Telegram Web Link
በዲያጎ ጆታ አሳዛኝ ህልፈት አዝነናል “ ሊቨርፑል እግር ኳስ ክለብ

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል የተጫዋቻቸውን ህልፈተ ህይወት ባወጡት አጭር መግለጫ ይፋ አድርገዋል።

የ 28ዓመቱ ዲያጎ ጆታ እና ወንድሙ ህይወት በመኪና አደጋ ማለፉን ክለቡ ማወቁን ገልጿል።

ሊቨርፑል እግር ኳስ ክለብ ለተጫዋቹ እና ለቤተሰቡ ደህንነት ሲል ተጨማሪ መረጃን ለጊዜው እንደማይሰጥ አሳውቋል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
“ አንተን በጭራሽ አልረሳህም “ ሩበን ኔቬዝ

ፖርቹጋላዊው ተጨዋች ሩበን ኔቬዝ በዲያጎ ጆታ ህልፈት የተሰማውን ሀዘን በማህበራዊ ትስስር ገፁ ገልጿል።

“ ሰውን የምታጣው ስትረሳው ብቻ ነው ይባላል “ ሲል መልዕክቱን ያጋራው ሩበን ኔቬዝ “ አንተን በጭራሽ አልረሳህም “ በማለት ተናግሯል።

ዲያጎ ጆታ በእግርኳስ ውስጥ የቅርብ ጓደኛው ሩበን ኔቬዝ መሆኑን ከዚህ በፊት በሰጠው አስተያየት ተናግሮ ነበር።

የቀድሞ የቡድን አጋሩ ስቴፋን ባቼቲች በበኩሉ “ ሁልጊዜም እናስታውስሀለን ጓደኛዬ “ ሲል ሀዘኑን ገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ አደጋው የደረሰው ጎማው ፈንድቶ ነው “

ዲያጎ ጆታ እና ወንድሙ ያጋጠማቸው የመኪና አደጋ መንስኤው የመኪናው ጎማ መፈንዳቱ መሆኑን የአካባቢው ፖሊስ አስታውቋል።

ሁለቱ ተጨዋቾች ሲጓዙበት የነበረው ላምበርጊኒ መኪና ሌላ መኪና ለማለፍ በሚሞክርበት ወቅት የጎማ መፈንዳት አደጋ እንዳጋጠመው ፖሊስ ገልጿል።

ይህንንም ተከትሎ መኪናው ጎማው በመፈንዳቱ መንገድ ስቶ በመውጣት አደጋው እንደደረሰበት ተገልጿል።

መኪናው በአደጋው ሙሉ ለሙሉ በእሳት በመቃጠሉ ምክንያት የተጨዋቾቹ ህይወት ሊያልፍ እንደቻለ ተነግሯል።

በስፍራው የነበሩ ሰዎች ለፖሊስ ማሳወቃቸው ሲገለፅ በወቅቱ መኪናው በእሳት ጋይቶ እንደነበር ምስክርነት መስጠታቸው ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" የተፈጠረውን ማመን አልቻልኩም " ክርስቲያኖ ሮናልዶ

የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን አምበል ክርስቲያኖ ሮናልዶ የዲያጎ ጆታን ህልፈት " ማመን አልቻልኩም “ ሲል ሀዘኑን ገልጿል።

" የተፈጠረውን ማመን አልቻልኩም በብሔራዊ ቡድኑ አብረን ነበርን የትዳር ህይወትህን ገና መጀመርህ ነው “ ሲል ሮናልዶ ተናግሯል።

“ ለቤተሰቡ እና ለሚወዱህ ሁሉ መፅናናትን እመኛለሁ በእነሱ እና በእኛ ልብ ውስጥ ለዘለዓለም እንደምትኖር አውቃለሁ ሁለታችሁንም ነብስ ይማር “ ሮናልዶ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Update

የዲያጎ ጆታ የቅርብ ጓደኛ እና የቀድሞ የቡድን አጋር ሩብን ኔቬስ በከፍተኛ ሀዘን ውስጥ እንደሚገኝ የሳውዲ አረቢያ የመገናኛ ብዙሀን እየዘገቡ ይገኛሉ።

የአል ሂላል ክለብ አመራሮች ተጫዋቹ በወሳኙ የነገው የክለቦች አለም ዋንጫ ጨዋታ ላይ በነፃነት ውሳኔው እንዲያሳውቅ መፍቀዳቸው ተገልጿል።

ሩብን ኔቬስ በጥሩ የአዕምሮ ጥንካሬ ላይ እንደማይገኝ ሲገለፅ በቅርብ ጓደኛው ስርዓተ ቀብር ላይ እንደሚገኝ መረጃው አስነብቧል።

አል ሂላል በነገው ዕለት በክለቦች የአለም ዋንጫ በሩብ ፍፃሜ መርሐ ግብር ፍሉሚኔንሴን የሚገጥሙ ይሆናል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ሊቨርፑል አርማውን ዝቅ አድርጓል !

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል የዲያጎ ጆታን ህልፈት ተከትሎ በክለቡ ውስጥ የሚገኘው አርማ ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ አድርጓል።

ደጋፊዎቹ በበኩላቸው ከአንፊል ስታዲየም አቅራቢያ አበባ በማስቀመጥ በተጫዋቹ ህልፈት ሀዘናቸውን እየገለፁ ይገኛሉ።

የሊቨርፑል ተጨዋቾች እንዲሁ ሀዘናቸውን ሲገገልፁ ዳርዊን ኑኔዝ “ የተሰማኝን ህመም የምገልፅበት ቃል የለኝም “ ብሏል።

ዳርዊን ኑኔዝ አክሎም " ሁልጊዜም ከፈገግታህ ጋር አስታውስሀለሁ ምርጥ የቡድን አጋር ነበርክ።“ ብሏል።

የፖርቹጋሉ ክለብ ፖርቶ በተመሳሳይ በክለቡ አርማው ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ በማድረግ ሀዘናቸውን እየገለፁ ነው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
በጣም ትናፍቀናለህ “ የርገን ክሎፕ

የቀድሞ የሊቨርፑል ዋና አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ በቀድሞ ተጫዋቻቸው ዲዮጎ ጆታ ህልፈተ ህይወት ማዘናቸውን ገልፀዋል።

“ ሁሌም እንናፍቅሀለን “ ያሉት የርገን ክሎፕ “ ይህ ጊዜ ሀዘኔን የምገልፅበት ነው ፣ ልቤ በሀዘን ተሰብሯል “ ብለዋል።

“ ዲያጎ ጆታ ጥሩ ተጫዋች ብቻ አይደለም “ የሚሉት ክሎፕ “ ለቡድን አጋሮቹ ጥሩ ጓደኛ እንዲሁም ለቤተሰቦቹ አሳቢ እና ወዳጅ ነበር “ ሲሉ ሀዘናቸውን ገልፀዋል።

“ በጣም ትናፍቀናለህ “ የርገን ክሎፕ

@tikvahethsport @kidusyoftahe
#Wanawsportswear✔️

ዋናው ፕሪምየም ኳሊቲ ሙሉ ትጥቅ
ይህ የስፖርት ትጥቅ ብቻ አይደለም የቡድንዎትም ጋሻ ጭምር ነው።
💪አቅምዎትን የሚያሳይ
⭐️በራስ መተማመንን የሚያጎናጽፍ
🏃🏻በእያንዳንዱ ግጥሚያ እና እንቅስቃሴ አይረሴ የሚያደርግዎት

🛒ብዛት ከ20 ጀምሮ ሲያዙ =ነጻ የጂም ቲሸርት ከዋናው ስፖርት
🛒ብዛት ከ50 በላይ ሲያዙ =ነፃ 1ኛ ደረጃ ኳስ
💰 በ2200ብር | ማሊያ • ቁምጣ • ካሶተኒ

📞ለማዘዝ
8️⃣2️⃣8️⃣9️⃣
➡️+251901138283
➡️+251910851535
➡️+251913586742
🚚ኢትዮጵያ እና ባህር ማዶ ለምታዙ ያሉበት ድረስ እናደርሳለን

🔗 ማህበራዊ ገጾቻችን🔗
Instagram|Facebook |TikTok |X|Youtube
🔥🔥🔥🔥በኢትዩጵያ የተመረተ🔥🔥🔥🔥
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-SPORT
" ፖግባ አይመለስም አብቅቶለታል " ፖግባ ፈረንሳዊው የአንድ ጊዜ አለም ዋንጫ አሸናፊ ተጨዋች ፖል ፖግባ ከዚህ በፊት በነበረው የእግርኳስ ህይወቱ የስፖርት ማህበረሰቡን ቀልብ የገዛበት የእግርኳስ ችሎታው በድጋሜ እንደማይመለስ ገልጿል። የቀድሞ የጁቬንቱስ እና ማንችስተር ዩናይትድ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ፖል ፖግባ በቅርቡ በአበረታች ንጥረ ነገር ጋር በተያያዘ ለአራት አመታት ከእግር ኳስ መታገዱ አይዘነጋም።…
“ ያነባሁት የደስታ እንባ ነበር “ ፖግባ

ለሞናኮ ፊርማውን ያኖረው ፈረንሳዊው አማካይ ፖል ፖግባ በፊርማ ስነስርዓቱ ወቅት ስሜታዊ ሆኖ ሲያለቅስ ተስተውሎ ነበር።

" ስሜታዊ ሆኜ እንደነበር አልደብቅም " ያለው ፖግባ “ ብዙ ጊዜ እንደዚህ አይነት ስሜት አይሰማኝም ነገርግን በውስጤ ብዙ ነገሮች ነበሩ ታሪኩን ታውቁታላችሁ ብሏል።

ወደ እግርኳስ ተመልሶ በእሱ ለሚያምን ክለብ መፈረሙ ስሜታዊ እንዳደረገው የገለፀው ፖግባ “ ስፈርም ሁሉም ነገር ነው ወደ እኔ የመጣው ነገርግን ደስታ ብቻ ነበር “ ሲል ተናግሯል።

“ እንደ እኔ ቢሆን ነገውን ሜዳ መመለስ እፈልጋለሁ ነገርግን ታጋሽ መሆን አለብኝ መመለስ የምፈልገው ሜዳ ላይ ለመሆን ሳይሆን በትልቅ ደረጃ ነው።" ፖግባ

አክሎም " ቡድኑን ለመረዳት 100% ዝግጁ መሆን እፈልጋለሁ 50% ሆኜ ቡድኑን መርዳት አልፈልግም በጣም ዝግጁ ነኝ ምንም እንደማያቆመኝ ታውቁኛላችሁ።"ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ሊዮኔል ሜሲ ኢንተር ሚያሚን ይለቅ ይሆን ? ከኢንተር ሚያሚ ጋር ያለው ውል በ 2025 መጨረሻ የሚያበቃው ሊዮኔል ሜሲ ውሉን ለማራዘም ንግግር ላይ ይገኛል። ሊዮኔል ሜሲ ውሉን እስከ 2026 ሊያራዝም መሆኑን ከዚህ በፊት ታማኝ የመረጃ ምንጮች መዘገባቸውም አይዘነጋም። አሁን ላይ ሊዮኔል ሜሲ ውሉ ሲጠናቀቅ ተፎካካሪ ወደሆነ ሊግ ስለማቅናት ሊያስብ እንደሚችል ተዘግቧል። ሊዮኔል ሜሲ ከ 2026…
የሊዮኔል ሜሲ የኢንተር ሚያሚ ቆይታ ?

ኢንተር ሚያሚ ከክለቦች አለም ዋንጫ ከተሰናበተ በኋላ የአርጀንቲና መገናኛ ብዙሀን ሊዮኔል ሜሲ ክለቡን ሊለቅ እንደሚችል ሲዘግቡ ነበር።

ይሁን እንጂ ሊዮኔል ሜሲ እና ቤተሰቡ አሜሪካ ውስጥ ተደላድለው መቀመጣቸው እንዲሁም ሜሲ በኢንተር ሚያሚ እቅድ ደስተኛ መሆኑ ተገልጿል።

ሜሲ በቀጣይ እየተዘገበ እንደሚገኘው ወደ መጀመሪያ የልጅነት ክለቡ ወይም ባርሴሎና የመመለስ እድል እንደሌለው ተነግሯል።

ኢንተር ሚያሚ እና ሊዮኔል ሜሲ ውላቸውን ለማራዘም አሁንም በንግግር ላይ መሆናቸው ሲገለፅ ሜሲ ውሉን ቢያንስ እስከ 2026 ያራዝማል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገልጿል።

ቀጣዩ አለም ዋንጫ በአሜሪካ መዘጋጀቱ ሊዮኔል ሜሲን በሀገሪቱ እንዲቆይ ከሚያደርጉት ምክንያቶች አንዱ መሆኑ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሞሀመድ ሳላህ የእረፍት ጊዜውን ያቋርጣል !

ሞሀመድ ሳላህ በቡድን አጋሩ ዲያጎ ጆታ ህልፈተ ህይወት ምክንያት አመታዊ የእረፍት ጊዜውን ለማቋረጥ መወሰኑ ተገልጿል።

በግሪክ የእረፍት ጊዜውን በማሳለፍ ላይ የሚገኘው መሐመድ ሳላህ ከዲያጎ ጆታ ሞት ዜና በኋላ ለመሰረዝ መወሰኑን የግብፅ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

ሞሀመድ ሳላህ በቡድን አጋሩ ዲያጎ ጆታ ድንገተኛ ህልፈት ምክንያት ከፍተኛ ሀዘን ውስጥ መግባቱ ተነግሯል።

ይህንንም ተከትሎ መሐመድ ሳላህ ነገ ወደ እንግሊዝ ሊቨርፑል ይመለሳል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተዘግቧል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ሶስት ህፃናት ከ እንቅልፋቸው ያለ አባታቸው ነቅተዋል “

የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን እና አል ሂላል ተጫዋች ጇ ካንሴሎ በብሔራዊ ቡድን አጋሩ ዲያጎ ጆታ ህልፈተ ህይወት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጿል።

“ ሁለት እግር ኳስ ተጫዋቾችን ብቻ አላጣንም “ ያለው ካንሴሎ “ በጠዋት የሰማነው ህልፈት ህይወት በድንጋጤ ውስጥ ከቶናል “ ብሏል።

“ ልጆች ያለ አባታቸው ፣ እናት እና አባት ያለ ልጃቸው እንዲሁም ሚስት ያለ ባሏ ከ እንቅልፋቸውን ነቅተዋል “ በማለት የዲያጎ ጆታ ህልፈተ ህይወት ከባድ መሆኑን ገልፆታል።

“ ህይወት ጊዜያዊ መሆናችንን እንዲሁም ምንም ዋስትና እንደሌለው የሚያስታውሰን ነው “ ጇ ካንሴሎ

@tikvahethsport @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የሮድሪጎ የሪያል ማድሪድ ሁኔታ ? ብራዚላዊው ተጨዋች ሮድሪጎ የክለቦች አለም ዋንጫ የመጀመሪያ ጨዋታዎች ላይ ባለመሳተፉ ደስተኛ ስላለመሆኑ በቅርቡ ያሉ ሰዎች ተናግረዋል። የተጨዋቹ የሪያል ማድሪድ ሁኔታ በቀጣይ የዝውውር መስኮቱ መነጋገሪያ ርዕሰ ሊሆን እንደሚችል ተገልጿል። ሎስ ብላንኮዎቹ ማስታንቱኖን ከሪቨር ፕሌት ማስፈረማቸው የሮድሪጎን ሚና ሊቀንሰው እንደሚችል ተሰግቷል። በሌላ በኩል የቡድኑ…
ማድሪድ ሮድሪጎን ለመሸጥ ዝግጁ መሆኑ ተገለጸ !

ሪያል ማድሪድ እና አሰልጣኝ ዣቢ አሎንሶ ብራዚላዊውን ተጨዋች ሮድሪጎን በዚህ ክረምት ለመሸጥ ዝግጁ መሆናቸው ተገልጿል።

ትክክለኛው የዝውውር ሒሳብ የሚቀርብ ከሆነ ክለቡ በተጨዋቹ መንገድ ላይ ላለመቆም ከስምምነት መደረሱ ተዘግቧል።

የ 24ዓመቱ ሮድሪጎ ሪያል ማድሪድ በክለቦች አለም ዋንጫ የመክፈቻ ጨዋታ ሲያደርግ ከ 53 ቀናት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ መሰለፉ ይታወሳል።

ተጨዋቹ በውድድሩ በአሰልጣኝ ዣቢ አሎንሶ እድል ተሰጥቶት የተጫወተው ለ 23 ደቂቃዎች ነው።

የሮድሪጎ ፈላጊ የሆነው አርሰናል ባለፈው ሳምንት ከተጨዋቹ ተወካዮች ጋር የመጀመሪያ ንግግር ማድረጉ ተነግሯል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
“ ያነባሁት የደስታ እንባ ነበር “ ፖግባ ለሞናኮ ፊርማውን ያኖረው ፈረንሳዊው አማካይ ፖል ፖግባ በፊርማ ስነስርዓቱ ወቅት ስሜታዊ ሆኖ ሲያለቅስ ተስተውሎ ነበር። " ስሜታዊ ሆኜ እንደነበር አልደብቅም " ያለው ፖግባ “ ብዙ ጊዜ እንደዚህ አይነት ስሜት አይሰማኝም ነገርግን በውስጤ ብዙ ነገሮች ነበሩ ታሪኩን ታውቁታላችሁ ብሏል። ወደ እግርኳስ ተመልሶ በእሱ ለሚያምን ክለብ መፈረሙ ስሜታዊ እንዳደረገው…
ፖል ፖግባ መቼ ወደ ሜዳ ይመለሳል ?

የሞናኮው ሀላፊ ቲያጎ ስኩሮ በፈረንሳይ ሊግ የመጀመሪያ ሳምንት መርሐ ግብር ፖል ፖግባን ሜዳ ላይ #እንደማንመለከተው አስታውቀዋል።

“ ሞናኮ ከሌ ሀቭሬ ጋር በሚያደርገው የመጀመሪያ ጨዋታ ፖል ፖግባ እንደማይኖር አረጋግጥላችኋለሁ " ሲሉ ሀላፊው ተናግረዋል።

" ግልጽ መሆን አለብን " ያሉት ሀላፊው ፖል ፖግባ አቅሙን መልሶ እንዲያገኝ የሶስት ወር የስልጠና ሂደት እንጠብቃለን ሲሉ ገልጸዋል።

“ በትልቅ ደረጃ ያለን ስፖርት በቲቪ ስንመለከተው ቀላል ሊመስል ይችላል ነገርግን የሚያስፈልገውን ጥንካሬ መገንዘብ አለብን “ ሲሉ ሀላፊው ጨምረው ተናግረዋል።

“ ሞናኮ በፈረንሳይ ሊግ እና አውሮፓ ላይ በአጨዋወቱ ጠንካራ ከሚባሉ ቡድኖች አንዱ ነው ፣ ተጨዋቾቻችን ደግሞ ሜዳ ላይ ለመገኘት በጥሩ ቁመና ላይ መሆን አለባቸው።"ቲያጎ ስኩሮ

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሊቨርፑል የአገልግሎት ተቋማቱን ዘጋ !

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል የተጨዋቹ ዲያጎ ጆታን ህልፈተ ህይወት ተከትሎ አገልግሎት ተቋማቱ ዝግ እንደሚደረጉ አስታውቋል።

ይህንንም ተከትሎ የክለቡ ቁሳቁስ መሸጫ ሱቅ ፣ ሙዚየም እና የጉብኝት አግልግሎት ዝግ እንደሚደረግ ክለቡ ይፋ አድርጓል።

አግልግሎቱ ለሚቀጥሉት አራት ቀናት ዝግ ሆኖ እንደሚቆይ ተገልጿል።

ሊቨርፑል አሁን ላይ በክለቡ እንግዳ መቀበያ የሀዘን መግለጫ ደብተር በማዘጋጀት ሀዘን እና የስንብት መልዕክት እየተቀበለ መሆኑን ገልጿል።

በተጨማሪም የክለቡ አርማ ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ ማድረጉን ክለቡ አሳውቋል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
ፔድሮ ኔቶ ልምምድ አልሰራም !

በክለቦች አለም ዋንጫ ውድድር እየተሳተፈ የሚገኘው ቼልሲ የዛሬ ልምምዱን ለዲያጎ ጆታ የህሊና ፀሎት በማድረግ ጀምሯል።

በቡድኑ ልምምድ ላይ ፖርቹጋላዊው የቡድኑ የፊት መስመር ተጨዋች ፔድሮ ኔቶ አለመሳተፉ ተገልጿል።

ተጨዋቹ የቅርብ ጓደኛው ዲያጎ ጆታን ህይወት ማለፍ ተከትሎ በልምምድ እንዳልተሳተፈ ተዘግቧል።

ፔድሮ ኔቶ በስነልቦና ዝግጁ ላይሆን ስለሚችል በነገው የፓልሜራስ ሩብ ፍፃሜ ጨዋታ ላይሳተፍ እንደሚችል ተነግሯል።

ቼልሲ ነገ ሌሊት 10:00 ሰዓት ከብራዚሉ ክለብ ፓልሜራስ ጋር የሩብ ፍፃሜ ጨዋታውን ያደርጋል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ጆታ የሁላችንም ተወዳጅ ነበር “ አርኔ ስሎት

የሊቨርፑሉ ዋና አሰልጣኝ አርኔ ስሎት በተጨዋቻቸው ዲያጎ ጆታ እና ወንድሙ ህልፈት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልጸዋል።

ስለ ሀዘኑ እና ህመሙ ቃላት አላገኝም ሲሉ የገለፁት አሰልጣኝ አርኔ ስሎት “ ሀሳቤ ክፉኛ ስለተጎዱት ቤተሰቦቻቸው ነው “ በማለት ተናግረዋል።

“ ተጨዋቾቹ ፣ ቡድኑ ፣ ደጋፊው እንዲሁም መላው የስፖርት ቤተሰብ ከጎናችሁ ነው " ሲሉ ቤተሰቡን ያፅናኑት አርኔ ስሎት " you will never walk alone " ብለዋል።

“ ጆታ ተጨዋች ብቻ አይደለም ሁላችንም የምንወደው ሰው ነበር እሱ በሁሉም መልኩ የተለየ ተጨዋች ነበር “ አርኔ ስሎት

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
2025/07/05 15:56:27
Back to Top
HTML Embed Code: