Telegram Web Link
ሩድ ቫን ኔስትሮይ ከሌስተር ሲቲ ጋር ለተለያየ !

ከእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የወረደው ሌስተር ሲቲ አሰልጣኝ ሩድ ቫን ኔስትሮይን ከሀላፊነት ማሰናበቱ ተገልጿል።

አሰልጣኝ ሩድ ቫን ኔስትሮይ ሌስተር ሲቲን ተረክቦ በ 24 ጨዋታዎች መምራት ቢችልም ቡድኑን ከመውረድ አልታደገም።

አሰልጣኝ ሩድ ቫን ኔስትሮይ ሌስተር ሲቲን እየመራ ማሸነፍ የቻለው አራት ጨዋታዎችን ነው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
91😁43😢21👍7
ዩናይትድ የግብ ጠባቂውን ውል አራዘመ !

በአሰልጣኝ ሩበን አሞሪም የሚመሩት ቀያይ ሴጣኖች የግብ ጠባቂያቸው ቶም ሂተንን ኮንትራት ማራዘማቸውን ይፋ አድርገዋል።

እንግሊዛዊው የ 39 ዓመት ግብ ጠባቂ ቶም ሂተን በማንችስተር ዩናይትድ ቤት ለተጨማሪ አንድ የውድድር አመት ለመቆየት ውሉን ማራዘሙ ተገልጿል።

" በማንችስተር ዩናይትድ በመቀጠሌ ኮርቻለሁ ቡድኑን ለማገዝ ዝግጁ ነኝ።"ሲል ቶም ሂተን ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
😁19976👎32👍19🤔3🥰2🤩1
የፈረንሳይ ሊግ መርሐግብር ይፋ ሆነ !

የ 2025/26 የውድድር ዘመን የፈረንሳይ ሊግ የጨዋታ መርሐግብር ይፋ ተደርጓል።

የወቅቱ የሊጉ አሸናፊ ፒኤስጂ የመጀመሪያ ጨዋታውን ከሜዳው ውጪ ከናንትስ ጋር ያደርጋል።

- ሞናኮ ሌ ሀቭሬ
- ኦሎምፒክ ሊዮን ከሌንስ
- ሬኒስ ከ ኦሎምፒክ ማርሴይ ጋር ተደልድለዋል።

ኦሎምፒክ ሊዮን ይግባኙ ተቀባይነት ካጣ እና ከሊጉ መውረዱ ከተረጋገጠ በመርሐግብሩ ከሬምስ ጋር ቦታ የሚቀያየሩ ይሆናል።

የፈረንሳይ ሊግ የሚቀጥለው የውድድር አመት አርብ ነሐሴ 9/2017 ዓ.ም የሚጀምር ይሆናል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
59👍14👏4😁2🤔1
TIKVAH-SPORT
" ለእንግሊዝ ትልቁ ክለብ መጫወት መታደል ነው " ኬርኬዝ ሀንጋራዊው የግራ መስመር ተጨዋች ሚሎስ ኬርኬዝ ወደ ሊቨርፑል መምጣቱን “ መታደል ነው " ሲል ገልፆታል። “ በጣም ደስ ብሎኛል ይህ ለእኔ ክብር ነው “ ያለው ሚሎስ ኬርኬዝ ከአለም ምርጥ ክለቦች አንዱ እና ለእንግሊዝ ትልቁ ክለብ መጫወት መታደል ነው ብሏል። አክሎም " ከእረፍት ተመልሼ ቡድኑን እስከምቀላቀል እና የቅድመ ውድድር ዝግጅት…
ሚሎስ ኬርኬዝ ምን አይነት ተጨዋች ነው ?

ሊቨርፑል ሚሎስ ኬርኬዝን ከበርንማውዝ በማስፈረም የግራ መስመር ቦታቸውን አጠናክረዋል።

ሀንጋራዊው ተጨዋች ሚሎስ ኬርኬዝ በቡድኑ የማጥቃት እንቅስቃሴ ውስጥ ሲሳተፍ ሚናውን በተለይ ኃይል መወጣት ይችላል።

ባለፈው አመት ለበርንማውዝ ሁሉንም የሊግ ጨዋታዎች ያደረገው ተጨዋቹ ከጨዋታ መጀመሪያ እስከመጨረሻ ደቂቃ ያለድካም በሚያደርገው ሩጫው ይታወቃል።

ሚሎስ ኬርኬዝ ያገኛቸውን አጋጣሚዎች ሁሉ ወደ ተጋጣሚ ግብ ክልል ይዞ መሮጥ የሚፈልግ አይነት የመስመር ተጨዋች እንዳልሆነ ተገልጿል።

ኬርኬዝ የቡድኑን ማጥቃት እንቅስቃሴ ማገዝ ቢያስደስተውም የተሰጠውን የመከላከል ስራ በቁምነገር የሚመለከት ተጨዋች ነው።

ተጨዋቹ በቀድሞ ክለቡ ሙሉ ጨዋታውን የተጋጣሚውን የክንፍ ተጨዋች ያለመዘናጋት ጠብቆ በመያዝ የተሰጠውን ሀላፊነት ሲወጣ ታይቷል።

ተጨዋቹ ቡድኑ ኳስ ሲቀማ ተጋጣሚው ኳስ መስርቶ እንዳይጫወት በማደናቀፍ መልሶ ለማግኘት የሚያደርገው የማጥቃት ጫና ለሊቨርፑል ተጋጣሚውን ለማቆም ያግዘዋል ተብሎ ይጠበቃል።

በተጨማሪም ተጨዋቹ ያለው ተከላካዮችን ኳስ አታሎ የማለፍ ክህሎቱ እና የሚያሻማቸው ኳሶች ለሊቨርፑል ትልቅ ነገር እንደሚጨምሩ ይጠበቃል።

ተጨዋቹ እስካሁን ባለው የእግርኳስ ህይወቱ ከባድ የሚባል ጉዳት ገጥሞት አያውቅም።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
🔥151106😁9👍5👏5👎4🤩3
ቀጣይ አመት በሊጉ ምን አዲስ ነገር ይኖራል ?

በሚቀጥለው የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ውድድር አመት አዳዲስ ለውጦችን እንደምንመለከት ተገልጿል።

በጨዋታ ወቅት ተቀይረው የሚወጡ ተጨዋቾች ተቀያሪ ወንበር ላይ አስተያየት እንዲሰጡ ለማድረግ መታሰቡ ተነግሯል።

ግብ ከተቆጠረ በኋላ የሚኖረውን የደስታ አገላለጽ ለመቅረጽ ካሜራ ወደ ሜዳ ውስጥ ማስገባት እንደሚፈቀድም ተነግሯል።

በተጨማሪም በተወሰነ መልኩ ካሜራዎች ወደ ተጨዋቾች መልበሻ ክፍል እንዲገቡ እንደሚደረግ ቴሌግራፍ አስነብቧል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
🔥217110👎48😁20👍3😱1
ጃራድ ብራንዝዌት ውሉን ሊያራዝም ነው !

የመርሲሳይዱ ክለብ ኤቨርተን የመሐል ተከላካይ ጃራድ ብራንዝዌት ኮንትራቱን ለተጨማሪ አመታት ለማራዘም መቃረቡ ተገልጿል።

በክለቡ እስከ 2027 የሚያቆይ ውል ያለው ተጨዋቹ አዲስ የረጅም ጊዜ ኮንትራት ለመፈረም መቃረቡ ተነግሯል።

የ 23ዓመቱ ተጨዋች ብራንዝዌት ባለፈው አመት ከማንችስተር ዩናይትድ ጥያቄ ቀርቦለት ኤቨርተን ውድቅ ማድረጉ አይዘነጋም።

ተጨዋቹ ከአምስት አመታት በፊት ቡድኑን ከተቀላቀለ ወዲህ በ 88 ጨዋታዎች ተሰልፎ ቡድኑን ማገልገል ችሏል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
105😁15👍13👏3🥰1
ብሬንትፎርድ አዲስ አሰልጣኝ ሾመ !

የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊጉ ክለብ ብሬንትፎርድ አዲስ አሰልጣኝ በሀላፊነት መሾሙን በይፋ አስታውቋል።

ከአሰልጣኝ ቶማስ ፍራንክ ጋር ከተለያየ ወዲህ ያለ አሰልጣኝ የሚገኘው ብሬንትፎርድ ኬት አንድሪውስን በዋና አሰልጣኝነት ሾሟል።

አሰልጣኝ ኬት አንድሪውስ እስካሁን በብሬንትፎርድ የቆሙ ኳሶች አሰልጣኝ በመሆን እያገለገሉ ነበር።

አሰልጣኙ አሁን ላይ ክለቡን በዋና አሰልጣኝነት ለመምራት የሶስት አመታት ኮንትራት ፈርመዋል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
158👍39😁11👎4
#WanawSportswear ✔️

ዋናው ስፖርት X ኢትዮጵያ መድን

እንኳን ደስ አላችሁ ኢትዮጵያ መድን የ2017 ኢትዮጵያን ፕሪምየር ሊግ ዋንጫን ከዋናው ስፖርት ጋር ከፍ አድርጋችሁ ለካፍ ሻምፒዮን ሊግ መድረክ ስለቀረባችሁ ዋናው ስፖርት በኢትዮጵያ መድን የተሰማውን ኩራት ሲገልፅላችሁ ደስታ ይሰማዋል::
ይሄ ነው ዋናው! የኛ ሻምፒዮኖች!



ለበለጠ መረጃ
8️⃣2️⃣8️⃣9️⃣

🔗 ማህበራዊ ገጾቻችን🔗
Instagram|Facebook |TikTok |X|Youtub
🔥🔥🔥🔥በኢትዮጵያ የተመረተ🔥🔥🔥🔥
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
36
🔉 ጎልልልልልል- የኳስ መረጃዎችን በየቀኑ በስልካችን!

ከሳፋሪኮም ቁጥራችን 'A’ ብለን ወደ 30002 SMS በመላክ ወይም ወደ *799# በመደወል አሁኑኑ ቴስታ ጎል እንቀላቀል! በቀን 1 ብር ብቻ!

በቴስታ ጎል ትኩስ ስፖርታዊ መረጃዎች በሽ በሽ ነው!⚡️

#SafaricomEthiopia
#1Wedefit
#Furtheraheadtogether
25👍2
ኤንድሪክ ወደ አሜሪካ ያቀናል !

ብራዚላዊው የፊት መስመር ተጨዋች ኤንድሪክ ነገ ወደ አሜሪካ ሚያሚ በማቅናት የሪያል ማድሪድን ስብስብ እንደሚቀላቀል ተገልጿል።

ተጨዋቹ ባለፉት ሳምንታት በማድሪድ በመቆየት ከጉዳቱ በማገገም ላይ እንደነበር ይታወቃል።

ይሁን እንጂ ኤንድሪክ በክለቦች አለም ዋንጫ ውድድር ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ እንደማይጫወት ተገልጿል።

ተጨዋቹ ወደ አሜሪካ ያቀናው አሰልጣኝ ዣቢ አሎንሶ እና አዲሱ የአሰልጣኝ ቡድን ስር በቅርበት ለመስራት መሆኑ ተነግሯል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
🔥8360👍10🥰3😁3😢1
የማውሪዝዮ ሳሪ የላዚዮ ቆይታ ?

ጣልያናዊው አሰልጣኝ ማውሪዝዮ ሳሪ ከ 25 ቀናት በፊት ላዚዮን ከአንድ አመት በኋላ በድጋሜ መረከባቸው ይታወሳል።

አሰልጣኙ አሁን ላይ ክለቡን ለቀው ለመሄድ በማሰብ ላይ መሆናቸውን የጣልያን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

አሰልጣኝ ማውሪዝዮ ሳሪ ከአንድ አመት በፊት ላዚዮን በገዛ ፍቃዳቸው ለቀው የነበረ ቢሆንም ከሳምንታት በፊት ክለቡ በድጋሜ ጠርቶ ሾሟቸዋል።

ክለቡ እስከ ጥር ወር ተጨዋች እንዳያስፈርም መታገዱን ዘግይተው የሰሙት ማውሪዝዮ ሳሪ በዚህ ሁኔታ አልቀጥልም ማለታቸው ተነግሯል።

አሰልጣኙ ዛሬ ከክለቡ ጋር ለንግግር መቀመጣቸው የተዘገበ ሲሆን በክለቡ ለመቀጠል ሳይስማሙ እንዳልቀሩ ተገልጿል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
😁8668👍7😢5👏3
ዴቪድ አላባ በድጋሜ ጉዳት አጋጠመው !

በቅርቡ ከረጅም ጊዜ ጉዳት ወደ ሜዳ የተመለሰው የሪያል ማድሪዱ የመስመር ተጨዋች ዴቪድ አላባ ሌላ ጉዳት እንዳጋጠመው ተገልጿል።

ተጨዋቹ በግራ እግሩ ላይ አዲስ የጡንቻ ጉዳት እንዳጋጠመው ተነግሯል።

ይህንንም ተከትሎ ዴቪድ አላባ ለአንድ ወር ከሜዳ ከሜዳ እንደሚርቅ ሲገለፅ ቀሪው የክለቦች አለም ዋንጫ ውድድርም ያመልጠዋል።

በዘንድሮው የውድድር ዘመን ጉዳት ያላጋጠማቸው የሪያል ማድሪድ ተጨዋቾች ሉካ ሞድሪች እና አርዳ ጉለር ብቻ መሆናቸው ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
😢11765😁32👎10👍6🤩5🥰4👏3😱2
የብሪያን ምቤሞ የዩናይትድ ዝውውር ?

ካሜሮናዊው ተጨዋች ብሪያን ምቤሞ ብሬንትፎርድን የሚለቅ ከሆነ ማንችስተር ዩናይትድን ብቻ መቀላቀል እንደሚፈልግ ለክለቡ እና ቶተንሀም ማሳወቁ ተገልጿል።

ማንችስተር ዩናይትዶች በበኩላቸው ለተጨዋቹ ሁለተኛ የዝውውር ሒሳብ አቅርበው የነበረ ቢሆንም ውድቅ እንደተደረገባቸው ተነግሯል።

ማንችስተር ዩናይትድ ለሁለተኛ ጊዜ አቅርቦ የነበረው የዝውውር ሒሳብ ተጨማሪ ክፍያን ጨምሮ 62.5 ሚልዮን ፓውንድ እንደነበር ተገልጿል።

ሁለቱ ክለቦች በተጨዋቹ ዝውውር ላይ ከስምምነት ለመድረስ የሚያደርጉትን ንግግር አጠናክረው መቀጠላቸው ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
253😁47👍24👎18🔥7🤔3🤬2
ቪንሰስ ጁኒየር ሪያል ማድሪድን ስንት ጠየቀ ?

ብራዚላዊው የፊት መስመር ተጨዋች ቪንሰስ ጁኒየር በሪያል ማድሪድ ቤት ውሉን ለማራዘም በንግግር ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል።

ቪንሰስ ጁኒየር ሪያል ማድሪድ በአዲሱ ኮንትራት መሰረት በአመት 30 ሚልዮን ዩሮ ክፍያ መጠየቁን ለተጨዋቹ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ገልጸዋል።

ቪንሰስ ጁኒየር ባለፈው አመት የፊፋ የአመቱ ምርጥ ሽልማት ማሸነፉን ተከትሎ አመታዊ ክፍያው ወደ 15 ሚልዮን ዩሮ ማደጉ ይታወቃል።

ተጨዋቹ ኮንትራቱን ለማራዘም ከክለቡ ጋር የሚያደርገው ንግግር አሁንም በሂደት ላይ መሆኑ ተገልጿል።

ቪንሰስ ጁኒየር ስለ ኮንትራቱ ተጠይቆ “ ሁለት ቀሪ አመታት አሉኝ ነገርግን ሙሉ የእግርኳስ ህይወቴን እዚህ መቀጠል እፈልጋለሁ “ ሲል ምላሽ ሰጥቷል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
266😁115👍36👎9👏2🤬2
#WanawSportswear ✔️

ዋናው ስፖርት X Esfna 2025
ነገ ሰኔ 21 የሀበሻውያን አንድነት,ኩራት አና ታሪክ በሲያትል ሜዳ ላይ ዋናውን ተጎናፅፈው ዙፋናቸውን ይይዛሉ::
ESFNA | ⭐️ ከዋናው ጋር ወድፊት


📍ሲያትል፣ ሰሜን አሜሪካ🇺🇸
🤝ዋናው ስፖርት የሲልቨር ደረጃ ስፖንሰር
🗓ሰኔ 21| june 28 በይፋ ይጀመራል

ለበለጠ መረጃ
8️⃣2️⃣8️⃣9️⃣

🔗 ማህበራዊ ገጾቻችን🔗
Instagram|Facebook |TikTok |X|Youtub
🔥🔥🔥🔥በኢትዮጵያ የተመረተ🔥🔥🔥🔥
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
33🥰2
"የአቪዬተር ቻሌንጅ ቀጥሏል!
ደንበኞች እያሸነፉ ነው! እርስዎስ?
በአቪዬተር የከፍታ ተልእኮዎች ይሳተፉ ፣ ከመሪዎቹ አንዱ ይሁኑ ፣ እስከ 7500 ብር ያሸንፉ!
ከፍተኛውን የማባዣ ድምር በመሰብሰብ ወደ መሪነት ሰሌዳው ላይ ይውጡ፣ነጻ በረራዎችን ያግኙ።
ከፍታውን ይቀዳጃሉ? አሁኑኑ መብረር ይጀምሩ!
https://www.betika.com/et/mobile/#/crash-games
ቤቲካ - የአሸናፊዎች ቤት"
17🤬2😁1
የክለቦች አለም ዋንጫ ተመልካች ቁጥር ምን ይመስላል ?

በአሜሪካ እየተካሄደ የሚገኘው የክለቦች አለም ዋንጫ ውድድር  የምድብ ጨዋታዎች ተደርገው ተጠናቀዋል።

ውድድሩ ከሚያካሂዳቸው 63 ጨዋታዎች 48 ጨዋታዎች ሲደረጉ በቀጣይ እስከ ፍፃሜው 15 ጨዋታዎች ይቀራሉ።

ፒኤስጂ ከአትሌቲኮ ማድሪድ ያደረጉት ጨዋታ 80,619 ተመልካቾችን በማስመዝገብ እስካሁን የውድድሩ ሪከርድ የተመልካች ቁጥር ሆኗል።

በተጨማሪም ጨዋታው በክለቦች አለም ዋንጫ ውድድር ታሪክ በርካታ ተመልካቾች የታደሙት ጨዋታ በመሆን ሪከርድ ሆኖ ተመዝግቧል።

በውድድሩ አነስተኛ ቁጥር ያለው ተመልካች የተገኘበት ጨዋታ የማሜሎዲ ሰንዳውንስ እና ኡልሳን ኤችዲ ጨዋታ ሲሆን 3,412 ተመልካቾች ተገኝተዋል።

በውድድሩ አንስተኛ ቁጥር ይሆን እንጂ በውድድሩ ታሪክ አነስተኛ ተመልካች የተመዘገበበት ጨዋታ በ 2023 ክለብ ሊዮን እና ኡራዋ ሬድ ዳይመንድስ ጨዋታ ሲሆን 2,525 ተመልካቾች ተገኝተው ነበር።

የ 2025 ክለቦች አለም ዋንጫ አማካይ የተመልካች ቁጥር 34,759 ሆኖ መመዝገቡን የፊፋ መረጃ ያሳያል።

በውድድሩ በተመሳሳይ ቀን የተደረገው የሰንዳውንስ እና ፍሉሚኔንስ እንዲሁም ሞንቴሬይ እና ኡራዋ ሬድ ዳይመንድስ ጨዋታ እንደ አጋጣሚ ተመሳሳይ 14,312 ተመልካቾች ተከታትለውታል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
154😁23👏11👎9👍3
“ ስህተት ከሰራን በማግስቱ ወደ ቤታችን ነን “ ማሬስካ

የሰማያዊዎቹ ዋና አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ ዛሬ ምሽት ከቤኔፊካ ጋር የሚያደርጉት የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ከባድ እንደሚሆን ገልጸዋል።

“ እነሱ ባየር ሙኒክን አሸንፈዋል “ ያሉት ማሬስካ “ በጨዋታው ላይ ምን ያህል ጥሩ እንደሆኑ እና ምን ማድረግ እንደሚችሉ አሳይተዋል “ ብለዋል።

“ ተመጣጣኝ ጨዋታ እንደሚሆን እርግጠኛ ነኝ ጨዋታዎች ከባድ ነው “ ሲሉ አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ ጨምረው ተናግረዋል።

“ አሁን ያለነው ጥሎ ማለፍ ላይ ነው ምንም ሊፈጠር ይችላል ፤ ተጨዋቾቹ በዚህ ሰዓት ስህተት የሚሰራው ቡድን በጨዋታው ማግስት ወደ ቤቱ የሚሸኘው ቡድን መሆኑን ያውቃል። “ ኢንዞ ማሬስካ


ቼልሲ ዛሬ ከምሽቱ 5:00 ሰዓት የክለቦች አለም ዋንጫ ጥሎ ማለፍ ጨዋታውን ከቤኔፊካ ጋር ያደርጋል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
182😁44👏22👍8🙏2
የጆሽ አቻምፖንግ የቼልሲ ቆይታ ?

የሰማያዊዎቹ ዋና አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ ለወጣቱ ተከላካይ ጆሽ አቻምፖንግ የሚበጀው በክለቡ ቢቆይ መሆኑን ገልጸዋል።

ተጨዋቹ በዚህ ክረምት ቼልሲን ሊለቅ እንደሚችል ሲዘገብ የነበረ ሲሆን ኒውካስል ዩናይትድ እና ቦርስያ ዶርትመንድ ሊያስፈርሙት ይፈልጋሉ።

ሁለገቡ ተከላካይ ጆሽ አቻምፖንግ ባለፈው አመት ለቼልሲ በሁሉም ውድድሮች 12 ጨዋታዎች ማድረግ ችሏል።

ሰማያዊዎቹ በዚህ ክረምት ወጣቱን ተከላካይ የመሸጥ ፍላጎት እንደሌላቸው ለክለቡ ቅርብ ምንጮች አረጋግጠዋል።

የ 19ዓመቱ ተከላካይ ጆሽ አቻምፖንግ በቼልሲ የወደፊት አቅድ ውስጥ ትልቅ ቦታ የተሰጠው ተጨዋች መሆኑ ተገልጿል።

ኢንዞ ማሬስካ በሰጡት አስተያየት “ አቻምፖንግን እወደዋለሁ ባለው አቅም የክለቡ ምርጥ ተከላካይ መሆን ይችላል ለእሱ ቢቆይ ጥሩ ነው “ ብለዋል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
162👍18🔥2👏1😁1🤔1
2025/07/14 02:56:02
Back to Top
HTML Embed Code: