Telegram Web Link
ሮናልዲንሆ የብራዚልን ጨዋታ እንደማይመለከት ገለጸ !

ብራዚላዊው የቀድሞ ኮከብ ሮናልዲንሆ በቀጣዩ የኮፓ አሜሪካ ውድድር የሀገሩ ብራዚልን ጨዋታዎች መመልከት እንደማይፈልግ በኢንስታግራም የማህበራዊ ትስስር ገፁ አሳውቋል።

የብራዚል ብሔራዊ ቡድኑ በመጥፎ ሁኔታ ውስጥ መሆኑን የተናገረው ሮናልዲንሆ " በቀጣዩ ኮፓ አሜሪካ የብራዚልን ጨዋታዎች አልመለከትም በድሎችም አልደሰተም " ሲል ተናግሯል።

" ብሔራዊ ቡድኑ ባለፉት አመታት እስካሁን ካየሁት ሁሉ እጅግ ደካማው ነው በጣም ያሳዝናል " ሲል የገለፀው የቀድሞ ተጨዋቹ ክብር የሌላቸው ሀላፊዎች እና የማልያ ፍቅር ማጣት ይስተዋላል ሲል ተችቷል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ብራይተን አሰልጣኝ አነጋግሯል ! ከአሰልጣኝ ሮቤርቶ ዲ ዘርቢ ጋር የተለያየው ብራይተን የጀርመኑ ክለብ ሴንት ፓውሊውን አሰልጣኝ ፋብያን ሁርዜሌርን ለመሾም ማነጋገራቸው ተገልጿል። የ 31ዓመቱ ጀርመናዊ አሰልጣኝ ፋብያን ሁርዜሌርን የአሰልጣኝ ሮቤርቶ ዲዘርቢ ተተኪ ለመሆን የብራይተን የመጀመሪያ ተመራጭ መሆኑ ተዘግቧል። ብራይተን የቀድሞ አሰልጣኛቸውን ግራም ፖተር በድጋሜ ለመሾም ፍላጎት እንዳላቸው…
ብራይተን በይፋ አሰልጣኝ ሾመዋል !

በቅርቡ ከጣልያናዊው አሰልጣኝ ሮቤርቶ ዲ ዘርቢ ጋር የተለያየው ብራይተን አዲስ አሰልጣኝ በሀላፊነት መሾማቸውን ይፋ አድርገዋል።

ብራይተን የጀርመኑ ክለብ ሴንት ፓውሊ አሰልጣኝ የነበሩትን አሰልጣኝ ፋብያን ሁርዜሌርን በሀላፊነት መሾማቸውን ይፋ አድርገዋል።

የ 31ዓመቱ ጀርመናዊ አሰልጣኝ ፋብያን ሁርዜሌር በፕርሚየር ሊጉ ታሪክ የምንግዜም በእድሜ ትንሹ አሰልጣኝ በመሆን አዲስ ታሪክ ፅፈዋል።

አሰልጣኙ በብራይትን የቡድን ስብስብ ውስጥ ሰባት በእድሜ የሚበልጧቸውን ተጨዋቾች የሚያሰለጥኑ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
27 '  ስፔን 1 - 0 ክሮሽያ

ሞራታ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
32 '  ስፔን 2 - 0 ክሮሽያ

ሞራታ
ሩይዝ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
45 '  ስፔን 3 - 0 ክሮሽያ

ሞራታ
ሩይዝ
ካርቫል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
እረፍት | ስፔን 3 - 0 ክሮሽያ

ሞራታ
ሩይዝ
ካርቫል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሲዳማ ቡና ድል አድርጓል !

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የሀያ ሰባተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሲዳማ ቡና ከሀምበሪቾ ዲራሜ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የሲዳማ ቡናን የማሸነፊያ ግቦች አበባየሁ ዮሐንስ እና ማይክል ኪፕሩቪ ከመረብ አሳርፈዋል።

ሀምበሪቾ ዲራሜ በውድድር ዘመኑ ሀያ አንደኛ ሽንፈታቸውን አስተናግደዋል።

የሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ምን ይመስላል ? 

1️⃣2️⃣ ሲዳማ ቡና :- 34 ነጥብ

1️⃣6️⃣ ሀምበሪቾ ዱራሜ  :- 8 ነጥብ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ስፔን የመጀመሪያ ጨዋታዋን አሸንፋለች !

በአውሮፓ ዋንጫ የምድብ የመጀመሪያ ጨዋታ የስፔን ብሔራዊ ቡድን ከክሮሽያ ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደረገውን ጨዋታ 3ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የስፔን ብሔራዊ ቡድንን የማሸነፊያ ግቦች አልቫሮ ሞራታ ፣ ፋብያን ሩይዝ እና ዳኒ ካርቫል ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

የ 16ዓመቱ ስፔናዊ ተጨዋች ላሚን ያማል በአውሮፓ ዋንጫው ታሪክ ተሰልፎ የተጫወተ በእድሜ ትንሹ ተጨዋች በመሆን አዲስ ታሪክ ፅፏል።

በተጨማሪም ላሚን ያማል በአውሮፓ ዋንጫው ታሪክ ለግብ የሆነ ኳስ አመቻችቶ ማቀበል የቻለ በእድሜ ትንሹ ተጨዋች መሆን ችሏል።

በምድቡ ሁለተኛ ጨዋታ ቀጣይ ሳምንት ሐሙስ ስፔን ከጣልያን እንዲሁም እሮብ ክሮሽያ ከአልባንያ ጋር ይገናኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፍ !

4:00 ጣልያን ከ አልባንያ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ሜሲ በያማል እድሜ የሱን ያህል ጥሩ አልነበረም "

የቀድሞ ስፔናዊ ተጨዋች ፈርናንዶ ሎሬንቴ ላሚን ያማል በትንሽ እድሜው ሜዳ ላይ እያደረገ የሚገኘው ነገር እንዳስገረመው በሰጠው አስተያየት ተናግሯል።

" ላሚን ያማል በ16ዓመቱ የሚያደርገውን ነገር ሊዮኔል ሜሲ በዚህ እድሜው እንኳን አያደርገውም ነበር " የሚለው ፈርናንዶ ሎሬንቴ ላሚን ያማል የተለየ ነው ከማንም ጋር ሊወዳደር አይችልም ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
1 ' ጣልያን 0-1 አልባንያ

ባህራሚ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
11' ጣልያን 1-1 አልባንያ

ባስቶኒ                ባህራሚ

*አልባንያ ጣልያን ላይ በሀያ ሁለት ሰከንዶች ያስቆጠሩት የመሪነት ግብ በአውሮፓ ውድድር ታሪክ ፈጣኑ ግብ በመሆን ተመዝግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
18' ጣልያን 2-1 አልባንያ

ባስቶኒ                ባህራሚ
ባሬላ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
እረፍት | ጣልያን 2-1 አልባንያ

ባስቶኒ                ባህራሚ
ባሬላ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ጣልያን ውድድሯን በድል ጀምራለች !

በአውሮፓ ዋንጫ የምድብ የመጀመሪያ ጨዋታ የጣልያን ብሔራዊ ቡድን ከአልባንያ ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደረገውን ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የጣልያን ብሔራዊ ቡድንን የማሸነፊያ ግቦች አሌሳንድሮ ባስቶኒ እና ኒኮሎ ባሬላ ከመረብ ሲያሳርፉ ለአልባንያ ነዲም ባህራሚ አስቆጥሯል።

ምድቡን ስፔን እና ጣልያን በግብ ክፍያ ተበላልጠው በሶስት ነጥብ አንደኛ እና ሁለተኛ በመሆን መምራት ጀምረዋል።

በምድቡ ሁለተኛ ጨዋታ ቀጣይ ሳምንት ሐሙስ
ጣልያን ከስፔን እንዲሁም እሮብ አልባንያ ከክሮሽያ ጋር ይገናኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሽመልስ በቀለ 1⃣8⃣ ገስት ሀውስ

በውቢቷ ሀዋሳ ቆይታዎ የት ለማረፍ አስበዋል ? ንፁህ እና በደንበኞቻችን ተወዳጅ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን መጥተው የእረፍት ጊዜውን ያሳልፉ።

እንግዶቻችንን ተቀበልን ለእይታ ሳቢ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን ማስተናገድ ከጀመርን አመታትን አስቆጥረናል።

አድራሻችን :- ሀዋሳ አርቴፍሻል ስታዲየም መንገድ ላይ ያገኙናል።

ለተጨማሪ መረጃ እና ለትዕዛዝዎ ይደውሉልን :- 0928684848

#ShemelesBekele18
🌙 እንኳን ለዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

ዒድ ሙባረክ!!
" ስፔን ማሸነፍ ይገባታል " ሞድሪች

የክሮሽያ ብሔራዊ ቡድን አምበል ሉካ ሞድሪች በትላንት ምሽቱ የአውሮፓ ዋንጫ የምድብ የመጀመሪያ ጨዋታ ስፔን በክሮሽያ ላይ የተቀዳጀችው ድል እንደሚገባት ተናግሯል።

" አንዳንድ ቀን እንደሚፈጠረው ሁሉ ዛሬ ነገሮች በፈለግነው መንገድ አልሄዱልንም " ሲል ከጨዋታው በኋላ አስተያየቱን የሰጠው ሞድሪች ስፔን ማሸነፍ ይገባት ነበር ብሏል።

ሉካ ሞድሪች ቀጥሎም " ዛሬ ብንሸነፍም በቀጣዩ ጨዋታ የተሻልን እንደምንሆን እና እንደሚሳካልን እርግጠኛ ነኝ አልባንያን ግዴታ ማሸነፍ አለብን " ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ሮናልዲንሆ የብራዚልን ጨዋታ እንደማይመለከት ገለጸ ! ብራዚላዊው የቀድሞ ኮከብ ሮናልዲንሆ በቀጣዩ የኮፓ አሜሪካ ውድድር የሀገሩ ብራዚልን ጨዋታዎች መመልከት እንደማይፈልግ በኢንስታግራም የማህበራዊ ትስስር ገፁ አሳውቋል። የብራዚል ብሔራዊ ቡድኑ በመጥፎ ሁኔታ ውስጥ መሆኑን የተናገረው ሮናልዲንሆ " በቀጣዩ ኮፓ አሜሪካ የብራዚልን ጨዋታዎች አልመለከትም በድሎችም አልደሰተም " ሲል ተናግሯል። " ብሔራዊ…
" ሮናልዲንሆ ትኬት ሲጠይቅ ነበር " ራፊንሀ

የብራዚል ብሔራዊ ቡድን የፊት መስመር ተጨዋች ራፊንሀ ብራዚላዊው የቀድሞ ተጨዋች ሮናልዲንሆ የጨዋታ መመልከቻ ትኬቶች ሲጠይቅ እንደነበር ገልጿል።

ሮናልዲንሆ በቀጣይ የብራዚል ጨዋታዎችን መመልከት እንደማይፈልግ መግለፁን እንደተመለከተ የተናገረው ራፊንሀ " ነገርግን ሮናልዲንሆ ከቀናት በፊት ቪንሰስ ጁኒየርን የጨዋታ መመልከቻ ትኬት ጠይቆት ነበር " ብሏል።

ሮናልዶንሆ ትላንት በማህበራዊ ትስስር ገፁ በብራዚል ብሔራዊ ቡድን ደካማ አቋም ምክንያት ከዚህ በኋላ ጨዋታዎቹን መመልከት ማቆሙን ገልፆ ነበር።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/06/16 06:42:18
Back to Top
HTML Embed Code: