Telegram Web Link
ቡናማዎቹ ድል አድርገዋል !

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የሀያ አራተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ቡና ከወላይታ ድቻ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የቡናማዎቹን የማሸነፊያ ግቦች መስፍን ታፈሰ እና መሐመድ ኑር ናስር ከመረብ ማሳረፍ ሲችሉ ለወላይታ ድቻ ብዙአየሁ ተስፉ አስቆጥሯል።

ኢትዮጵያ ቡና ከሶስት ጨዋታዎች በኋላ ወደ ድል የተመለሱበትን ውጤት አስመዝግበዋል።

የሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ምን ይመስላል ? 

5️⃣ ኢትዮጵያ ቡና :- 38 ነጥብ

1️⃣2️⃣ ወላይታ ድቻ :- 28 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታ ምን ይመስላል ?

እሁድ -  ኢትዮጵያ ቡና ከ ሻሸመኔ ከተማ

ሐሙስ - ወላይታ ድቻ ከ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
30 ' ኖቲንግሃም 1 - 1 ቼልሲ

ቦሊ                  ሙድሪክ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
እረፍት | ኖቲንግሃም 1 - 1 ቼልሲ

ቦሊ                  ሙድሪክ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
🏆🏆 አል ሂላል ሻምፒዮን ሆኗል 🏆🏆

የሳውዲ አረቢያ ሮሸን ሊግን እየመራ የሚገኘው አል ሂላል ከአል ሀዜም ጋር ያደረገውን ጨዋታ 4ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፉን ተከትሎ ሻምፒዮን መሆኑን አረጋግጧል።

በአሰልጣኝ ጆርጅ ጄሱስ የሚመራው አል ሂላል በታሪኩ አስራ ዘጠነኛ የሳውዲ አረቢያ ሊግ ዋንጫውን ማሳካት ችሏል።

አል ሂላል በአመቱ ውስጥ ምን አሳካ ?

- በሳውዲ አረቢያ ሊግ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በአንድ አመት ከዘጠና አምስት ግቦች በላይ በማስቆጠር አዲስ ታሪክ ፃፈ።

- በሊጉ ታሪክ በተከታታይ ሀያ አራት ጨዋታዎችን በማሸነፍ አዲስ ሪከርድ አስመዘገበ።

- አል ሂላል በሊጉ ታሪክ ትልቅ ውጤት የሆነውን 9ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ አዲስ ታሪክ ፃፈ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
75 ' ኖቲንግሃም 2 - 1 ቼልሲ

     ቦሊ               ሙድሪክ
ሁድሰን ኦዶዬ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
80 ' ኖቲንግሃም 2 - 2 ቼልሲ

     ቦሊ               ሙድሪክ
    ሁድሰን ኦዶዬ ስተርሊንግ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
82 ' ኖቲንግሃም 2 - 3 ቼልሲ

     ቦሊ               ሙድሪክ
    ሁድሰን ኦዶዬ  ስተርሊንግ
ጃክሰን

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ተጠናቀቀ | ግራናዳ 0 - 4 ሪያል ማድሪድ

አርዳ ጉለር
ጋርሺያ
ብራሂም ዲያዝ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሰማያዊዎቹ ወሳኝ ድል አሳክተዋል !

በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ሰላሳ ሰባተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ቼልሲ ከኖቲንግሃም ፎረስት ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 3ለ2 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የሰማያዊዎቹን የማሸነፊያ ግቦች ሙድሪክ ፣ ራሂም ስተርሊንግ እና ኒኮላስ ጃክሰን ማስቆጠር ሲችሉ ለኖቲንግሀም ቦሊ እና ሁድሰን ኦዶይ ከመረብ አሳርፈዋል።

ኒኮላስ ጃክሰን በዘንድሮው የውድድር አመት አስራ አራተኛ የፕርሚየር ሊግ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

እንግሊዛዊው ተጨዋች ኮል ፓልመር በመጀመሪያ አመቱ ከአስር በላይ ግቦች አስቆጥሮ እና ከአስር በላይ ለግብ የሚሆኑ ኳሶች አመቻችቶ ማቀበል የቻለ የመጀመሪያው የቼልሲ ተጨዋች ሆኗል።

በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ስንተኛ ናቸው ?

7️⃣ ቼልሲ :- 57 ነጥብ

1️⃣7️⃣ ኖቲንግሀም ፎረስት :- 29 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታ ምን ይመስላል ?

እሮብ - ብራይተን ከ ቼልሲ

እሁድ - በርንሌይ ከ ኖቲንግሃም

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኤሲ ሚላን ድል አድርጓል !

በጣልያን ሴርያ የሰላሳ ስድስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኤሲ ሚላን ከካግሊያሪ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 5 ለ 1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የኤሲ ሚላንን የማሸነፍ ግቦች ክርስቲያን ፑልሲች 2x ፣ ቤናክር ፣ ቲጃኒ ሬንደርስ እና ራፋኤል ሊያኦ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

የካግሊያሪን ብቸኛ ግብ ናሂታን ናንዴዝ ከመረብ አሳርፏል።

የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

2️⃣ ኤሲ ሚላን :- 74 ነጥብ

1️⃣5️⃣ ካግሊያሪ :- 33 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታ ምን ይመስላል ?

ቅዳሜ - ቶሪኖ ከ ኤሲ ሚላን

እሁድ - ሳሱሎ ከ ካግሊያሪ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from HEY Online Market
•PlayStation 5, 73,000 Birr
•Playstaion 5 Slim, 78,000 Birr

•PlayStation 4 Slim, 35,000 Birr
•PlayStation 4 Pro, 43,000 Birr

•Playstaion portal, 35,000 Birr
•Meta Quest 2, 60,000 Birr
•Meta Quest 3, 83,000 Birr

Contact
0953964175 @heymobile

@heyonlinemarket
የዛሬ ተጠባቂ ጨዋታዎች !

9:00 ሻሸመኔ ከተማ ከ ሀድያ ሆሳዕና

12:00 ሀምበሪቾ ዱራሜ ከ መቻል

12:30 ማንችስተር ዩናይትድ ከ አርሰናል

12:30 ባየር ሙኒክ ከ ዎልፍስበርግ

1:00 ጁቬንቱስ ከ ሳለርኒታና

2:30 ቦህም ከ ባየር ሊቨርኩሰን

3:45 አታላንታ ከ ሮማ

4:00 ፒኤስጂ ከ ቱሉስ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" የቶተንሀም ጨዋታ እውነተኛ ፍፃሜ ነው " ጋርዲዮላ

የማንችስተር ሲቲው ዋና አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ቡድናቸው ቀጣይ ማክሰኞ ከቶተንሀም ጋር የሚያደርገውን የሊግ መርሐ ግብር " እውነተኛ ፍፃሜ " ሲሉ ገልጸውታል።

" ከቶተንሀም ጋር የምናደርገው ጨዋታ እውነተኛ ፍፃሜ ነው " በማለት የገለፁት አሰልጣኙ በመጨረሻም ጨዋታ እጣፈንታችንን በእጃችን አድርገን በሜዳችን መጫወት እንፈልጋለን ለዚህም ቶተንሀምን ማሸነፍ አለብን ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አርቴታ ቴንሀግ ጊዜ ሊሰጣቸው እንደሚገባ ገለጹ !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ዋና አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ የዛሬ ተጋጣሚያቸው ማንችስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ጊዜ ሊሰጣቸው እንደሚገባ ገልጸዋል።

" ኤሪክ ቴንሀግ ጥሩ አሰልጣኝ ነው ሁልጊዜም በአያክስ እና ዩናይትድ የሰራውን አደንቃለሁ " ያሉት ሚኬል አርቴታ በቂ ጊዜ እንደሚሰጠው ተስፋ አለኝ ምክንያቱም በዚህ ሊግ መወዳደር ምን ያህል ከባድ እንደሆነ እናውቃለን " በማለት ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" እንድለቅ የሚፈልጉት የኳስ እውቀት የሌላቸው ናቸው " ቴንሀግ

የማንችስተር ዩናይትዱ ዋና አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ከክለቡ ሀላፊነት እንዲባረሩ እየጠየቁ የሚገኙ ሰዎች የእግርኳስ እውቀት የሌላቸው ናቸው በማለት ተናግረዋል።

አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ በንግግራቸውም " የእኔን መባረር እየጠየቁ የሚገኙ ሰዎች ወይ የእግርኳስ እውቀት የሌላቸው ወይ ቡድን እንዴት እንደሚመራ የማያውቁ ሰዎች ናቸው።"ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ኦልድትራፎርድ ለመጫወት የምወደው ቦታ ነው " ሳካ

እንግሊዛዊው የመድፈኞቹ የፊት መስመር ተጨዋች ቡካዩ ሳካ የአርሰናል አዲስ ፈራሚ ተጨዋቾች ለቡድናቸው ጥሩ ግልጋሎት በመስጠት ላይ መሆናቸውን ተናግሯል።

" ዴክላን ራይስ እና ካይ ሀቨርትዝ ብዙ ጨዋታዎች አድርገዋል ለቡድኑ ወሳኝ ግቦችንም አስቆጥረዋል ፣ በየጨዋታው ያላቸውን ሁሉ ይሰጣሉ አዲስ ፈራሚዎች ለቡድኑ ድንቅ ናቸው።"ሲል ቡካዩ ሳካ ተናግሯል።

ከአሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ጋር ጥሩ ግንኙነት እንዳለው የሚገልጸው ቡካዩ ሳካ " እሱ እኔን ያምነኛል ከእኔ ጥሩ ነገር እንዳገኘ ይሰማኛል እሱን አመስጋኝ ነኝ " ብሏል።

ስለምሽቱ ጨዋታ ያነሳው ቡካዩ ሳካ " ኦልድትራፎርድ ስታዲየም የተወሰነ ጨዋታ አድርጌያለሁ ፕርሚየር ሊግ ውስጥ ለመጫወት የምወደው ታላቅ ስታዲየም ነው።"ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ዋንጫውን ያሸነፍነው በብቃት ነው " ፍሎረንቲኖ ፔሬዝ

ሰላሳ ስድስተኛ የስፔን ላሊጋ ዋንጫውን ያሸነፈው ሪያል ማድሪድ በዛሬው ዕለት በማድሪድ ከደጋፊዎቻቸው ጋር ድላቸውን እያከበሩ ይገኛሉ።

በክብረበዓሉ ላይ ንግግር ያደረጉት የሪያል ማድሪዱ ፕሬዝዳንት ፍሎረንቲኖ ፔሬዝ መላውን የቡድን አባላት በማመስገን " ዋንጫውን ያሳካነው በብቃት እና በጨዋ ደንብ አሳምነን ነው።"ብለዋል።

ፕሬዝዳንቱ ቀጥለውም " በአለም ተወዳጁ ክለብ እኛ ነን " ያሉ ሲሆን አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ በታሪክ ካሉ ምርጥ አሰልጣኞች አንዱ ሲሉ ገልጸዋቸዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ናፖሊ የጨዋታ ቀን እንዲቀየርለት መጠየቁ ተገለጸ !

የጣልያኑ ክለብ ናፖሊ ፕሬዝዳንት ዲ ላውረንቲስ ክለባቸው የፊታችን አርብ ከፊዮሬንቲና ጋር የሚያደርገው የሊግ መርሐ ግብር ቀን እንዲቀየርላቸው መጠየቃቸው ተገልጿል።

ፕሬዝዳንቱ የቀን ይቀየርልን ጥያቄውን ያቀረቡት ጣልያን ውስጥ አርብ እና ቀን 17 ሲገጣጠሙ መጥፎ እድል ያመጣል የሚል እምነት መኖሩን ተከትሎ እንደሆነ ተዘግቧል።

አወዳዳሪው አካል በጥያቄው መሰረት ጨዋታውን ወደ ቅዳሜ ለማዘዋወር እያሰበ እንደሚገኝ ተጠቁሟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
በሊጉ መገባደጃ ዋዜማ በ37ኛ ሳምንት ጨዋታ ዩናይትድ የዋንጫ ተፎካካሪውን አርሰናልን በኦልትራፎርድ ያስተናግዳል። በጨዋታው 3 ነጥቡ የማን ይሆናል?

በጨዋታው ለመወራረድ - betika.et
ቤቲካ! የአሸናፊዎች ቤት!
" ዛሬ አማራጫችን መፋለም ብቻ ነው " ቴንሀግ

የቀያይ ሴጣኖቹ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ቡድናቸው ዛሬ ያለው አማራጭ ከባለፈው ሳምንት ሽንፈት አገግሞ በመነሳት መፋለም ብቻ መሆኑን ገልጸዋል።

" በክፓላስ ጨዋታ ያሳየነው እንቅስቃሴ የማንችስተር ዩናይትድን ደረጃ የሚመጥን አይደለም " ያሉት አሰልጣኙ የተመዘገበው ውጤት ተቀባይነት የለውም ዛሬ ብቸኛ አማራጫችን መነሳትና መፋለም ብቻ ነው ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/06/16 11:13:31
Back to Top
HTML Embed Code: