙏8👎5👏2
TIKVAH-SPORT
“ ይሸነፋሉ ስለተባለ ጫናው ይቀንስልናል “ ሌቪ ኮልዊል የሰማያዊዎቹ ተጨዋች ሌቪ ኮልዊል ቡድናቸው በእሁዱ ፍፃሜ በብዙዎች የተሸናፊነት ግምት ማግኘቱ ያለ ጫና  እንዲጫወት እንደሚረዳው ተናግሯል። “ ሰዎች ፍፃሜውን እንደምንሸነፍ እያሰቡ ነው ስለዚህ ይህ ለእኛ ብንሸነፍ የምናጣው ነገር እንደሌለ ይነግረናል “ ሲል ሌቪ ኮልዊል ተናግሯል። ቡድናቸው አነስተኛ የማሸነፍ ግምት ማግኘቱ ጨዋታውን እንዳይፈራ…
" እኛ ቼልሲዎች ማንንም አንፈራም " ኮልዊል

የሰማያዊዎቹ ተጨዋች ሌቪ ኮልዊል ቡድናቸው ፍፃሜውን ለማሸነፍ ወደ ሜዳ ይገባል ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል።

" ለቼልሲ ስትጫወት ማንንም ለመግጠም አትፈራም “ የሚለው ሌቪ ኮልዊል ወደዚህ የመጣነው ለፍፃሜ ለመጫወት ብቻ አይደለም ብሏል።

አክሎም " ፒኤስጂ ጠንካራ ቡድን ነው " ያለው ተጨዋቹ ነገርግን እኛ ዋንጫውን ማሸነፍ እንፈልጋለን በማለት ገልጿል።

@Tikvahethsport       @kidusyoftahe
😁255👏12572🔥13👍12🥰7👎2
በርንማውዝ ግብ ጠባቂ ለማስፈረም ተስማማ !

በርንማውዝ የ 25ዓመቱን ግብ ጠባቂ ፒትሮቪች ለማስፈረም ከቼልሲ ጋር ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል።

ሰማያዊዎቹ ግብ ጠባቂውን በ 25 ሚልዮን ፓውንድ ለመሸጥ ከስምምነት መድረሳቸውን ዘ አትሌቲክ አስነብቧል።

ሰርቢያዊው ግብ ጠባቂ ፒትሮቪች የጤና ምርመራውን እንዲያደርግ ፍቃድ የተሰጠው ሲሆን በቀጣይ የአምስት አመት ውል እንደሚፈርም ይጠበቃል።

በርንማውዝ የኬፓ አሪዛባላጋን መልቀቅ ተከትሎ ለቡድኑ ቁጥር አንድ ግብ ጠባቂ በማፈላለግ ላይ ነበሩ።

ባለፈው አመት በውሰት በስትራስቡርግ ያሳለፈው ፒትሮቪች በበኩሉ ክለብ እንዲያፈላልግ በክለቡ ተነግሮት መቆየቱ ይታወቃል።

@Tikvahethsport       @kidusyoftahe
125👍21🔥4😁4😢2
ባርሴሎና ከኮንጎ ጋር ንግግር ላይ ነው !

የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ከአፍሪካዊቷ ሀገር ዲሞክራቲክ ኮንጎ ጋር የስፖንሰርሺፕ ስምምነት ለመፈፀም ንግግር ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

ባርሴሎና ከ ዲሞክራቲክ ኮንጎ ቱሪዝም ሚኒስቴር ጋር በቱሪዝም ዙሪያ ለመስራት ንግግር ላይ መሆናቸው ተዘግቧል።

ባርሴሎና ከስምምነቱ በአመት 10 ሚልዮን ዩሮ ያገኛል የተባለ ሲሆን ባርሴሎና በአንፃሩ የሀገሪቱን ቱሪዝም እንደሚያስተዋውቅ ተገልጿል።

ስምምነቱ የሚፈፀም ከሆነ ባርሴሎና በእጄታው ላይ " ኮንጎ የአፍሪካ ልብ  " የሚል ፅሁፍ እንደሚያሰፍር ተነግሯል።

የ ዲሞክራቲክ ኮንጎ ስፖርትና ቱሪዝም ሚኒስቴር በቅርቡ ወደ ባርሴሎና አቅንተው በጉዳዩ ዙሪያ መነጋገራቸው ተጠቁሟል።

@Tikvahethsport       @kidusyoftahe
164😁55👍36👎13🔥11👏1
" ማዱኬን ልቀቅ ያለው የለም መሄድ ፈልጎ ነው " ማሬስካ

የሰማያዊዎቹ አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ ኖኒ ማዱኬ አርሰናልን እንደሚቀላቀል አረጋግጠዋል።

ከፍፃሜ ጨዋታው በፊት አስታያየታቸውን እየሰጡ የሚገኙት ኢንዞ ማሬስካ “ ኖኒ ማዱኬ ከወደፊት ክለቡ ጋር እየተነጋገረ ነው " ብለዋል።

አክለውም ዝውውሩ በሚቀጥሉት ሰዓታት መቋጫ ያገኛል የሚል እምነት አለኝ በማለት አረጋግጠዋል።

" ማዱኬን መልቀቅ አለብህ ያለው የለም “ ያሉት ኢንዞ ማሬስካ እሱ ለመልቀቅ ወስኗል ያንን የሚፈልግ ከሆነ እኛም ለእሱ ደስተኞች ነን ብለዋል።

@Tikvahethsport       @kidusyoftahe
😁17373👏73👍23👎1
ዩናይትድ ሁለት ታዳጊዎችን ለማስፈረም እያነጋገረ ነው !

ማንችስተር ዩናይትድ ሁለት ወጣት የ 16ዓመት የመሐል ሜዳ ተጨዋቾች ለማስፈረም በንግግር ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል።

ማንችስተር ዩናይትድ ለማስፈረም እያነጋገረ የሚገኘው የመጀመሪያው ተጨዋች የእንግሊዝ ከ 17 አመት በታች ቡድን አምበል ሴዝ ሪድጎን መሆኑ ተነግሯል።

ሌላኛው ተጨዋች ከማንችስተር ሲቲ ጋር ለመለያየት የተቃረበው ታይረስ ኑቢሴ የማንችስተር ዩናይትድ ኢላማ መሆኑ ተገልጿል።

ሴዝ ሪድጎን በአሁን ሰዓት በፉልሀም የአጥቂ አማካይ ሲሆን ከዩናይትድ በተጨማሪም በቼልሲ ፣ ሊቨርፑል እና ማንችስተር ሲቲ ይፈልጋል።

ሁለቱም ተጨዋቾች በማንችስተር ዩናይትድ ተጋብዘው ኦልድትራፎርድ ስታዲየም እና ካሪንግተንን መጎብኘታቸው ተዘግቧል።

@Tikvahethsport       @kidusyoftahe
😁217196🔥12👏11😢6👍1
TIKVAH-SPORT
ኒውካስል ኢላንጋን ለማስፈረም ተስማማ ! ኒውካስል ዩናይትድ የኖቲንግሀም ፎረስቱን የፊት መስመር ተጨዋች አንቶኒ ኢላንጋ ለማስፈረም ከስምምነት ደርሰዋል። ኒውካስል ተጫዋቹን 55 ሚልዮን ፓውንድ በሚደርስ የዝውውር ሒሳብ ለማስፈረም ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል። አንቶኒ ኢላንጋ በኒውካስል ዩናይትድ ቤት የረጅም ጊዜ ውል እንደሚፈርም ፋብሪዝዮ ሮማኖ ዘግቧል። የ 23ዓመቱ አንቶኒ ኢላንጋ ባለፈው…
ኒውካስል በይፋ ተጨዋች አስፈረመ !

ኒውካስል ዩናይትድ የኖቲንግሀም ፎረስቱን የፊት መስመር ተጨዋች አንቶኒ ኢላንጋ ማስፈረማቸውን በይፋ አስታውቀዋል።

ኒውካስል ተጫዋቹን 52 ሚልዮን ፓውንድ በሚደርስ የዝውውር ሒሳብ በአምስት አመት ኮንትራት ማስፈረማቸውን አስታውቀዋል።

አንቶኒ ኢላንጋ ከማላጋ በነፃ ዝውውር ከፈረመው አንቶኒዮ ኮርዴሮ ቀጥሎ ሁለተኛው የክረምቱ የኒውካስል ዩናይትድ ፈራሚ ሆኗል።

የ 23ዓመቱ አንቶኒ ኢላንጋ ባለፈው አመት በሁሉም የፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎች ለኖቲንግሀም ግልጋሎት ሰጥቷል።

ተጨዋቹ በጨዋታዎቹ ስድስት ጎሎች አስቆጥሮ 11 አመቻችቶ ማቀበልም ችሏል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
159👍31🔥13😁3
TIKVAH-SPORT
ሊቨርፑል ሀያ ቁጥር መለያን በክብር ሰቀለ ! በ 2020 የውድድር ዘመን ክለቡን የተቀላቀለው ሀያ ቁጥር ለባሹ ዲያጎ ጆታ ድንገተኛ ህልፈት ተከትሎ ሊቨርፑል የማልያ ቁጥሩን በክብር እንደሚሰቅሉ ይፋ ሆኗል። የክለቡን ሀያኛ የሊግ ዋንጫ ስኬት መጎናፀፍ የቻለው ዲያጎ ጆታ ክብር ሲባል ሊቨርፑል ይህን ውሳኔ ሊወስን ችሏል። ይህንንም ተከትሎ በሊቨርፑል ቤት ከዚህ በኋላ የ 20 ቁጥር ማልያ የማይለበስ…
ሊቨርፑል ሀያ ቁጥር መለያን በየትኛውም ቡድን አይጠቀምም !

ሊቨርፑል በቅርቡ ህይወቱ ያለፈው ዲያጎ ጆታ የሚጠቀመው የ 20 ቁጥር ማልያ ጥቅም ላይ እንዳይውል ማድረጉን አስታውቋል።

ክለቡ ከዚህ በፊት ማልያ በሊቨርፑል ዋናው ቡድን ጥቅም ላይ እንዳይውል ማድረጉ ተዘግቦ ነበር።

ሊቨርፑል አሁን ላይ ማልያውን በወንዶች እና ሴቶች በየትኛውም እድሜ ክልል ቡድኖቹ ላይ እንደማይጠቅም አሳውቋል።

ሊቨርፑል ውሳኔውን ያሳለፈው ከዲያጎ ጆታ ባለቤት እና ቤተሰብ አባላት ጋር ከመከረ በኋላ መሆኑን አስታውቋል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
👍445187👏48😢32💯9👎4🥰2
TIKVAH-SPORT
ኒውካስል በይፋ ተጨዋች አስፈረመ ! ኒውካስል ዩናይትድ የኖቲንግሀም ፎረስቱን የፊት መስመር ተጨዋች አንቶኒ ኢላንጋ ማስፈረማቸውን በይፋ አስታውቀዋል። ኒውካስል ተጫዋቹን 52 ሚልዮን ፓውንድ በሚደርስ የዝውውር ሒሳብ በአምስት አመት ኮንትራት ማስፈረማቸውን አስታውቀዋል። አንቶኒ ኢላንጋ ከማላጋ በነፃ ዝውውር ከፈረመው አንቶኒዮ ኮርዴሮ ቀጥሎ ሁለተኛው የክረምቱ የኒውካስል ዩናይትድ ፈራሚ ሆኗል። …
ኒውካስል የኢላንጋን ዝውውር በምን መልኩ ይፋ አደረገ ?

ኒውካስል ዩናይትድ አንቶኒ ኢላንጋን ማስፈረሙን ይፋ ያደረገው ለየት ባለ መልኩ የአንድ ህፃን ደጋፊ ገጠመኝ በመግለፅ ነበር።

የክለቡ ደጋፊ ህፃን በተለቀቀው ተንቀሳቃሽ ምስል ባለፈው የውድድር አመት ስለገጠመው ገጠመኝ ተናግሯል።

የህፃኑ ገጠመኝ ምን ነበር ?

በቪዲዮው የታየው ህፃን ኒውካስል ባለፈው የውድድር አመት ከአርሰናል ጋር በሚጫወትበት ዕለት ህመም አጋጥሞኛል በማለት ከትምህርት ቤት ቀርቶ ነበር።

ኒውካስል ዩናይትድ ግብ ባስቆጠረበት ወቅት ህፃኑ በደስታ ሲጨፍር በቀጥታ ስርጭት በቴሌቪዥን መስኮት ታይቷል።

የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር በበኩላቸው ህፃኑን በቴሌቪዥን ቀጥታ ስርጭት ተመልክተውት እንደነበር ተገልጿል።

የትምህርት ቤቱ ሀላፊዎችም " ልጁን ኳስ ሲከታተል እና ሲጨፍር አይተነዋል በጉዳዩ ላይ መነጋገር እንፈልጋለን " የሚል መልዕክት ለወላጆቹ መላካቸው ተነግሯል።

ኒውካስል ዩናይትድም የልጁን ገጠመኝ የአንቶኒ ኢላንጋን ዝውውር ይፋ ሲያደርጉ አስተዋውቀውታል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
381😁55👍35👎5🤩5🤬3🥰2😢2👏1
“ በጨዋታው ያለንን እንሰጣለን “ ኢንዞ ማሬስካ

የሰማያዊዎቹ ዋና አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ ከእሁድ የክለቦች አለም ዋንጫ ፍፃሜ ጨዋታ በፊት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ ምን አሉ ?

- " ለደጋፊው ያለኝ መልዕክት ድጋፋቸው እንደሚያስፈልገን ነው ፤ ቡድኑ እምነታቸው ያስፈልገዋል ምክንያቱም ምርጥ የውድድር አመት ነው ያሳለፈው።

- ፒኤስጂ ምናልባት በአሁኑ ሰዓት የአለም ምርጡ ቡድን ነው ፤ ጥሩ ጨዋታ ለማድረግ ያለንን ሁሉ ለመስጠት እንሞክራለን።

- ካይሴዶ ለእኛ በጣም አስፈላጊ ተጨዋች ነው ዛሬ ሙሉ ልምምዱን አልጨረሰም በጨዋታው መሳተፍ እንደሚችል ተስፋ እናደርጋለን።

- ጇ ፔድሮ አስደናቂ ተጨዋች ነው ወደዚህ ያመጣነው ያግዘናል ብለን አስበን ነው እሱ ትልቅ አቅም አለው።" ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
241😁46👍23🔥7😢5
ኦዶች ዛሬም ከፍ ብለዋል!
ታዲያ ምን ይጠብቃሉ? ለማሸነፍ በተመቻቹ ኦዶች ይወራረዱ!
አሁኑኑ Betika.et ላይ ብቻ!
ቤቲካ የአሸናፊዎች ቤት!
10
2025/07/13 18:41:34
Back to Top
HTML Embed Code: